ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 195 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(90) ሴት(105) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ1-85 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 85 ሰዎች(73 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከኦሮሚያ፣ 5 ከአማራ እና 2 ከትግራይ ክልሎች) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 934 ነው።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(144)፣ ከኦሮሚያ ክልል(4)፣ከአማራ ክልል(12) ፣ ከትግራይ ክልል(12)፣ከጋምቤላ ክልል(3)፣ ከድሬዳዋ(7)፣ ከሶማሌ ክልል(4)፣ ከሀረሪ ክልል(2) እና ከአፋር ክልል(7) በድምር 195 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3954 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 27 ነው።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 2 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 65 ነው።
@YeneTube @FikerAssefa

ዋልታ ቴሌቪዥን የፍርድ ቤቶች ጣልቃ ገብነት የምርመራ ዘገባዎችን ለመስራት እንቅፋት ሆኖብኛል አለ።
የፍርድ ቤቶች ጣልቃ ገብነት የምርመራ ዘገባዎችን ለመስራት እንቅፋት እንደሆነበት ዋልታ ቴሌቪዥን ገለጸ፡፡የዋልታ ቴሌቪዥን "ዋልታ ምርመራ" በተሰኘ ፕሮግራሙ በሰብዓዊ መብት፣ መልካም አስተዳደርና በሙስና ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የምርመራ ዘገባዎችን ያቀርባል።ይሁን እንጂ ተቋሙ በሚሰራቸው የምርመራ ዘገባዎች ላይ እጃቸው የረዘመ ፈርጣማ ክንዶችና የፍርድ ቤቶች ጣልቃ ገብነት ፈተና እንደሆነበት ይገልጻል።የተቋሙ የምርመራ ዘገባ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ብርሃኑ ወልደሰማያትና ጋዜጠኛ ጀማል መሀመድ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የምርመራ ዘገባዎችን መስራት የማይታሰብ ሆኗል።የምርምራ ዘገባዎች ሲሰሩ በአንድ በኩል ከማስረጃዎቹ ጀርባ የተደበቁ በጉልበት፣ በገንዘብ ወይም በስልጣን የፈረጠሙ ክንዶች አደጋ እየፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ዋልታ ቴሌቪዥን መረጃዎችን ከሁሉምክ አቅጣጫ አጣርቶ የህዝብ ቅሬታዎችን እየሰራ ቢሆንም በአቋራጭ በፍርድ ቤት በኩል በሚመጣ እገዳ ዘገባዎች እንዳይተላለፉ እየተደረገ ነው ብለዋልም፡፡በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተደረገውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአፋር ክልል በአፍዴራ ጨው ላይ የሚደረገውን ምዝበራ በተመለከተ የተዘጋጁ የምርመራ ዘገባዎች ለህዝብ ሳይደርሱ በፍርድ ቤት እገዳ ተጥሎባቸው ለህዝብ ጆሮ ሳይደርሱ መቆየታቸውን ጋዜጠኞቹ አንስተዋል፡፡በተመሳሳይ ሰሞኑን በሶደሬ ሪዞርት ዙሪያ የቀረበውን ቅሬታና ሌሎች ተያያዥ ዘገባዎች በፍርድ ቤት እግድድ ከተጣለባቸው ናቸውም ነው ያሉት።ፍርድ ቤቶች ለቆሙለት አላማ ለእውነትና ለፍትህ መስራት ሲገባቸው በተቃራኒው መቆማቸው ትክክል አለመሆኑንም ጋዜጠኞቹ ገልጸዋል።የምርምራ ዘገባዎችን ከሁሉም ወገን ለማጣራት ጥረት እንደሚደረግ ገልጸው በዘገባው ላይ ስህተት ከተፈጠረ ስህተቱ በዝርዝር ቀርቦ በማስረጃ በህግ መጠየቅ ይገባው ነበርም ሲሉ አስረድተዋል።የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በተሰጠው ስልጣን መሰረት እየደረሰብን ያለውን በደል ሊያይልን ይገባል በማለትም ጋዜጠኞቹ ጠይቀዋል።
የባለስልጣኑን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁን በአካል አግኝተን በጉዳዩ ላይ መረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቃቸውም "ጉዳዩ ከብሮድካስት ስልጣን ውጭ በመሆኑ ምላሽ መስጠት አልችልም" ብለውናል።ጠበቃና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ጋዜጠኛው በቦታው ተገኝቶ በማስረጃ የሚያቀርባቸው ዘገባዎች የአስፈፃሚው አካል አጋዥ ናቸው ብለዋል።በመሆኑም የመገናኛ ብዙሃን የሚሰሯቸውን ዘገባዎች ለህዝብ ከመድረሳቸው በፊት እንዳይተላለፉ ማድረግ በህግም ተቀባይነት የለውም ብለዋል።ፍርድ ቤቶች የእግድ ትዕዛዝ ለማስተላለፍ ከሳሽና ተከሳሽ ቀርበው ማስረጃዎችን ከተመለከተ በኋላ መሆን እንዳለበትም ገልጸዋል።ተቋማት ወይም ግለሰቦች ትዕዛዝ የሚተላለፍባቸው ቢያንስ ሶስት ጊዜ መጥሪያ ከቀረበባቸው በኋላ መሆኑንም ጠቁመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ሰበር ዜና!
ነባሩ የደቡብ ክልል እና አዲሱ የሲዳማ ክልል የስልጣን ርክክብ አካሄዱ!
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ነባሩ የደቡብ ክልል እና አዲሱ የሲዳማ ክልል በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው የስልጣን ርክክብ አካሂደዋል፡፡የስልጣን ርክክቡ ከመካሄዱ በፊት በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በአዳዲስ መዋቅሮች ለመደራጀት የቀረበ ጥያቄ ምላሽና የውሳኔ ሀሳብ የያዘ ሰነድ ለምክርቤቱ ቀርቧል፡፡በቀረበው ሰነድ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እርስቱ ይርዳ ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡የሲዳማ ክልል እራሱን ችሎ በመውጣቱ በሌሎች ህዝቦች ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ እንደማይኖር ተናግረዋል፡፡የህዝቦች አብሮነት ከዚህ ቀደምም ለረጅም አመታት ተጠናክሮ የቀጠለ ነው ያሉት አቶ እርስቱ ነባሩ ክልል እና አዲሱ ክልል በመደገፍ ለጋራ እድገት እንሰራለን ብለዋል፡፡የምክር ቤቱ አባላት ለሲዳማ ክልል ህዝብ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡
Via SNNPR Communication

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 144 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማዋ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2887 ደርሷል፡፡በአዲስ አበባ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በህክምና ማዕከል ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ ሁለት (2) ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የከተማዋ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት ሰባ ሶስት (73) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 18
👉ቦሌ 11
👉ጉለሌ 13
👉ልደታ 10
👉ኮልፌ ቀራንዮ 5
👉ቂርቆስ 7
👉አራዳ 10
👉የካ 9
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 7
👉አቃቂ ቃሊቲ 54
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፤-
👉አዲስ ከተማ 18
👉ቦሌ 11
👉ጉለሌ 13
👉ልደታ 10
👉ኮልፌ ቀራንዮ 5
👉ቂርቆስ 7
👉አራዳ 10
👉የካ 9
👉ንፋስ ስልክ ላፍቶ 7
👉አቃቂ ቃሊቲ 54
#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል በተነሱ የአደረጃጀት ጥያቄዎች ላይ የተዘጋጀ የውሳኔ ሃሳብ ዛሬ ለክልሉ ምክር ቤት እንደቀረበ ኢትዮጵያን ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡ ምክር ቤቱ በሰነዱ ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ ሰነዱ የአደረጃጀት ጥቄዎች መነሻዎችን፣ ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት የተጠኑ ጥናቶችን፣ የወደፊት አቅጣጫዎችን እና በፌደሬሽን ምክር ቤት የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችን የያዘ ነው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የፀሐይ ግርዶሹን ያለመመልከቻ መነጽር መመልከት የዐይን ብርሐንን ሊያሳጣ እንደሚችል ኢንስቲትዩቱ አስጠነቀቀ፡፡
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ኢንስቲዩት እና የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡የፊታችን እሁድ ሰኔ 14/2012 ዓ.ም በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ ከ60 እስከ 80 በመቶ ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ ይታያል፡፡ከ80 በመቶ በላይ ያለው ዋናውን ግርዶሽ ግን ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ ቦታዎች ጎልቶ እንደሚታይ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖልጅ ኢኒስቲዩት አስታውቋል፡፡
በመግለጫው እንደተመላከተው ክስተቱ ከወለጋ አካባቢ ጀምሮ ከፊል ጎጃም እና ከፊል ጎንደርን አልፎ ከዚያም ላል ይበላን አቋርጦ ይሄዳል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ፀሐይ እስክ 99 በመቶ ተሸፍና ቀለበታዊውን ግርዶሽ ማየት እንደሚቻልም ነው የተገለጸው፡፡ቀለበታዊ ግርዶሽ ማየት ከሚችሉ አነስተኛ ከተሞች (ቦታዎች) መካከል ቡሬ፣ አገው ግምጃ ቤት፣ እንጅባራ፣ ግሽ አባይ፣ ሞጣ፣ ዳሞት፣ ጋይንት፣ ነፋስ መውጫ፣ ጋሸና፣ ሙጃ፣ ዋጃ፣ ቆቦ፣ ኮረም፣ አላማጣ፣ ጊራራ እና ላሊበላ ይገኙበታል፡፡በአዲስ አበባ፣ ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ መቀሌ፣ ደሴ፣ አዳማ፣ ቤጊ፣ ሜቲ፣ መንዲ፣ ጫልቱ፣ በመሳሰሉት ከተሞች ደግሞ ቀለበታዊ ግረዶሽ ባይኖርም ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ግን እንደሚኖራቸው በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
ግርዶሽ ሲፈጠር ክፍተኛ ሃይል ከፀሐይ ሊረጭ ስለሚችል በባዶ ዐይን ማየት ለችግር እንደሚጋልጥ ያመላከተው መግለጫው ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ በማድረግና መነጽር በመጠቀም የታሪኩ አካል መሆን እንዳለበትም አስታውቋል፡፡ወቅቱ የኮሮና ባይሆን ኖሮ ክስተቱን ለመመልከት ከ20 ሺህ በላይ ጎብኝዎች ተመዝግበው እንደነበር በማመላከትም ይህ ደግሞ በዓለማችን ላይ ውድ ቱሪዝም የሆነው የስፔስ ቱሪዝም አካል ያደርገን እንደነበር ነው ተገለጸው፡፡ከዚህም ሌላ ኢትዮጵያ በስፔስ ሳይንስ ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ለዓለም የበለጠ ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል እንደነበር ነው የተገለጸው፡፡የግርዶሽ መመልከቻ መነጽር ማግኘት የማይችሉት መስታዎትን ትቁር ጥላሸት በመቀባት የቤት ውስጥ መስኮትና ቀዳዳዎችን በደንብ መሸፈን በሚችል ጥራዝ ሸፍነው ማየት እንዳለባቸውም ተቋማቱ አስጠንቅቀዋል፡፡
ምንጭ:አብመድ

ሰሶስት ሺህ አዳዲስ የከተማ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን ወደ ስራ ለማስገባት በግዢ ሂደት ላይ መሆኑን የሸገር ብዙሃን የትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ያለውን የትራንስፖርት ተጠቃሚ ፍላጎትን የሚመጥን አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል የከተማ አስተዳደሩ እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል። የትራንስፖርት አቅርቦቱ ከፍላጎቱ ጋር የተጣጣመ ባለመሆኑ በተለይም በስራና በተማሪዎች መግቢያና መውጫ ሰዓት ከፍተኛ መጨናነቅ እንደሚፈጠር ይታወቃል።ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ከሚሰጡት መካከል አንዱ የሆነው ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት 325 መደበኛ የህዝብ ማመላለሻና 100 የተማሪዎች ማመላለሻ በድምሩ 425 አውቶቡሶችን በማሰማራት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ምንጭ: ኢፕድ

በአማራ ክልል ኦሮሞ ልዩ ዞን እና በአፋር ክልል አዋሳኝ ቀበሌዎች ባለፉት 5 ቀናት ባገረሸ ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። በኦሮሞ ልዩ ዞን ባቲ ወረዳ በምትገኘው የጫጫቱ ቀበሌ መኖሪያ ጎጆዎች ተቃጥለዋል።
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
የፀሐይ ግርዶሽ እና ዓይናችን
(ዶ/ር ጸደቀ አሳምነው ፤ የዓይን ሐኪም፣ የቪትሮ-ሬቲና ድህረ-ስፔሻሊስት)
በሰኔ 14, 2012 ዓ.ም የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ እንደሚታይ ከመዘገቡ ጋር ተያይዞ የፀሐይ ግርዶሹን ለማየት ሲባል ቀጥታ ወደ ፀሐይ ማየት ስለሚያስከትለው ጕዳትና እንዴት መከላከል እንደሚቻል ማብራሪያ ለመስጠት እሞክራለሁ።
በፀሐይ ጨረር የሚመጣ የሬቲና (የብርሃን መቀበያ) ጉዳት በእንግሊዝኛ, solarretinopathy, photic retinopathy, foveomacular retinitis, solar retinitis, and eclipse retinopathy ይባላል።
ይኽ ጉዳት የሚከሰተው በቀጥታ ፀሐይን ወይም የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ሲሞከር የሚከሰት ችግር ሲሆን የብርሃን መቀበያችን (ሬቲና) ላይ ጉዳት በማድረስ ዕይታችንን ይቀንሳል፡፡ ጨረሩን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ያዩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
በዚህ ምክኒያት የሚከሰተው ጉዳት ለመዳን ከ3-6 ወር ሊፈጅ ይችላል። እንደዛም ሆኖ ግን ወደ ቀድሞው የዕይታ አቅም ሳይመለስ ዘለቄታዊ የዕይታ መቀነስ ሊያስከትል ይችላል። የዚህ ችግር ዋና መንስዔ ከፀሐይ የሚወጣው ጨረር ቢሆንም በብረት ብየዳ ጊዜ ከሚወጣ ጨረር ፣ ከትክክለኛው ኃይል በላይ የሚለቀቁ ሌሎች የብርሃንና የሌዘር ምንጮችም ሊከሰት ይችላል። ጨረሩን (በተለይ ልዕለ ሐምራዊ-ለ Ultraviolet-B ) በቀጥታ የብርሃን መቀበያና መጋቢ ህዋሳት ላይ ኬማካዊ ለውጥ በመፍጠር ጉዳት ያስከትላል።
❓አጋላጭ ሁኔታዎች፡-
.
- ህጻናትና ወጣቶች የተፈጥሮ ሌንሳቸው ሞራ ያልጀመረው ስለሚሆን በቀጥታ ፀሐይን ሲያዩ ሊጐዱ ይችላሉ፡፡
- ባንጻራዊነት እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ሞራ ስለሚጀምር ወደ ዓይን የሚገባው ጨረር ይቀንሳል፡፡
.
- ሆኖም የሞራ ቀዶ ጥገና አድርገው አርቲፊሻል ሌንስ የገባላቸው ሰዎች ወደ ፀሐይ ቀጥታ ማየት የለባቸውም፡፡
- የአዕምሮ ህመም ወይም ውስንነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ወደፀሐይ ቀጥታ ሊያዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄና እርዳታ ያሻቸዋል፡፡
.
- ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- ነጮች ከጥቁሮች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- በብየዳ ጊዜ ተገቢውን መነጽርና የፊት ጋሻ አለመጠቀም ለተመሳሳይ ጉዳት ይደርጋል።
.
❓ምልክቶቹ፦
.
በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ለጨረሩ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ጊዜ በሁለቱም ዓይን ላይ፦
- የዕይታ መቀነስ
- በዕይታ አድማስ ውስጥ የሚታይ ጥላ
- የዕይታ ቅርጽ መዛባት (የሚያዩት ነገር የተጣመመ ፣ በመጠን ያነሰ ወይም የተለቀ መምሰል)
- በተጨማሪም በግንባርና በጭንቅላት ጐን አካባቢ ራስ ምታት ሊከሰት ይችላል፡፡
ይህን ችግር መከሰቱን ለማወቅ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በማይክሮስኮፕ በማየት ወይም ሬቲናውን ፎቶ በማንሳት ወይም OCT በሚባል መሳሪያ በማየት ችግሩ መከሰቱን ማረጋገጥ ይቻላል።
❓ህክምናው፦
ምንም እንኳን ይህን ችግር ለማከም የተለያዩ መድኃኒቶች (ስቴሮይድን ጨምሮ) ቢሞክሩም አጥጋቢ ውጤት አላመጡም፡፡ ስለዚህ ዋነኛው ነገር ችግሩ እንዳይከሰት አስቀድሞ መከላከል ነው።
❓መከላከያ መንገዶች፦
⛔ ፀሐይን ፣ ፀሐይ ግርዶሽን ፣ የብየዳ ጨረርና ሌሎች ኃይለኛ ብርሃን የሚረጩ ነገሮችን በቀጥታ አለማየት ፣
በፀሐይ ግርዶሽ በዓመታት አንዴ የሚታይ በመሆኑና ብርሃኑም የቀነሰ ስለሚመስለን ለማየት ሊያጓጓን ይችላል... ሆኖም በፍጹም በቀጥታ ማየት የለብንም።
⚠️ ህጻናት፣ የአዕምሮ ህመምና ውስንነት ያለባቸውን ሰዎች ወደ ፀሐይ እንዳያዩ መከላከል ፣ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ መርዳት
✅ የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ዓላማ የተሰሩ ISO እና CE ሰርቲፊኬት ያላቸው ልዕለሐምራዊ (UV) ንዑሰ - ቀይ (Infrared) ጨረሮችን 99 - 1ዐዐ% የሚከላከሉ ጥቁረታቸው (shade no 12) የሆኑ መነጽሮችን ብቻ መጠቀም ይቻላል። ሆኖም እንደነዚህ ዓይነት መነጽሮች በሀገራችን ስለመግባታቸው እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ቱሪስቶች ወደ እኛ ሀገር ሲመጡ ይዘው ይመጡ ይሆናል፡፡
❓የተለመዱትን የፀሐይ መነጽሮች ማድረግ ይቻላል ?
❌ በፍጹም! ምንም እንኳን የፀሐይ መነጽሮች ጐጂ ጨረሮችን መቀነስ ቢችሉም በቀጥታ ወደ ፀሐይ ለማየት ተብሎ ስላልተሰሩ ተጨማሪ ጨረሮችን ወደ ዓይን ያስተላልፋሉና በፍጹም እነዚህን መነጽሮች ተማምነው ወደ ፀሐይ/ ፀሐይ ግርዶሽ ማየት የለብዎትም፡፡ ጥቁር መነጽር መሆኑ ብቻ ጨረሮቹን ይከላከላል ማለት አይደለም። ጥላሸት የተቀባ መነጽር፣ የራጅ ፊልም፣ የተለመደ የፀሐይ መነጽር፣ ካሜራዎች ወዘተ የሚታዩ የብርሃን ጨረሮችን ቢቀንሱም አደገኛ የሆኑትን ልዕለሐምራዊና ንዑስቀይ ጨረሮችን መከላከል አቅም ስለሌላቸው በነሱ መተማመን አይገባም፡፡መንግስት ይኽን አጋጣሚ ተጠቅመው ጥራታቸው ያልተረጋገጠ መነጽሮች እንዳይሸጡ ቁጥጥር ማድረግ ይገባዋል።
Via St Paul Millennium Hospital

የሲሚንቶ ዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት ተገኝቶባቸዋል!
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም (ንኢሚ) በገበያ ላይ የተከሰተውን የሲሚንቶ እጥረት እና የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች በሲሚንቶ ምርትና ግብይት ሂደቱ ላይ ውጤት ማሳየቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንዳሉት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በአቅርቦት ችግር ምክንያት በሙሉ አቅማቸው ባለማምረታቸው እና ነጋዴ ያልሆኑ አካላት በነጋዴ ስም በህገ-ወጥ መንገድ ምርቱን በመያዛቸው የሲሚንቶ ምርት እጥረትና ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተከስቷል፡፡የአቅርቦት ችግሩን ለመቅረፍ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከውጪ የሚያስመጡትን ጥሬ እቃ ከሀገር ውስጥ እንዲጠቀሙ በመደረጉ 20 በመቶ ብቻ ከሀገር ውስጥ ይጠቀሙት የነበረውን የድንጋይ ከሰል አሁን ከ60-100% ከሀገር ውስጥ ተጠቅመው እያመረቱ ይገኛሉ፡፡ፋብሪካዎች የሀገር ውስጥ ግብዓቶችን መጠቀማቸው የማምረት አቅማቸውን ከመጨመሩም በዘለለ ሀገራችን ያለባትን የውጪ ምንዛሪ እጥረት ለማቃለልና የማምረቻ ዋጋቸውን በመቀነስ ሲሚንቶን ተወዳዳሪ በሆነ ዋጋ እንዲያቀርቡም ያስችላል፡፡
በተጨማሪም በሲሚንቶ ግብይት ውስጥ ያሉትን ህገ-ወጦች ከገበያው ስርዓት ውስጥ ለማሶጣት በቅርቡ በተዘረጋው አሰራር ህጉን ለማክበር ፈቃደኛ የሆኑ ነጋዴዎችና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ብቻ ሲሚንቶ ከፋብሪካ ገዝተው እንዲያከፋፍሉ በመደረጉ የስርጭት ሂደቱ ጤናማ ሆኗል ያሉት ሚኒስትሩ የአቅርቦቱ ችግር እየተስተካከለ፣ ህግ የማስከበርና ግብይቱን በስርዓት የመምራቱ ስራ እየተሰራ ስለሆነ አሁን ያለው የሲሚንቶ ዋጋ በቀጣይ በእጅጉ ይቀንሳል ብለዋል፡፡አቶ መላኩ አክለውም ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ በሲሚንቶ ላይም ሆነ በምግብ ሸቀጦች ላይ የተፈጠረውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የተሰሩ አቅርቦትን የማሻሻልና የቁጥጥር ስራዎች ውጤታማ ነበሩ ያሉ ሲሆን በቀጣይም አቅርቦቱን የማስተካከልና ህግ የማስከበር ስራዎችን ሳይነጣጠሉ ህብረተሰቡንና ነጋዴውን ባሳተፈ መልኩ በመስራት አሁን ያለውን የገበያ ሁኔታ ይበልጥ ለማረጋጋት ይሰራልም ብለዋል፡፡
ዘገባው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

ኢዜማ የጣና ሀይቅ 672 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚያክል ክፍሉ ወደ የብስነት መቀየሩን አስታወቀ!
ኢዜማ ‹የእምቦጭ አረም በጣና ሐይቅ እና የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ የደቀነው አደጋ› በሚል ርዕስ የ14 ገፅ ጥናታዊ ፅሁፍ አውጥቷል፡፡ በፓርቲው የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲ ቡድን የተዘጋጀ ነው የተባለው ጥናታዊ ፅሁፍ በጣና ሀይቅ ላይ ስለተደቀነው አደጋ በሰፊው ያብራራል፡፡በፅሁፉ ላይ የሀይቁ 672 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚያክል ክፍል ወደ የብስነት መቀየሩ ተገልጿል፡፡ በዚህም ሳቢያ 3,672 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የነበረው የጣና ሀይቅ ስፋት ወደ 3,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር መውረዱ ተጠቁሟል፡፡ ፅሁፉ ይህንን በምሳሌ ሲያስረዳ "በሌላ አነጋገር የሐዋሳ እና የዝዋይ ሐይቅ ተደምሮ የሚያክለው የሐይቁ ክፍል፣ ወይም 125,579 የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎችን የሚያክል የቦታ ስፋት ያለው የጣና ሐይቅ ወደ የብስነት ተቀይሯል ማለት ነው፡፡" ብሏል፡፡
በተጨማሪም የጉማራ ወንዝ ከጉና ተፋሰስ ይዞት በሚመጣው ደለል ምክንያት ጣና ቂርቆስ ደሴት ‹ከደራ ወረዳ ጋር በመቀላቀሉ ደሴትነቱ ታሪክ ሆኗል› በማለት በሀይቁ ላይ እየደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ጉዳት ይዘረዝራል፡፡ በዚህም ሳቢያ በጣና ሀይቅ ይገኙ የነበሩ የደሴቶች ቁጥር ከ37 ወደ 36 ዝቅ እንዳሉ የኢዜማ ጥናታዊ ፅሁፍ ያስረዳል፡፡የፓርቲው ጥናታዊ ፅሁፍ በሀይቁ ላይ እየደረሰ ያለው መጠነ ሰፊ ጉዳት መነሻ ምክንያት ያላቸውንም ዘርዝሯል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በሀይቁ ዙሪያ ያሉ ተፋሰሶች የዕፅዋት ሽፋን መውደምና በዚህም ምክንያት ደለል በብዛት ወደ ሀይቁ መግባቱ ፣ የእንቦጭ አረም መስፋፋት ፣ ውሃው ዳርቻ ድረስ የእርሻ ስራ መከናወኑ ፣ በዙሪያው በከተሞች መስፋፋት ምክንያት የመኖሪያ እና ፋብሪካ ቆሻሻ ወደ ሐይቁ መለቀቅ ሀይቁ ላይ ከፍተኛ የመጥፋት ሥጋት ያሳደሩ ተደራራቢና ተመጋጋቢ ችግሮች መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም በሀይቁ ላይ የተከሰተው የእንቦጭ አረም በአባይ ወንዝ ላይ መታየቱ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑ በፅሁፉ ላይ ተጠቁሟል፡፡ ይህ አረም በአባይ ውሃ አማካኝነት በአጭር ጊዜ ግድቡ ጋር ሊደርስ እንደሚችልም ያሳስባል፡፡በመሆኑም መንግስት አረሙ በአስቸኳይ በሰው ኃይል የሚወገድበትን የተቀናጀ አሠራር ሥርአት እንዲተገብር አሳስቧል፡፡ ይህም ሲሆን የኮሮናቫይረስ የመከላከል ጥንቃቄዎች መወሰዳቸው መረሳት እንደሌለበት አሳስቧል።
Via Asham TV

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በክ/ከተማው ለሚገኙ አርሶ አደሮች 1 ሺህ 85 ኩንታል ማዳበርያ ድጋፍ አደረገ፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በክ/ከተማው ለሚገኙ አቅም ለሌላቸው አርሶ አደሮች 1 ሺህ 85 ኩንታል ማዳበርያ ድጋፍ አድርጓል፡፡የከተማ አስተዳደሩ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አንድም መሬት ጾም ማደር የለበትም በሚል ሁሉንም መሬቶች በዘር ለመሸፈን እየተሰራ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል፡፡በዚህም አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በክ/ከተማው ለሚገኙ የመግዛት አቅም ለሌላቸው 450 አርሶ አደሮች 1 ሺህ 85 ኩንታል ማዳበርያ ድጋፍ አድርጓል፡፡በተጨማሪም ክፍለ ከተማው 233 ኩንታል የጤፍ፤የስንዴ፤የሽንብራ፤የምስር እና የጤፍ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮቹ ድጋፍ አድርጓል፡፡ለአርሶ አደሮቹ ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ በክ/ከተማው በግብርና ለተደራጁ 1ሺህ 500 ወጣቶችም የአትክልት ምርጥ ዘር ድጋፍ ተደርጓል፡፡በክፍለ ከተማው በተያዘው የክረምት ወር 2 ሺህ 300 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ መንገዶች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ብቻዬን ልቋቋመው አልቻልኩም አለ።
መንገዶች የሁሉም ማኅበረሰብ ሀብት በመሆናቸው ከሁሉም ነዋሪ አስፈላጊው ጥንቃቄ ሊደረግላቸው እንደሚገባም ጥሪ አስተላልፏል፡፡በመዲናዋ በየአመቱ በርካታ የመንገድ ፕሮጀክቶች እንደሚከናወኑ ይታወቃል፡፡ይሁንና መንገዶቹ ለታለመላቸው ጊዜ አገልግሎት ሣይሰጡ ሲበላሹም ይስተዋላል፡፡የአዲስ አበባ መንገዶች የግንባታና የአስተዳደር ኃላፊነት የተሰጠው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በበኩሉ መንገዶች የሁሉም ሀብት በመሆናቸው ከመንግሥት ባሻገር ሌላው ማኅበረሰብም ጥንቃቄ ሊያደርግላቸው ይገባል ብሏል፡፡ ይሁንና ይህንን ኃላፊነት የባለስልጣኑ ብቻ አድርጎ መመልከትና በመንገዶች ላይ የሚፈፀም ህገ-ወጥ ተግባርን ችላ ማለት መልሶ የሚጎዳው የሚገለገልበት ኅብረተሰብ በመሆኑ ሁሉም በቅንነት ሊረባረብ ይገባል ተብሏል።
ምንጭ: አሐዱ ሬዲዮ

ኬኒያ የፀጥታው ምክር ቤት መቀመጫን አሸነፈች!
ኬኒያ ጂቡቲን በድምፅ ብልጫ አሸንፋ አፍሪካን በመወከል የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት ማግኘቷ ተዘገበ።የምሥራቅ አፍሪካወዊቷ ሀገር ኬኒያ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ያልሆነ መቀመጫ የነበራትን ደቡብ አፍሪካን ትተካለለች።ኬኒያ 129 ድምፅ ያገኘች ሲሆን የጅቡቲ ደግሞ 62 ነው። ኒጀርና ቱኒዚያ ሌሎች የአፍሪካ አህጉር ተወካዮች ናቸው ሲል ቢቢሰ ዘግቧል ፡፡የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ሀገራቸው ማሸነፏንም ተከትሎ እንደተናገሩት ሀገሪቷ እያደገችና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በልማት አጋርነቷ እየፈጠረች ያለውን እመርታ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱም አያይዘው ጅቡቲንም በጥሩ ተፎካካሪነቷ አመስግነው የአፍሪካ ኅብረትም ድጋፍ ስለቸራቸው አመስግነዋል።ጅቡቲና ኬኒያ በአንደኛው ዙር ምርጫ ሁለት ሦስተኛውን (128 ድምጾች) አላገኙም ነበር ፡፡ፕሬዚዳንት ኡሁሩ እንዳሉት አፍሪካ እንደ አህጉር በፀጥታው ምክር ቤት ያላትን ተሰሚነት መጨመሩን ገልጸው ፤ለጉባኤው ምርጫ ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን ባለ አሥር ነጥብ አጀንዳም እንደሚያስተዋውቁ መናገራቸውን መረጃው አስታውሷል።
#ENA

ኢትዮጵያ ዴክሳሜታሶንን ለመጠቀም ወሰነች!
"ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል፡፡ የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ መሰረት በማድረግ፣ ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት ዴክሳሜታዞን እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወስኗል ። ህክምናውን አስመልክቶ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ ይወጣል።"
-የጤና ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ

"ከየካቲት እስከ ሰኔ ድረስ በረራ በመከልከሉ 1 ቢሊዮን ዶላር አጥተናል"
-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአየር ትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጫናን ማሳረፉን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳጣ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ገልፀዋል።
የኮሮናቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ በአየር መንገዶች ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ ማምጣቱን እንዲሁም ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኛ በረራዎች መቆማቸውን ለቢቢሲ የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ያንን ተከትሎ ደግሞ ከየካቲት እስከ ሰኔ መጨረሻ ድርጅቱ መንገደኛ በማጓጓዝ ሊያገኘው ይገባ የነበረው ወደ አንድ ቢሊየን ዶላር ገቢ ሳያገኝ መቅረቱን ገልፀዋል
#BBC

የኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት በትግራይ ጥሩ ቆይታ እንደነበረው ገለጸ!
በትግራይ ክልልና በፌዴራል መንግስት መካከል የሚስተዋለውን አለመግባባት ለመፍታት ወደ መቀሌ አቅንተው የነበሩ የሃገር ሽማግሌዎች ጥሩ ቆይታ እንደነበራቸው የኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ገለጸ። የሽምግልናውን የመቀሌ ቆይታ በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው አሉታዊ ወሬም ትክክል አይደለም ተብሏል።በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግስት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በውይይት እንዲፈቱ ለሁለቱም ወገኖች ጥያቄ ማቅረቡን የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ገልጿል።
የኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እና ምክትል ሰብሳቢዎች ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴና ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫውም ሽምግልናው በክልሉና በፌዴራል መንግስት መካከል ያለውን ፖለቲካዊ አለመግባባት በውይይት እንዲፈቱ ለማቀራረብ ነው ብለዋል፡፡የሽምግልና ሂደቱ የተጀመረው ቀደም ብሎ እንደነበር ገልፀው ኮቪድ 19 እና እሱን ተከትሎ መንግሥት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳዘገየውም ገልጸዋል።
ነገር ግን ሂደቱ ተካርሮ ችግር ከሚፈጠር ቀድሞ መፍትሔ እንድበጅለት ለማወያየት ወደ መቀሌ ማቅናታቸውን ገልጸዋል። የሀገር ሽማግሌዎቹ በመግለጫው "ከሁለቱም ወገን ችግር የለም፤ ችግሩ ተቀራርቦ አለመወያየት ብቻ ነው" ብለዋል፡፡የሀገር ሽማግሌዎቹ ወደ ትግራይ ባቀኑበት ወቅት የክልሉ ህዝብና መንግስት በአግባቡ ተቀብሎ እንዳስተናገዳቸው ተናግረው፤ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በአሉታዊ መልኩ የሚሰራጨው ወሬ እውነታ የሌለው መሆኑንም አብራርተዋል።ለሽምግልና ወደ ትግራይ ክልል አቅንተው የነበሩ 34 የሃገር ሽማግሌዎች ጥሩ ቆይታ እንደነበራቸውም ተገልጿል፡፡
ምንጭ: ኢዜአ