የተማሪዎች ነፃ ዝውውር ውሳኔ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ ያለመ ነው:- ትምህርት ሚኒስቴር
በትምህርት ሚኒስቴር የ ተላላፈው ከ 8ኛና 12ኛ ክፍል ውጪ ያሉ ተማሪዋች ነፃ ዝውውር ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማበረታታት መሆኑ ተገለፀ ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂ ጌታሁን መኩሪያ ውሳኔው በኮሮና ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው የትምህርት መርሃ ግብር ሲጀመር ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማበረታታት እና ወረርሽኙ የፈጠረውን ጫና ለመቀነስ የታሰበ ነው ብለዋል።
በአሁን ሰዓት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ያለነው ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ላይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ በቀጣይም ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት ከተመለሱ በኋላ የትምህርት ጥራቱ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የትምህርት ጥራቱን በዘላቂነት ለመፍታትም በ 2014 ዓ.ም ወደ ተግባር የሚገባ አዲስ ስርዓተ ትምህርት እየተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል ።
በነፃ ዝውውር የተዘዋወሩ ተማሪዋች የትምህርት ምዕራፉ ሲጀመር በተዘዋወሩበት የትምህርት ክፍል ባለፈው የትምህርት ምዕራፍ ላይ ማካካሻ ወስደው ቀጣዪን የትምህርት መርሃ ግብር የሚቀጥሉ ይሆናል።
በኮሮና ወረርሽኝ ምክኒያት ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ከ 26 ሚሊየን በላይ ተማሪዋች ከ ትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው ።
የትምህርት ሚኒስቴር ከ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዋች ውጪ የነፃ ዝውውር ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው።
@Yenetube @FikerAssefa

ህንድ በኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር በአለም አራተኛ ሀገር ሆናለች
ይህም ሀገሪቱን ከአሜሪካ ብራዚል እና ሜኪስኮ ቀጥሎ አራተኛዋ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበባት ሀገር ያደርጋታል።
በሃገሪቱ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት 47 ሺ 033 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን የተጠቂዎች ቁጥርም 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ደርሷል፡፡
ጆንሆፕስኪንስ ዩኒቨርስቲ ባወጣው መረጃ መሰረት በህንድ በቀን ከ66 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ይያዛሉ።
አንዳንድ ባለሙያዎች ለቫይረሱ በስፋት መሰራጭት የሃገሪቱ የህዝብ ቁጥር ብዛት ከፍተኛ ሚና አለው ሲሉ ስጋታቸውን መግለጻቸውን #ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የኮሮና ቫይረስ ያደርሳል ተብሎ ከተተነበየው አስከፊ ጉዳት ታድጎናል" ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጻም መርማሪ ቦርድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለተቋቋመው የሚኒስትሮች ኮሚቴ የመስክ ምልከታ ግብረ መልስ አቅርቧል።
የቦርዱ አባላት በኦሮሚያ፣ አማራና የደቡብ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች በማቅናት ነው የመስክ ምልከታውን ያከናወኑት።
አባላቱ እንዳሉት በዝግጅት ምዕራፍ በተከናወኑ ተግባራት በተለይ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ አደረጃጃቶችን በአጭር ጊዜ በማቋቋም ረገድ ጠንካራ ስራ ተሰርቷል።
የምርመራ አቅምን በማሳደግ ረገድ የተከናወነውን ስራም በመልካም ጎኑ አንስተዋል።
በአዋጁ አፈጻጸም ወቅትም ምንም አይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለመከሰቱን ተናግረዋል።
በድንበሮች አካባቢ በቂ የቁጥጥር ስርዓት አለመኖሩንና በማህበረሰቡ ዘንድ መዘናጋቶች መኖራቸውን ደግሞ በድክመት ለይተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አዋጁ ቫይረሱ ሊያስከትል ከሚችለው ከፍተኛ ጉዳት ታድጎናል ነው ያሉት።
በማህበረሰብ አቀፍ የመከላከል፤ ምርመራና ንቅናቄ አማካኝነትም እስከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ድረስ በመውረድ ቫይረሱን የመከላከል ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በድንበሮች አካባቢ ያለውን የሰዎች እንቅስቃሴ ለመገደብም ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያን በቫይረሱ የከፋ ጉዳት ሳይደርስባት ወደ መጪው ዘመን ለማሸጋጋርም ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
Via:- ENA

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኮሮና ቫይረስ ካስመዘገቡ አስር የአፍሪካ ሀገራት አንዷ ሆነች
ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኮሮና ቫይረስ ካስመዘገቡ አስር የአፍሪካ ሀገራት አንዷ መሆኗን የአለም የጤና ድርጅት በየሳምንቱ የሚያወጣው የሁናቴ ሪፖርት (Situation Report) ሲሆን ሪፖርቱ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ስለሚገኘው የኮርና ቫይረስ ወረርሺኝ የተለያዩ መረጃዎችን ይዟል።
ከሪፖርቱ መረዳት እንደሚቻለው ከሆነ በአፍሪካ በወቅቱ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 905,782 ሲሆን ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 05 2012 ዓ.ም ብቻ 75,326 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ተገኝተዋል። ይህም ካለፈው ሳምንት ሪፖርት ጋር ሲነፃፃር የ12% ጭማሬ እንደሚያሳይ የአለም የጤና ድርጅት ቁጥሮች የሚያስረዱ ሲሆን 60% የሚሆኑት አዲስ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ከደቡብ አፍሪካ መገኘታቸውን መረጃው ጨምሮ ያስረዳል። ከላይ ከተጠቀሰው ቁጥር መካከል 89% ያህሉ ማለትም 802,414 ከአስር ሀገራት የተገኘ ሲሆን ከእነዚህ አገራት መካከል ሀገራችን ኢትዮጵያ አንዷ እንደሆነች መረጃው ይጠቁማል።
ከዚህ በተጨማሪ ጋምቢያ በአንድ ቀን ከፍተኛ የታማሚ ቁጥርን ለተጨማሪ ሳምንት ማስመዝገቧን ያስታወሰው ዘገባው ጋምቢያ ባለፉት ሶስት ሳምንታት እንዳሳየችው ከፍተኛ የህሙማን ቁጥር ጭማሬን አሳይታለች ብሏል። እንደአለም የጤና ድርጅት ከሆነ ጋምቢያ ከ799 የኮሮና ታማሚያን ወደ 1,477 ማደጉ የ85% ጭማሬን ያሳያል። ሌሎች በተጠቀሰው ወቅት ከፍተኛ የህሙማን ቁጥር ጭማሬን ያሳዩ ሀገራት ቦትስዋና፣ ናሚቢያ፣ አንጎላ፣ ሞዛምቢክ፣ ዛምቢያ እና ኢትዮጵያ እንደሆኑ ሪፖርቱ ይገልፃል።
ይህ እንዳለ ሆኖ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር በሳምንቱ የ17% ጭማሪ እንደታየ ያስረዳው ሪፖርቱ ደቡብ አፍሪካ ከተመዘገበው የሞት ቁጥር 76 በመቶ ያህሉን እንዳስመዘገበች አክሎ ገልጿል። ኢትዮጵያ በዚህ ዝርዝር 97 አዲስ የሞት ቁጥሮችን በማስመዝገብ በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ ያስገደዳት ሲሆን ሌሎች ከፍተኛ የሞት ቁጥርን ካስመዘገቡ አገራት መካከል አልጄርያ፣ ናይጄርያ፣ ዛምቢያ፣ ማዳጋስካር እና ጋና ይገኙበታል።
በመጨረሻም በአፍሪካ በወቅቱ ከተረጋገጡት 905,782 የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች መካከል 663,827 የሚሆኑት (73% መሆኑ ነው) ህክምናቸውን ተከታትለው ከበሽታው ማገገማቸውን የገለፀው መረጃ ይህ ቁጥር አበረታች ቢሆንም ከአፍሪካ አገራት የመመርመር አቅም እና ፖሊሲ አንፃር የአለም የጤና ድርጅት ቁጥሩ በጥንቃቄ መታየት አለበት ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ በቫይረሱ አማካኝነት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 17,154 ወይንም 1.9% መሆኑን መረጃው ያስረዳል።
Via:- Addis Zeyeb

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት በየመንና ሳውዲ አረብያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት ጥሰት እየደረሰባቸው ነው አለ
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት፣ ሂውማን ራይትስ ዋች (Human Rights Watch) እንደዘገበው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመንና በሳውዲ አረብያ ሰብዓዊነት የጎደለው ግድያና እስር እየገጠማቸው ይገኛል። ዘገባው ባሳለፍነው መጋቢት ወር የሰሜን የመን አካባቢዎችን የሚቆጣጠረው የሁቲ ታጣቂ ቡድን ብዙ ኢትዮጰያውያንን የኮሮና ቫይረስን እያስፋፉ ነው በማለት ባፈናቀለበት ወቅት ቁጥራቸው በቅሉ ያልታወቁ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን ያስቀመጠ ሲሆን ተፈናቃዮቹ በጠዋቱን ሸሽተው ወደ ሳውዲ አረብያ ባቀኑበት ወቅት ከፀጥታ አካላት በተከፈተ ተኩስ ተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መገደላቸውን አክሎ ገልጿል።
ከቆይታ በኋላ ቢሆንም የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን ወደ ሳውዲ አረብያ እንዲገቡ በወቅቱ ቢፈቀድላቸውም ስደተኞቹ የጤና ችግርን የመፍጠር አቅም ባላቸውና ንፅህና በጎደላቸው ማቆያ ማእከሎች እንደታሰሩ በተንቀሳቃሽ ምስል አስደግፎ ዘግቧል። ይህም ከኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝም ሆነ ከሰብዓዊ መብትና የስደተኞች ህግ አንፃር ተቀባይነት እንደሌለው ሂውማን ራይትስ ዋች አስረግጦ ተናግሯል።
በስደት በተለያዩ የአረብ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለይም በኮሮና ቫይረስ ወቅት እየደረሰባቸው ስለሚገኘው በደልና ስለሚገጥሟቸው አስከፊ ሁኔታዎች ይህን ዘገባ ጨምሮ የተለያዩ ዘገባዎች የወጡ ሲሆን ባሳለፍነው በቤሩት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ዙሪያ የቀረቡ መረጃዎችንና አለማቀፍ የእርዳታ ጥሪዎችን መጥቀስ ይቻላል።
Via:- Addis Zeyeb
@Yenetube @Fikerassefa

በሱዳን በተከሰተ የእርስ በእርስ ግጭት 32 ሰዎች ተገደሉ
በምስራቅ ሱዳን ሰሞኑን በተከሰተ የእርስ በእርስ ግጭት 32 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት የደህንነት ስራውን አጠናክሯል፡፡
ወትሮውንም ዘላቂ መግባባት በሌላቸው የቤን አሚር እና ኑባ ጎሳዎች መካከል በተከሰተው ግጭት ህይወታቸውን ካጡት 32 ሰዎች በተጨማሪ 98 ሰዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የሱዳን የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው መንግስት ችግሩ በተፈጠረበት የቀይ ባህር ግዛት የሚያከናውነውን የጸጥታ ስራ ያጠናከረ ሲሆን በፖርት ሱዳን ደግሞ ሰዓት እላፊ ታውጇል፡፡
ከግጭቱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 85 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይ ግጭቱ ጎልቶ በተከሰተበት ፖርት ሱዳን የመንግስት ጦር ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
ከአመት በፊት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አል-ባሽር ከስልጣን ከተወገዱ ወዲህ መረጋጋት የተሳናት ሱዳን በተለያዩ ግዛቶቿ በተለያየ ጊዜ የሚከሰቱ ግጭቶች እና የኢኮኖሚ ቀውስ ፈተና ሆነውባታል፡፡
Via:- አል አየን

ዩኤኢ እና እስራኤል ታሪካዊ ከተባለ ስምምነት ደረሱ
ዩኤኢ እና እስራኤል ታሪካዊ ካሉት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ፡፡
ስምምነቱ እስራኤል የፍልስጤም ግዛቶችን ወደ ራሷ ለማካተት የጀመረችውን ጥረት እንድታቋርጥ ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡
Via:- አል አየን
@YeneTube @FikerAssefa

ከወላይታ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩ አመራሮች በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ
የወላይታ ዞን ምክር ቤት ሴክሬታሪያት አቶ አምሳሉ መሰሜ፤ ከወላይታው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩ አመራሮች እያንዳንዳቸው በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ
መወሰኑን ለቢቢሲ ገለፁ።
በወላይታ ተፈጥሮ ከነበረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 20 አመራሮች ናቸው በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ የተወሰነው።
ከታሰሩት መካከል ሁለቱ ትላንት በዋስ እንዲወጡ የተወሰነ ሲሆን፤ የተቀሩት 20 ሰዎች ደግሞ ዛሬ በዋስ እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። በወላይታ በተከሰተው አለመረጋጋት ከ16 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያሳያል።
Via:- BBC

በጀዋር ሞሐመድ ቤት ተገኘ የተባለው ሕገወጥ የሳተላይት መቀበያ መሳሪያ ከጉምሩክ ደንብ ውጭ ወደ ሀገር እንደገባ ዐቃቤ ሕግ መናገሩን የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡
መሳሪያው ከኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ውጭ፣ ከ5 እስከ 25 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በተጠርጣሪው እጅ የተገኙ 9 ሬዲዮ መገናኛዎችም የኢትዮ ቴሌኮም ወይም የሌሎች መንግሥታዊ አካላት ፍቃድ እንደሌላቸው ገልጧል፡፡
Via:- Wazema
@YeneTube @Fikerassefa
መሳሪያው ከኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ውጭ፣ ከ5 እስከ 25 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በተጠርጣሪው እጅ የተገኙ 9 ሬዲዮ መገናኛዎችም የኢትዮ ቴሌኮም ወይም የሌሎች መንግሥታዊ አካላት ፍቃድ እንደሌላቸው ገልጧል፡፡
Via:- Wazema
@YeneTube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1086 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ16 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 14,6880 የላብራቶሪ ምርመራ 1086 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪም 394 ሰዎች አገግመዋል።በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 26,204 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 420 ደርሷል፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 11,428 ደርሰዋል።
@YeneTube @FikerAssefa1

በምዕራብ ሸዋ ዞን በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ 500 አባወራዎች ተፈናቀሉ
በምዕራብ ሸዋ ዞን በአዋሽ ወንዝ ሞልቶ የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶችና አካባቢ በማጥለቅለቁ የተነሳ 500 አባዎራዎች መፈናቀላቸውን የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ድሪብሳ ዋቁማ ለቢቢሲ ገለፁ።
አስተዳዳሪው አክለውም የጎርፍ አደጋው ከደረሰበት ሰዓት አንስቶ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ከፍተኛ ርብርብ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልፀው "በዚህም ተሳክቶልናል" ብለዋል።
ጀልባዎችን ከተለያዩ ስፍራዎች በማስመጣት የሰዎችን ህይወት መታደግና ንብረታቸው ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ እየሰሩ እንደሆነም ጨምረው አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የሠላም ኖቤል ተሸላሚው ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታራቂና የሚያቀራርቡ ንግግሮቻቸውን ወደ ተግባር እንዲለውጧቸው ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ጠየቀ።
ቡድኑ በተጨማሪም ያለውን ውጥረት ለማርገብ አስፈላጊ ከሆነም የአፍሪካ ሕብረት ወይም የአፍሪካ መሪዎች በማሸማገሉ በኩል ተሳትፎ ሊያደርጉ ይችላሉ ከማለት በተጨማሪ በተለይ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ ብሏል።
ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️
https://telegra.ph/PPtplf-08-14

በኢትዮጵያ እና በጎረቤት ሀገሮች የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ -19) ወቅታዊ ሁኔታ
#ኢትዮጵያ
በበሽታው የተያዙ - 26,204
ህይወታቸው ያለፈ - 479
#ሱዳን
በበሽታው የተያዙ - 12,115
ህይወታቸው ያለፈ - 792
#ደቡብ ሱዳን
በበሽታው የተያዙ - 2,478
ህይወታቸው ያለፈ - 47
ኤርትራ
በበሽታው የተያዙ - 285
ህይወታቸው ያለፈ - 0
#ሶማሊያ
በበሽታው የተያዙ - 3,227
ህይወታቸው ያለፈ - 93
#ኬንያ
በበሽታው የተያዙ - 28,753
ህይወታቸው ያለፈ - 460
@Yenetube @Fikerassefa
#ኢትዮጵያ
በበሽታው የተያዙ - 26,204
ህይወታቸው ያለፈ - 479
#ሱዳን
በበሽታው የተያዙ - 12,115
ህይወታቸው ያለፈ - 792
#ደቡብ ሱዳን
በበሽታው የተያዙ - 2,478
ህይወታቸው ያለፈ - 47
ኤርትራ
በበሽታው የተያዙ - 285
ህይወታቸው ያለፈ - 0
#ሶማሊያ
በበሽታው የተያዙ - 3,227
ህይወታቸው ያለፈ - 93
#ኬንያ
በበሽታው የተያዙ - 28,753
ህይወታቸው ያለፈ - 460
@Yenetube @Fikerassefa
መንግስት ለጤና ባለሙያዎች ደህንነት ትኩረት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አሳሰበ።
የሰውን ህይወት ለመታደግ እየሰሩ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎችን፣ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር እና የኢትዮጵያ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ጠይቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት ፣ዶ/ር ተግባር ይግዛው በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በዕየለቱ ሲነገር ፣ በህክምና ሙያ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ ሲጠቁ መረጃው ይፋ እንደማይደረግ ተናግረዋል።
ግዳጃ ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን በተመለከተ በለይቶ ማቆያ ምን ያህለ እንዳሉ ፣ ምን ያህሉ ደግሞ በጽኑ የታመመ ዶክተሮች ፣ ነርሶች ፣ የፋርማሲ ባለሙያ እና በጤና ተቋም የሚሰሩ ሌሎች ባለሙያዎች ያለበት የጤና ሁኔታ የሚገልጽ ወቅታዊ መረጃ የለም፡፡
ታዲያ መንግስት የሰው ህይወት ለመታደግ የህክምና ባለሙያዎች ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባውም ዶክተር ተግባር ጠይቀዋል፡፡
ወቅታዊ መረጃ ባይሆንም ከዚህ በፊት በሀገራችን በየዕለቱ ከሚወጡት የኮሮና ተያዥ ቁጥር ውስጥ 5 በመቶ የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች ነበሩ ብለዋል ዶ/ር ተግባር ፡፡
የኢትዮጵያ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዶክተር ማርቆስ ፈለቀ በበኩላቸው የጤና ባለሙያዎችና በጤና ተቋመት የሚሰሩ ሌሎች ባለሙያዎች፣ ምንም ያህል ጥንቃቄ ቢያደርጉ ተጋልጭ ናቸው፤ በመሆኑም ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ማርቆስ አሁን ያለው መዘናጋት በተመከተ አላስፈላጊ ዋጋ እንዳያስከፍለን የቅድመ መከለከል ስራው መረሳት የለበትም ሲሉም አሳስበዋል፡፡
በኮሮና ቫይረስ የተያዙ እና በጽኑ የታመሙ ሀኪሞች እንዲሁም በጤና ተቋማት የሚሰሩ ሌሎች ባለሙያዎች፣ ምን ያህል እንደሆኑ ወቅታዊ እና አሁናዊ መረጃ ከጤና ሚኒስቴር ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም፡፡
Via:- Ethio FM

የትግራይ ክልል ለ1 ሺህ 568 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል 1 ሺህ 568 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
ታራሚዎቹ በይቅርታ እንዲፈቱ የተወሰነው በክልሉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል መሆኑን የቢሮው ሃላፊ ተኪኡ ምትኩ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎቹ መካከል 38ቱ ሴቶቸ መሆናቸውንም የቢሮው ሃላፊ ገልፀዋል።
ሃላፊው ታራሚዎቹ ይቅርታ እንዲደረግላቸው ለኮማንድ ፖስቱ ከቀረቡት 1 ሺህ 704 ታራሚዎች ውስጥ 1 ሺህ 568 የሚሆኑት በይቅርታ እንዲወጡ ተወስኗል ብለዋል።
ቀሪዎቹ 136 ታራሚዎች ደግሞ ከግድያ፣ አስገድዶ መድፈር እና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ የወንጀል ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ በይቅርታ ውሳኔው እንዳልተካተቱ ጠቁመዋል።
ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ የኮሮና ቫይረስን በመከላከል እና ለበደሉት ማህበረሰብ ዘላቂ ሰላም አጋዥ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል።
ኮማንድ ፖስቱ በዚህ ዓመት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በመጋቢት እና ሚያዝያ ወር በተመሳሳይ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲወጡ መወሰኑ ይታወሳል።

በአዲስ አበባ እስካሁን ከ17 ሺህ በላይ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በአዲስ አበባ እስካሁን ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ላይ የኮሮና ቫይረስን ለመለየት ናሙና መወሰዱን ጤና ቢሮው አስታውቋል።
ቢሮው ናሙና ከሰጡት 300 ሺህ 547 ነዋሪዎች ውስጥ ከ17 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ገልጿል።
ባለፉት 24 ሰዓታትም ለ4 ሺህ 773 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ601 ሰዎች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘባቸውም ነው የገለጸው።
ጤና ቢሮው እስካሁን ቫይረሱ በክፍለ ከተማ ደረጃ ያለበትን ሁኔታም በቅደም ተከተል ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሠረት ቫይረሱ ቦሌ ክፍለ ከተማ 2 ሺህ 551፣ ጉለሌ 2 ሺህ 145፣ አዲስ ከተማ 1 ሺህ 878፣ አራዳ 1 ሺህ 736፣ የካ 1 ሺህ 684፣ ኮልፌ ቀራኒዮ 1 ሺህ 563፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ 1 ሺህ 421፣ ቂርቆስ 1 ሺህ 409፣ ልደታ 1 ሺህ 369 እንዲሁም አቃቂ 988 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል።
በተጨማሪም አስገድዶ ማቆያ ውስጥ ያሉ 320 እና አድራሻቸው ያልታወቁ 271 ሰዎች ላይም ቫይረሱ መገኘቱን ያስታወቀው ጤና ቢሮው፤ በአዲስ አበባ እስካሁን ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 17 ሺህ 335 መድረሱንም አመላክቷል።
ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ከአዲስ አበባ ብቻ 14 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉንም ቢሮው ማስታወቁን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
Via:- FBC

በእነ አቶ እስክንድር ነጋ ላይ የዐቃቤ ሕግ የቀዳሚ ምርመራ ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ለነሐሴ 12 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ
ፍርድ ቤቱ በወንጀል ጉዳይ በተጠረጠሩት እነ አቶ እስክንድር ነጋ ላይ የዐቃቤ ሕግ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ያቀረባቸውን ቀሪ ምስክሮች ለመስማት ለነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ቁጥር 215730 የቀረቡት አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልና ወይዘሮ ቀለብ ስዩም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የአራዳ ተረኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
በተጠርጣሪዎቹ ላይ ዐቃቤ ሕግ የቀዳሚ ምርመራ አራት ምስክሮችን አቅርቦ ምስክርነታቸውን አሰምቷል።
ተጠርጣሪዎች ከዚህ ቀደም ነሐሴ 6 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ‘በክርክር ሂደቱ አንሳተፍም’ በማለት ተከላካይ ጠበቆቻቸውን በማሰናበታቸው ፍርድ ቤቱ መንግስት ተከላካይ ጠበቃ በፍርድ ቤቱ እንዲመደብላቸው በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተከላካይ ጠበቃ ቀርበው ነበር።
Via:- EPA

የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በግንባሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በጊዜያዊነት ከኃላፊነታቸው መታገዳቸውን የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ተናገሩ።
@Yenetube @FikerAssefa
@Yenetube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1038 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ13 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 17,323 የላብራቶሪ ምርመራ 1038 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል።በተጨማሪም 232 ሰዎች አገግመዋል።በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 27,242 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 492 ደርሷል፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 11,660ደርሰዋል።