የአዋሽ ወንዝ ከመጠን በላይ በመሙላቱ መተሐራ ከተማ በጎርፍ መጥለቅለቋ ተሰማ!
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በመተሐራ ፣ አዲስ ከተማና መርቲ የአዋሽ ወንዝ ከመደበኛ መፍሰሻው ወጥቶ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአል ዐይን ገለጹ፡፡ነዋሪዎቹ እንዳሉት አሁን ላይ የነፍስ አድንሥራ እየተሰራ ነው፡፡
የሥኳር ፋብሪካው በሚገኝበት መርቲና ከመተሃራ ወደ ሥኳር ፋብሪካው በሚወስደው መንገድ ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አዲስ ከተማ ላይ ነው ወንዙ ሰብሮ ጉዳት ያደረሰው፡፡ በጎርፍ አደጋው የደረሰው የአደጋ አይነት እና መጠን በዝርዝር አልታወቀም፡፡
በአሁኑ ሰዓት ጎርፉ አዲስ ከተማን ማጥለቅለቁንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ የአዲስ ከተማ አንቀጸ ሰላም መድኃኒዓለም ገዳም በጎርፉ እንደተጥለቀለቀ የተገለጸ ሲሆን ካህናቱና ዲያቆናቱ የቃልኪዳን ታቦታቱን እና ንዋየ ቅዱሳቱን ይዘው በመተሐራ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንደሚገኙም ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የገለጹት፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa

ተጨማሪ 74 ዜጎች ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ ገብተዋል!
ከ8ኛው ዙር የትራንስፖርት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን ወደ አገር ቤት ለመጓዝ ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ ከነበሩ ዜጎች ውስጥ ተጨማሪ 74 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ነሐሴ 27 ቀን ወደ አገራቸው ገብተዋል፡፡ባለፉት ሶስት ቀናት ወደ አገር ቤት ከተመለሱት ውስጥ፣ በእስር ቤት የነበሩ፣ የመኖሪያ ፍቃድ ያልነበራቸው፣ በአሰሪዎቻቸው በደል ደርሶባቸው እርዳታ ሲደረግላቸው የነበሩ፣ እንዲሁም ሆስፒታል ህክምናዋን እንድትከታተል እገዛ ሲደረግላት የነበረች ኢትዮጵያዊት በአጠቃላይ 329 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ ነሐሴ 27 ማታ እና በመጭዎቹ ቀናት 81 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ሊባኖስ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንጽላ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
[EPA]

በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ላይ የዐቃቤ ህግ የቀዳሚ ምርመራ ምስክሮችን የመስማት ሂደት ዛሬም ቀጥሏል።
የዐቃቤ ህግ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ቁጥር 215585 አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ቀርበዋል።የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትናንት በልደታ አዳራሽ በተጠርጣሪዎች ላይ ምስክሮችን ሲሰማ መዋሉ የሚታወስ ነው።ችሎቱ የዐቃቤ ህግ የቀዳሚ ምርመራ ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ለዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፤ በዚሁ መሰረት ምስክሮችን የመስማት ሂደት ካቆመበት ዛሬ ቀጥሏል።
የዛሬው የምስክር መስቀለኛና ማጣሪያ ጥያቄ ከመቅረቡ በፊት አቤቱታ ቀርቧል።11ኛ ተጠርጣሪ አቶ ሀምዛ አዳነ ባቀረቡት አቤቱታ በመገናኛ ብዙሃን፣ በፌስቡክና በዩቲዩብ እንዲሁም በጋዜጦችና መጽሔቶች ስማቸው እየጠፋ መሆኑን በመግለጽ አቤቱታ አቅርበዋል።የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ተጠርጣዎቹ ትናንት ችሎቱ ሙሉ ቀን የዋለ ቢሆንም ምሳቸውን ሳይበሉ መቆያታቸውን አስታውሰው፤ ዛሬም ችሎቱ ሙሉ ቀን የሚውል በመሆኑ ምሳ እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል።
ችሎቱ አቶ ሀምዛ አዳነ ባቀረቡት አቤቱታ መገናኛ ብዙሃኑ እነማን እንደሆኑና ምን አንዳቀረቡ በዝርዝር ካላስረዱ ፍርድ ቤቱ እርምጃ መውሰድ እንደማይችል ገልጿል።
በተጠርጣሪ ጠበቆች ምግብን አስመልክቶ ለቀረበው አቤቱታ የፌደራል ፖሊስ በችሎቱ ቀርቦ ፍርድ ቤቱ ትናንት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የተጠርጣሪ ቤተሰቦች ቀደም ብለው ምግብ እንዲያቀርቡ በማድረግ ቁርስ እንዲመገቡና በተመሳሳይ ለምሳቸውም ይዘው እንዲመጡ ማድረጉን አስረድቷል።ፖሊስ ይሄን ያደረገውም ንክኪን በመቀነስና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ በሚያስችል አግባብ መሆኑን ገልጿል።ችሎቱ አቤቱታዎቹን በመስማት ከትናንት የቀጠለው የቀዳሚ ምርመራ ቀሪ ምስክሮችን የመስማት ሂደት ቀጥሏል።
[ENA]

የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ። በዕለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የሚካሔደው የምክር ቤቱ ስብሰባ የመወያያ አጀንዳ አልተገለጸም።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ-19 ተፅዕኖ የተጎዱ የቱሪዝም ዘርፍ ተዋናዮችን ለማገዝ ያለመ የኦንላይን ፎቶ ኤግዚቢሸን ሊደረግ ነው!
ኮቪድ-19 ተፅዕኖ የተጎዱ የቱሪዝም ዘርፍ ተዋናዮችን ለማገዝ ያለመ ‘የኦንላይን ፎቶ ኤግዚቢሸን ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ሆቴልና ማርኬቲንግ ማህበር ገለፀ።ማህበሩ ወደ አፍሪካ የሚገቡ የውጭ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን መዳረሻ ለሚያደርጉ ‘የቱሪስት ፓኬጅ’ም እያዘጋጀሁ ነው ብሏል።
የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታዲዎስ ክንፉ ለኢዜአ እንደተናገሩት ኑሮአቸውን ጎብኚዎችን በማስተናገድ ብቻ ያደረጉ የቱሪስት መዳረሻዎች አሁን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ”በእጅጉ” ተጎድተዋል። በዚህም ማህበሩ የዘርፉ ተዋናዮች ከደረሰባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂና ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴሮች ጋር በመተባበር የኦንላይን ኤግዚቢሽን ለማዘጋጀት እየሰራ ነው ብለዋል።
ኤግዚቢሽኑን ለማድረግ የሚያስችለው መተግበሪያም 80 በመቶው ሥራው መጠናቀቁን የገለጹት አቶ ታዲዎስ፤ ለአንድ ዓመት የሚቆየው መተግበሪያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ክፍያውን በመፈጸም ኤግዚቢሽኑን የሚሳተፉበት ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል። ማህበሩ ባደረገው ጥናት በኤግዚቢሽኑ ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱን አስረድተዋል።
[Addis Zeybe]

መንግስት ከውጪ የሚያስመጣው ፓልም የምግብ ዘይት ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በሃገር ውስጥ በከፊል ሊመረት ነው፡፡
መንግስት በዜጎች ላይ የኑሮ ውድነት እንዳይፈጠር መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦችን በድጎማ ከውጪ ከሚያሥገባቸው ሸቀጦች ውስጥ አንዱ የሆነውን ፓልም የምግብ ዘይት ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በሃገር ውስጥ ለማምረት እንቅስቃሴ መጀመሩን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ትራንስፎርሜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር አቶ አድማሱ ይፍሩ ተናገሩ፡፡ፌቬላ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ደብሊው ኤ የዘይት ማምረቻና ማከፋፈያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ሸሙ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና አል ኢምፔክስ ዘይት ማምረቻ የተባሉት አራት ፋብሪካዎች ዘይቱን ለማምረት ፍቃድ የተሰጣቸው መሆኑን አቶ አድማሱ ገልጸዋል፡፡
እነዚህ ኩባንያዎች የምርት ሂደታቸውን በቅርቡ እንደሚጀምሩ የገለጹት ዳይሬክተሩ ለግብዓትነት የሚጠቀሙበትን የዘይት ድፍድፍ ከውጪ ለማስመጣት ይቻል ዘንድ ከብሄራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ ጥያቄ አቅርበው አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ ተናግረዋል፡፡ሃማሬሳ የምግብ ዘይት ማምረቻ አክሲዮን ማህበርም ዘይቱን ለማምረት ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ሂደቱ ታይቶ ፈቃድ መስጠት ሲጀመር ሚኒስቴር መ/ቤቱ ለድርጅቱ ምላሽ እንደሚሰጠው ይጠበቃል ያለው ንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ነው፡፡
[AMN]

ቤትፌር የተባለው ታዋቂው የውርርድ ድርጅት ዶናልድ ትራምፕ በመጪው ህዳር በሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የማሸነፍ ግምቱን ሰጥቷቿል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተቀናቃኛቸው ጆይ ባይደን ግምቱ የተሰጣቸው የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ግምቱ ወደ ትራምፕ ዞሯል። በተያያዘ ዜና 81 የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሰዎች ለጆይ ባይደን፣ ቢመረጡ የተሻለ ነገር ያሳይሉ የሚል ይሁንታ እንደሰጧቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት አጀማመርና የኮቪድ -19 ተፅዕኖ ላይ ውይይት ተደረገ!
39ኛው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ጉባኤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት አጀማመርና የኮቪድ -19 ተፅዕኖ እንዲሁም ሰላማዊ መማር ማስተማር ላይ ትኩረት በማድረግ ተካሂዷል፡፡ነሐሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው ምክክር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራስን ከመግዛትና የባህል ብዝሃነትን ከማስተናገድ አንፃር የተማሪዎች ህብረት ሚና ምን መሆን አለበት የሚለው በሰፊው ተዳሷል፡፡
የተማሪዎች ህብረት አመራሮች በመማር ማስተማር ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ሂደት ተገቢውንና ትክክለኛውን አቅጣጫ በመያዝ በሰላማዊ መንገድ ሊሰሩ ይገባል ተብሏል፡፡በጉባዔዉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንትና አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተጋበዙ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች እና አሰልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡
[EBC]

የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ ሊያቀርብ የነበረውን የ2 ቢልዮን ዶላር የድጋፍ እና ብድር ስምምነት አቋርጧል የሚል ዜና ዛሬ በዋዜማ ሬድዮ ተሰርቶ በስፋት ሶሻል ሚድያ ላይ ተጋርቷል።
በዘገባው መሰረት የተቋረጠው ስምምነት የኮሮና ቫይረስ ጫናን ለመከላከል እና ለሰብዓዊ ስራዎች ከሚውለው ውጪ ለኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ባንኩ ሊያቀርበው የነበረውን ነው።
መረጃውን ለማጣራት ለኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም ለአለም ባንክ ኢትዮጵያ ቼክ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
የኢትዮጵያ መንግስት መረጃው የሀሰት እንደሆነ ገልፆ "ይህ በለጋሽ ሀገራት እና በኢትዮጵያ መሀል ያለውን ግንኙነት ለማጠልሸት ታስቦ የተሰራጨ ነው። እንኳን ድጋፉ ሊቋረጥ በዚህ ዙርያ ምንም አይነት ውይይትም ሆነ ንግግር አልነበረም" ብሏል።
የአለም ባንክ የ2 ቢልዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ አቋረጠ መባሉን አስመልክቶ ከመንግስት እና ከባንኩ የደረሱንን መረጃ አጋርተናችሁ ተጨማሪ መረጃ ዛሬ ከባንኩ እንደሚጠበቅ ገልፀን ነበር።
ከባንኩ ቃል አቀባይ ዴቪድ ኤም ቴኺስ ከደቂቃዎች በፊት ለኢትዮጵያ ቼክ የደረሰው ይህ መረጃ እንደሚያመለክተው ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና ለሚያስፈልገው የፋይናንስ አቅም "ሙሉ ድጋፍ" እንደሚሰጥ ባንኩ አስታውቋል።
ባንኩ በIDA-19 እቅዱ ኢትዮጵያ ውስጥ ፋይናንስ የሚያረጋቸው የልማት ፕሮግራሞች 2.9 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ጠቅሶ ለባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ የሚቀርቡ ፕሮጀክቶች የተለመደ ሂደታቸውን ጠብቀው እያለፉ እንደሆነ ገልጿል።
Via @EthiopiaCheck

በአዲስ አበባ በደረሰው የእሳት አደጋ 12 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ!
የእሳት አደጋ መከላከል ሰራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ዛሬ 6 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲኤም ሲ በደረሰ የእሳት አደጋ 12 ሚሊዮን 856 ሺ 620 ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ አደጋው ከዚህ በላይም ጉዳት ሊያደረስ ይችል እንደነበር ለአል ዐይን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ከ 48 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረትን ከውድመት መታደግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠር አራት ሰዓት ከ15 ደቂቃ መፍጀቱን ያነሱት አቶ ጉልላት አምስት የአደጋ ሰራተኞች በሥራ ላይ ሳሉ ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ብለዋል።ከ70 በላይ የአደጋ መከላከል ሰራተኞችና ከ14 በላይ ከባድ ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል።

ወደፊት የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ የሚሰጣቸው 2 የውጭ ኩባንያዎች በውድድር፣ ታሪፍ እና ሲም ካርድ አቅርቦት ረገድ ሊከተሏቸው የሚገቧቸውን መመሪያዎች የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለስልጣን ማዘጋጀቱን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ መመሪያዎቹ የቴሌኮም ገበያውን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ እና የገበያውን ስነ ምግባር ለመቆጣጠር እና የአገልግሎት ደረጃ ለማውጣት ያለሙ ናቸው፡፡ ባለሥልጣኑ የሲም ካርድ አሰጣጥን እንደሚቆጣጠር፣ የሲም ካርድ ተመዝጋቢዎችን መረጃ እንደሚይዝ እና ከኦፕሬተሮች ወቅታዊ መረጃዎችን እንደሚቀበል በመመሪያዎቹ ተደንግጓል፡፡
[Wazema & Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema & Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
ዐቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ ዘጠኝ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አሰምቷል።
ዐቃቤ ህግ 15 የቅድመ ምርመራ ምስክሮች ማዘጋጀቱን የገለፀ ሲሆን፥ ከ15 ምስክሮች ውስጥ 4ቱ በተለያዩ ምክንያቶች እና የምስክር ጊዜ ላለማራዘም ማሰማት አልፈልግም ሲል ለችሎቱ ገልጿል።ዐቃቤ ህግ በ11ኛ እና 14ኛ ተራ ቁጥር ያስመዘገባቸው ቀሪ ሁለት ምስክሮች ስልካቸው ባለመስራቱ ለነሃሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ከመጋረጃ በስተጀርባ ምስክርነት ይሰማልኝ በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በልደታ አዳራሽ የተገኙት አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ የዐቃቤ ህግ ቀሪ ሁለት ምስክሮች ዛሬ ተሰምተዋል።
በዚህም ሂደትም ዐቃቤ ህግ የሚያሰማቸው እና የማያሰማቸው ቀሪ ምስክሮች ዝርዝር ይገለፅልን ሲሉ የተጠርጣሪ ጠበቆች ጠይቀዋል።ዐቃቤ ህግም ለደህንነታቸው ሲባል ዝርዝራቸውን አልገልፅም፤ ከዚህ በፊት ምስክር የነበሩ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ሽጉጥ ጉዳት ደርሶባቸው ፓሊስ ጣቢያ ማደራቸውን ጠቅሶ በተለያዩ ጊዜ ምስክሮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰ በመሆኑ ለደህንነታቸው ሲል ዝርዝራቸውን መግለፅ እንደማይፈልግ አብራርቷል።ተጠርጣሪዎችም የተለያዩ አቤቱታዎቻቸውን ለፍርድ ቤት አስመዝግበዋል።
አቶ በቀለ ገርባ የባንክ ሂሳባቸው መታገዱን እና የግል ተሽከርካሪያቸው እንዳልተመለሰላቸው አቤቱታ አቅርበዋል። እንዲሁም የማረሚያ ቤት አያያዛቸው እንዲስተካከል ጠይቀዋል።አቶ ሃምዛ አዳነ በአንድ መፅሄት እንዲሁም በሌሎች ጋዜጦች ስሜ እየጠፋ ነው ሲሉ አመልክተዋል።አቶ ሸምሰዲን ጠሃ የተባሉ ተጠርጣሪም የጆሮአቸውን ህመም በሚፈልጉት የህክምና ተቋም እንዲታከሙ ፍርድ ቤቱ ያዘዘው ትዕዛዝ አልተፈፀመም ሲሉ በድጋሜ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዋል።ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም በተነሱ አቤቱታዎች ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት እና ሁለት የዐቃቤ ህግ ከመጋረጃ ጀርባ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለነሃሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል
[FBC]

በአፋር ክልል በተከሰተው ጎርፍ የተከበቡ ሰዎችን ለማውጣት ጥረት እየተደረገ ነው!
በአፋር ክልል አሚበራ ወረዳ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ የተከሰተውን ጎርፍ ተከትሎ በውሃ የተከበቡ ሰዎችን ለማውጣት በሄሊኮፕተር የታገዘ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ቀደም ሲልም ተከስቶ በነበረው ጎርፍ የተጉዱ ወገኖችን ለመደገፍ ሲሰራ ቆይቷል።በጽህፈት ቤቱ የቅድመ-ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ አይዳሂስ ያሲን እንደገለጹት፤ በክልሉ መካከለኛው አዋሽ የቆቃ ግድብ ሞልቶ የተለቀቀ ውሃ በአሚበራ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ጎርፍ አስከትሏል።ጎርፉ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ባያደረስም በውሃ የተከበቡ ሰዎችን ለመታደግ በሄሊኮፕተርና ጀልባ በመታገዝ ከአካባቢው ለማውጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ጎርፉ በእንስሳትና እርሻ መሬት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷልም ብለዋል።በውሃ ለተከበቡና ለተፈናቀሉ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስና የጉዳቱን መጠን ለመለየት እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።የአሚበራ ወረዳ የአርብቶ አደርና ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀሰን ዲኒ እንዳሉት በወረዳው ከትናንት ማታ አራት ሰዓት ተኩል ጀምሮ በሰባት ቀበሌዎች ጎርፍ ተከስቷል።ጎርፉ ከባድ በመሆኑ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በውሃ የተከበቡ ነዋሪዎችን በማውጣት በሌላ አካባቢ ለማስፈር በሄሊኮፕተር የታገዘ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።ለተጎጂዎቹ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለማድረስ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ቀደም ሲል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የተጎዱ ወገኖች በመንግስትና በበጎ አድራጊዎች ድጋፍ ሲደረግ መቆየቱን ይታወቃል።

አቃቤ ህግ በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ክስ ሊመሰርት አልቻለምና በአስቸኳይ ከእስር ይፈቱ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አሳሰበ፡፡
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከተገደለው ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ወጣቶችን አስተባብረው ሁከትና ግጭት ሊፈጥሩ ነበር በሚል በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ይታወሳል፡፡እስከ አሁንም ለበርካታ ጊዜያት ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ክስ ግን አልተመሰረተባቸውም ነው ያለው፡፡ፍርድ ቤቱም ዐቃቤ ህግ በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ አለኝ የሚለውን ማስረጃና ምስክሮች አሰባስቦ ለባለፈው ማክሰኞ ክስ እንዲመሰረት ትዕዛዝ አስተላልፎ እንደበረ የተናገሩት የፓርቲው ተጠባባቂ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ ናቸው፡፡አቶ ገለታው ዐቃቤ ህግ የተሠጠውን የ15 ቀናት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አክብሮ ክስ ሊመሰርት አልቻለምና ከእስር ሊፈቱ ይገባል ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
[አሐዱ ሬዲዮ]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1105 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል!
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 21 ሺህ 360 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 105 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 54 ሺህ 409 ደርሷል።በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 416 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 19 ሺህ 903 ሆኗል።ካለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ የ18 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 846 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት 33 ሺህ 658 ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች በለይቶ ማቆያ ሕክምና ላይ ሲገኙ 303 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 949 ሺህ 813 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መመሪያ የኮሮና ቫይረስ እለታዊ ሪፓርት
ዛሬ በላብራቶሪ የተመረመሩ ብዛት :- 325
ዛሬ የተያዙ :- 4
ዛሬ ህይወታቸው ያለፈ :- 0
ዛሬ ከበሽታው ያገገሙ :- 8
____________________________
በአጠቃላይ የተመረመሩ :- 10,916
በበሽታው የተያዙ :- 1036
በአሁን ሰዕት ህክምና ላይ ያሉ :- 478
ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ያገገሙ :- 544
@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ በላብራቶሪ የተመረመሩ ብዛት :- 325
ዛሬ የተያዙ :- 4
ዛሬ ህይወታቸው ያለፈ :- 0
ዛሬ ከበሽታው ያገገሙ :- 8
____________________________
በአጠቃላይ የተመረመሩ :- 10,916
በበሽታው የተያዙ :- 1036
በአሁን ሰዕት ህክምና ላይ ያሉ :- 478
ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ያገገሙ :- 544
@Yenetube @Fikerassefa