YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖረው ያልተረጋጋ ሰላም ምርጫው ላይ ችግር እንዳይፈጥር መንግሥትን ተስፋ በማድረግ እየሰራ መሆኑን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የምርጫ ቦርድ አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ ያለው ሰላምና መረጋጋት እጅግ ፈታኝ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም የተለያዩ ችግሮች በየጊዜው ይታያሉ፡፡

ስለሆነም ምርጫው እንዳይደናቀፍ መንግሥት በሚገባ መስራት አለበት፡፡ ምርጫ ቦርድ ምርጫው ሰላማዊና ነፃ እንዲሁም ፍትሃዊ እንዲሆን እየሰራ ነው፡፡ ሆኖም የጸጥታ ማስከበሩና ሰላማዊ ምርጫ እንዲካሄድ የማድረጉ ኃላፊነት የመንግሥት ነውና እርሱን ተስፋ አድርገን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ዶ/ር ጌታሁን፡፡

ሰላምን የሚያደፈርስ አካል ካለ እርምጃውንም ሆነ ሥራውን መስራት ያለበት መንግሥት ነው ያሉት ዶ/ር ጌታሁን ምርጫ ቦርድ ምርጫው ነፃ፤ ፍትሃዊና ተአማኒ እንዲሆን ከመስራት ውጪ ሊያደርገው የሚችለው ነገር እንደማይኖር ገልጸዋል፡፡

ምርጫ ቦርድ የሰላም ማስከበር ሥራን ለመስራት ኃላፊነቱ እንደማይፈቅድለት የሚያስረዱት ዶክተር ጌታሁን፤ በአገር ደረጃ ከ45ሺ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች በመኖራቸው መንግሥት በእነዚህ ጣቢያዎች ላይ ሰላማዊ ምርጫ እንዲኖር ያደርጋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-ኢፕድ
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በተዘጋጀው የመገናኛ ብዙሃንና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የስነ ምግባርና አሰራር ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተዘጋጅቶ በቀረበው የመገናኛ ብዙሃንና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የስነ ምግባርና አሰራር ረቂቅ መመሪያ ላይ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡

ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን ከምርጫ ጣቢያዎች በ2 መቶ ሜትር ርቀት ዙሪያ ሁነው ለመዘገብ እንዲችሉ እውቅና እንዲሰጣቸው ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችሉም በረቂቅ መመሪያው ላይ ተመልክቷል፡፡
የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎቻቸውን ማንኛውም ፓርቲን ከመደገፍና ከማጥላላት የፀዱ መሆን እንዳለባቸውም ተመላክቷል፡፡

ጋዜጠኞችና መገናኛ ብዙሃን እውነተኛ በማፈላለግ ረገድ ምንጩን በሚያውቁት እውነታ ላይ ተመስርተው ዘገባዎቻቸውን መስራት እንዳለባቸው ረቂቅ መመሪያው ይገልጻል፡፡
የስነ ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት ፈቃድ አሰጣጥ እና ስነምግባር ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ መመሪያም በውይይቱ ላይ ቀርቧል፡፡

በሁለቱ መመሪያዎች ላይ ውይይት ተደርጎ የሚገኙ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ የዛውሬው መድረክ መዘጋጀቱን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa
የየኔቲዩብ ቤተሰቦች የኢትዮጵያ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ለመርዳት የቦኩሎን ይወጡ!!

#የኔ_ዜማ የተሰኛውን የዳዊት ፅጌ አልበም ኦርጅናሉን በመግዛት በቀጥታ አርቲስቱን ይርዱ!!

ለመልካም ተግባራችሁ እናመሰግናለን!!
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎊እንኳን አደረሳችሁ🎉
ፈረስ ለበዓሉ አንድ ሙክት በግ እና ሁለት ዶሮዎች አዘጋጅቶላችኋል 🎁🎁🎁

ከዚህ ሽልማት አሽናፊ ለመሆን
1. ፈረስ ይዘዙ እና የሄዱበትን ሂሳብ ስክሪን ሻት አድርገው ይላኩልን
2. ይህንን ፓስት ላይክ እና ሼር ያድርጉ

ደንብና ግዴታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ።
Forwarded from YeneTube
Samsung Galaxy A10s
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot

📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞

@CloudTrading @CloudTrading
🔥1
"ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊታችን የኩራታችን ምንጭ ነው"
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ
ዛሬ ከመከላከያ ሠራዊታችን አመራሮች ጋር በአዲስ አበባ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ሂደት ተከታትለናል ሲል ዶ/ር አብይ አህመድ በfacebook ገፃቸው አስታውቋል ።

@YeneTube @Fikerassefa
Ethiopian Airlines would like to express its profound joy up on the inscription of Ethiopian Epiphany as intangible world cultural heritage by UNESCO. The Airline wishes all Christians a Happy Epiphany.

Via:- Ethiopian airline
@Yenetube @FikerAssefa
የመከላከያ ምኒስትር ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ ጦር የጦርነት ኮሌጅ (War College) መክፈቱን እንደተናገሩ ኢቲቪ ዘግቧል። ጦሩ አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ከ700 በላይ ቢሮዎች የሚኖሩት ባለ 5 ፎቅ አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት እየገነባ ነው።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም የጥምቀት በዓልን በማስመልከት በአዲስ አበባ ጃንሜዳ እና በጎንደር ፋሲለደስ ጥምቀተ ባህር ነፃ የዋይ ፋይ አገልግሎት ማቅረቡን ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
Forwarded from YeneTube
Samsung Galaxy A10s
2019 Model Phone
Brand New Packed &
Original with Full Accessories
6.2inch screen size
32GB Storage
13MP camera 1080HD
4000mAh battery capacity
Dual Sim Slot

📩 @CloudMultiTrading 📩
📞 0944182119 📞

@CloudTrading @CloudTrading
የውጭ ሀገራት እና የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ለጥምቀት በዓል ጎንደር ከተማ እየገቡ ነው

በነገው ዕለት በጎንደር ለሚከበረው የጥምቀት በዓል ለመታደም የውጭ ሀገራት እና የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ጎንደር ከተማ እየገቡ ይገኛሉ፡፡

በበዓሉ ከ 2 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች እንደሚታደሙ አብመድ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዚህ ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ የሚሆኑት የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ናቸው ተብሏል፡፡

ምንጭ:- አብመድ / EBC
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለጥምቀት በዓል ያስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክት።
@YeneTube @Fikerassefa
የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ነድያንን መገቡ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለጥምቀት በዓል ጎንደር ከተማ ገቡ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጎንደር ሲደርሱም የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።በተመሳሳይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ለበዓሉ ጎንደር ገብተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማም በተመሳሳይ ለበዓሉ ከተማዋ ደርሰዋል።በጎንደር ዛሬ የከተራ በዓል ነገ ደግሞ የጥምቀት በዓል በድምቀት ይከበራል።ለበዓሉ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የውጭ ሀገራት ጎንደር ከተማ በመግባት ላይ ይገኛሉ። ዛሬ ማለዳ ላይም ቁጥራቸው ከፍ ያለ የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች በበዓሉ ላይ ለመታደም ጎንደር ገብተዋል።የጥምቀት በዓልም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ዘንድሮ መመዝገቡ ይታወሳል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070