YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በምዕራብ ኦሞ ዞን በደረሰ የእሳት አደጋ ከ586 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ!

በምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቤሮ ወረዳ፣ ሾላ ቀበሌ ትላንት በተከሰተ የእሳት አደጋ ከ586 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ።የቤሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዶንተስ ባይከን ለኢቢሲ እንደተናገሩት፣ የእሳት አደጋው ትላንት ታኅሣሥ 19 ቀን 2013 ከቀኑ11:00 ሰዓት አካባቢ ሾላ ቀበሌ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።በቀበሌው በተከሰተው የእሳት አደጋ 16 ሺህ 709 ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እንደተፈናቀሉም አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

በአካባቢው የባንክ አገልግሎት ባለመኖሩ በርካታ ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ በአደጋው 1ሺህ 840 መኖሪያ ቤቶች እና 547 የንግድ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውንም አቶ ዶንቶስ ለኢቲቪ በስልክ ገልጸዋል።

የእሳት አደጋ መንስኤው በመጣራት ላይ መሆኑን የገለጹት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ፣ በወረዳው በወርቅ ስራ የሚተዳደሩ 37 ማኅበራት ንብረታቸው ሙሉ ለሙሉ መውደሙንም አመልክተዋል።ከአደጋው የተረፉ የተወሰኑ ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች ቤት ንብረታቸው ለተቃጠለባቸው ዜጎች መጠለያነት እንዲሆኑ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል።ለተጎጂዎች የሰብአዊ እርዳታ እየተሰጠ መሆኑንና ተጨማሪ ድጋፎች ከፌዴራል እና ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልላዊ መንግሥት እንዲደረግላቸው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዶንተስ ጥሪ አቅርበዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሲሊንደር ጋዝ ዋጋ በሁለት ሳምንት የ350 ብር ጭማሪ አሳየ!

በአዲስ አበባ የሲሊንደር ጋዝ ዋጋ በኹለት ሳምንት ውስጥ እስከ 350 ብር ጭማሪ ማሳየቱን የሲሊንደር ጋዝ የሚጠቀሙ ምግብ ቤቶች ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።በአዲስ አበባ ለተጠቃሚዎች ሲሊንደር ጋዝ በችርቻሮ በሚሸጡ ጋዝ ቤቶች ከኹለት ሳምንት በፊት 650 ብር ሲሸጥ የነበረ 12 ኪሎ ግራም ሲሊንደር ጋዝ እስከ አንድ ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑን ተጠቃሚዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

ጋዜጣው የተጠቃሚዎቹን ጥቆማ ይዞ በአዲስ አበባ ሲሊንደር ጋዝ ለተጠቃሚዎች የሚቸረችሩ ጋዝ ቤቶችን ተዘዋውሮ እንደተመለከተ የገለፀ ሲሆን የገበያ ሁኔታው በትክክልም የተባለው የዋጋ ጭማሪ መኖሩን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

የሲሊንደር ዋጋ ለመጨመሩና በአንዳንድ ነዳጅ መሽጫ ሱቆች የዋጋ ጭማሪው ለመታየቱ ዋነኛው ምክንያት በቂ የሆነ የአቅርቦት ችግር በመከሰቱ መሆኑን እሽቱ ለማ የግዮን ጋዝ አከፋፋይ ለአዲስ ማለዳ አረጋግጧል። የአቅርቦት ችግር በመታየቱ ዋና አከፋፋዮች ለቸርቻሪዎች ወይም በቀጥታ ለተጠቃሚ ለሚሸጡ ነጋደዎች ሲሊንደር ጋዝ መሽጥ ማቆማቸው ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ዳንኤል ሜኤሳ ከአዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ቢሮው መሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ በመጥቀስ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ አይመለከተንም ሲሉ ምለሻቸውን ሰጥተዋል።የንግድ ውድድር እና ሽማቾች ጥበቃ ባለስልጣን በበኩሉ የኔ ስልጣን ዋጋ መቆጣጠር አይደለም ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
20 በመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ለመከተብ የሚያስችል የኮሮና ክትባት በቅርቡ አገር ውስጥ ይገባል ተባለ!

ከኮቫክስ የተገኘውና 20 በመቶ ለሚሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የኮሮና ክትባት በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ እንደሚመጣ የጤና ሚኒስትሯ አስታወቁ።ኮቫክስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት ለደሃ አገሮች በዕርዳታ መልክ ለማቅረብ ካቀደው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ውስጥ፣ ኢትዮጵያ እስከ 20 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት መጠን በጥቂት ወራት እንደምታገኝ የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ማስታወቃቸውን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሁለት ሕፃናት ወድቆ ያገኙትን ቦምብ ሲነካኩ ፈንድቶ የአንዱ ህጻን ህይወት ሲያልፍ ሌላኛው ህጻን እግር ላይ ጉዳት ደረሰ።

በአዲስ አበባ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ደራርቱ ቱሉ መሰናዶ ት/ቤት ጀርባ ታኅሣሥ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ገደማ ሁለት ሕፃናት ወድቆ ያገኙትን ቦምብ ሲነካኩ ፈንድቶ መጎዳታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

በአደጋው የአምስት ዓመት ዕድሜ ያለው ጸጋዬ ተክለማርያም የተባለ ሕፃን ሕይወቱ ሲያልፍ፣ ግዛው አንተንአየሁ የተባለ የስምንት ዓመት ሕፃን በእግሩ ላይ ጉዳት ደርሶበት ሕክምና ማግኘቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ በመተከል የጸጥታ ችግር እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ም/ል ሃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ ገልጸዋል፡፡

የዞኑ ሠላም ወደ ቀደመ ሁኔታ እስኪመለስ ከጸጥታ ችግሩ ጋር እጃቸው ያላባቸውን አመራሮች ጨምሮ ሌሎችንም ግለሰቦች የማደን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አቶ ሙሳ ጨምረው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮዉ ዘመነ-ትምህርት ይማራሉ ተብለዉ ከተጠበቁ ተማሪዎች ከአንድ ሚሊየን የሚበልጡት ትምህርት አለመቀጠላቸዉን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ትምሕር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኤፍሬም ተሰማ ለዶይቼ ቬሌ እንዳሉት መስሪያ ቤታቸዉ፣ ዘንድሮ 11.2 ሚሊየን ወጣቶችን ለማስተማር አቅዶ ነበር። አሁን በመማር ላይ ያሉት ተማሪዎች ቁጥር ግን ከ10 ሚሊየን ያነሰ ነው፡፡ ለተማሪዉ ቁጥር  መቀነስ ያለ ዕድሜ ጋብቻና የጸጥታ ሥጋት እንደ መምክንያት ተጠቅሰዋል። በኦሮሚያ የኮሮና ተዋሲ ስርጭትን ለመከላከል፣ አምና ትምሕርት በመቋረጡ ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎች ያለ ዕድሜያቸዉ  እንዲያገቡ ሰበብ መሆኑም ተነግሯል። በቄለም ወለጋ፣ ጉጂ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ደግሞ በፀጥታ ችግር ምክንያት አሁንም  ያልተከፈቱ ትምህርት ቤቶች መኖራቸው ተነግሯል፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
🎓🌎✈️


📣Hope Travel Agents and Consultants📣

የውጭ ሀገር የትምህርት ዕድል ለማግኘት አቅድዋል ?
መልስዎ አዎ ከሆነ እና ህልሞን ለማሳካት የሚሹ ከሆነ HOPE የትምህርት ጉዳዮች አማካሪ የእርስዎን ህልም ለማሳካት ከጎናችሁ ነው ።

መሀል አውሮፓ አንቱታን ባተረፋ ዩኒቨርሲቲዎች በመማር አለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው ትምህርት ከ ዕውቀት ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ከፈለጉ መፍትሄው እኛ ጋር አለ።

የብዙዎችን ህልም ዕውን አድርገናል እርሰዎም መተው ይቀላቀሉን።

አድራሻ

☎️+48 739667468
@Dagides

@s_tudyeurope.....join our channel


📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡ ስምንት ትምህርት ቤቶች ለርክክብ ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ!

በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በመገንባት ላይ የሚገኙ ግንባታቸው ከዚህ ቀደም ተጠናቆ ለአገልግሎት ከበቁ ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታወቀ።

የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፋንታው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የሚያስገነባቸው የትምህርት ተቋማት ፕሮጀክቶች በአብዛኛው በመጠናቀቅ ላይ ናቸው። ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጠናቀው ስራ ከጀመሩት በተጨማሪ የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።

ግንባታቸው ተጠናቆ ርክክብ የሚፈጸምባቸው ትምህርት ቤቶች በአፋር ክልል ዱብቲ፣ በጋምቤላ አኝዋክ ዞን፣ በቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ እና መተከል ዞን ፣ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ዞን ፤ በዲላ ከተማ 02 እና 06 ቀበሌዎች፣ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ከተማ እና ዋግኸምራ ዞን ሳህላ ሰለምት ወረዳ የተገነቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ግንባታቸው ቀድመው የተጠናቀቁና ርክክባቸው ተፈጽሞ ስራ የጀመሩት አምስት ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፤ በአማራ ክልል ጎንደር ሎዛ ቀበሌ፣ ደቡብ ወሎ ጦሳ ሰላማ ቀበሌ (አልብኮ ወረዳ)፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሊበን ጭቋላ ቀበለ (ቢሾፍቱ አካባቢ)፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞን ውጫሌ ወረዳ ጃክ ቀበሌ (ሙከጡሪ አካባቢ) የሚገኙት መሆናቸውንና አሁን ላይ ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ምርጫ የዕጩዎች የድጋፍ ፊርማ እንዲቀር ፓርላማውን ጠየቀ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲከናወን ቀን ለተቆረጠለት ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ፣ ዕጩዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸው የነበረው የድጋፍ ፊርማ እንዲቀርና አገልግሎት ላይ እንዳይውል እንዲደረግ ፓርላማውን ጠየቀ፡፡

በምርጫ ለመወዳደር የሚፈልግ የግልም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲን፣ ግንባርን ወይም ቅንጅትን ወክለው በዕጩነት የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች፣ ከ5,000 እስከ 750 የሚደርሱ የድጋፍ ፊርማዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸው ነበረ፡፡ ይሁንና በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የወረቀት ንክኪን በተቻለ መጠን ለመቀነስና የሚመጡ የድጋፍ ፊርማዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ካለው የጊዜ መጣበብ ጋር በተገናኘ አዳጋች ስለሚሆን፣ ፓርላማው ከግንዛቤ አስገብቶ በአዋጁ ላይ ይኼንን ጉዳይ ማሻሻያ እንዲያደርግበት ጥያቄ መቅረቡን፣ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ታኅሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ገልጸዋል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢንቨስትመንቶች ለሚደርስባቸው ውድመት ወጥ የሆነ የካሳ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው!

የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ ጉዳት ሲደርስባቸው ለደረሰባቸው ውድመት ማካካሻ የሚያገኙበት አንድ ወጥ መመሪያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን እየተዘጋጀ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።

ከዚህ ቀደም የተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ በተደጋገጋሚ በተለይም ከግጭቶች ጋር በተያያዘ ፕሮጀክቶች ሲወድሙ ፣ ሲቃጠሉ ፣ ሲጎዱ እና በነዚህ ጥፋቶች ኪሳራ ውስጥ ሲገቡ ይስተዋላል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በክሮሺያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ቢያንስ 7 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ!

በማዕከላዊ ክሮሺያ ከመዲናዋ ዛግሬቢ በደቡብ ምስራቃዊ በምትገኘው ፒትሪንጃ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የደረሰ ሲሆን ህይወታቸው ካለፉ 7 ሰዎች በተጨማሪ ከ 20 በላይ ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል፡፡በክሮሺያ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ጎረቤት ሀገራት ሰርቢያ ፣ ቦስኒያና ኸርዜጎቪኒያ እና በኦስትሪያ መዲና ቬና ድረስ ንዝረቱ ተሰምቷል፡፡የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በሬክተር ስኬል 6.4 የተለካ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ጥንታዊ የክሮሺያ ህንፃዎች የጉዳት ሰለባ ሆነዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከዳያስፖራ ትረስት ፈንድ 7 ሚሊዮን ዶላር ተሰበሰበ!

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ ማሰባሰቡን ገልፀ፡፡ፈንዱ ከ9 ሀገራትከ26ሺህ በላይ ለጋሾችን ማፍራት መቻሉንም አክሏል፡፡

በተጨማሪም 48 የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ምዕራፎችን በማቋቋም በተለያዩ መስኮች የሚያገለግሉ ከ 200 በላይ በጎ ፈቃደኞችን ማሰባሰብ መቻሉን ገልጿል፡፡

ባለፉት ሁለት አመታት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታዎችን መለየት፣ ፋይናንስ ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ሂደት የመዘርጋትበ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱንም አክሏል፡፡

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ በድጋሚ ተጀመረ!

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ኖት ቅያሬ ድጋሚ ተጀምሯል፡፡የብር ቅያሬው ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት በአዲስ አበባ ሁለት ዝነኛ የምሽት ቤቶችን ዘጋ።

በቦሌ የሚገኙት ታዋቂዎቹ ኤክሶ ኤክሶ እና በዕምነት የተሰኙት የምሽት ቤቶች በመንግስት ውሳኔ መታሸጋቸው ተገልጿል።ከቦሌ መሰናዶ ት/ቤት ጀርባ የሚገኙት ታዋቂዎቹ በዕምነት ባርና ሬስቶራንት ቁጥር 1 እና 2 እና XOXO የምሽት ክለብ በነዋሪዎች ቅሬታ ታሽገዋል።በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የሚገኙ ነዋሪዎች በአካባቢው በሚገኙ ንግድ ቤቶች በተለይም በምሽት መዝናኛዎች ድምፅ ብክለትና ሌሎች ችግሮች መማረራቸውን ወረዳው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል።

ነዋሪዎቹ ከግሮሰሪ እስከ ማሳጅ ቤት በመኖሪያ ቤት አካባቢ መኖር በማይፈቀድላቸው ንግድ ቤቶች ተማረው ፤ ቅሬታቸውን ከወረዳ እስከ ከተማ አስተዳደሩ ድረስ አቅርበዋል።በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ አልባስ ሀይሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በመኖርያ አካባቢ ለምን ፍቃድ ተሰጠ የሚለውን ክ/ከተማው ስለሚያይ ነዋሪዎቹን ወደዛ ልከናል።ድምፅ ብክለትን በተመለከተ ግን ፤ XO XO የምሽት ክለብና እና በእምነት ባርና ሬስቶራንት ከሚፈቀደው 45 ዴሲቤል በላይ ሆነው ስላገኘን ከተደጋጋሚ ምክርና ማስጠንቀቂያ በኋላ ባለመስማታቸው ትናንት አሽገንባቸዋል ብለዋል።

የምሽት ክለቦቹ ከት/ቤት ምን ያህል መራቅ አለባቸው? ከቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር ባለ የንግድ ፍቃድ አሰጣጥ ጋር በተገናኘ፣ መዝናኛዎቹ ጋር የሚቆሙት መኪኖች ስለሚበዙ በፓርኪጉ ምክንያት መተላለፍ አለመቻላቸውን፣ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል ብለዋል ሀላፊዋ።እኛ በወረዳ ደረጃ የሚመለከተውን እንፈፅማለን፣ በዚህም መሰረት 2ቱን ቤቶች በድምፅ ብክለት ምክንያት አሸገናቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ ከ100 በላይ መጠጥ ቤቶች ላይ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ባለሙያዎች ባደረጉት የድምፅ ልኬት አካባቢ እና ህብረተሰቡ የሚያዉክ ድምጽ ማዉጣታቸዉ በመረጋገጡ የማስተካከል እርምጃ እንዲወሰድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው አብዛኛዎቹ መጠጥ ቤቶች ቢያስተካክሉም
በቦሌ ክፍለ ከተማ እና በአቂቃ ቃሊቲ ክፍል ከተማ የሚገኙት 11 መጠጥ ቤቶች ከተፈቀደዉ 45 ዴስባል የድምፅ መጠን በላይ አልፍዉ እሰከ 85 ዴሲባል መጠን ሲጠቀሙ በመገኝታቸዉ መታሸጋቸው መገለፁ የሚታወስ ነው።

ከዚራ ባርና ሬስቶራንት፣ ሰለሞን ጀርመን ሀዉስ ፣ ፋልከን ላወንጂ፣ ሴራኒ ባርና ሬስቶራንት፣ አዲናስ ባርና ሬስቶራንት ፣ ዊንግ ላዉንጂ፣ፋድ ዞን፣ ኤልቢስ ትሮ ባርና ሬስቶራንት ፣ሚሚስ አዲስ ባርና ሬስቶራንት፣ ሮያል ባርና ሬስቶራንት እንዲሁም ተክላኋይማኖት ግሮሰሪ መታሸጋቸው ተገልፆ ነበር፡፡ሆኖም ግን እንደ አካባቢ ጥበቃ ሀላፊዋ እንደ ወ/ሮ አልባስ ከሆነ መመርያው ክፍተት አለበት።

በመጀመርያ ዙር የታሸገበት ከ 5 ቀን እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 5 ሺህ ብር ከፍሎ ይከፈትለታል፣ ለሁለተኛ ዙር መመርያውን ጥሶ ከተገኘ 25 ሺህ ብር ይቀጣል፣ ከዚህ በኋላ ለሶስተኛ ጊዜ መመርያውን ሲጥስ ከተገኘ ነው ንግድ ፍቃዱ የሚነጠቀው።በዛ ላይ ይሄ ሂደት የኮሚቴ ስራ ስለሆነ የራሱ ክፍተት አለው ብለዋል።ህብረተሰቡ በሚኖርበት አካባቢ ብክለት የሚያደርሱ ተቋማትን በ6713 የስልክ መስመር ጥቆማ ማድረስ እንደሚችል የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን መልዕክት አስተላልፈዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን የደህንነትና መከላከያ ም/ቤት ከኢትዮጵያ ጋር ባለው የድንበር ውዝግብ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጓል!

የሱዳን የደህንነትና መከላከያ ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ ጋር ባለው የድንበር ውዝግብ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጓል፡፡በሀገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን መሪነት በተካሔደው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎች መተላለፋቸው ተገልጿል፡፡ ይሁንና ስለውሳኔዎቹ በግልጽ የተባለ ነገር የለም፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግጭት በተመለከተ ፣ "አል ፋሻቃ አካባቢ የሱዳን ጦር የሀገሪቱን ድንበር ለማስከበር እና ለመከላከል የወሰደውን እርምጃ የደህንነትና መከላከያ ምክር ቤቱ ማድነቁን" የመከላከያ ሚኒስትሩ ጄኔራል ያሲን ኢብራሂም ተናግረዋል፡፡አንድ የሱዳን ባለሥልጣን ማክሰኞ ታህሣሥ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከአል አረብያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ላለው የድንበር ውጥረት ሰላማዊ መፍትሄዎችን እንደምትቀበል አስታውቀዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ጁማህ ኪንዳ እንደተናገሩት ሀገራቸው "ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም ትፈልጋለች ፣ ግን ድንበሯን ታስከብራለች" ብለዋል፡፡ኪንዳ “የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች በድንበር ላይ የተደረገው ውጊያ እንዲባባስ ምክንያት ሆነዋል” ሲል የከሰሰ ሲሆን “የሱዳን ጦር ምላሽ መስጠት ነበረበት” ብሏል፡፡በኢትዮጵያ ተይዞብኝ ቆይቷል ካለችው ቦታ እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን በኃይል አስመልሻለሁ ያለችው ሱዳን ፣ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት የአል ፋሻቃ አካባቢ ከፍተኛ ጦር ማሰማራቷ ይታወቃል፡፡

Via Al-ain
@YeneTube @FikerAssefa
ለጃዋር መሃመድ አራት ሲም ካርዶችን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሊያቀብል ሲል ተይዟል የተባለው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ ሃምዛ ጀማል መሃመድ ይባላል፡፡የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተጠርጣሪው ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. 1ኛው ሲም ካርድ በኦ ኤም ኤን ድርጅት ስም ማውጣቱን ጠቅሶ ሶስቱ ሲም ካርዶች ደግሞ በግለሰብ ስም የወጡ መሆናቸውን ከኢትዮ ቴሌኮም መጣራቱን ገልጿል፡፡ግለሰቡ እነዚህን ሲም ካርዶች በመያዝ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በመሄድ ጃዋር መሃመድን ልጠይቅ ነው በሚል ገብቶ ሲም ካርዶችን ለጃዋር መሃመድ ሊያቀብል ሲል መያዙንም አብራርቷል፡፡ተጠርጣሪው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ጉዳዩ እየታየ ነው፡፡
(FBC)
@YeneTube @FikerAssefa
ሚድሮክ ወርቅ በሚቀጥለው ወር ምርት ሊጀምር መሆኑ ተጠቆመ!

ከአካባቢ ብክለት ጋር በተያያዘ የምርት ፈቃዱ ከሁለት ዓመታት በላይ ታግዶበት የነበረው ሚድሮክ ወርቅ፣ በለገደንቢ የወርቅ ምርት በሚቀጥለው ወር እንደሚጀምር የሪፖርተር ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡በአካባቢው ማኅበረሰብ በተነሳ ተቃውሞ ምክንያት የማምረት ፈቃዱ ታግዶበት የነበረው ሚድሮክ ወርቅ፣ የተነሱበት ጥያቄዎች ምላሽ በማግኘታቸውና የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ማረጋገጥ በመቻሉ፣ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር እግዱን እንዳነሳለትና በቀጣይ ወር (ጥር ወር ውስጥ) የማምረት ሥራውን እንደሚጀምር ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) መናገራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ 

@YeneTube @FikerAssefa
በኢሉ አባቦር ዞን 12 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ገለጸ!

በኢሉ አባቦር ዞን 12 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ 34 የጦር መሳሪያዎችና በርካታ ጥይቶች መያዛቸውንም የኢሉ አባቦር ዞን ፖሊስ ጽ/ቤት መግለጹን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በጣልያን ገጠራማ ቦታ በግብርና ስራ ትተዳደር የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ አጊቱ ጉደታ መሞቷን በጣልያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታወቀ።

በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዳስታወቀው በአጊቱ ጉደታ ድንገተኛ ሞት ማዘኑን ገልጿል።

ኤምባሲው የግድያ ሁኔታው በቶሎ ተጣርቶ እንዲገለፅና ወንጀለኛ ተለይቶ ለፍትህ እንዲቀርብ ከጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።

አጊቱ ጉደታ በጣሊያን ገጠራማ ስፍራ መሬት ገዝታ ፍየል እያረባች፤ አይብ በማምረት ትተዳደር እንደነበረ ሪፐብሊካ የተባለ የጣልያንኛ ጋዜጣ በሰራው ዘገባ አስፍሯል።

Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኖ የፀሐይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

የ12ቱ ትናንሽ የፀሐይ ሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ፓይሌት ፕሮጀክት አንድ አካል የሆነውና ከሐረር ከተማ 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚኖ ከተማ የተገነባው የሶላር ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡የግንባታ ስራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የሚኖ ፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 225 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን የግንባታ፣ ፍተሻና የሙከራ ስራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa