"117 አመት የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ግንኙነት የሁለቱ ሀገር የጋራ ባልሆነ ጉዳይ አይበላሽም ብለን ተስፋ እናደርጋለን " አምባሳደር ፍፁም አረጋ
ፋይናንሽያል ታይምስ መፅሄት ከህዳሴ ግድብ ሙሌት ጋር በተያያዘ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምትሰጠው ዓመታዊ እርዳታ የተወሰነውን ልትቀንስ መወሰኗን በተመለከተ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን አቶ ፍፁም አረጋን አናግሮ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል; " አሜሪካ ውሳኔዋን እንድታጤነው ጠይቀናል። አየጠበቅንም እንገኛለን ።የሁለቱ ሀገራት 117 አመት ዲፕሎማቲክ ግንኙነት የእነሱ የጋራ ባልሆነ ጉዳይ አይበላሽም ብለን ተስፋ እናደርጋለን " በማለት አምባሳደሩ መልስ ሰጥተዋል።
[Fidelpost]
@YeneTube @FikerAssefa

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ እና ምስራቅ ሸዋ ዞን ተፈናቃዮች ከ27 ሚሊየን 500ሺ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ መደረጉን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ።
የቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገው በባቱ እና በሻሸመኔ ከተሞች እንዲሁም ከሁለቱ ዞኖች ለተመረጡ ወረዳዎች ነው።
የድጋፉ አላማ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት ቤትና ንብረታቸው ለወደመባቸው ዜጎች ነው፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የኮከሱ አባል የሆኑት ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ እንደገለጹት ለተፈናቃዮች የተደረገው የምግብ ነክ እና የአልባሳት ድጋፍ በጥሬ ገንዘብ ሲተመን ከ27 ሚሊየን 500ሺ ብር በላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
[ETV]

የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት አቃቢ ህግና ፖሊስ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ አቀርባለሁ ያሉትን ማስረጃ ባለማቅረባቸው ለነገ ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ እንዳሉት የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በዋለው ችሎት አቃቤ ህግና ፖሊስ በ አቶ ልደቱ አያሌው ላይ አለን ያሉትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ ቢጠይቅም አቃቤ ህግ ና ፖሊስ ማስረጃውን አላቀረቡም፡፡
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ና ፖሊስ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ አለን ያሉትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ ለነገ ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን አቶ አዳነ ተናግረዋል።
ፍርድ ቤቱ በጠዋቱ ቀጠሮው ማስረጃውን አይቶ ከሰዓት 8 ላይ ውሳኔ እስጥበታለሁ ማለቱን አቶ አዳነ ተናግረዋል፡፡
[ኢትዮ ኤፍ ኤም]

በአማራ ክልል ተጨማሪ 50 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ 71 ሰዎች ደግሞ አገገሙ።
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ለ7 ሺህ 176 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ50ዎቹ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።የክልሉ ጤና ቢሮ እንዳስታወቀው በክልሉ እስከ ዛሬ ድረስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 593 ደርሷል፤ ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 462 ሰዎች አገግመዋል።በክልሉ እስከዛሬ ምርመራ የተደረገላቸው ቁጥር 151 ሺህ 58 መሆኑም ታውቋል።
[አብመድ]

በኦሮሚያ ክልል ባለፈው 24 ሰዓት ለ3021 ሰዎች በተደረገ ምርመራ 142 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ሳዑዲ ዐረቢያ ኮሮና ቫይረስን እንዳያስተላልፉ በሚል በለይቶ ማቆያዎች ያጎረቻቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኛ አፍሪካዊያን ከባድ ሥቃይ ውስጥ እንደሆኑ በምስል እና ቪዲዮ አስደግፎ ቴሌግራፍ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ከስደተኞቹ መካከል በርካታ ኢትዮጵያዊያን ይገኛሉ፡፡ እንደ ገሃነም በሚቆጠሩ ማጎሪያ ጣቢያዎች ስደተኞች ከባድ ድብደባ ይፈጸምባቸዋል፤ በርካቶችም በከባድ ርሃብ እና ሙቀት ለህልፈት ተዳርገዋል- ብሏል ዘገባው፡፡…
ሳዑዲ ዐረቢያ በአሰቃቂ ማጎሪያዎች ያጎረቻቸው ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ስላሉበት አሰቃቂ ሁኔታ ቪዲዮዎችን እና ምስሎችን በማኅበራዊ ሜዲያ ማሰራጨት ካላቆሙ በሕግ እንደሚጠየቁ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዳስጠነቀቃቸው ቴሌግራፍ ዘግቧል። ጋዜጣው ይህን ያወቀው፣ ጅዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ሰኔ 17 ከጻፈው ምስጢራዊ ደብዳቤ እንደሆነ ጠቅሷል። ቆንስላው ስለጉዳዩ ያወቀው ከጋዜጣው ዘገባ እንደሆነ ቢገልጽም፣ ደብዳቤው የሚያሳየው ግን ስደተኞቹ ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከሁለት ወራት በፊት ያውቅ እንደነበር ነው ብሏል ዘገባው። ሳዑዲ እና ተመድ ጋዜጣው ዕሁድ'ለት ስለ ስደተኞቹ ሰቆቃ ያወጣውን ዘገባ እያጣራን ነው ብለዋል።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ ከኢትዮጵያ ላይ ያገደችው የገንዘብ ዕርዳታ፣ ለሕጻናት አልሚ ምግብ፣ ቀጠናዊ እና ድንበር ጸጥታ፣ ለፖለቲካ ውድድር እና ለሀገራዊ ይሁንታ ግንባታ የታሰቡ የገንዘብ ድጋፎችን እንደሚያካትት ከአሜሪካ ኮንግሬስ ምንጮች መስማቱን ሮይተርስ ዘግቧል። ከታገደው 100 ሚሊዮን ዶላር ያህል ገንዘብ፣ 26 ሚሊዮን ዶላሩ በተያዘው የፈረንጆች ዐመት ማለቂያ የሚያበቃ ነው። እገዳው ለኤችአይቪ፣ ለፍልሰት፣ ለስደተኞች እና ለምግብ ለሰላም መርሃ ግብሮች የታሰበውን አያካትትም። የእገዳው ምክንያት የሕዳሴ ግድብ ደኅንነት ሳይረጋገጥ እና ያለሦስትዮሽ ስምምነት ኢትዮጵያ ግድቡን ውሃ መሙላቷ፣ የአሜሪካን አመኔታ በመሸርሸሩ እንደሆነ ምንጮች ነግረውኛል- ብሏል ዘገባው።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በጀርመን ዞሊነን ከተማ አንዲት እናት 5 ህጻናት ልጆቿን መግደሏ ተሰማ!
በምዕራብ ጀርመን በምትገኘው ዞሊነን ከተማ በሚገኝ አንድ አፓርታማ ዉስጥ 3 ሴት እና 2 ወንድ በድምሩ 5 ህጻናት በእናታቸው ተገድለው መገኘታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ቢልድ የተሰኘ ተነባቢ የጀርመን ጋዜጣን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ በዘገባው እንደገለጸው ህጻናቱ ዕድሜያቸው 1፣ 2 ፣ 3 ፣ 6 እና 8 ዓመት ነው፡፡የህጻናቱ አያት ናቸው የ27 ዓመት ልጃቸው እና የህጻናቱ እናት 5 ልጆቿን መግደሏን ለፖሊስ ደውለው ያሳወቁት፡፡ አንድ የ11 ዓመት ልጇ ግን ግድያው በተፈጸመበት ወቅት ከአያቱ ጋር በአያቱ ቤት በመሆኑ ማምለጡንም ለፖሊስ ገልጸዋል፡፡የልጆቿን ህይወት ያጠፋችው እናት የባቡር መንገድ አቅራቢያ ዘላ ብትወርድም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት በህይወት ተርፋለች፡፡
ድርጊቱ ለምን እንደተፈጸመ እናቲቱን ሳያናግር እና ተጨማሪ ማጣራት ሳያደርግ ማብራሪያ እንደማይሰጥ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
[Al Ain]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 804 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ10 ሰዎች ሕይወት ደግሞ አልፏል!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 20,778 የላብራቶሪ ምርመራ 804 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡
ባለፋት 24 ሰዓታት የ10 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 856 አድርሶታል።
በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 380 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 20,283 አድርሶታል፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 55,213 ደርሷል፡፡

በለስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ያለበትን ችግር በቶሎ መቅረፍ ካልቻለ እስከመዘጋት ሊደርስ እንደሚችል ተገለጸ፡፡
የኃይል ማመንጫ ጣቢያው 2002 ላይ ተመርቆ አግልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በሀገሪቱ ላለው የኃይል አቅርቦት በዋናነት ይሰራል፡፡ተንሳፋፊ ሳርና የመለዋወጫ አቅርቦት ስራውን እያስተጓጎለ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡ተንሳፋፊ ሳሩን ለማንሳትና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የጀልባ ግዢና ሌሎች ግብዓቶችን ሟሟላት ዋናው መፍትሄ ነው ተብሏል። አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት ካልተቻለ ጣቢያው ስራውን እስከማቆም እንደሚደርስ ገልጸዋል፡፡
[አሐዱ ሬዲዮ]

የአሌ ብሔረሰብ የአገር ሽማግሌዎች አቤቱታቸውን ለፌዴራል መንግስት አሰሙ!
«በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ድንበሮች ላይ የሚታየውን ደም አፋሳሽ ግጭት ለማስቆም የፌዴራሉ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ይሰጠን» ሲሉ የአሌ ብሔረሰብ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ምሁራንና የብሔሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጠየቁ። አባላቱ ዛሬ የሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ ለተለያዩ የፌዴራሉ መንግሥት ተቋማት ባስገቡት አቤቱታ እንዳሉት ከወራት በላይ ያስቆጠረውን ግጭት ለማስቆም በአካባቢው ባለሥልጣናትም ሆነ በደቡብ ክልል መንግሥት በኩል የሚደረጉት ጥረቶች ውጤት እያስገኙ አይደለም። የፌዴራሉ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በአካባቢው በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት አንዲታደግ ሲሉም አቤቱታቸውን ለተቋማቱ አሰምተዋል። በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት አንድ የደቡብ ክልል ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን በበኩላቸው መንግሥት ህዝብን በማጋጨት ትርፍ የሚሰበስቡ «የብሔር ነጋዴዎች» ባላቸው አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቀዋል። ግጭቱን በባህላዊ መንገድ ለመፍታትም በሁለቱ ማኅበረሰብ የአገር ሽማግሌዎች በኩል ጥረት እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
[DW]

በቤይሩት የነፍስ አድን ሰራተኞች በሊባኖስ ዋና ከተማ የደረሰው ከባድ ፍንዳታ አንድ ወር ከሞላው በኋላ በህንጻዎች ፍርስራሽ ውስጥ ህይወት መኖሩ የሚያሳይ ምልክት በመታየቱ ፍለጋ መጀመራቸው ተገለፀ።
ማር ሚካዔል በመባል በሚታወቀው ስፍራ በሚገኘው ህንጻ ፍርስራሽ ውስጥ የልብ ምት ተሰምቷል የሚለው ያልተረጋገጠ ዜና ከተሰማ በኋላ በህይወት ያለን ነገር የሚለይ መሳሪያ ወደ አካባቢው መላኩ ተገልጿል።ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ፍለጋው ምሽት ላይ የተቋረጠ ቢሆንም በጎ ፈቃደኞች ግን በእጃቸው ፍለጋውን መቀጠላቸው ተሰምቷል።ሐሙስ እለት በአንድ በፈራረሰ ህንጻ አካባቢ የተሰባሰቡ ከቺሊ የመጡ የህይወት አድን ሰራተኞች ፍለጋ ሲጀምሩ በርካቶች የሚፈጠረውን ተዓምር ለማየት ተሰባስበው ነበር።
በፍርስራሹ ውስጥ በህይወት ያለ ሰው መኖር አለመኖሩ አሁንም አልተረጋገጠም።የነፍስ አድን ሰራተኞች ፍርስራሹን የሚያነሳላቸው ክሬን ማግኘት ስላልቻሉ እንዲሁም ህንጻው ሊደረመስ ይችላል የሚል ስጋት በመፈጠሩ ምሽት ላይ ፍላጋቸውን አቋርጠዋል።የአካባቢው ነዋሪዎች ግን በእጃቸው ፍለጋቸውን ለማካሄድ ቆርጠው እየፈለጉ የነበረ ሲሆን ግለሰቦች ክሬን በማምጣት ፍለጋው እንዲቀጥል መደረጉን በአካባቢው ያለ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ተመልክቷል።
ከዚህ በኋላም ከቺሊ የመጡ የነፍስ አድን ሰራተኞችም ወደ ስፍራው መመለሳቸው ታውቋል።ረቡዕ እለት በፍርስራሹ አጠገብ አነፍናፊ ውሻ ይዘው የሚያልፉ የነፍስ አድን ሰራተኞች፣ ውሻው በህይወት ያለ ሰው መኖሩን ምልክት እንደሰጣቸው ተናግረዋል።
ሐሙስ እለት በድጋሜ ውሻው በተመሳሳይ ስፍራ በህይወት ያለ ሰው መኖሩን ምልክት ሰጥቷል። ቡድኑ ፍለጋውን ለማካሄድ የልብ ምት ወይንም ትንፋሽ መኖሩን ለማረጋገጥ ስካነር (መመርመሪያ) ከተጠቀመ በኋላ ፍርስራሹን ለማንሳት መሳሪያዎችን ይዞ መጥቷል።የነፍስ አድን ሰራተኞቹ በሰባት ቡድን በመከፋፈል ህንጻው ዳግም እንዳይደረመስ በመስጋት ፍርስራሹን አንድ በአንድ ማንሳት ጀምረዋል። በስፍራው የነበረው የቢቢሲ ጋዜጠኛ እንደተመለከተው በህይወት ያለ ሰው ለመፈለግ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግም ምንም ምላሽ የሚሰጥ አካል የለም።
[BBC]

ጳጉሜ 1 የብስክሌት እና የእግረኞች ቀን ሆኖ ይውላል - ትራንስፖርት ሚኒስቴር
ጳጉሜ 1 ቀን 2012 ዓ.ም የብስክሌት እና የእግረኞች ቀን ሆኖ እንደሚውል ትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።ቀኑ በሀገር ደረጃ በሁሉም ክልል ዋና ከተሞች እና በሌሎች አካባቢዎች የሚከበር እንደሚሆንም ነው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የገለጸው።በ2013 ዓ.ም ዓመቱን ሙሉ ወር በገባ በመጨረሻው እሑድ የብስክሌት እና የእግረኞች ቀን ይሆናልም ብሏል።በእግር እና ብስክሌት የሚደረግ ጉዞ የትራፊክ መጨናነቅ እና አደጋዎችን እና የአካባቢ አየር ብክለት ችግሮችን ለመቀነስ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል።በተጨማሪም የማኅበረሰቡ ጤናም እንዲጠበቅ እና ተመራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት ጥያቄዎችን በማስተናገድ የበኩሉን የሚያበረክት የትራንሰፖርት ዘርፍ እንደሆነም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።የኢፌዴሪ የትራንፖርት ሚኒስቴር የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም ገልጿል።
[EBC]

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለነገ የጠራው አስቸኳይ ስብሰባ አጀንዳው ካልተነገራቸው የትግራይ ተወካዮች እንደማይሳተፉ የክልሉ ም/ቤት አስታወቀ!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ አስቻኳይ ስብሰባ ነሐሴ 30/2ዐ12 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ እንደሚካሔድ መግለጹ ይታወቃል፡፡ለስብሰባው የም/ቤቱ አባላት ነሐሴ 29 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም በፌዴሬሽን ም/ቤት ጽ/ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉም አስታውቋል፡፡
ይሁንና የስብሰባው አጀንዳ ካልታወቀ የትግራይ ክልል ተወካዮች እንደማይገኙ የክልሉ ም/ቤት ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ ማሳወቁን የትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ በፌስ ቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡በፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልሉ ተወካዮች አጀንዳውን አውቀው ሳይዘጋጁ መሳተፍ እንደማይችሉ ነው በደብዳቤው ላይ የተገለጸው፡፡

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነርስ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አለፈ!
በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በነርስነት እያገለገሉ የነበሩት አንበሳአውድም ዮሃንስ በትናንትናው ዕለት በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ሆስፒታሉ አስታውቋል።ነርስ አንበሳአውድም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህዝቡን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውንም ከሆስፒታሉ ፌስቡክ ገፅ መረዳት ተችሏል።ነርሱ የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላም በትናንትናው ዕለት ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
[BBC]
ፎቶ፦ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ነው!
መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የስኳር እጥረት እንዳይከሰት ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ተገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንደገለጹት መጪውን የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር ፍላጎት ለማሟላትና የአቅርቦት እጥረት እንዳይገጥም 2 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ግዥ ተፈጽሞ ወደ ሀገር ውስጥ በመግባት ላይ ነው፡፡
መሰረታዊ የምግብ ምርት የሆነው ስኳር በሀገር ውስጥ እየተመረተ ለህብረተሰቡ የሚሰራጭ ሲሆን ፍላጎቱ ከአቅርቦቱ በላይ በሚሆንበት ጊዜ ከውጪ ተገዝቶ እየመጣ የሀገሪቱን የሥኳር ገበያ የማረጋጋት እና ህብረተሰቡ የሚያስፈልገውን የስኳር መጠን እንዲያገኝ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከስኳር ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ እየሰራ ስለሚገኝ የአቅርቦት ችግር የለም፡፡
በስኳር ኮርፖሬሽን የአቅርቦት ክትትልና ዌር ሀውስ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ተሰማ በበኩላቸው ወደ ሀገር ውስጥ በመግባት ላይ ያለው ስኳር እንዳለ ሆኖ ለቀጣይ ሁለት ወራት ለሀገራችን ህብረተሰብ ፍጆታ የሚሆን በቂ ስኳር በክምችት ስላለ እጥረት አይገጥመንም ብለዋል፡፡
[የን/ኢ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት]

የትግራይ ክልል ምክርቤት 5ተኛ የስራ ዘመን 10ኛውን አስቸኳይ ጉባኤ በቪድዮ ኮንፈረንስ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
[ድምፂ ወያኔ አማርኛ]
@YeneTube @FikerAssefa
[ድምፂ ወያኔ አማርኛ]
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መከላከያ 77 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ።
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ወይም ዩኤስ ኤይድ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል 77 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።የድርጅቱ ሀላፊዎች ድጋፉን ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስረክበዋል።ድርጅቱ ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍም በትዊተር ገጹ አስታውቋል።በኢትዮጵያ እስከ ትናንትናው ዕለት ድረስ ብቻ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 55 ሺህ 213 ሲደረስ 856 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን እንዳጡ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መረጃ ያስረዳል።
[Ethio FM]

ፍርድ ቤቱ ፖሊስ በአስራት ጋዜጠኞች ላይ አለኝ የሚለውን መረጃ ለጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም እንዲያቀርብ ቀጠሮ ሰጠ።
ፖሊስ ለዛሬ ነሃሴ 29/2012 ዓ/ም በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ አለኝ የሚለውን መረጃ እንዲያቀርብ ቀጠሮ ተሰጥቶት የነበር ቢሆንም ሳያቀርብ መቅረቱ ተገልጿል።በዛሬው ችሎት ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን እንዲሰጠው ጠይቆ የነበር ቢሆንም የተከሳሾቹ ጠበቃ ፖሊስ በተደጋጋሚ እያስቀጠረ መረጃ ማቅረብ አለመቻሉን ጠቅሰው ተቃውመዋል። ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ለጳጉሜ 2/2012 አለኝ የሚለውን መረጃ እንዲያቀርብ ተጨማሪ 3 ቀን ፈቅዷል።በሌላ በኩል ባለፉት የችሎት ውሎዎች ፍርድ ቤቱ የአሥራት ጋዜጠኞች የእስር ቤት አያያዝ እንዲሻሻል ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ትዕዛዙ እንዳልተከበረ ጋዜጠኞቹ እና ጠበቃቸው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።ፍርድ ቤቱም ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹን አያያዝ በህጉ መሰረት እንዲይዝ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነርስ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አለፈ! በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በነርስነት እያገለገሉ የነበሩት አንበሳአውድም ዮሃንስ በትናንትናው ዕለት በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ሆስፒታሉ አስታውቋል።ነርስ አንበሳአውድም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህዝቡን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውንም ከሆስፒታሉ ፌስቡክ ገፅ መረዳት ተችሏል።ነርሱ…
ወገናቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተይዘው ህይወታቸው ያለፈው የነርስ አምበሳአውድም ዮሃንስ የአስክሬን ሽኝት በሆስፒታሉ ሰራተኞችና የስራ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
.
ነርስ አንበሳአውድም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተይዘው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ በትላንትናው እለት ነሀሴ 28 2012 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
Via Hakim
የኔቲዩብ ለቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል!