በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጄሬ ወረዳ ዲቡ አርሶ አደር ቀበሌ የአዋሽ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በመፍሰሱ 526 አባወራዎችን ለችግር አጋልጧል፡፡የጎርፍ አደጋው ለጊዜው ግምቱ የማይታወቅ ንብረትን አውድሟል፡፡ጎርፉ በቀበሌው ከለሊቱ 6 ሰዓት የተከሰተ በመሆኑ ተጎጂ አባወራዎች ከነቤተሰባቸው መውጫ መንገድ አጥተዋል፡፡የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዲሪርሳ ዋቁማ ተጎጂ አካላትን የማውጣት ስራ እየተከናወ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሆኖም ግን ያለው ጀልባ ትንሽ በመሆኑ ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ተገልጧል፡፡ለዜጎቹ መጠለያ እና ምግብ እንዲሁም የከብቶች መኖ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የዞኑ አስተዳደር ገልጿል።
#OBN
@YeneTube @FikerAssefa1
#OBN
@YeneTube @FikerAssefa1