📷: ደቡባዊ ብሪታንያ ውስጥ በፍጥነት እየተዛመተ ባለው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሃገሮች ከብሪታንያ የሚነሱ መንገደኞችን እንዳገቡ በመከልከላቸውና በደቡብ ምስራቅ ብሪታኒያ፣ አሽፎርድ አጠገብ ወደሚገኘው ዶቨር ወደብ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ፣ የእቃ ጭነት ማመላለሻ መኪናዎች ተሰልፈው የቆሙበትን ኤም 20 የተሰኘ መተላለፊያ ፖሊሶች ጥበቃ እያደረጉ ነው።
በክልከላው ምክንያት መንቀሳቀስ ያልቻሉት ወደ አውሮፓ በመጓዝ ላይ የነበሩት የጭነት መኪናዎች ከብሪታንያ የመውጣት ፈቃቶ ቶሎ እናገኛለን ብለው በተስፋ እየተጠባበቁ ነው።
የደቡብ ምስራቅ ብሪታኒያ ዋና የወደብ መተላለፊያ በሆነው አውራ ጎዳና ላይ እና የተለመደውን አገልግሎት መስጠት ባቆመው ወደብ ላይ የተሰለፉት ከ 1500 የሚበልጡ መኪናዎች በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ምክንያት ብሪታኒያ ምን ያክል እንደተገለለች ያመላክታል።
[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው ከኢትዮጵያ መንግስት ተጻራሪ በመሆን እያደረጉት ያለው ተግባር ተገቢ አይደለም ሲሉ በሲውዝርላንድ ጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ ተናገሩ።
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እያደረጉት ባለው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ መንግስት ደስተኛ አይደለም ያሉት አምባሳደር ዘነበ፤ ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ መንግስት አቅራቢነትና ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ መሆናቸውን አስታውሰዋል።ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ድጋፍ ጭምር አሁን ላሉበት ከፍተኛ የስራ ሃለፊነት መብቃታቸውን ያስታወሱት አምባሳደሩ፤ በዚህ ከፍተኛ ቦታ ላይ ሆነው በእንደዚህ አይነት ወገንተኝነት የታየበት ተግባር ላይ መሰማራታቸው ደስተኞች አይደለንም ብለዋል።ይህንን የዶ/ር ቴድሮስ ተግባር መንግስት አግባብ ባለው መልኩ የሚሄድበትና ምላሽ የሚሰጥበት ይሆናል” ሲሉም ነው አምባሳደሩ የገለጹት።
[EPA]

በቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት ባደረሱ 42 ፀረ-ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ ተወሰዷል ተባለ!
በክልሉ መተከል ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት ያደረሱ 'ፀረ-ሰላም' ኃይሎች ላይ መከላከያ ሰራዊት ተከታትሎ በወሰደው እርምጃ 42ቱ ተደምስሰዋል ተብሏል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት በወሰደው እርምጃም ጸረ-ሠላም ኃይሎች ለጥፋት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና እና ቀስቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

የአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ለ“ትንሿ ኢትዮጵያ” ህጋዊ እውቅና ሰጠች!
በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ “Little Ethiopia ወይንም “ትንሿ ኢትዮጵያ” ለሚባለው አካባቢ የተሰጠው ስያሜ ህጋዊ እውቅና ማግኘቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።አምባሳደር ፍፁም አረጋ የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አስተዳደር እና የአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለ"ትንሿ ኢትዮጵያ" እውቅና እንዲያገኝ ላበረከቱት ድጋፍና አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።በዋሽንግተን ዲሲ ለ"ትንሿ ኢትዮጵያ" የተሰጠው እውቅና ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማሳደጉም በላይ በማህበራዊ እና በባህላዊ ጉዳዮች ወዳጅነታቸውን እንደሚያጎለብተው ነው አምባሳደሩ በማህበራዊ ገፃቸው የገለፁት።

ብሪታንያ ውስጥ በደቡብ አፍሪካ በተከሰተው ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዓይነት የተያዙ 2 ሰዎች መገኘታቸው ተሰማ፡፡
በደቡብ አፍሪካው ልውጥ የኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ብሪታንያውያን በቅርቡ ወደዛው ተጉዘው የተመለሱ እንደሆኑ ቢቢሲ ፅፏል፡፡በብሪታንያም ከደቡብ አፍሪካው የተለየ ልውጥ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱ የተነገረው ሰሞኑን ነው፡፡
በልውጦቹ ቫይረሶች መገኘት የተነሳ ሁለቱም አገሮች የእርስ በርስ የጉዞ እገዳ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ብሪታንያውያን የጤና ሊቃውንት የደቡብ አፍሪካውን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ማጥናት እንደጀመሩ ተሰምቷል፡፡ሁለቱም አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ልውጥ ዝርያዎች በፍጥነት እየተስፋፉ ነው ተብሏል፡፡
✍Sheger

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ያካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተጀመረው ከማላዳ 3 ሰዓት አካባቢ ሲሆን እስከ 5 ሰዓት ድረስ በዝግ ተወያይቷል፡፡
የመገናኛ ብዙሃን እንዳይገቡ በተከለከለበት እና 2 ሰዓት በወሰደው የውይይት ጊዜው የብሔር ማንነትን መሰረት አድርጎ እየተፈፀመ ያለው ግድያ እየተባባሰ ስለሄደበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉዳይ እንደሆነ ከአንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ሸገር ሰምቻለው ብሏል፡፡
ዝርዝር ጉዳዩንና እንዴት ያለ ስምምነት ላይ እንደደሱ ግን ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ለእለቱ በያዘው አጀንዳ ላይ መወያየት የጀመረው ምክር ቤቱ የተለያዩ አጀንዳዎችን ተመልክቷል፡፡
የመጀመሪያ ያደረገው ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 3 አዳዲስ የቦርድ አባላት ሹመት የተመለከተውን ነው፡፡
በዚህም መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እጩ ሆነው የቀረቡት ዶ/ር አለሙ ስሜ የኢቢሲ የቦርድ ሰብሳቢ፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄና አቶ የሸዋስ አሰፋ ደግሞ የቦርድ አባል ሆነው ሹመታቸው ፀድቆላቸዋል፡፡በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈፅመው ሀላፊነታቸው ተረክበዋል፡፡
በዛሬው የምክር ቤቱ 7ኛ መደበኛ ስብሰባ የመገናኛ ብዙሃን ረቂቅ አዋጅንም የተመለከተ ሲሆን ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡
መደበኛ ስብሰባው የቀጠለ ሲሆን የጤና ሚኒስትሯን ለዶ/ር ሊያ ታደሰ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቦ ማብራሪያና ምላሽ ማድመጥ ጀምሯል፡፡
Via Sheger FM

አዲስ የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ መንግስት በክልሉ የሚገኙ የመንግስትና የክልል መስሪያቤቶች በሀላፊነት ደረጃ ያሉ ሠራተኞችን በሙሉ ሊያነሳ መሆኑን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤቱ ሻለቃ አዲስ ተድላ እና ሻለቃ ብርሃኑ ባየህ ከጣሊያን ኤምባሲ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጠ!
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም የክስ መዝገብ የተከሰሱና በጣሊያን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለ30 ዓመታት በጥበቃ ስር የነበሩ ሻለቃ አዲስ ተድላና ሻለቃ ብርሃኑ ባየህ ጉዳይ ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት ሻለቃ አዲስ ተድላና ሻለቃ ብርሃኑ ባየህ ከጣሊያን ኤምባሲ በአመክሮ እንዲለቀቁ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ትዕዛዙ በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለጣሊያን ኤምባሲ፣ እንዲሁም ለሻለቃ አዲስ ተድላና ለሻለቃ ብርሃኑ ባየህ እንዲደርስ ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡በሻለቃ አዲስ ተድላና ሻለቃ ብርሃኑ ባየህ ላይ የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ነበረ ሲሆን፣ በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ለሁለቱ የሞት ፍርድን ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮላቸው የእድሜ ልክ እስር የተፈረደበት ሰው ደግሞ በአመክሮ መፈታት የሚችለው 20 ዓመት ውስጥ እስር ላይ መሆኑን ከግምት በማስገባት ውሳኔው የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡
Via EBC

አድማሱ ሞርካ(ከላይ የሚታዩት) የተባሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለሥልጣን ከመተከል ዞን ግድያ በተያያዘ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። የክልሉ ገጠር መንገድ እና ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ነበሩ። አድማሱ ሞርካ በተለያዩ ጊዜያት የመተከል ዞን አስተዳዳሪ፣ የአካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር ቢሮዎችን በኃላፊነት መርተዋል።
በተመሳሳይ በነሐሴ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የጋራ ግዥ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ገመቹ አመንቴ(ከታች የሚታዩት) እንደታሰሩ ክልሉ አስታውቋል። የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባ ነበሩ፤ የታሰሩት ትናንት አምስት ዛሬ ሁለት በአጠቃላይ 7 ባለሥልጣናት መሆናቸው ነው።
Via Eshete Bekele

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አዲስ የካቢኔ አባላትን ይፋ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የጊዜያዊ አስተዳደሩ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ካሳ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ስራ ጀምረዋል፡፡በክልሉ ከሚያስፈልጉ 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ መጀመራቸውንም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1.ዶ/ር ካህሣይ ብርሃኑ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ
2.ኢንጂነር አሉላ ሃብተአብ የኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ
3.ዶክተር ፋሲካ አምደ ስላሴ የጤና ቢሮ ሃላፊ
4.አቶ አበራ ንጉሴ የፍትህ ቢሮ ሃላፊ
5.ወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ
6.አቶ ዮሴፍ ተስፋይ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ
7.ዶክተር ተስፋይ ሰለሞን የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
8.ዶክተር ገብረህይወት ለገሠ የውሃ ጥናትና ዲዛይን ቢሮ ሃላፊ
9.አቶ ሰለሞን አበራ የውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ
10.አቶ አብርሃ ደስታ የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ
11.አቶ ገብረመስቀል ካሣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ሃላፊ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል፡፡
ሌሎች ያልተሟሉ የካቢኔ አባላት በቀጣዮቹ ሳምንታት ተሟልተው ወደ ስራ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

በትግራይ ክልል የጦር መሳሪያ የመሰብሰብ ሂደቱ በሰላም እየተከናወነ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮምሽን አስታወቀ፡፡
በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ህግ ለማስከበር በተደረገው ዘመቻ በክልሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራ አቁመው የቆዩ ቢሆንም አሁን ላይ ግን በክልሉ ሰላም መስፈኑን ተከትሎ ወደ ስራ መግባታቸው ተነግሯል፡፡ሰላምን ለማስፈን በተወሰደው ርምጃ አሁን ላይ ህገወጥ የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦችን በመጠቆም የክልሉን ሰላም ለማስከበር የጦር መሳሪያ እተሰበሰበ እንሚገኝ የፌደራል ፖሊስ ኮምሽን አታውቋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጄላን አብዲ ለአሀዱ እንደተናገሩት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ በጋር በወሰዱት አሰሳ የጦር መሳሪያ እየተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ የጋራ ተልዕኮ ይዘው እየሰሩ ሲሆን በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና ለሽብር የተዘጋጁ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አቶ ጄላን አስታውቀዋል፡፡
[አሐዱ ሬዲዮ]

ምርጫ ቦርድ የመጪውን ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ነገ ይፋ ሊያደርግ ነው!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጪውን ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ በነገው ዕለት ይፋ ሊያደርግ ነው። ቦርዱ በምርጫ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ከ47 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ለመምከር ለነገ ስብሰባ ጠርቷል።
በአዲስ አበባው ራዲሰን ብሉ ሆቴል በሚካሄደው በነገው የምክክር መድረክ ላይ፤ የድምጽ መስጫ ቀንን ጨምሮ ዝርዝር የምርጫ ክንውኖችን የያዘ የጊዜ ሰሌዳ ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚቀርብ የቦርዱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሶልያና ሽመልስ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት መጨረሻ ሊካሄድ ቀን ከተቆረጠለት በኋላ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የተራዘመው ስድስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ፤ በያዝነው ዓመት ግንቦት ወር መጨረሻ አሊያም ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ እንደሚካሄድ ቦርዱ ቀደም ሲል ጠቁሞ ነበር።
Via Ethiopia Insider

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ኢትዮጵያንም እንደሚያሰጋ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
በእንግሊዝና ደቡብ አፍሪካ የተገኘው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ኢትዮጵያን ያሰጋታል ተብሏል።የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የአስቸኳይ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ 19 ምላሽ ምክትል አስተባባሪ አቶ ዘውዱ አሰፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የኮሮና ቫይረስ ራሱን ቀይሮ ሊመጣ እንደሚችል ይጠበቅ ነበር ብለዋል፡፡
ሆኖም ግን አሁን የተገኘው ቫይረስም እንደሌሎች የአለም ሀገራት ሁሉ ኢትዮጵያንም ያሰጋታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ቫይረሱ እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ ስለመግባቱ የሚያመላክት መረጃ የለም ያሉት አቶ ዘውዱ ህብረተሰቡ እራሱን ከቫይረሱ መከላከል የሚያስችሉ የመከላከል እርምጃዎችን ማድረጉን እንዲቀጥል አሳስበዋል።ለዚህም የቫይረሱ አሁንም ያልታወቁ ባህሪያት መኖርን እንደምክንያት ጠቅሰዋል፡፡
ሆኖም አስቀድሞ ለመከላከል ጤና ሚኒስቴርና ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንዳለ ተናግረዋል።አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለመጀመርያ ጊዜ በእንግሊዝ የተከሰተ ሲሆን አገሪቱ የቫይረሱ ስርጭት ከአቅሟ በላይ መሆኑን ተከትሎ በርካታ አገራት የጉዞ እገዳ መጣላቸውን ቀጥለዋል።ይህ አዲስ የቫይረስ ዝርያ እስካሁን ከእንግሊዝ ውጭ በዴንማርክ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ አሜሪካ ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎች አገራት መከሰቱን የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያስረዳል።አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ከቀድሞው በ70 በመቶ የመሰራጨት እድል እንዳለውም ድርጅቱ ገልጿል።
[Ethio FM]

ኢትዮጵያ የፓሪስ ክለብ ከተባለው ማኅበር አባል ከሆኑ አበዳሪ ሃገራት የተሰጣትን ገንዘብ የምትመልስበት የጊዜ ገደብ እንደተራዘመላት ማኅበሩ አስታወቀ። ይኽው የዓለም ዓቀፍ አበዳሪዎች ማኅበር ዛሬ እንዳስታወቀው፣ ኢትዮጵያ የብድር መመለሻ የጊዜ ገደቡ እስከ ጎርጎሮሳዊው ሰኔ 30 ቀን 2021 ዓመተ ምህረት ተራዝሞላታል። የኢትዮጵያን የብድር መመለሻ ጊዜ ያራዘሙት የፓሪስ ክለብ አባላት ፈረንሳይ፣ ኢጣልያ ፣ ጃፓን፣ የኮሪያ ሪፐብሊክና የሩስያ ፌደሬሽን መሆናቸውን ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
[Reuters/DW]
@YeneTube @FikerAssefa
[Reuters/DW]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
videotogif_2020.11.17_05.08.23.gif
1.2 MB
📌አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው ትሪትመንት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ👉🏼 አላድግም ብሎ ለቀረ
👉🏼 ራሰ በርሃ ለሆነ
👉🏼 ወደራሰ በርሃነት የተጠጋ ለሳሳ ፀጉር
👉🏼 ወደውስተጥ ለገባ ፀጉር
👉🏼 ፐረም ወይም ጄል ለጨረሰው ፀጉር
👉🏼ላሽ ለበላው #ፂም #ፀጉር
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን ☞@Brandlife1
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] {Wireless Wifi router}+ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡➡️ ☎️+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g

TOP book series 📚ቶፕ የተማሪዎች አጋዥ መፅሀፍት
📌ከ 1-12 ክፍል በ ተለያዩ ቋንቋ የተዘጋጀ
📌በ ኦሮምኛ
📌በ አማርኛ
📌በ እንግሊዘኛ በሁሉም አይነት ትምህርት የተዘጋጀ
- maths chemistry biology physics ...
📌ለ 8 እና 12ኛ ክፍል ፈተና የሚያዘጋጁ
📌ለ ልጆችም 20 አይነት ተረት መጽሀፍት ታትሞዋል
❗️❗️በሁሉም መፅሀፍት ቤት ይጠይቁ
ዋና አከፋፋይ : ኤደን መጽሀፍት ቤት
* * መገናኛ ሀይሌ ህንፅ ፊት ለ ፊት
📞 0911238057
0912732493
@TOPBOOkSERIES
📌ከ 1-12 ክፍል በ ተለያዩ ቋንቋ የተዘጋጀ
📌በ ኦሮምኛ
📌በ አማርኛ
📌በ እንግሊዘኛ በሁሉም አይነት ትምህርት የተዘጋጀ
- maths chemistry biology physics ...
📌ለ 8 እና 12ኛ ክፍል ፈተና የሚያዘጋጁ
📌ለ ልጆችም 20 አይነት ተረት መጽሀፍት ታትሞዋል
❗️❗️በሁሉም መፅሀፍት ቤት ይጠይቁ
ዋና አከፋፋይ : ኤደን መጽሀፍት ቤት
* * መገናኛ ሀይሌ ህንፅ ፊት ለ ፊት
📞 0911238057
0912732493
@TOPBOOkSERIES
ሞትን በፍጹም መላመድ የለብንም - ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ በደረሰው የህይወት ህልፈትና አካል ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ሞትን በፍጹም መላመድ የለብንም ብለዋል።
በመተከል በንጹሃን ዜጎች፥ ሴቶች፥ ሕጻናት እና ቤተሰብ ላይ በየጊዜው የሚፈጸሙ ግድያ በጽኑ የሚወገዝ ነው ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ከታሪክ ሳይማሩ በእሳት መጫወት አዙሪት ውስጥ የሚከተን ስለሆነ ተቀናጅተን እንድንሰራ በአደራ ጭምር እጠይቃለሁ ብለዋል።

ባለቤታቸውንና 9 ልጆቻቸውን ያጡት አርሶ አደር
የ41 ዓመቱ አርሶ አደር አቶ በላይ ዋቅጅራ ነዋሪነታቸው ታጣቂዎች በድንገት ጥቃት ፈጽመው ከ120 በላይ ሰዎች በተገደሉባት የበኩጂ ቀበሌ ውስጥ ነው።በጥቃቱ በሰዓታት ውስጥ ባለቤታቸውና 9 ልጆቻቸው ተገድለዋል። አቶ በላይ "ባለቤቴ፣ 5 ሴት ልጆቼ እና 4 ወንድ ልጆቼ ናቸው የተገደሉት" ይላሉ በሐዘን በተሰበረ ድምጽ።ቤተሰቡ በእንቅልፍ ላይ እንዳለ ቤታቸው ላይ በተከፈተው ተኩስ መላው ቤተሰባቸውን ያጡት አቶ በላይ ወገባቸው ላይ በጥይት ተመትተው አሁን ቡለን ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ።
"ረቡዕ ሌሊት 12 ሰዓት አካባቢ መጥተው ከበቡን። ከዚያም በር ሰብረው ገቡና ተኩስ ከፈቱብን። አስሩንም የቤተሰቤን አባላት አጠገቤ ነው የገደሏቸው" ይላሉ።ለ27 ዓመት በትዳር አብረው በመኖር አስር ልጆች ያፈሩት የባለቤታቸው ስም ኦብሴ ፉፋ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ በላይ ጥቃት ፈጻሚዎቹ "ከገደሏት በኋላ አንገቷ ላይ የነበረውን ወርቅ ወስደው ሄዱ" በማለት ገልጸዋል።አርሶ አደሩ አቶ በላይ ሐዘናቸው ከባድ ነው። በግፍ የተጨፈጨፉትን የልጆቻቸውን ስም ደጋግመው ይጠራሉ።
ቢቢሲ ሲያናግራቸውም "ከትልቋ ጀምሬ የልጆቼን ስም ልዘርዝርህ. . . ሹመቴ በላይ የጀመሪያ ሴት ልጄ ናት። ከዚያ በኋላ ደራርቱ በላይ፣ ቀጥላ ሲዲቄ በላይ፣ ቀጥላ ጸሃይነሽ በላይ . . ." እያሉ ሳግ ቢተናነቃቸውም አላቋረጡም።ከእንባቸው ጋር እታገሉ "የወንዶቹ ታላቅ መገርሳ ይባላል። ቀጥሎ አያና በላይ እና ደረጄ በላይ። ኤሊያስ የመጨረሻው ልጄ ነው" እያሉ እንባቸው ገነፈለ።ብቻቸውን የቀሩት አባት ቆስለው ሆስፒታል ናቸው።
በጭካኔ የተገደሉት ባለቤታቸውና ልጆቻቸውን ማን እንደሚቀብራቸው ያሳስባቸዋል። "ሰው ሁሉ ከአካባቢው ሸሽቶ ወጥቷል። ማን ይቅርበራቸው? በሸራ ተጠቅልለው ነው ያሉት" ብለዋል።የአስር ልጆች አባት የነበሩት አቶ በላይ አንዲት ልጃቸው ተርፋለች "እንደ አጋጣሚ አጎቷ ጋር ወንበራ ከተማ ሄዳ ነው የዳነችው። ከቤተሰቡ እሷ ብቻ ናት የተረፈችው።"ረቡዕ ጎህ ከመቅደዱ በፊት የተኩስ ድምጽ በአካባቢያቸው መስማታቸውን የሚገልጹት አርሶ አደሩ "ባለቤቴን በጥይት ሲመቱ እሷን እከላከላለሁ ብዬ ስሄድ እኔንም መቱኝ። ከዚያ ሮጥኩ። እኔን ፍለጋ ሲመጡ ዝም ብዬ ተኛሁ። ሳያገኙ አለፉ" ይላሉ ከጥቃቱ እንዴት እንደተረፉ ሲያስረዱ።ጥቃት አድራሾቹ ከሁኔታቸው ወታደር እንደሚመስሉና ጥይት በሻንጣ መያዛቸውን የሚናገሩት አቶ በላይ "በዓይን የምናቃቸው ሰዎች አሉበት። አንዳንዶቹን መልካቸውንም አይተን አናውቅም" ይላሉ።
ከጥቃቱ ለማምለጥ የሮጡ ሰዎችን በጥይት ተኩሰው እንደገደሏቸውና ከጎረቤታቸው ከሚገኝ አንድ ቤት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን "ከጎረቤቴ አንድ ጎጃሜ ቤት 13 ሰው ታርዷል" ብለዋል።"ይሄ ይከሰታል ብለን አልጠበቅንም። መንግሥት አካባቢያችን 'ሰላም ነው'፣ 'የልማትና የእድገት ቦታ ነው'፣ 'እናንተን የሚነካ የለም፤ ሥራችሁን ሥሩ' ብለው አታለው ጨረሱን።"በጥቃቱ ከአቶ በላይ ቤተሰብ በተጨማሪ በርካታ ሰው ተገድሏል። ቤቶች ተቃትለዋል። እሳቸው እንደሚሉት "መከላከያ ገባ እንጂ አንድም ሰው አይርፍም ነበር"።
"እኔ አካባቢ 80 አስክሬን ተቆጥሯል። ሜዳ ውስጥ ገና ያልተቆጠረ አስክሬንም አለ። እንዲህ አይነት ነገር አይተን አናውቅም። እኔ እንኳን የጦር መሳሪያ ጦር የለኝም። መንግሥት ሰላም ነው እያለ አታለለን። እኛ ምንም የምናወቀው ነገር የለም" ሲሉ በምሬት ለቢቢሲ ተናግረዋል።ባለቤታቸውንና ዘጠኝ ልጆቻቸውን በግፍ የተነጠቁት አቶ በላይ ተስፋ የቆረጡ ይመስላሉ።"ከዚህ በኋላ ሰው እዚያ ይኖራል ብዬ አልገምትም። አንዳንዶች ንብረትም ሰብስበው ወጥተዋል። ሰው ተስፋ ቆርጧል። ከእንግዲህ ሰው እዚያ ሰፍሮ የሚኖር አይመስለኝም።"
Via BBC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን በአመክሮ እንዲለቀቁ ያሳለፈው ውሳኔ የትኛውንም ወገን እንደማይጎዳና የህግ ጥሰት እንደሌለበት ተናገሩ!
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በሰብዓዊ መብት መርኅ አስተሳሰብ የሞት ቅጣት በጣም ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስለሚያስከትል ወደ እድሜ ልክ እሥራት መቀየሩ ተገቢና ፍትሐዊ እርምጃ ነው።
በቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናት ላይ የተወሰነው ፍርድም ሕጉን ተከትሎ የተፈጸመ ሂደት ነው። እድሜ ልክ ቅጣት የሚፈረድበት ሰው 20 ዓመታት ከታሰረ በኋላ በአመክሮ ሊለቀቅ እንደሚችል የሚደነግግ ሥርዓት በመኖሩ ውሳኔው ማንንም የማይጎዳና የሕግ ጥሰትም የሌለበት ነው።
እንደ ዶክተር ዳንኤል ገለጻ፤ የቀድሞ መንግስት ባለ ሥልጣናት የነበሩ ሰዎች በፍርድ ቤት ጥፋተኛነትና የቅጣት ውሳኔ ከተወሰነባቸው በኋላ የሞት ቅጣት ወደ እድሜ ልክ እስራት ሲቀየር የመጀመሪያው አይደለም። ከዚህ በፊትም የእስር ዘመናቸውን ጨርሰው የተለቀቁ ብዙ ታሳሪዎች የሞት ቅጣቱ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮላቸው ነው የእስር ዘመናቸውን ያጠናቀቁትና ከእስር የወጡት።