YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአገሪቱን የ10 ዓመት እቅድ አጸደቀ!

በጠቅላይ ሚንስትር አብይ "ሀገራችንን ወደ ዕድገት ማማ በማስፈንጠር አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያስችላት ነው" የተባለው የኢትዮጵያ የዐሥር ዓመት ብሔራዊ ዕቅድ ጸድቋል።

በተጨማሪም፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኅትመት እና የብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን መተዳደሪያ ሆኖ የሚያገለግለውን እና ለማኅበራዊ ሚዲያ የሕግ ማሕቀፍ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚተገበረውን፣ ረቂቅ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ዐዋጅ አጽድቋል። የዘርፉን ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች የሚተነትነው ዐዋጅ፣ የመረጃ እና የፕሬስ ነጻነት ተግባራዊነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚደግፍ እንደሆነም ጠቅላይ ሚንስትሩ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሴኮቱሬ መኝታ ቤት 2 የእጅ ቦምብ፣ 17 ሽጉጥና ሌሎች መሳሪያዎች መገኘታቸውን የልጁ ባለቤት ለችሎት አስረዳ!

የሴኮቱሬ የልጁ ባለቤት አብነት ኃይሉሸዋ በሚኖርበት መኖሪያ የተገኘው ሁለት የእጅ ቦምብ፣ 17 የእጅ ሽጉጥ እና ሌሎች መሳሪያዎች ሴኮቱሬ በመኝታ ቤቱ ያስቀመጠው እንጂ የኔ አይደለም ሲል ተከራከረ።ተጠርጣሪው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቧል።የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምርመርራ አባልም በተጠርጣሪው ላይ የሰራቸውን የምርመራ ስራዎችን ለችሎቱ ገልጻል።ተጠርጣሪው ሀገርን በመካድ በሀገሪቱ ላይ ጥቃትና አመጽ እንዲንቀሳቀስ ከሚሰሩ የህወሓት የጸረ ሰላም ቡድኖች ጋር ተልዕኮ ተቀብሎ ሲሰራ እንደነበር መረጃ ሰብስቤያለው ሲል መርማሪ ፖሊስ ለችሎት አስረድቷል።

በዚህ መሰረትም “በርካታ የምርመራ ስራዎችን አከናውኛያለሁ፤ ተጠርጣሪው በሚኖርበት መኖሪያ ቤትም ብርበራ አድርጌ ሁለት የእጅ ቦምብ፣ 17 ሽጉጥ 30 ፍሬ የክላሽ ጥይት እና በርካታ የጦር መሳሪያዎች አግኝቻለሁ” ሲል ነው የገለጸው።እንዲሁም ያገኛቸውን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ለቴክኒክ ምርመራ መላኩንና ለቀሪ ምርመራ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።ተጠርጣሪው “ሴኮቱሬ የባለቤቱ አባት ነው፤ እኔ የምኖርበት ቤት ቀደም ሲል በመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ለሌላ ተሰጥቶ የነበረና በተዘጋው የሴኮቱሬ መኝታ ቤት ውስጥ ነው ቦምቡና መሳሪያዎቹ የተገኙት፤ እኔን የሚመለከቱ አይደሉም” ሲል ተከራክሯል።ጉዳዩን የተከታተለው ችሎትም ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ ሰባት ቀናት የፈቀደ ሲሆን፥ በችሎቱ ሌሎች ጉዳዮችንም ተመልክቷል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ወንጀል ችሎት አቶ ልደቱ አያሌው የ30 ሺህ ብር አስይዘው እንዲወጡ አዟል፡፡
ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ባሻሻለው ሁለተኛው ክስ ላይ አቶ ልደቱ ያቀረቡትን ዋስትና ጥያቄ ተቀብሏል፡፡
እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ፣ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ልደቱ የተሸሻለው ክስ ዋስትና አያስከለክልም ሲል ነው ዋስትናውን የፈቀደላቸው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ልደቱ አያሌው ተፈቱ!

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ወንጀል ችሎት ዓቃቤ ሕግ ባሻሻለው 2ኛው ክስ ላይ ልደቱ አያሌው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ተቀብሏል፡፡በዚህም ልደቱ አርብ ከሰዓት ተፈተው በአሁኑ ሰዓት ቢሾፍቱ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መግባታቸውን የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አዳነ ታደሰ ለአሐዱ ቴሌቪዥን አረጋግጠዋል፡፡ፖለቲከኛው ልደቱ አያሌው የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በቢሾፍቱ አመፅን በማስተባባር በሚል ወንጀል ነበር በሰኔ 2012 ለእስር የተዳረጉት፡፡

የኢዴፓ መስራቹ ልደቱ ከዚህ ቀደም ዋስትና ቢፈቀድላቸውም ፖሊስና ዐቃቤ ሕግ በሌሎችም ወንጀሎች እንደሚጠረጥሯቸው በመግለፅ ይግባኝ ማለታቸውን ተከትሎ ሳይፈቱ ከርመዋል፡፡ ጉዳዩ መነጋገሪያ ከመሆን በሻገር እንደ ኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽኝ ያሉ ተቋማትም የፍርድ ቤት ውሳኔ ሊከበር ይገባል ሲሉ የፖሊስና ዐቃቤ ሕግን ድርጊት በመግለጫ መቃወማቸው አይዘነጋም፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
በኮንታ ልዩ ወረዳ እናትን ገድሎ የ15 ዓመት ልጇን አስገድዶ የደፈረ ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡

ተከሳሽ አብርሃም አመለ ቦንጆሬ በልዩ ወረዳው የግንባ አጋሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጫባ መንደር ነዋሪ ነው፤ ይህ ዕድሜው ሰላሳዎቹን ያልተሻገረው ወጣት ሰኔ 25/2012 ዓ.ም ከገበያ ወደ ቤት በመመለስ ወደ መንደሩዋ የቀረበችውን የ15 አመት ልጅ አልማዝ አለማየሁን በመጥለፍ ጫካ የገባ ሲሆን ከተጠላፊዋ ጋር በነበረች ህፃን ጥቆማ መነሻ የልጇን ጩሄት የሰማችሁ እናት ተከታትላ በደረሰችበት ወቅት ሟች አይናቴ ኬቶን በአሰቃቂ ሁኔታ በመደብደብ በጩቤ ሶስት ቦታ በመውጋት ገድሎ ገደል ውስጥ መወረወሩን የኮንታ ልዩ ወረዳ ፍርድ ቤት በችሎቱ አሰምተዋል፡፡

ከዚህም በኃላ የጠለፋትን ልጅ አስገድዶ መድፈሩ በምርምራ ተረጋግጧል፡፡ከምስክሮችና ከዐቃቤ ህግ መረጃ መነሻ በኢትዮጵያ ወንጀለኞች መቅጫ ድንጋጌ 88/2 መሰረት በሶስት ወንጀሎች ማለትም

በ1ኛ. ክስ በጭካኔ የመግደል ወንጀል እርከን 38፣

በ2ኛ. ክስ ጠለፋ የመፈፀም ወንጀል እርከን 24 እና

በ3ኛ. ክስ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል እርከን 27 ላይ የሚውሉ ወንጀሎች መፈፀማቸውን ፍርድ ቤቱ በችሎቱ አረጋግጧል፡፡

በመሆኑም የኮንታ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታህሳስ 2/2013 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት ተከሳሽ አብርሃም አመለ በፈፀማቸው ሶስት ከባድ ወንጀሎች ምክንያት በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን ከልዩ ወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ አዲስ አበባ የፈለሱትን የኤርትራ ስደተኞች ወደ ትግራይ ክልል ለመመለስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ነቀፈ፡፡

በዛሬው ዕለት የእቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በሁለት የስደተኞች ማቆያ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች በተሳሳተ መረጃ ወደ አዲስ አበባ እየፈለሱ ነው ሲል መውቀሱ ይታወሳል፡፡
ማጣሪያው ዛሬ ከሰዓት ባወጣውና መደበኛ ያልሆነ የኤርትራዊያን ስደተኞች እንቅስቃሴ የሚል ስያሜ በሰጠው መግለጫ ማይ-አይኒ እና አዲ-ሃሩሽ ከተባሉት የስደተኞች ማቆያ ጣቢያዎች በመልቀቅ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ነው ሲል ወቅሷል፡፡በተሳሳተ መረጃ ተገፋፍተው ያልተለመደና መደበኛ ያልሆነ እንቅስቃሴ የሚያደርጉት ኤርትራዊያን ስደተኞች ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው መንግስት ለሚያደርግ ሁለንተናዊ ድጋፍ ዕክል ይፈጥራል ሲል ተናግሯል፡፡መንግስት በሀገር ውስጥ ላስጠለላቸው ስደተኞች ሳይደክምና ሳይሰለች በሙሉ አቅሙ ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን በመግለጫው ጠቁሟል፡፡ስለዚህም ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከማቆያ ጣቢያ የወጡትን ስደተኞች ወደ ቀድሞ ስፍራቸው የመመለስ ስራ እንደሚያከናውን ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግሥት እርምጃ ተከትሎ ከጥቂት ሰዓታት በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መግለጫ አውጥቷል፡፡በመግለጫው የድርጅቱ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቃል አቀባይ ባባር ባሎች የኢትዮጵያ መንግሥት ኤርትራዊያን ስደተኞችን ወደ ትግራይ ክልል ለመመለስ ያቀደውን ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ነቅፎታል፡፡ቃል አቀባዩ የትግራይ ክልል ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ሳይረጋገጥ ስደተኞቹን ወደ ስፍራው ለመመለስ የሚያደርገውን እቅድ በፅኑ ነቅፎታል፡፡ኢትዮጵያ በዚህ ሰዓት ቁጥራቸው አንድ ሚሊዮን ያህል ስደተኞችን ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማልያና ኤርትራ ተቀብላና አስጠልላ እንደምተገኝም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በመግለጫው አስታውሷል፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት ተከማችተው የተገኙ 199 የተለያዩ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ጸጥታ አካላት አስታወቁ።

በክልሉና ፌዴራል ፖሊስ አባላት አንዲሁም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልገሎት የተቀናጀ ጥረት በቁጥጥር ስር የዋሉት ህገ ወጥ መሳሪዎች 148 ታጣፊ እና 51 ባለሰደፍ ክላሺንኮቭ ጠብንጃዎች በተጨማሪም 178 የጥይት መያዣ ካርታዎች እንደሚገኙበት ተመልክቷል።የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ቱት እንዳሉት ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ጋር ሰፊ የድንበር ወሰን ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይገባል።ይህም ለሽብር ወንጀል ወደ መሃል አገር ለማሳለፍ እንደሚሞከር አመልክተዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ኮማንደር ኡማን ኡጋላ በበኩላቸው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት ከህዝብ የደረሰን ጥቆማ መሰረት በማድረግ በተደረገ የተጠናከረ ክትትል ነው፣ በአሁኑ ወቅት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ተከማችተው የተገኙበት ቤት ባለቤትን ጨምሮ አዘዋዋሪዎችንና ግብረ አበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
ሌ/ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳዔን ጨምሮ 40 የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሃይል፣ የሀገር መከላከያና የፖሊስ አመራሮች ላይ የመያዣ ትእዛዝ ወጣ።

ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው እነዚህ አመራሮች በሀገር ክህደትና የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲታገቱ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረዋል። ከህወሀት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በመምራት በማስተባበርና በመፈጸም በሀገር ላይ ከፍተኛ አደጋ ያደረሱ በመሆናቸው ለህግ እንዲቀርቡ የእስር ትዕዛዝ የወጣባችው መሆኑ ተመልክቷል። የቀድሞ ኤታማዦር ሹም ሌ/ጀ ጻድቃን ጦርነቱ ከመጀመሩ አንድ ሳምንት በፊት ከሀገር መውጣታቸው ይታወሳል። ፌደራል ፖሊስ እነዚህን ተጠርጣሪዎች አድኖ ለመያዝ በሚደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 422 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 2234 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 807 የላቦራቶሪ ምርመራ 422 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 115 ሺህ 782 ደርሷል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 2234 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 91 ሺህ 209 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 791 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 22 ሺህ 780 ሰዎች መካከል 283 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
videotogif_2020.11.17_05.08.23.gif
1.2 MB
📌አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው ትሪትመንት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ👉🏼 አላድግም ብሎ ለቀረ
👉🏼 ራሰ በርሃ ለሆነ
👉🏼 ወደራሰ በርሃነት የተጠጋ  ለሳሳ ፀጉር
👉🏼 ወደውስተጥ ለገባ ፀጉር
👉🏼 ፐረም ወይም ጄል ለጨረሰው ፀጉር
👉🏼ላሽ ለበላው #ፂም #ፀጉር
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን ☞@Brandlife1
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] {Wireless Wifi router}+ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡➡️ ☎️+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
Forwarded from YeneTube
💥 Adidas 👟

📎 #ORIGINAL 💯

Size:- 40-41-42

📌 Made in Vietnam
📌 Price 1500 birr
📌 With delivery
📞 0949231405

@gebeyaadis
በዘንድሮ ዓመት በአማራ ክልል በመኸር ወቅት በሰብል ከተሸፈነው 4ሚሊየን 282 ሺህ 517 ሄክታር መሬት እስካሁን 65 በመቶ ያህሉ ምርት መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በክልሉ በዘንድሮ ዓመት በመኸር ወቅት 4ሚሊየን 282ሺህ 517 ሄክታር መሬት በሰብል የተሸፈነ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት ወደ 2ሚሊየን 800 ሺህ156 ሄክታር መሬት (65 በመቶው) የደረሰ ምርት መሰብሰብ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የሰብል አሰባሰብ የሚካሄድበት ወቅት እንደመሆኑ፤ በተለይም ለዘር የሚሆኑ የጤፍ፣ የስንዴና የበቆሎ ምርጥ ምርቶች ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተስፋሁን፤ ለዚህም የደረሱ ሰብሎች ለመሰብሰብ የሚረዱ 104 የሚሆኑ ኮምባይነሮችን በመጠቀም ሰብል እየተሰበሰበ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በኮምባይነሮች ከ19ሺህ 481 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ ያለ ሰብል የታጨደ ሲሆን፤ ከዚህም 715 ሺህ 698 ኩንታል ምርት ተሰብስቧል።

ኮቪድ ጋር ተያይዞ ሰብል አሰባሰብ ሂደት በርካታ የሰው ኃይል ለመጠቀም አስቸጋሪ መሆኑ ኮምባይነሮቹ እጅግ ጠቃሚ ናቸው የሚሉት ምክትል ኃላፊው፤ በተለይ በኩታ ገጠም በሆኑ ማሳዎች ላይ የተዘሩ ሰብሎችን ለመሰብሰብ ኮምባይነሮቹ ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑን ተናግረዋል።ይሄም በሰው ጉልበት ከ10 እስከ 20 ቀናት የሚወስድ የምርት አሰባሰብ ሂደት ከአንድ እስከ ሁለት ባሉት ቀናት ውስጥ እንዲሰበሰብ ማድረግ ማስቻሉን ተናግረዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በሚኒስትር እና በዳይሬክተር ደረጃ ያሉ የመንግስት ሹሞች ወደ ውጭ ሀገርም ሆነ ወደ ክልል ሲጓዙ ከጠ/ ሚ ቢሮ የይለፍ ወረቀት እንዲያፅፉ የሚያዝ ሰርኩላር ተላለፈ።

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ከፍተኛ ሃላፊዎች በሃገር ውስጥ በሚያደርጉት ጉብኝት እንዲሁም በውጭ ሃገራት በሚያደርጉት የትኛውም አይነት ጉዞ ቅድሚያ ከጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ፈቃድ እንደሚያስፈጋቸው ለማወቅ ተችሏል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲስ ለሚያስገነባው ባለ12 ወለል ሁለገብ ህንፃ የመሠረት ድንጋይ በስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተ/ም/ ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ተቀምጧል።

ፌዴሬሽኑ የሚገነባው ሁለገብ ህንፃ የህክምና ማዕከል፣ ሙዚየም፣ ጅምናዚየም፣ ላይብረሪ፣ ቢሮዎች እና ለሌሎች አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎች እንደሚኖሩት ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በህዳር ወር 268,146,693 ብር የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ ወጥ ገንዘብ መያዝ ተችሏል!

ግምታዊ ዋጋቸው ብር 213,620,309 የሆኑ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ-ወጥ ገንዘብ ግምታዊ ዋጋቸው 54,526,384 ብር ወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ-ወጥ ገንዘብ ከሃገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል፡፡ በአጠቃላይ በህዳር ወር ብር 268,146,693 ብር የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ ወጥ ገንዘብ መያዝ ተችሏል፡፡

በገቢ ከንትሮባንድ ከተያዙ እቃዎች ከፍተኛውን ደረጃ የያዙት ኤልክተሮኒክስ፣ ኮንትሮባንድ ጭነውና በኮንተሮባንድ የገቡ ተሽከርካሪዎች፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ኮንተሮባንድ ጭነው የተቀጡ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ምግብና መጠጥ ነክ ቁሳቁሶች ናቸው፡፡ገቢ ኮንትሮባንድ በስፋት የተያዘበት ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችን ስንመለከት ጅግጅጋ፣ ሀዋሳ፣ ድረደዋ፣ ሞያሌ እና አዋሽ ሲሆኑ ሌሎች ቅረንጫፍ ፅ/ቤቶችም በየደረጃው ገቢ ኮንተሮባንድን መያዝ ችለዋል፡፡

በወጪ ኮንተሮባንድ ከፍተኛ ውጤት ያስምዘገቡ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ሞያሌ፣ አዋሳ፣ ባህርዳር፣ አዲስ አባባ ኤርፖርት፣ ድሬደዋ ከ1-5 ያለውን ደረጃ ያያዙ ሲሆን አሶሳ፣ ጅማ፣ ጅጅጋ እና ጋላፊ በተመሳሳይ የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሲያስተምራቸው የነበሩ 2 ሺህ 444 ተማሪዎችን አስመረቀ።

በ2012 ዓ.ም መመረቅ የነበረባቸው ተመራቂዎቹ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት በመቋረጡ የምረቃ ፕሮግራማቸው ዛሬ ተካሂዷል።በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጫላ ዋታ ትምህርታቸው በወረርሽኙ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ማካካሻ ወስደው ዛሬ ለምርቃት መብቃታቸውን አንስተዋል።ዩኒቨርሲቲው በ2013 የትምህርት አመት የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን ተግባራዊ በማድረግ ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት ማድረጉን አስረድተዋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መድሃኒቶችንና የህክምና መገልገያዎችን የጫኑ የቀይ መስቀል መኪኖች መቐለ መግባታቸውን የአፍሪካ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር የፋይዘር/ባዮንቴክ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለአስቸኳይ ጊዜ አገልገሎት እንዲውል ፈቃድ ሰጠ።

ተቋሙ እንዳለው ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ መስጠቱ አስካሁን በአሜሪካ ውስጥ ከ295 ሺህ በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገውን ወረርሽኝ በመከላከል በኩል "ታላቅ እርምጃ" እንደሆነ አመልክቷል።በሽታውን በመከላከል በኩል አስከ 95 በመቶ ድረስ አስተማማኝ እንደሆነ የተነገረለት ክትባቱ ደኅንነቱ የተጠበቀና ውጤታማ መሆኑን የምግብና መድኃኒት አስተዳደር መስክሯል።የአገሪቱ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕም የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት "ከ24 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ መስጠት ይጀመራል" ብለዋል።"አገራችን በህክምናው ዘርፍ ታላቅ የሚባል እመርታን አስመዝግባለች" በማለት የተናገሩት ፕሬዝደንት ትራምፕ "በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ውጤታማና ደኅንነቱ የተጠበቀ ክትባት መስራት ችለናል" ብለዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa