YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ በአካባቢው የተከሰተውን የፀጥታ ችግር መፍታት በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት ተካሄዷል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
አሮጌው የብር ኖት በትግራይ ክልል እያገለገለ መሆኑ ተገለፀ!

በተቀረው የአገሪቱ ክፍል የመገበያያ ጊዜው ያበቃለት አሮጌው የብር ኖት በትግራይ ክልል ከአዲሱ ጋር በአንድ ላይ እያገለገለ እንደሆነ ካፒታል ዘግቧል።በትግራይ በነበረው ጦርነት ምክንያት ባንኮች እስካሁን ዝግ እንደሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በነዚያ ጊዜያት በወረቀት አገልግሎት በመሰጠቱና ያ ወደ ወደ ሲስተም ገብቶ ሲያልቅ ባንኮች እንደሚከፈቱ መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የወሳኝ ኹነት አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ!

በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት አገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ ወሳኝ ኹነት ኤጀንሲ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ መደረጉን የአዲስ አበባ ወሳኝ ኹነት ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።የአዲስ አበባ ወሳኝ ኹነት ኤጀንሲ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደተደረገ ለአብነትም መታወቂያ ፣ የጋብቻ ሰርተፍኬት ፣ ያላገባ ሰርተፍኬት ፣ የልደት ሰርተፍኬት ፣ ላይ ዋጋ ማሻሻያ እንዳደረገ ኤጀንሲው ለአዲስ ማለዳ አስረድቷል።

ለዲጂታል መታወቂያ ማሳተሚያ የሚወጣው ወጪ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ እና ከዚህ ቀደም ደንቡ ባለመሻሻሉ ምክንያት በ20 ብር መታወቂያ ሲሰጥ እንደነበር አስታውቋል።ከዚህ በፊት የነበረው የመታወቂያ ዋጋ በወረቀት ሲሠራ የነበረ ዋጋ እንደሆነና ነገር ግን አሁን የሚሰጠው የመታወቂያ ዓይነት ዲጂታል መታወቂያ ወይም የዲጂታሉ ማንዋል ስለሆነ የነበረው ዋጋ የሚወጣውን ወጪ መሸፈን ስለማይችል ማሻሻያ የተደረገበት መሆኑን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጭማሪውም አዲስ የሚያወጣ ፣ የጠፋበት ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ ፣ በወቅቱ ያወጣ ፣ ጊዜ ገደቡ ያለፈበት እያለ ዋጋው እንደሚለያይ ጠቁመዋል።

ለአብነትም በአሁኑ ሠዓት መታወቂያ ለማውጣት አዲስ ዲጂታል መታወቂያ 100 ብር ፣ የዲጂታሉ ማንዋል (በወረቀት የሰፈረ ነገር ግን ደግሞ የራሱ መለያ ቁጥር ወይም ባር ኮድ ያለው) 80 ብር ፣ ዲጂታል መታወቂያ የጠፋበት 200 ብር ፣ የዲጂታሉ ማንዋል የጠፋበት ደግሞ 150 ብር እንደሚከፈል ለማወቅ ተችሏል።

የጋብቻ ሰርተፍኬት ለማውጣት ኢትዮጵያዊ ከሆኑ ወቅታዊ ምዝገባ 120 ፣ የዘገየ ምዝገባ 200 ብር ፣ የጊዜ ገደብ ያለፈበት 250 ብር ፣ ለእርማት ለእድሳት 150 ብር ፣ ሲሆን ከተጋቢዎች አንዱ ኢትዮጵያዊ ከሆነ እና በወቅቱ ካወጣ 600 ፣ ብር ሁለቱም የውጪ አገር ዜጋ ከሆኑ አንድ ሺሕ ሀምሳ ብር ይከፈል።

ያላገባ ሰርተፍኬት ለማውጣት ኢትዮጵያውያን ከሆኑ 200 ብር ፣ እድሳት ግልባጭ 250 ብር ፣ ለትውልደ ኢትዮጵያውያን ያላገባ ለማውጣት 400 ብር እንደሆነ አዲስ ማለዳ ከወሳኝ ኹነት ኤጀንሲ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

[@addismaleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕግ ማስከበር ያልቻሉ አመራሮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሕግ የበላይነትን ማስከበር ያልቻሉ የክልልና የፌዴራል አመራሮች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ነዋሪዎች ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት ለማድረግ መጓዛቸው ይታወቃል፡፡በመከተል የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ እርቀ ሰላምን ጨምሮ ሌሎች የመፍትሔ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውም ተገልጿል፡፡በውይይቱ ላይ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

(ኢዜአ)
@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤቱ ተሻሽሎ ለቀረበው የእነ እስክንድር ነጋ ክስ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ!

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ተሻሽሎ የቀረበውን ክስ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወይዘሮ ቀለብ ሥዩም እና ወይዘሮ አስካለ ደምሌ ይገኙበታል።ተከሳሾቹ ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በተለይ በአዲስ አበባ በተፈጠረው ሁከትና ግጭት ተጠርጥረው ነው ክስ የተመሰረተባቸው።

ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስም እነ አቶ እስክንድር ነጋ የፌስቡክ አካውንቶችን ለማኅበራዊ ሚዲያዎችና ለሌሎች መገናኛ ዘዴዎች እንዲሁም ለአባሎቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው በመስጠት ስም ማጥፋታቸውን ገልጿል።ይሁንና የፌስቡክ ስያሜውና ሚዲያዎቹ በግልጽ ተጠቅሰው ባለመቅረባቸው አቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።በዚሁ መሰረት አቃቤ ሕግ የተሻሻለውን ክስ ዛሬ በጽሑፍ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተሻሽሎ የቀረበውን ክስ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለታሕሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

(ኢዜአ)
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ለሚከሰቱ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ሰዎችን ለመያዝ የቤት ለቤት አሰሳ መጀመሩ ተሰማ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕግ ማስከበር ያልቻሉ አመራሮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ረፋዱን አስታውቀው ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ነዋሪዎች ጋር ማክሰኞ ረፋዱን ውይይት አድርገዋል።በውይይቱ በነዋሪዎች ዘንድ ለሰላምና ለአንድነት ያለውን ፍላጎት ስለማስተዋላቸው በመጥቀስ፤ ‹‹ይህንን ፅኑና አስተዋይ ሕዝብ ይዘን ችግሮቹን እንዳይደገሙ አድርገን እንፈታቸዋለን›› ሲሉ አክለዋል።በመተከል ተደጋጋሚ የሆነ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ክልል ባለስልጣናትን በመግለጫ እያዋቀሰ ይገኛል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ሁለተኛዋን ሳታላይት አመጠቀች፡፡

ኢትዮጵያ ኢቲ ስማርት አር ኤስ ኤስ ( ET-Smart-RSS )የተባለች ሳተላይት ማምጠቋን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በማህበራዊ ገጹ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አዲስ ፓስፖርት መስጠት አቆመ።

ኤጀንሲው እንዳስታወቀው በዋናው ዳታ ቤዝ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አዲስ ፓስፖርት ማውጣት ለጊዜው ማቆሙን ገልጿል።በመሆኑ ደንበኞች ኤጀንሲው ባጋጠመው የሰርቨር ችግር ምክንያት የተቋረጠው አገልግሎት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈቶ ወደ ቀደመ አገልግሎቱ እንስኪመለስ በትእግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

የኤጀንሲው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስታዳደር ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፍራኦል ጣፋ እንደተናገሩት ኤጀንሲው ካጋጠመው የሰርቨር ችግር ውጪ በድረ-ገጽ አማካኝነት የሚሰጠው የፓስፖርት አገልግሎት አልተቋረጠም ብለውናል፡፡በኤጀንሲው ዋና ሰርቨር ላይ ያጋጠመው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በኤጀንሲው ድረገጽ ላይ በመግባት ቀጠሮ ማያዝ እንደሚችሉ አቶ ፍራኦል ነግረውናል።ያጋጠመውን ችግር ዛሬ ወይንም ነገ አልያም በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ለመፍታት እየሰራ መሆኑንም ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ከሚኖሩ ቤተ እስራኤላዊያን ውስጥ 2 ሺሕ የሚሆኑትን እስከ ታኅሣሥ 2014 ወደ እስራኤል ለመውሰድ አቅዶ እየሰራ መሆኑን የእስራኤል መንግሥት አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞራሽ ለአሐዱ ቴሌቪዥን ሲገልፁ፤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት ማገርሸቱን ተከትሎ የማጓጓዝ ሂደቱ ላይ እክል ፈጥሯል ብለዋል።ከ2 ሳምንት በፊት 316 ቤተ እስራኤላዊያን ወደ አገሪቱ መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ቤኔ ጋንትዝ አቀባበል እንዳደረጉላቸው አይዘነጋም።በሌላ በኩል ከኮቪድ 19 ክትባት ጋር ተያይዞ እስራኤል አዲስ የክትባት ዓይነት ለማበልፀግ በሂደት ላይ እንዳለች በመጥቀስ፤ በጉዳዩ ላይ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ተባብሮ የመሥራት እቅድ እንዳላት አክለዋል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
ትእምት (ኢፈርት) በጥቂቶች ተይዞ ቢቆይም የህዝብ ሃብት ስለሆነ ስራው እንዲቀጥል መንግስት መወሰኑን ዶ/ር አብርሃም በላይ አስታወቁ!

ትእምት (ኢፈርት) ምንም እንኳ በጥቂቶች ተይዞ ቢቆይም የህዝብ ሃብት ስለሆነ ስራው እንዲቀጥል መንግስት መወሰኑን የትግራይ ብልፅግና ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ አስታወቁ።ዶክተር አብርሃም ዛሬ ለጋዜጠኞች በመቐለ ከተማ በሰጡት መግለጫ ÷ትእምት (ኢፈርት) በጥቂት የጁንታው አባላት ተይዞ ቆይቷል ብለዋል።ይሁን እንጂ ተቋሙ የህዝብ ሃብት ስለሆነ ስራው እንዲቀጥል መንግስት ወስኗልም ነው ያሉት።ዶክተር አብርሃም አያይዘውምበተቋሙ ላይ የተጀመረው የፍርድ ቤት ጉዳይ ጎን ጎን ይቀጥላል ብለዋል።

ከዚያም ባለፈ የትእምት ሰራተኞች ስራቸውን እንዲጀምሩ አቅጣጫ መቀመጡን ገልጸው÷አመራሩ በባለአደራ እንዲመራ መንግስት አምኖበት ለፍርድ ቤት ለውሳኔ አቅርቧል ነው ያሉት።

የባለ አደራ ቦርዱ 7 አባላት ያሉት ሲሆን 5ቱ በትምህርት እና በተመሳሳይ ዘርፍ ልምድ ያላቸው ናቸው መሆናቸውን ጠቁመው÷ሁለቱ ደግሞ ከገንዘብ እና ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተመረጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።የትእምት ጉዳይ በፍርድ ቤት የተያዘ ቢሆንም የተወረሰ ነገር የለም ያሉት ዶክተር አብረሃም ÷ የተቋሟቱ ሰራተኞች ደሞዝ እንዲከፈል እና ሰራተኞቹ ስራ እንዲጀምሩ መንግስት ወስኗል ብለዋል።ከህግ ማስከበር ዘመቻው በተቃራኒ በመቆም በውግያ የተሳተፉ የተቋማቱ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ጉዳይም በህግ አግባብ ይታያል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ የአክሲዮን ገበያ ማቋቋሚያ ዐዋጅ፣ ለባንክ ተቀማጭ የሚሆን የኢንሹራንስ አሠራርን የተመለከተ ደንብ፣ እንዲሁም ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊትን የሚያጠናክር የተሻሻለውን ዐዋጅ ማፅደቁን ጠ/ሚር አብይ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራና በአፋር አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ተፈጥሮ ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለስልጣናት አመለከቱ።

በአማራ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የባቲ ከተማ ነዋሪ እንዳሉት ግጭቱ የተከሰተው ከሳምንታት በፊት የአፋር ታጣቂዎች ሀብላሎና ቦረን በተባሉ አካባቢዎች መንደሮችን ካቃጠሉ በኋላ ነው።በግጭቱ በርካታ ንብረት መውደሙንና ሕይወት መጥፋቱንም እኚሁ ነዋሪ አመልክተዋል።በአማራ ክልል የአሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ አሊ መሀመድ እንዳሉት የግጭቱ ምክንያት ዐይታወቅም ሆኖም በሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፣ ግጭቱም ከበፊቱ የተለየ ከባድ እንደሆነ ተናግረዋል።«በፊት ከምናውቀው ግጭት የተለየ ነው።አንድም በከባድ መሣሪያ ነው ሁለትም ደግሞ በጣም ስልታዊ በሆነ አግባብ ነው ተኩሱ የሚካኬደው።»

ዶይቸ ቨሌ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የአፋር ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ ወደ ሌሎች ባለስልጣናት የእጅ ስልክ ላይ ቢደውልም ስልካቸው አልተነሳም።በሰላም ሚኒስቴር የቅድመ ማስጠንቀቂያና ዘላቂ መፍትሔ ዳይሬክተር ጀነራል ምግባሩ አያሌው ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ግጭቱ ታኅሣሥ 3 ቀን፣ 2013 ዓ.ም መከሰቱን ጠቁመው ክስተቱ ግን ከማኅበረሰብ ግጭት ከፍ ያለ ነው ብለዋል።«ማኅበረሰብ ከማኅበረሰብ በተለያየ ሁኔታ፦ በግጦሽ፣ በውኃ፣ በከብት፣ በሰብል እንደዚህ ጸብ ይኖራል ግን ይኼ በፍጹም ያልተለመደ ሁኔታ ነው።ማኅበረሰቡ ከሚያውቀው ሁኔታ ውጪ የተፈጠረ ግጭት ነው።»አጠቃላይ የጉዳቱ መጠን አልታወቀም ያሉት አቶ ምግባሩ የተፈጠረውን ግጭት ለማስወገድም እየተሠራ አንደሆነ ተናግረዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሁሉም ፓለቲካ ፓርቲዎች ማሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች በጽሁፍ እንዲደርሳቸው ቢያደርግም ማሟላት ያለባቸውን ሰነዶች ያላቀረቡ 26 የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረዙን አስታወቀ።

በተለያዩ ምክንያቶች የተሰረዙ፣ የማጣራት ስራቸው የተጠናቀቀና ገና እየተካሄደ የሚገኝባቸው ፓርቲዎች ዝርዝር ከላይ ቀርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች የአያያዝ ሁኔታ የሚገመግሙ ሁለት ቡድኖቹ ወደ ክልሉ መግባታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ቡድኖቹ ትናንት ሰኞ ወደ ክልሉ መግባታቸውን የገለጹት የኮሚሽኑ ሃላፊ ሚሼል ባሸሌት የኢትዮጵያ መንግስት በተደረሰው ስምምነት መሰረት ያልተቆራረጡ ሰብዓዊ አቅርቦቶች እንዲኖሩ መፍቀዱን መቀበላቸውን አስታውቀዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በየዕለቱ ከ300 በላይ የኮቪድ ታማሚዎች ወደ ጽኑ ህክምና እንደሚገቡ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ!

በየቀኑ ኮቪድ-19 ከሚገኝባቸው ሰዎች ውስጥ ከ300 በላይ የሚሆኑት ጽኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን እና ከእነዚህ ውስጥ እስከ 50 የሚደርሱት የመተንፈሻ አካልን የሚረዳ ማሽን የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ይህን ተከትሎም ለስድስት ወራት የሚቆይ ኮቪድ 19ን የመከላከል ንቅናቄ ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በኮቪድ የሚሞቱና ጽኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ በየቀኑ ቫይረሱ ከሚገኝባቸው ሰዎች ውስጥ ከ300 በላይ የሚሆኑት ጽኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ፤ ከዚህ ውስጥ ከ40 እስከ 50 የሚሆኑት ደግሞ የመተንፈሻ አካልን የሚረዳ ማሽን ያስፈልጋቸዋል፡፡

በየቀኑ የሚገለጸው ቁጥር ምርመራ ከተደረገላቸው ውስጥ ብቻ ስለሆነ ትክክለኛውን ቁጥር አያሳይም ያሉት ዶክተር ደረጀ፤ አሁን እየተመረመረ ያለው በቀን ከ4ሺ እስከ 5ሺ ሰው በመሆኑ አሁን ከሚመረመረው በሶስትና አራት እጥፍ ከፍ ቢደረግ ውጤቱም በተመሳሳይ ከፍ ማለቱ እንደማይቀር ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት በሽታው የሚገኘው በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እንደነበረና አሁን ላይ ግን ከ900 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች እንደተገኙም ገልጸዋል። ከዚህ በፊት ከተመረመረው ከሶስት እስከ አራት በመቶ ብቻ ቫይረሱ የሚገኝባቸው እንደነበርና አሁን ግን ከ10 እስከ 15 በመቶ በአንዳንድ ቦታዎች ላይም ከ30 እስከ 40 በመቶ ቫይረሱ እየተገኘ መሆኑንም ተናግረዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የመንገድ ደህንነት ማስተግበሪያ ሕግጋት እየተዘጋጁ ነው!

አዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በጋራ በመሆን መንገድን ለተጠቃሚው ምቹ ከማድረግ አንፃር የመንገድ ደህንነት ኦዲት ማስተግበሪያ ሕግጋት እየተዘጋጀ መሆኑን አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው አዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ሀብታሙ ንጉሤ አስታወቁ።የመንገድ ደህንነት ኦዲት ማስተግበሪያ ማለት መንገዶች ከዲዛይን ጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የመከታተል ሂደት ነው ያሉት ሀብታሙ እነዚህ ሕግጋት እንዲዘጋጁ የተፈለገው በዋነኝነት የመንገድ ተጠቃሚዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ታስቦ እንደሆነ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa