YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቁጥጥር ስር ስለሚገኙት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ፖሊስ እና አቃቤ ሕግ በቅርቡ ማብራሪያ እንደሚሰጡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባቦት ቃል አቀባዩ ሬድዋን ሁሴን ገለጹ፡፡

የህወሓት የቀድሞ አመራሮች አዲስአለም ባሌማ (ዶ/ር) እና ኬሪያ ኢብራሂም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው ቃላቸውን እየሰጡ እንደሚገኙም ነው ቃል አቀባዩ ለውጭ መገናኛ ብዙሃን የተናገሩት።ግለሰቦቹ በቅርቡ ስለነበሩበት ሁኔታ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ሬድዋን ገልጸዋል።በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ምን እንደተፈፀመ ተጨማሪ መረጃ ሊገኝ እንደሚችልም ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግሥት የገለልተኛ አጣሪ ቡድን ምርመራ ያድረግን ጥያቄ እንደማይቀበል አሳወቀ፡፡

መንግሥት ለመመርመር እንዳልቻለና እንደወደቀ ሲሰማው ብቻ ገለልተኛ አጣሪ ቡድንን እንደሚጋብዝ ነው የገለፀው፡፡ኅዳር 29 ለውጭ አገራት መገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ የሰጡት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባቦት ቃል አቀባይ ሬድዋን ሁሴን የገለልተኛ አጣሪ ቡድን ለምን ወደ ኢትዮጵያ አይገባም የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ምላሻቸው አጭር ሲሆን ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት እንደወደቀና እንዳልቻለ ሲሰማው ብቻ የገለልተኛ አጣሪ ቡድንን ለምርመራ ይጋብዛል፤ የትኛውም ወገን እኛ እስክንጠራው መጠበቅ አለበት የሚል ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት አገርን እንዴት መምራት እንደሚችል የሚያውቅ ነው በማለትም የቅኝ ግዛት እሳቤን ለማንፀባረቅ መሞከር ቅቡልነት እንደማይኖረው ነው ያሰመሩበት።መንግሥት በማይካድራም ሆነ በአጠቃላይ ትግራይ ክልል ስለነበረው ሁኔታ የአገሪቱንና የዓለም አቀፍ መርሆዎችና ደረጃዎችን ያሟላ ምርመራ ውጤትን ለፍርድ ቤት ያቀርባል፤ ያሉት ቃል አቀባዩ የትኛውም ወገን የምርመራ ሰነዱን ካየ በኋላ ጥርጣሬ ካለው መጠየቅ ይችላል እንጂ እኛ እንመርምርላችሁ የሚለው እንደማይታሰብ ነው ያሳወቁት፡፡

አሐዱ
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ ቡድኖች የጥፋት ተልእኮ ለመቀበል የተደራጀ አንድ ለ20 የሚል ቡድን በምርመራ ማግኘቱን አስታወቀ።

በኮሚሽኑ የወንጀል ምርመራ ቢሮ አገኘሁት ያለውን መረጃ ያብራራው በእነ ሜጀር ጄነራል ገብረ መድህን ፍቃዱ 7 ተጠርጣሪዎች እና በእነ ብርጋዴር ጄነራል አሊጋዝ ገብሬ 4 ተጠርጣሪዎች የተካተቱባቸውን የምርመራ መዝገቦች ለፍርድ ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው።ፖሊስ በእነ ሜጀር ጄነራል ገብረ መድህን ፍቃዱ መዝገብ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀደም ሲል በሰጠው የምርመራ ጊዜ ከተጠርጣሪዎች አገኘሁ ካላቸው መረጃዎች አንዱ ከሕወሓት አመራሮች ተልእኮ በመቀበል የሰሜን እዝ ኔትወርክ ተቋርጦ የመከላከያ ሠራዊቱ እንዲመታ ስለማድረጋቸው የሚያስረዱ የምስክሮችን ቃል መቀበል የሚለው ይጠቀሳል።

ተጠርጣሪዎቹ ከኦነግ ሸኔ አመራሮች ጋርም ግንኙነት ሲያደርጉ እንደነበር የሚያስረዱ ምስክሮችን ቃል ስለመቀበላቸውም ተሰምቷል።በሌላ በኩል ችሎቱ የመከላከያ አካዳሚ ኮሌጅ አመራር የነበሩ እነ ብርጋዴር ጄነራል አሊጋዝ ገብሬ ላይም መሰል የምርመራ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጿል።በሁለቱም የምርመራ መዝገቦች አዲስ አበባ ውስጥ በኅቡዕ ድብቅ የፖለቲካ እና የጥፋት አጀንዳ በሚያራምደው እና 1 ለ 20 በሚል በተቋቋመው ቡድን ውስጥ ዐሥራ አንዱም ተጠርጣሪዎች የነበራቸውን ተሳትፎ ፖሊስ ለችሎቱ ገልጿል።

በሌላ በኩል በሁለቱም የምርመራ መዝገቦች የሚገኙ ተጠርጣሪዎች የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን በማንሣት የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ፖሊስም ዋስትናውን በመቃወም ተከራክሯል።የግራ ቀኙን ክርክር የሚመራው ችሎቱ በእነ ሜጀር ጄነራል ገብረ መድህን ፍቃዱ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለነገ ታኅሣሥ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሲይዝ በእነ ብርጋዴር ጄነራል አሊጋዝ መዝገብ ላይ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀናት 12 ቀናት ፈቅዷል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በሦስት ተጨማሪ ቋንቋዎች ሥርጭት ሊጀምር ነው!

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ባስገነባው ስቱዲዮ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ በትግረኛ፣በኦሮምኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑንም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሙሉቀን ሰጥየ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል ።

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን በተነሳ ግጭት 83,131 ሰዎች ሲፈናቀሉ ከመቶ በላይ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡

የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ለካፒታል ጋዜጣ ከነገረው መረጃ በተጨማሪ ከ40 በላይ ሰዎች ሲጎዱ 6,000 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡በድንበር ይገባኛልና ዞን ለመሆን ይገባናል በሚል በተነሳው ግጭት እስካሁን ከመቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተገልፃል፡፡ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን የሰዎች መፈናቅልና ሞት በገለልተኛ ቡድን ለማጣራት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ወደ ቦታው እንደላከ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
የ"ሲንቄ/ሲቆ" ባህላዊ ስርዓት ምንነና በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ያላትን ሚና የሚዳስስ መጽሀፍ ተመረቀ።

መጽሀፉን የመረቁት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው እና የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ከበደ ደሲሳ ናቸው።በመጽሀፍ ምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በኦሮሞ ብሔር ትልቅ ቦታ ያለው የገዳ ስርዓት የዲሞክራሲ ስርዓት ሲሆን በውስጡም የ"ሲንቄ/ሲቆ" ባህላዊ ስርዓት የሴቶችን ጉልህ ድርሻ ይዞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲያስተላልፈው የቆየ ባህላዊ ክዋኔ መሆኑ ተገልጿል።

[ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ከመጭው ሀገራዊ ምርጫ በፊት አባሎቹ እንዲፈቱ ጠየቀ!

ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በሀገሪቱ ዶሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ የበኩሉን ሲያበረክትና በተለያዩ ምርጫዎች ሲሳተፍ መቆየቱን አመለክቷል።ኦፌኮ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫን ለማካሄድ በምርጫ ቦርድ በኩል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጾ፤ በመጭው ዓመት 2013 በሚካሄደው ምርጫም ለመሳተፍ እንደሚፈልግ አመልክቷል።ይሁን እንጅ ምርጫው በታቀደለት ጊዜ ተዓማኒነት ባለውና በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲካሄድ ከተፈለገ፤መንግስት ከምርጫው በፊት የታሰሩ አመራሮች እንዲፈቱ፣በመንግስት ሀይሎች የተዘጉ ፅ/ቤቶች እንዲከፈቱና በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት እንዲከበርና የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ጠይቋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ለመከላከያ ሠራዊት እና ለተጎዱ ዜጎች ማቋቋሚያ የሚውል የ200 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ድጋፉን ለመከላከያ ሠራዊት የውጭ ግንኙነት ሓላፊ ኮሎኔል የኑስ ሙሉ አስረክበዋል።በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በክብር እንግድነት ተገኝተው ባንኮች ስላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።ድጋፉን ያደረጉት የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር አባል የሆኑ 18 ባንኮች ናቸው ተብሏል።

ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100 ሚሊየን ብር ያበረከተ ሲሆን፣ አዋሽ፣ ዳሸን፣ አቢሲንያ፣ ሕብረት፣ ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እያንዳንዳቸው 10 ሚሊየን፣ ንብ ኢንተርናሽናል፣ ዘመን፣ አንበሳ ኢንተርናሽናል፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል እና ብርሃን ባንክ እያንዳንዳቸው አምስት ሚሊየን ብር እንዲሁም ወጋገን፣ ዓባይ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል፣ እናት፣ ቡና ኢንተርናሽናል እና ደቡብ ግሎባል ባንክ እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በበኩሉ ለመከላከያ ሠራዊት የአምስት ሚሊየን ብር ድጋፍ አስረክቧል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሃት ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የእዙ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ህወሃት ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የእዙ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ። Via ENA @YeneTube @FikerAssefa
ህወሃት ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የእዙ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ።

የህወሃት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያህል የሰሜን እዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሰሩት የጋራ አሰሳ አስለቀቁ።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሃመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት የህውሃት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የእራት ግብዣ ብሎ ከጠራ በኋላ አፍኖ በመውሰድ አግቷቸው ቆይቷል።የጁንታው ሃይል መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን በሸሸበት ቦታ ሁሉ ይዟቸው ሲጓዝ ቆይቶ በቀድሞው የትጥቅ ትግል ወቅት የማዘዣ ቤዝ በነበረው አዴት በሚባል ቦታ አግቷቸው እንደነበርና የጁንታው ታጣቂ ሃይል መደበቁ በአሰሳና በጥናት ተደርሶበታል።

በዚሁ መሰረት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት የጋራ አሰሳ እና እርምጃ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጁንታው አስለቅቀዋል።ሰራዊቱ ያስለቀቃቸው 1 ሺህ ያክል የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች አሁን ላይ ሰራዊቱን መቀላቀላቸውን ሜጀር ጀነራል መሀመድ ገልጸዋል።ሰራዊቱ ከጁንታው ካስለቀቃቸው መካከል የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴም ይገኙበታል።

የጁንታውን አባላት የማደን ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ሜጀር ጀነራል መሀመድ፤ የመጨረሻ ምእራፍ በሆነው ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምእራፍ የተደበቀውን ጁንታ አስሶ የመያዙ ስራ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ የጋራ ቅንጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።ወደፊትም የጁንታውን ቡድንና ወንጀለኞቸን ለህግ የማቅረብና የማደን ስራ ውጤት በየጊዜው ለህዝብ እንደሚገለፅ ጨምረው ገልጸዋል።

(ኢዜአ)
@YeneTube @FikerAssefa
የልዩ ዕድል ሎተሪ ወጥቷል!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የልዩ ዕድል ሎተሪ ህዳር 3 0/2013 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

👉1ኛ. 20,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር -------1705090
👉2ኛ.10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር-----0729356
👉3ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር -----1206064
👉4ኛ. 3,000,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር -------0923071
👉5ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር -------1877734
👉6ኛ. 750,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር -------0340162
👉7ኛ.300, 000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር ------1510522
👉8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 20,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------- 31075
👉9ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------34772
👉10ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-----5632
👉11ኛ.200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 2,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------1071
👉12ኛ.200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------345
👉13ኛ.2, 000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-----065
👉14ኛ.20, 000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------87
👉15ኛ. 200,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------ 5 ሆኗል፡፡

@YeneTube @FikerAsse
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ሰሞኑን ባደረገዉ ፍተሻ «ሕገ ወጥ» ያላቸዉን ከአራት መቶ የሚበልጡ ሽጉጦችና ሌሎች የጦር መሳሪዎች መያዙን አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ የኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ እንደተናገሩት ከሽጉጦቹ በተጨማሪ ክላሺንኮቭ ጠመንጃዎች፣ ቦምቦችና የጦር ሜዳ መነፅሮች ተይዘዋል።የጦር መሳሪዎቹን በመደበቅ ወይም በመያዝ የተጠረጠሩ ከ350 በላይ ሰዎችን ፖሊስ እየመረመረ መሆኑንም ኢንስፔክተር ቶሎሳ አስታዉቀዋል።የድሬዳዋዉ ወኪላችን የመሳይ ተክሉ ዘገባ መሳሪያዎቹ የተያዙበትን ትክክለኛ ቀንና ሥፍራ አልጠቀሰም።በሌላ በኩል እዚያዉ ምስራቅ ሐረርጌ ዉስጥ በየጊዜዉ መንገድ የሚዘጉ የመንግስት ተቃዋሚዎች መኖራቸዉን ኢንስፔክተር ቶሎሳ ገልጠዋል።የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸዉን ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እንዲለቅ በመጠየቅ መንገድ የሚዘጉት ወገኖች አሁንም ለገና በዓል መንገድ ለመዝጋት ዝተዋል።የፖሊስ ኃላፊዉ ግን የተቃዋሚዎቹ ዓላማ «ከሽፏል» ባይናቸዉ።

[ዶቸ ቬለ]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በሚቀጥለው ሳምንት የመድረክ ቴአትሮችን ለተመልካች ማቅረብ ሊጀምር ነው!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የኮቪድ-19 መከላከል መመሪያን ተግባራዊ ባደረገ መልኩ በሚቀጥለው ሳምንት የመድረክ ቴአትሮችን ለተመልካች ማቅረብ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።ኮቪድ-19 ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎችን በመተግበር መድረኩን ለተመልካቾች ክፍት ለማድረግ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የቴአትር ክፍል ዳይሬክተር ደስታ አስረስ ገልጸዋል።ቴአትር ቤቱ በአንድ ጊዜ 1 ሺህ 200 ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ቢኖረውም አሁን ላይ በአንድ ጊዜ 300 ተመልካቾች ብቻ ይስተናገዳሉ ነው ያሉት።

“ተመልካቾች ወደ ቴአትር ቤት ሲመጡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ፣ ሳኒታይዘር በመጠቀም እና ተራርቆ በመቀመጥ እንዲመለከቱ ይገደዳሉ” ብለዋል።የመድረክ ትወና አቅራቢዎችም ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግና ከንክኪ በመራቅ ዝግጅታቸውን ለታዳሚ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።“ለቴአትር ሥራ የሚውሉ ቁሶችም ቴአትሩ ከመጀመሩ በፊት በሳኒታይዘር ይፀዳሉ” ብለዋል።የቴአትር መጀመር በኮቪድ-19 ምክንያት የተቀዛቀዘውን ባለሙያ ወደ ስራ የሚያስገባ መሆኑንም ገልጸዋል።ከታህሣሥ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ቴአትር ቤቱ ለተመልካች ክፍት ሆኖ በሳምንት ሶስት ቴአትሮችን ለማሳየት ዝግጅት መደረጉንም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

(ኢዜአ)
@YeneTube @FikerAssefa
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመተባባር ያለማውን የሰው ሃብት አስተዳደር ሲስተም አስመረቀ!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢ.መ.ደ.ኤ) ጋር በመተባባር ያለማውን የሰው ሀብት አስተዳደር ሲስተም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዲሁም የኢ.መ.ደ.ኤ ዋና ዳይሬክተሮች ዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ እና አቶ ይድነቃቸው ወርቁ በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።
የተመረቀው የሰው ሀብት አስተዳደር ሲስተም የተቋሙን የሰው ሃብት አስተዳደር መረጃዎች በሶፍትዌር ለማደራጀት እና ፈጣን እና ጥራት ያለው የሰው ሃይል አስተዳደር ስርዓት እና ውሳኔ አሰጣጥን ለመተግበር የሚያስችል ሲሆን ተቋሙ የሚሰጠውን አጠቃላይ የሰው ሃይል አገልግሎት በአውቶሚሽን ለመስጠት የሚረዳም ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሀብታም አገራት ያላግባብ የኮሮናቫይረስ ክትባት እያከማቹ እንደሆነና ይህም ድሀ አገራት ክትባቱን የሚያገኙበትን እድል እንደሚያጠበው ተገለጸ።

ለክትባት ፍትሐዊ ስርጭት የቆመው "ዘ ፒፕልስ ቫክሲን አልያንስ" የተባለው ስብስብ እንዳለው፤ ወደ 70 የሚጠጉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራች ከአስር ዜጎቻቸው ለአንድ ሰው ብቻ ነው ክትባት መስጠት የሚችሉት።ኦክስፎርድ እና አስትራዜንካ በጥምረት ከሚሠሩት ክትባት 64 በመቶውን በታዳጊ አገራት እንደሚያከፋፍሉ አስታውቀዋል።ክትባቱ በፍትሐዊ መንገድ ለመላው ዓለም እንዲከፋፈል እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው።ኮቫክስ የተባለው ጥምረት 700 ጠብታ ለ92 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት ለማከፋፈል ተስማምቷል።

"ዘ ፒፕልስ ቫክሲን አልያንስ" ውስጥ አምንስቲ፣ ኦክስፋምና ሌሎችም የመብት ተሟጋቾች ይገኙበታል።ይህ ስብስብ እንዳለው፤ ከሆነ በቂ ክትባት ባለመኖሩ መድኃኒት አምራቾች በርካታ ክትባት እንዲመረት የቴክኖሎጂ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።ሁሉም ክትባቶች ፍቃድ ካገኙ፤ ሀብታም አገራች ለመላው ዜጎቻቸው ከሚበቃው ሦስት እጥፍ ጠብታ ለመግዛት ከወዲሁ መስማማታቸው ተጠቁሟል።

ለምሳሌ ካናዳ ለእያንዳንዱ ዜጋዋ አምስት እጥፍ ክትባት ለማግኘት አስቀድማ ትዕዛዝ አስተላልፋለች።ሀብታም አገራች ከመላው ዓለም 14% ብቻ ቢሆኑም 53% ክትባት ገዝተዋል።የኦክስፋም የጤና ፖሊሲ ኃላፊ አና ማርዮት "ማንም ሰው ሕይወቱን የሚያተርፍ ክትባት ሊከለከል አይገባም።ክትባት ማግኘት እና አለማግኘት በአገር የገንዘብ አቅም መወሰን የለበትም" ብለዋል።አሁን ያለው ሁኔታ ካልተለወጠ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት ላያገኙ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።"ዘ ፒፕልስ ቫክሲን አልያንስ" ሁሉም መድኃኒት አምራቾች የኮቪድ-19 ክትባት ሂደትና ቴክኖሎጂውን በማጋራት ጠብታው በቢሊዮኖች እንዲመረት ጥሪ አቅርቧል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከሃገር የሸሹና በሃገር ውስጥ የተደበቁ በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን ለማስመለስ መዘጋጀቱን ገለፀ።

ተቋሙ እንዳሳወቀው በዋናነት በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን ለማስመለስ የሚያስችል የጥቆማ መቀበያ ስርአት እየዘረጋ ነው፡፡

ይህ እየተዘረጋ ያለው የጥቆማ መቀበያ ሰርአት በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን በማጣራት ማስመለስ የሚያስችል ነው።

ተቋሙ በአሁን ወቅት በኢሜይል እና በነጻ የስልክ ጥሪ ጥቆማ መቀበል የሚያስችለውን አሰራር መዘርጋቱን አሳውቋል፡፡

ይህም በህገወጥ መንገድ በግለሰብ የተያዙ የህዝብ ሃብትን በሚሰጥ በወንጀል የተገኙ ሃበቶችን አጣርቶ ለማስመለስ ያሰችላል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለሚዲያ አመራሮች ስልጠና እየሰጠ ነው!

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አዘጋጅነት ለአገር ውስጥ የሚዲያ አመራሮች በግጭት አዘጋገብ እና ለሰላም ከመቆም ጋር የተያያዘ ሥልጠና እና ውይይት እየተካሄደ ነው።የመገናኛ ብዙኃን ማሕበረሰብን ከማገልገል አኳያ ትልቅ ባለድርሻ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የምክክር መድረኩ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ካቢኔ በፈረንሳይ ጽንፈኛ እስላማዊነትን ይገታል ያሉትን አዲስ ሕግ አረቀቁ።

በቅርቡ ፈረንሳይ በጽንፈኞች ተደጋጋሚ ጥቃትን ስታስተናግድ ቆይታለች።ረቂቅ ሕጉ ሰዎች በሃይማኖት ጉዳይ የተሰማቸውን እንዲገልጹ የሚፈቅድ ከመሆኑም በላይ ታዳጊዎችን በቤት ማስተማር ላይ ጥብቅ ክልከላዎችን ይጥላል ተብሏል።የፈረንሳይ መንግሥት ሃይማኖትን ለማጥቃት ያወጣው ሕግ ነው በማለት በርካቶች ረቂቅ ሕጉን ተችተዋል።

የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንሰትር ጄን ካስቴክ ግን ሕጉ ሙስሊሞችን ከጽንፈኞች ነጻ የሚያደርግ ሕግ ነው ብለዋል።"የሪፐብሊካን መርሆችን" ይደግፋል የተባለው ረቂቅ ሕግ፤ በኢንተርኔት የሚፈጸሙ የጥላቻ ንግግሮች በጥብቅ እንዲመረመሩ ያዛል እንዲሁም በኢንተርኔት አማካይነት የሰዎችን ግላዊ መረጃ ማጋለጥን ይከለክላል።

ከሳምንታት በፊት የነብዩ መሐመድን የካርቱን ምስል ለተማሪዎቹ ማሳየቱን ተከትሎ የተገደለው ሳሙኤል ፓቲ፤ በኢንተርኔት አማካኝነት ዘመቻ ተፍቶበት ነበር ተብሏል።ፈረንሳይ ይህን መሰል ሕግ ለማውጣት ስታጤነው የቆየችው ጉዳይ ቢሆንም በቅርቡ በፈረንሳይ የደረሱ ጥቃቶች ሕጉ በፍጥነት እንዲወጣ አስገድደዋል።በቅርቡ በፓሪስ እና በመዲናዋ አቅራቢያ በጽንፈኛ ሙስሊሞች የተፈጸሙት ጥቃቶች የአገሪቱን ዜጎች አስቆጥተዋል።ፈረንሳይ ወደ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች የሚኖሩባት አገር ናት።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
እነ ብርጋዴር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዴ (ወዲነጮ) ጨምሮ ሰባት የመከላከያ ከፍተኛ የጦር መኮነኖች ላይ መርማሪ ፖሊስ ባከናወነው በርካታ ማስረጃ ለወንጀሉ መፈጸም የሚያመላክቱ ማስረጃዎች በመኖራቸው 12 ተጨማሪ ቀናትን ፈቀደ፡፡

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በይደር ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተጠርጣሪዎቹን አስቀርቦ መርማሪ ፖሊስ ሰፊ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎቹን መሰብሰቡን ነው የገለጸው፡፡ስለሆነም ቀሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ሲል ለመርማሪ ፖሊስ 12 ቀናት የፈቀደው ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎች ትናንት ባቀረቡት የስኳር ህመም መመርመሪያ የህክምና መሳሪያ ይግባልኝ ጥያቄ ተቀብሏል፡፡

በዚህም መሰረት መመርመሪያ ኪት እንዲገባላቸው አሊያም በማረፊያ ቤታቸው የህክምና ክትትል እንዲደረግላቸው አዟል።በተጨማሪም ችሎቱ ትናንት የቀረበው የባንክ ሂሳብ እግድ ይነሳልን ጥያቄያቸውን መርምሮ እግዱን ያገደው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እግዱን ያገደበት ምክንያት አስተያየቱን እንዲያቀርብ አዟል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
አብዛኞቹ የትግራይ ከተሞች እስከ እሁድ ድረስ መብራት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው!

በትግራይ ክልል ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያዎችን ወደ ቀደመው አገልግሎታቸው እንዲመለሱ በማድረግ የክልሉ አብዛኞቹ ከተሞች እስከ መጪው እሁድ መብራት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንዳስታወቀው በህወሓት አማካኝነት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የኃይል ማስተላለፊያዎች በአፋጣኝ ጥገና እየተደረገላቸው እንደሆነ እና አንዳንድ አካባቢዎች ላይም በከፊል መጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።

@YeneTube @FikerAssefa