YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በደቡባዊ ዳርፉር የጎሳ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ሱዳን በአካባቢው ወታደሮቿን ማስፈሯ ተሰማ!

በደቡባዊ ዳርፉር ግዛት ጎሳን መሰረት ያደረገ ግጭት ተቀስቅሶ ቢያንስ 15 ንፁሃን መገደላቸውን ተከትሎ መንግስት ከፍተኛ ቁጥር አላቸው የተባሉ የፀጥታ አካላትን በአካባቢው ላይ አስፍሯል፡፡

የዳርፉር ግዛት ከ 2003 አንስቶ ከፍተኛ ግጭት ያስተናገደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በውሃ የተነሳ የማሳሊት እና ፎልአታ ጎሳ አባላት በተደጋጋሚ ወደ ግጭት ውስጥ ይገባሉ፡፡

በዳርፉር ግጭት 300ሺ የሚጠጉ ሰዎች ሲገደሉ 2.5 ሚሊዮን ሰዎች ለስደት ተዳርገዋል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ውድመት ለደረሰባቸው ፋብሪካዎች ወትሮ ከሚመደበው ውጪ 45 በመቶ የውጪ ምንዛሪ በብሔራዊ ባንክ በኩል እንደተዘጋጀላቸው ተነገረ!

በትግራይ ክልል በነበረው ህግ የማስከበር ዘመቻ ወቅት በርካታ ፋብሪካዎች ለውድመት መዳረጋቸውን ባለሃብቶች አሳውቀዋል፡፡በርካታ ቁጥር ያላቸው ፋብሪካዎቹ ከ50 በመቶ እስከ 90 በመቶ የሚጠጋው ክፍላቸው ለውድመት መዳረጉን ለሚመለከተው አካል ያሳወቁ ሲሆን በአፋጣኝ ወደ ስራ የምንገባበትን መንገድ መንግስት ያመቻችልን ብለዋል፡፡

ጉዳዩን የሚመለከተው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በነበረው ህግ የማስከበር ዘመቻ ውድመት ደርሶባቸዋል የተባሉትን ፋብሪካዎች ለመገምገም መሞከሩ ተገልጿል፡፡

የንግድና ኢንዱስትር ሚኒስትር ድኤታው አቶ ዮሃንስ ድንቃየሁ እንደተናገሩት መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ ፋብሪካዎቹ ከእዚህ ቀደም ይፈቀድላቸው ከነበረው የውጭ ምንዛሬ አሁን ላይ 45 በመቶ ጭማሪ ተደርጎላቸው እንዲያገኙ ለማድረግ ከብሔራዊ ባንክ ጋር መግባባታቸውን ገልፀዋል፡፡

ከእዚህ ባሻገር የጥሬ አቅርቦት እቃ እና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮችን ለማሟላት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ እና በከፍተኛ ደረጃ ውድመት ደርሶባቸዋል ከተባሉት ፋብሪካዎች መካከል ዘኒት ገብስ እሸት ፤ አይካ ንግድና ኢንዱስትሪ ፤ ሼባ ሌዘር ፤ አክሎክ ጄነራል ትሬዲንግ ፤ ሳባና እርሻ እና AJJ የወተት ፋብሪካ እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

የፋብሪካዎቹ ተወካዮች እና ባለቤቶች ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር ያደረጉትን ውይይት ብስራት ሬድዮ ከስፍራው ተገኝቶ የተከታተለ ሲሆን እነዚህ ኢንዱስትሪዎች በአጭር ጊዜ ወደ ስራ መመለስ የሚችሉበት እድል ጠባብ መሆኑን ለመታዘብ ችሏል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ ተረከበ !

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ መረከቡን ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ አስታወቁ።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመውና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች የተካተቱበት ግብረ ኃይል በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል።የፀጥታ ኃይሉን የሚመሩት ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እንደገለጹት፤ የንፁሃንን ሕይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የማደን ስራው ቀጥሏል።

“በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአጭር ጊዜ የሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉም ተናግረዋል።ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በአሁኑ ወቅት በየደረጃው ከሚገኙ የማኅበረሰብ አባላትና አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን ወንጀለኞቹን በመለየት ለሕግ የማቅረቡ ስራም እንደሚቀጥል ሜጀር ጄኔራሉ ተናግረዋል።ከዚህ ጎን ለጎን የተፈናቀሉትን መልሶ የማቋቋምና የሕዝቡን የዕለት ተዕለት ኑሮ ቀድሞ ወደነበረበት የመመለስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
ሜጀር ጄኔራል አስራት ዴኔሮ “በመተከል ዞን የተጀመረው የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተልዕኮ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል” ብለዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ71,476 ተማሪዎች የተሰጠዉ የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት መሆኑን ትምህርት ቢሮው ገልጿል፡፡ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 80 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል መዛወራቸውን ትምህርት ቢሮው ይፋ አድርጓል፡፡የፈተናዉ ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች በዛሬዉ እለት የተሰራጨ ሲሆን ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ውጤታቸውን በየትምህርት ቤቶቻችው መመልከት እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በመቀሌ ከተማ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የባንክ አገልግሎት በመቀለ ከተማ መጀመሩን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ።ከንቲባው አቶ አታክልቲ ሀይለስላሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ እንዳስታወቁት፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ከሰሞኑ ባካሄደው ተከታታይ ውይይት የተነሳውን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ በተደረገው የተቀናጀ ስራ ከዛሬ ከሰአት በሁዋላ ጀምሮ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በጁንታው አማካኝነት በመቀሌ ከተማ ሆን ተብለው በተለቀቁ የህግ ታራሚዎችና ሌሎች ዘራፊዎች የተነሳ በከተማዋ ላይ የጸጥታ ችግር መኖሩን በማንሳት ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲያስተካክልላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የጠየቁ ሲሆን፤ በትናንትናው እለት በነበረው የወጣቶች ውይይትም ወጣቱ የከተማውን ሰላምና ጸጥታ ከአስተዳደሩ ጋር ሆኖ ለመጠበቅ ቃል መግባቱ ይታወሳል።

የከተማዋ ነዋሪና ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረትም የባንክ አገልግሎቱ ከዛሬ ከሰአት ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ሆኖ ደንበኞች መጠቀም መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ በየቅርንጫፎቹ ተገኝቶ ተመልክቷል።የግል ባንኮችም አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ትዛዝ እንደተላለፈላቸው የከተማዋ ከንቲባ አቶ አታክልቲ አስታውቀዋል።

Via AmanMichael Mesfin(EPA)
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተጠየቁትን መስፈርት ያላሟሉ ተጨማሪ 2 ፓርቲዎችን መሰረዙን አስታውቋል፡፡

1.የመላው ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /መኦሕዴፓ/ የመስራች ፊርማ ናሙና ማረጋገጫ ከ35 % በታች በመሆኑ እና የ1,142 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ያልተሟላ በመሆኑ፣

2. የሲዳማ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሲብዴፓ/ - 778 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ያልተሟላ በመሆኑ እና በምስክርም ስለ መረጋገጡ የቀረበ ነገር ባለመኖሩ

[NEBE]
@YeneTube @FikerAssefa
የአፋር ክልል የሶማሊ ብሄራዊ ክልል ባወጣው መግለጫ ቅሬታውን ገለፀ!

ከሰሞኑ ያጋጠውን የገዋኔ ወረዳ እና ፍሪትሊና ሪፎ ቀበሌ ያጋጠመውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የሶማሊ ክልላዊ መንግስት አንድ ሉዐላዊ በሆነ የጋራ ሀገር ውስጥ እየኖርን ግልፅ የጦርነት አዋጅ ማወጁን ቀጥሏል ሲሉ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ ኮሚኒኬሽን ዋና ሀላፊ አቶ አህመድ ከሎይታ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ትግስት ላቀው

የመግለጫውን ሙሉ ዝርዝር ከላይ በምስሉ ላይ አቅርበናል

@YeneTube @FikerAssefa
በዳውሮ ዞን የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል  ክትባት መሰጠት ተጀመረ!

በደቡብ ክል በዳውሮ ዞን ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም   የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል  ክትባት መሰጠት ተጀመረ ፡፡

ከዚህ ባለፈም በተርጫ ከተማ እና በተርጫ ዙሪያ  ወረዳ በቦጲ አራ እና በሜላ ቀበሌዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ  ስራ መሰራቱም ታውቋል።

ክትባቱ በተርጫ ከተማ በአራቱ ቀበሌዎች ተደራሽ ይደረጋሉ ተብሎ ከሚታሰበው 25 ሺህ 250 ሰዎች ውስጥ በሁለቱ ቀናት 9 ሺህ 595 ሰዎች  ክትባቱን ወስደዋል ነው የተባለው፡፡

እንዲሁም  በተርጫ ዙሪያ ወረዳ ቦጲ አራ ቀበሌ 3 ሺህ 210 ሰዎች ይከተባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን÷ በሁለቱ ቀናት ውስጥ 833 ሰዎች መከተባቸውም ተገልጿል።

በአካባቢዎቹ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች የማይተገበሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወረርሽኙ እንዳይባባስ ባለድርሻ አካላት የመከላከሉን ስራ በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል መረባረብ  እንደሚገባቸው መገለፁን ከዳውሮ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የሙለር ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተክለኪሮስ ያለአግባብ ሀብት በማፍራት የሙስና ወንጀል ፍርድ ቤት ቀረቡ!

አቶ ሙሉጌታን ፍርድ ቤት ያቀረበው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሙስና ወንጀል ምርመራ ባለሙያ ሲሆን ፖሊስ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የተጠረጠሩበትን ጉዳይ ይፋ አድርጓል፡፡ተጠርጣሪው አቶ ሙሉጌታ ለሀገረ ሰላም ኩባንያ 150 ሚሊየን ብር፣ ለሁዳድ ድርጅት ደግሞ 250 ሚሊየን ብር በጥቅሉ 400 ሚሊየን ብር በአፋር ክልል ሰመራ የጨው ማቀነባበሪያ ጅምላና ችርቻሮ ስራ በሚል 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ግምት ያለውን መክሊት ህንጻ አስይዘው ከአቢሲኒያ ባንክ ገንዘብ መበደራቸውን ጠቅሷል፡፡

ብድሩ በአግባቡ ስራ ላይ ያልዋለ እና በየደረጃው በብድር ህግ መሰረት የብድር ፕሮጀክት እየታየ የሚለቀቅ የነበረ ሲሆን የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ሳይታይ ብድሩ መለቀቁን በማንሳት ይህ አግባብነት የለውም ብሏል ፖሊስ፡፡እንዲሁም በለገጣፎ ለሪል ስቴት ኪስ በሚል 500 ካሬ ሜትር መሬት ያለአግባብ ወስደዋል ያለው ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል፡፡ብድሩ ለምን አላማ እንደዋለ እና ብድሩን ያለ አግባብ የለቀቁ የባንኩ ብድር ክፍል ባለሙያዎችን ጉዳይ እየመረመርኩ ነው ብሏል፡፡ ለተጨማሪ ምርመራም 14 ቀን እንዲሰጠው ችሎቱን ጠይቋል፡፡

አቶ ሙሉጌታ በሦስት ጠበቃ ተወክለው የቀረቡ ሲሆን ብድሩ ላይም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ብድሩን የወሰዱት ሁዳድ እና ሀገረሰላም ድርጅት ሲሆኑ በድርጅቶች ማህበራት መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ ሰባት መሰረት በስራ አስኪያጆቻቸው በኩል ነው ብለዋል፡፡ አቶ ሙለጌታ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ሳይሆኑ ባለአሲዮን እንደሆኑም ጠቅሰዋል፡፡መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ የሁለቱም ድርጅቶች ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ናቸው ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡የአቶ ሙሉጌታ ጠበቆች በበኩላቸው ከብድሩ መጠየቅ ጀምሮ እስከመፈረምና ብድሩን እስከመውሰድ ድረስ የደረሱት ስራ አስኪያጆቹ እንጅ አቶ ሙሉጌታ አይደሉም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

ከዚህ በፊትም በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ፍርድ ቤት አዞላቸው ዋስትናው ተከፍሎ ከእስር ሳይፈቱ ሌላ መዝገብ መከፈቱ አግባብ አይደለም ነው ያሉት፡፡ ፖሊስ ከዚህ በፊት የተጠረጠሩት በሽብር ወንጀል እና በገንዘብ በመደገፍ ወንጀል ነው፤ ይህ ደግሞ አዲስ ግኝት የሙስና ወንጀል ነው ሲልም ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ክርክሩን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ከታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ ፈቅዷል፡፡ይህ በእንዲህ እያለ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ለዛሬ ከሰአት በኋላ ቀጠሮ የያዘበት የአውራምባ ታይምስ ባለቤትና ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ላይ 12 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜን ለፖሊስ ፈቅዷል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ወረርሽኝ እና በወቅቱ በነበረው አንፃራዊ የሰላም ሁኔታ እንደወትሮው ሃይማኖታዊው በዓል ታዳሚ ባልተገኘበት የቁልቢ ገብርኤል በዓል ዛሬ ተከብሯል።

ከውጭ ሀገራት እና ከሀገር ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ ቦታው የሚያቀኑ እድምተኞች የሚገኙበት ሃይማኖታዊ በዓል የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚተገበሩ የጥንቃቄ መንገዶች በከፊል ይጠበቁበት እንጂ ከታዳሚው ብዛት አንፃር አስቸጋሪ መልክም ነበረው።በበዓሉ ታድመው ለዶይቼ ቬለ አስተያየት የሰጡት አቶ የማነ ክፍሌ ኮሮናን መከላከል ላይ መዘናጋት ማየታቸውን ገልፀዋል።በአጠቃላይ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እና ሰላም መደፍረስ መከበሩን የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጣልያን በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ ላለፉት ሶስት አስር አመታት ተጠልለው የቆዩ ሁለት የቀድሞ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ነፃ እንዲወጡ መፈቀዱን አደነቀች።

የጣልያን ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ዛሬ ሰኞ ባወጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ውሳኔ "ለረዥም ጊዜ ለዘለቀው ጉዳይ መቋጫ የሚያበጅ ነው" ብለዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገውን የምርጫ ሰሌዳ በተመለከተ የኦፌኮና ኢዜማ አስተያየት:

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባወጣው ረቂቅ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ የሚፈለገውን እንቅስቃሴ ለማድረግ እንደሚቸገር የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ/ኦፌኮ/አስታወቀ። የምርጫ ውሳኔውንም ወደ ፊት እንደሚያስታወቅ ገልጿል። ገዥው ፓርቲ ለምርጫው አስቻይ ሁኔታዎችን ለማስፋት እንደሚሰራ ቃል ገብቷል።

“ፍጽምነት ያለው የምርጫ ድባብ የለም” በሚል ምርጫን ማሻገር ችግር እንደማይፈታ ደግሞ ኢዜማ አስታውቋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
በቻይና ውሃን ከተማ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መቀስቀሱን የዘገበችው ጋዜጠኛ የአራት ዓመት እሰር ተፈረደባት!

የቻይና ዜግነት ያላት ጋዜጠኛ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት ከውሃን ከተማ የቀጥታ ስርጭት ዘገባዋን በማቅረብ የተያዘች ሲሆን በትላንትናው እለት የአራት ዓመት እስራት ተፈርዶባታል፡፡

የቀድሞ የሕግ ባለሙያ የሆነችው ዣንግ ዣን በተከሰተው ወረርሽኝ ዙርያ ሪፖርት በማድረጓ ችግርን በማነሳሳት ልትከሰስ ችላለች፡፡የቀጥታ ዘገባዋ እና ጽሁፏ በየካቲት ወር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው ተሰራጭተውላት ነበር፡፡ወረርሽኙን አስመልክቶ መንግስት የሰጠው ምላሽ ላይ የሰነዘረችዉ ትችት ለየቻይና መንግስት ባለሥልጣናት ትኩረት በማግኘት ለእስር ዳርጓት ቆይቷል፡፡

የ37 ዓመቷ ዣንግ እንደ ጠበቃዋ አስተያየት ከሆነ በሰኔ ወር የርሃብ አድማ የጀመረች ሲሆን በጤንነቷ ላይ ስጋት እንዳላቸዉና በአፍንጫ ቧንቧ በኩል እንድትመገብ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ከባድ ፍርድ ከተበየነብኝ ምግብ እስከመጨረሻው እምቢ ማለቱን በመቀጠል በእስር ቤት ውስጥ እንደምትሞት አሳስባለች ሲል ጠበቃዋ ሬን ኳንዩ ተናግረዋል፡፡

Bisrat FM/ስምኦን ደረጄ
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
ህወሓት በማያንሰራራበት ሁኔታ ተንኮታኩቷል ሲሉ የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል።

ጀነራሉ ይሄንን የተናገሩት በትግራይ ክልል የተካሄደው ጦርነት አሁንም እንዳልቆመ የሚገልፁ አንዳንድ አስተያየቶችን ባጣጣሉበት ምላሽ ነው።

በሌላም በኩል ንፁሃን ዜጎች የሚገደሉበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ችግር ህወሓት ቀርጿቸው ከነበሩ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው ሲሉ ኤታማዦር ሹሙ ጠቁመዋል።

በአካባቢው ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ሁለገብ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ለአሜሪካ ድምፅ አብራርተዋል።

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጋር ያደረጉት ቆይታ ከላይ ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን የድንበር ላይ ትንኮሳዋን የማታቆም ከሆነ አፀፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ኢትዮጵያ አስጠነቀቀች።

የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ ሱዳን በድንበር አካባቢ እያደረሰች ያለዉን ህገወጥ ድርጊት የማታቆም ከሆነ ኢትዮጵያ ሉኣላዊነቷን ለመጠበቅ ስትል እርምጃ ትወስዳለች ብሏል፡፡የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የሱዳን ኃይል የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በርካታ ህገወጥ ድርጊቶችን ፈፅሟል።ይህም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለዉን የህግ ማስከበር ተልዕኮ እንደ ክፍተት ተጠቅመዉ ኢትዮጵያን እና ሱዳንን ወደ ግጭት እንዲያመሩ ከከሚፈልጉ ሃይሎች የመነጨ ነዉ ብለዋል፡፡

“ኢትዮጵያ ሉኣላዊነቷን ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት ቃል አቀባዩ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ እንፈታለን ስንል ፍርሃት ከመሰላቸዉ ተሳስተዋል፤ ማንኛዉንም ጥቃት ለመመከት የፀጥታ ሃይሉ 24 ሰዓት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል” ብለዋል፡፡ቃል አቀባዩ የኢትዮጵያን ዉድቀት የሚመኙ አገራት መኖራቸዉን የተናገሩ ሲሆን ኢትዮጵያ በነጻነቷ ከመጡባት ማንንም እንደማትምር ከታሪካችን መረዳት ይኖርባቸዋልም ብለዋል።የሱዳን ህዝብ እና መንግስት ከሚጎትታቸዉ ሃይል እራሳቸውን እንዲቆጥቡም አምባሳደር ዲና አሳስበዋል፡፡

ሱዳን እና ኢትዮጵያ በበርካታ ዘርፎች ላይ ታሪካዊና መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸዉ በተደጋጋሚ ሲነገር ይደመጣል፡፡ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ሱዳን በህዳሴዉ ግድብ ላይ ያላትን አቋም መለዋወጥ ከጀመረች ሰንብታለች።አሁን ደግሞ የአገሪቱ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር በመጣስ በምእራብ ጎንደር አካባቢ በርካታ ጥፋቶችን እያደረሰ እንደሚገኝ በአካባቢው ነዋሪዎች እና አስተዳድር ተገልጿል፡፡የሱዳን ጦር እያደረገ ያለው ድርጊት ሙሉ በሙሉ የሱደን መንግስት አቋም ባይሆንም የሱዳንን ህዝብ ለዘመናት ሲገዙት የነበሩ አገራት ዛሬም ያንን ለመድገም በመፈለጋቸው መሆኑን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በየቀኑ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ወደ ሕክምና ማዕከል ከሚገቡት 10 ታማሚዎች ውስጥ በአማካይ አራቱ ሰዎች የሚሆኑት ጽኑ ሕክምና ክፍል እንደሚገቡ የሶማሌ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ የሆነው ዶክተር ዩሱፍ ተናግረዋል፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያት ህብረተሰቡ ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያለማድረጉ እንደሆነና የሚመለከታቸው አካላትም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት እየቀነሱ መምጣታቸው መሆኑ እንዲሁም የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የመጠቀም ባህል በክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋም ይሁን በሌሎች ከተሞች እየቀነሰ መምጣቱን መሆኑን ሐላፊው አክሏል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል የጅምላ ግድያና የሰብኣዊ ቀውስ ላይ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትንና ባለሥልጣናትን ያለመከሰስ መብት የሚያነሳው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ተቀምጧል፡፡

ከዚህ ቀደም እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪ ከፍተኛ ባልሥልጣናት የተያዙ ሲሆን፤ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በግድያው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የክልሉ ከፍተኛ የሲቪልና የፀጥታ ዘርፍ ባለሥልጣናት እጃቸው እንዳለበት በዳሰሳ ጥናቴ አረጋግጫለሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡ጉባኤው በመተከል ዞን በተፈፀመው ማንነትን መሰረት ባደረገ የንፁሃን ግድያ ለተገደሉና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የህሊና ፀሎት በማድረግ ጀምሯል፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል!

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነት ምስጋናው እንጅፈታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጠዋል፡፡አቶ አትንኩት የተያዙት በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት ችግር እጃቸው እንዳለበት ተጠርጥረው ነው ሲሉም ተናግረዋል።ዛሬ ረፋድ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከምክትል ኮሚሽነሩ አረጋግጫለው ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የቤኒሻንጉል ክልል ምክር ቤት የ4 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ 5 ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የአራት የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው

1. አቶ አድጎ አምሳያ
2. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ
3. አቶ ግርማ መኒ እና
4. አቶ አረጋ ባልቢድ ናቸው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa