YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Audio
በትግራይ ክልል በጣለው ከባድ ዝናብ በህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ!

በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አህፈሮም ወረዳ በአለፉት ተከታታይ ቀናት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የተከሰተ ጎርፍ በህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የVoA የድምፅ ዘገባ ያዳምጡ
@YeneTube @FikerAssefa
በመጪው ዓመት ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ ከመወሰኑ በፊት የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ተግባራት ሊከናወኑ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ተናገረ።

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ተጨማሪ 71 ዜጎች ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ ገብተዋል!

በ8ኛው ዙር የትራንስፖርት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን ለመጓዝ ተመዝግበው የነበሩ 71 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ሐሙስ ሴፕተምበር 3/2020 አገር ቤት መግባታቸውን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት መንግስት ቸልተኝነት አሳይቷል መባሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ አስተባበለ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃው ከሳውዲ መንግስት ከደረሰኝ ጊዜ ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ማለትም ከሰላም ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ሳደርግ ነው የቆየሁት ብሏል።

በዚህም ዝርዝር መረጃቸው የተላከልንን ወደ 2000 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያንን ከጳጉሜ 3 እስከ መስከረም 27 ባሉት ቀናት ውስጥ ለማስወጣት ተዘጋጅቻለው ብሏል።

ሙሉ የእንግሊዝኛ መግለጫውን ከላይ አያይዘናል👆👆

@YeneTube @FikerAssefa
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ጽ/ቤት ሃላፊ ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት 140 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

አቶ ኤፍሬም አለሙ የተባሉ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ ጽኅፈት ቤት ሃላፊ ለተገልጋይ ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት 140 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ባለጉዳዩ ለከንቲባ ጽ/ቤት እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባደረሰው ጥቆማ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በተደረገ ክትትል የጽህፈት ቤት ሃላፊውን ገንዘቡን ሲቀበል በቁጥጥር ስር መዋሉን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወንጀል ክትትል ሃላፊ ኮማንደር አወሉ አህመድ ተናግረዋል፡፡ህብረተሰቡ ህጋዊ ለሆነ አገልግሎት ጉቦ መሰል እጀ መንሻ የሚጠይቁ የመንግስት መዋቅር ላይ ያሉ አካላትን በማጋለጥ እና ጥቆማ በመስጠት ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 በተለምዶ ሱማሌ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከተለያዩ ቦታዎች የተሰረቁ የመኪና እቃዎች እንደሚሸጡ ለፖሊስ በደረሰው ጥቆማ በፍ/ቤት ትዕዛዝ መሰረት ብርበራ መደረጉን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ቲም ሃላፊ ኢንስፔክተር ታምራት ቻለው ተናግረዋል፡፡

ነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ/ም በሶስት ንግድ ቤቶች ላይ ፖሊስ ባደረገው ብርበራ የተሰረቁ በርካታ ስፖኪዮ፣ ፍሬቻ፣ የዝናብ መጥረጊያ እና ሌሎች የመኪና ዕቃዎች እንደተያዙ የገለፁት ኢንስፔክተር ታምራት ቻለው የተሰረቁ ዕቃዎችን ሲገዙ ነበር ተብለው የተጠረጠሩ እና በመኪና ዕቃ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሶስት ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

[Addis Ababa Police Commission]
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ልደቱ አያለው በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በሌላ መዝገብ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

አቃቤ ህግም በችሎቱ ተገኝቶ እጃቸው ላይ የተገኘ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ የሚል እና ለውጡን ተቃርኖ “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚል ርእስ የተሰጠው የፖለቲካ ይዘት ያለውና ህገ መንግስቱን ለመናድ አልሞ የተዘጋጀ ሰነዶችን ተከትሎ ክስ ለመመስረት እየመረመረ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል።አቶ ልደቱ አያለው በበኩላቸው “የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ በመንግስት ደረጃ አስገብቼው ተቀባይነት የለውም ተብዬ ያስቀመጥኩት ነው፤ ተጠያቂነት ቢኖረው ኖሮ መንግስት ተቀባይነት የለውም ብሎ ዝም አይለኝም ነበረ” ብለዋል።

ሁለተኛው ማለትም “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚለውም ቢሆን በረቂቅ ላይ ያለ ያልታተመ ነው፤ ልከሰስ የምችለው ሰነዱን አሳትሜ አሰራጭቼ ቢሆን ነበረ፤ በዚህች ሀገር ላይ ሳንሱር የለም ስለዚህ ሀሳቤን ነው እየገለፅኩ ያለሁት፤ ፍርድ ቤቱ ይህንን ሊረዳልኝ ይገባል” ሲሉም ተናግረዋል።

“ውጭ ሀገር ሄጄ የታከምኩት ሀብታም ነጋዴ ሆኜ ሳይሆን፤ ህክምናው እዚህ ስለሌለ ነው፤ ይህንን ፍርድ ቤቱ ከግምት ያስገባልኝ” ሲሉም ጠይቀዋል።

የአቶ ልደቱ አያለው ጠበቃም ለደንበኛቸው ዋስትና እንዲፈቅድላቸው ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል።የቢሾፍቱ ከተማ አቃቤ ህግ በበኩሉ፥ አቶ ልደቱ አያሌው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ አመጽና ሁከት በመቀስቀስ በህገ ወጥ መንገድ የመንግስት ምስረታ ለማከናወን አቅደው በመንቅሳቀስ ተጠርጥረው በቁጥጥር መዋላቸውን ለችሎቱ ገልጿል።የሁለቱን ክርክር የተከታተለው ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለከሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የዲቾቶ - በልሆ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ!

በኢትዮጵያ መንግስት በአፋር ክልል ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው 78 ኪሎ ሜትር የዲቾቶ - በልሆ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገደኞች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡በሲሚንቶ ኮንክሪት ደረጃ የተሰራው መንገድ፤ አዲሱን የታጁራ ወደብ ለመጠቀም ከማስቻሉም በላይ በነባሩ ጅቡቲ ወደብ ይፈጠር የነበረውን የትራንስፖርት ጫና ይቀንሳል ተብሏል፡፡

የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ በአነስተኛ ጥገና እስከ 40 አመት አገልግሎት መስጠት የሚችል በመሆኑ ለጥገና የሚወጣውን ወጪ በእጅጉ እንደሚቀንስ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ፕሮጀክቱ የአገሪቷ የወጪ ገቢ ንግድ የሚካሄድበት ኮሪደር እንደመሆኑ መስመሩን የሚጠቀሙ የጭነት ተሽከርካሪዎች ክብደት የመሸከምም አቅም እንዲኖረው ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ከዚህ ባሻገር በአካባቢው ያለውን የፖታሽ ክምችትም ሆነ ሌሎች ማእድናት በቀላሉ ካለምንም ውጣ ውረድ ወደ አቅራቢያ ወደብ ለማድረስ ያግዛል ተብሏል፡፡

[ERA & ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከእስር ተፈቱ!

የፓርቲያቸው ሥራ አስፈጻሚ አባል ምዕራፍ ይመር እንደገለጹት የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) ሊቀመንበር  ኢንጅነር ይልቃል ዛሬ በዋስትና ከእስር ተለቀዋል፡፡ፖለቲከኛው ኢንጂነር ይልቃል በተለምዶ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ በሚጠራው ማረሚያ ቤት ሁለት ወር ታስረዋል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በ2012 በጀት ዓመት 1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ኦነግ ከፓርቲው ህግና ስርአት ባፈነገጠ መልኩ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን አሳሳች መግለጫዎችን ሲሰጡ በነበሩ አመራሮቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።

የኦነግ ቃላ አቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንዳሉት የተወሰኑ ሰዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በመቅረብ አላስፈላጊ መግለጫዎችንና መልዕክት በማስተላለፋቸው ምክንያት በተፈጠረ ውዝግብ ላይ ብሔራዊ ምክር ቤቱ በጠቅላላ ጉባኤ በዲሲፕሊን እንዲጠየቁ የሚያስችል ውይይት ማድረጉን ተናግረዋል።በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በአመራሮች መካከል የርዕዮተ አለም ልዩነት እንዳለ የሚነገረው ትክክል አለመሆኑንም አቶ ቀጀላ ተናግረዋል፡፡

ይህ አይነት ነገር እንዲፈጠር ባደረጉት አመራሮች ላይ ግን የዲሲፕሊን እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል፡፡ቀደም ብሎ የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት መጋቢት ላይ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ቀጣዩ ጉባኤ የፊታችን ታህሳስ 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ በመወሰኑ ይህም ጉዳይ በዚህ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ቀርቦ እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡

ከዚያ በፊት ግን ብሔራዊ ምክር ቤቱ ተሰብስቦ አሁን የተፈጠሩትን ጉዳዩች በመመልከት ውሳኔ ከሰጠ በኃላ ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርባል ብለዋል፡፡የዲሲፕሊን እርምጃው የሚወሰድባቸው አመራሮች እነማን ናቸው? በሚል ላነሳንላቸው ጥያቄ ዝርዝር ጉዳዮች በውስጥ ጉዳይ የተያዙ በመሆናቸው መናገር አልችልም ብለዋል።ኦነግ በአመራሮቹ መካከል የተነሳውን ውዝግብ ለመፍታት ያለመ ውይይት ታዛቢዎች ባሉበት ማካሄዱ ይታወሳል።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ኢንቨስትመንት የታክሲ አገልግሎት ተጀመረ!

በ2.9 ቢሊዮን ብር ካፒታል ዘርፈ ብዙ የትራንስፖርትና ተጓዳኝ አገልግሎቶችን ለማቅረብ እንደተነሳ ያስታወቀው ዜብራ ራይድ የተሰኘ ድርጅት ሥራ ጀመረ፡፡ ዜብራ ራይድ በዘመናዊ የከተማ ትራንስፖርት፣ በበይነ መረብ ግብይት፣ በመኪና ኪራይ፣ ምርትና አገልግሎት በማጓጓዝ ሥራዎች ላይ የሚሠራ ዜብራ ዴሊቨሪ የተሰኘውን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ያጠቃለለ ሥራ ላይ ይሠማራል ተብሏል፡፡

የዜብራ ራይድ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ዲማ እንዳስረዱት፣ ከ2,000 በላይ ተሽከርካሪዎችን በስልክና በድረገጽ ጥሪ አማካይነት በጊዜያዊነት ወደ ትራንስፖርት አገልግሎት ያስገባል፡፡ በራሳቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ትራንስፖርት አገልግሎት ሥርዓቱ ከሚካተቱት ከእነዚህ በተጓዳኝ፣ ከሦስት ወራት በኋላ ተጨማሪ 5,000 ተሽከርካሪዎችን ለማካተት ከአስመጪዎች ጋር ድርድር መጀመሩን አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል።ከትራንስፖርት አገልግሎት በተጨማሪ በበይነ መረብ ወይም በኦንላይን አማካይነት ከአሜሪካ፣ ከአውስትራሊያ እንዲሁም ከእስያ ፓስፊክ አገሮች የቀጥታ ግብይት መፈጸም የሚያስችል ሥርዓት መዘርግጋቱን የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ አስታውቀዋል፡፡

ኩባንያው ግዥ ለሚፈጽምባቸው ተሽከርካሪዎች ከአዋሽ ባንክ ብድር አገልግሎት እንዳገኘ ጠቅሶ፣ ተሽከርካሪዎቹን የሚረከቡ ግለሰቦችም የ30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ በመፈጸም፣ የዜብራ ራይድ አሽከርካሪ መሆን የሚችሉበት ሥርዓት መዘርጋቱን አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡ የአንድ ተሽከርካሪ ሙሉ የክፍያ ዋጋ 800,000 ብር ሲሆን፣ የ240,000 ብር ቅድሚያ ክፍያ በመፈጸምና ቀሪው በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ የግላቸው የሚያደርጉበት ሥርዓት ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በአዳማ፣ በሐዋሳ፣ በድሬዳዋና በባህር ዳር በቅርቡ የሚጀመር ሲሆን ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኬንያ ናይሮቢ በወኪሎች አማካይነት በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገቡ አቶ ተስፋዬ ይገልጻሉ፡፡ በዚህ የሥራ ዘርፍ ብዙ ጥናት የተደረገበት ሲሆን በኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የትራንስፖርት ችግር ሊቀርፍ የሚችል ፕሮጀክት ነው፡፡ በአዲስ አበባ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች አብዛኛዎቹ የመነሻ ታሪፋቸው 50 ብር ሲሆን፣ ዜብራ ራይድ በ35 ብር መነሻ ሒሳብ ወደ ሥራ እንደገባ አስታውቋል፡፡ዜብራ ራይድ በአዲስ አበባ የሚገነባው የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ከሚገኘው ገቢ አምስት በመቶ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ወንድሙ ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ከ5,000 በላይ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ሲጠበቅ፣ በቅድሚያ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሠራም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ይገልጻሉ፡፡

አገልግሎቱ የሚቀርባቸው ተሽከርካሪዎች በላይ አብ ሞተርስን ጨምሮ ሌሎችም ከኩባንያው ጋር በአቅራቢነት ለመሥራት በሒደት ላይ እንደሚገኙ ሲገለጽ፣ ተሽከርካሪዎቹም ከአራት እስከ ሰባት ተሳፋሪ የመያዝ  አቅም እንደሚኖራቸው ተብራርቷል፡፡የሱዙዚኪ እንዲሁም የግሎሪ ኩባንያዎች ሥሪት የሆኑ መኪኖች ለዜብራ ራይድ አገልግሎት ከተመረጡት መካከል ሲሆኑ፣ 2,000 ተሽከርካሪዎች ግን ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ የገቡት አገልግሎት ሰጪዎች በግል ተሽከርካሪዎቻቸው አማካይነት እንደሚሆን አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል፡፡  

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
"117 አመት የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ግንኙነት የሁለቱ ሀገር የጋራ ባልሆነ ጉዳይ አይበላሽም ብለን ተስፋ እናደርጋለን " አምባሳደር ፍፁም አረጋ

ፋይናንሽያል ታይምስ መፅሄት ከህዳሴ ግድብ ሙሌት ጋር በተያያዘ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምትሰጠው ዓመታዊ እርዳታ የተወሰነውን ልትቀንስ መወሰኗን በተመለከተ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን አቶ ፍፁም አረጋን አናግሮ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል; " አሜሪካ ውሳኔዋን እንድታጤነው ጠይቀናል። አየጠበቅንም እንገኛለን ።የሁለቱ ሀገራት 117 አመት ዲፕሎማቲክ ግንኙነት የእነሱ የጋራ ባልሆነ ጉዳይ አይበላሽም ብለን ተስፋ እናደርጋለን " በማለት አምባሳደሩ መልስ ሰጥተዋል።

[Fidelpost]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ እና ምስራቅ ሸዋ ዞን ተፈናቃዮች ከ27 ሚሊየን 500ሺ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ መደረጉን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ።

የቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገው በባቱ እና በሻሸመኔ ከተሞች እንዲሁም ከሁለቱ ዞኖች ለተመረጡ ወረዳዎች ነው።

የድጋፉ አላማ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት ቤትና ንብረታቸው ለወደመባቸው ዜጎች ነው፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የኮከሱ አባል የሆኑት ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ እንደገለጹት ለተፈናቃዮች የተደረገው የምግብ ነክ እና የአልባሳት ድጋፍ በጥሬ ገንዘብ ሲተመን ከ27 ሚሊየን 500ሺ ብር በላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት አቃቢ ህግና ፖሊስ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ አቀርባለሁ ያሉትን ማስረጃ ባለማቅረባቸው ለነገ ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ እንዳሉት የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በዋለው ችሎት አቃቤ ህግና ፖሊስ በ አቶ ልደቱ አያሌው ላይ አለን ያሉትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ ቢጠይቅም አቃቤ ህግ ና ፖሊስ ማስረጃውን አላቀረቡም፡፡

በመሆኑም ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ና ፖሊስ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ አለን ያሉትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ ለነገ ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን አቶ አዳነ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱ በጠዋቱ ቀጠሮው ማስረጃውን አይቶ ከሰዓት 8 ላይ ውሳኔ እስጥበታለሁ ማለቱን አቶ አዳነ ተናግረዋል፡፡

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ተጨማሪ 50 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ 71 ሰዎች ደግሞ አገገሙ።

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ለ7 ሺህ 176 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ50ዎቹ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።የክልሉ ጤና ቢሮ እንዳስታወቀው በክልሉ እስከ ዛሬ ድረስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 593 ደርሷል፤ ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 462 ሰዎች አገግመዋል።በክልሉ እስከዛሬ ምርመራ የተደረገላቸው ቁጥር 151 ሺህ 58 መሆኑም ታውቋል።

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa