YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የምግብ ይዘትን በመከለስና በመለወጥ ለሽያጭ በሚያቀርቡ ግለሰቦች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እንደቀጠለ ቢሆንም በተጠርጣሪዎች ላይ በቂ የፍርድ ውሳኔ እየተሰጠ አለመሆኑን የአዲስ አበባ አስተዳደር የምግብና ጤና
ክብካቤ ባለስልጣን አስታወቀ።

@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ጠዋት በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ!

ጥቃቱ የትራፊክ እንቅስቃሴ በሚበዛበት የፍተሻ ጣቢያ አካባቢ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ የተፈጸመ ነው። ፖሊስ በበኩሉ ጥቃቱ በከተማዋ የሚገኝን የግብር መሰብሰቢያ ማዕከል ኢላማ ያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

በጥቃቱ ከሞቱት በተጨማሪም ከ100 በላይ ሰዎች ሆስፒታል ገብተዋል ነው የተባለው። ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም በታጣቂው አልሸባብ ሳይፈጸም አልቀረም ተብሏል። የሆስፒታል ምንጮች ደግሞ የሟቾቹ ቁጥር ከ30 በላይ መሆኑን ገልጸዋል።

Via FBC
ምንጭ: አልጀዚራ እና ቢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
መንግሥት ይከተለው የነበረውን የ70/30 የተማሪዎች ምደባ ወደ 55/45 ቀየረ!

መንግሥት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ ለምደባ ይሰራበት የነበረውን ለተፈጥሮ ሳይንስ 70 በመቶ እንዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ 30 በመቶ የምደባ ስርዓት ለተፈጥሮ ሳይንስ 55 በመቶ እንዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ 45 በመቶ እንዲሆን መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

መንግሥት ቀደም ሲል ለዓመታት ሲሰራበት የቆየው የ70/30 የድልድል ስርዓት በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የታሰበውን የሥራ ዕድል መፍጠር ባለመቻሉ በርካታ ተማሪዎች ያለፍላጎታቸው የተፈጥሮ ሳይንስን እንዲመርጡ የሚያስገድድና በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ውጤታማ መሆን አለመቻላቸው፤ የዩኒቨርስቲዎች የመቀበል አቅምን በማገናዘብና የሀገሪቱን የሰው ሀብት ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባትና በመሳሰሉት ምክንያቶች የምደባ ስርዓቱን መቀየር አስፈልጓል ተብሏል።

Via:-ኢፕድ
@YeneTube @Fikerassefa
⚽️ የእግር ኳስ ውርርዶችን ከኛ ጋር ያሸንፉ!⚽️

ከሀገር ዉጪ በመወራረድ ብዙ ብር ካተረፉ የእግር ኳስ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር እጅግ አስተማማኝ የሆኑትን የቀኑን ምርጥ የ እግር ኴስ ቅድመ ጨዋታ ውጤቶችን ለናንተ እናደርሳለን::

ውጤቶቻችን በባለሙያዎች የተመረጡ ስለሆኑ በራስ መተማመናችን የላቀ ነው::

ስለዚህም ከኛ ጋር ብዙ አትራፊ ይሁኑ እንልዎታለን::

T.me/oddcrackerET
T.me/oddcrackerET
ኢዜማ ከ400 በላይ ወረዳዎችን ያካተተ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) በባሕር ዳር ከተማ ከሚገኙ አባላቶቹና የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አድርጓል።

ኢዜማ በየትኛወም የሀገሪቱ ሕዝቦች የትኛውንም ቋንቋ፣ ባህልና እሴት ቢኖራቸም እንደ ዜጋ በእኩልነት የማስተናገድ ራዕይ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ አንደሚገኝ ተነግሯል። የዜጎች ማኅበራዊና ፍትሕ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እየታተረ እንደሚገኝም የሚገልፅ ሐሳብ ለውይይቱ መነሻ ቀርቧል።

‹‹ፓርቲው የሀገሪቱን ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ ምን አስቧል? በመጭው ምርጫ ተወዳዳሪ ለመሆን ምን እየሠራ ነው? ሠላማዊ ምርጫ እንዲኖር ለአባላት ግንዛቤ መፈጠር አለበት?›› የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተው ከፓርቲው ከፍተኛ ኃላፊዎች መልስ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

የፓርቲው ሊቀ መንበር የሺዋስ አሰፋ በሀገሪቱ የሚታዩት አለመረጋጋትና አደገኛ አካሄዶች የተፈጠሩት ከዜግነት ፖለቲካ ውጭ ሲደረጉ በነበሩ የዘር ፖለቲካ ሥርዓት የተፈጠሩ እንደሆኑና ከእንደዚህ ዓይነት የፖለቲካ ሥርዓት መውጣት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

‹‹ኢዜማ በዘር ሳይሆን ዜግነትን መሠረት ያደረገ፣ የሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ የሚችል የፖሊሲ አማራጭ ይዞ የመጣ ፓርቲ ነው›› ብለዋል አቶ የሺዋስ።

ፓርቲው በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የቆዩ አካላት የመሠረቱት ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ እንደሆነና በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ብቁ ሆኖ ለመቅረብ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ የሚገኝ መሆኑንም አስረድተዋል።

የኢዜማ ምክትል ሊቀ መንበር ጫኔ ከበደ (ዶክተር) ደግሞ የአባላቱን ቁጥር ለማብዛትና በምርጫው የተሻለ ድምፅ ለማግኘት ባለፉት ስድስት ወራት ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱ ተናግረዋል። በመላ ሀገሪቱ በ408 የምርጫ ወረዳዎች አድማሱን እንዳሰፋም ነው ያስረዱት።

ፓርቲው ‹‹በአማራ ክልል 137 ወረዳዎች፣ በኦሮሚያ ክልል 83 ወረዳዎች፣ በትግራይ ክልል 37 ወረዳዎችን አካልሎ እየሠራ ይገኛል›› ተብሏል። በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝም ተመላክቷል።
ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሠላማዊ እንዲሆን ኢዜማ የሚገባውን ሁሉ እያደረገ እንደሚገኝም ተጠቅሷል።

መጭው ምርጫ ውጤታማ እንዲሆን ሠላምና መረጋጋት መረጋገጥ እንዳለበት፣ ‹ለውጥ› የሚባለው ተቋማዊ መሆን እንደሚገባውና የፍትሕ ተቋማት ነፃነት፣ የሚድያና ሌሎችም አካላት ሙያዊ ኃላፊነት መከር እንዳለበትና በሐሳብ የበላይነት ወይም አማራጭ ፖሊሲዎች ተጠናክረው የሚመጡ ፓርቲዎች ቁጥር መበራከት እንለበት የፓርቲው እምነት መሆኑም ተመላክቷል።

Via:-AMMA
@Yenetube @Fikerassefa
ነገር በአኃዝ

23400000 ባለፈው አመት የተለታዩ መዳረሻዎች የጎበኙ አገር ውስጥ ጎብኚዎች ብዛት።

@Yenetube @Fikerassefa
10ቱ ከፍተኛ የውጪ ብድር ያለባቸው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በቢልየን ዶላር

1) ሱዳን (55.4)

2)ኬንያ (42.7)

3)ኢትዮጵያ (25.6)

4)ታንሳንያ (19.2)

5) ኡጋንዳ (12.5)

6) ሩዋንዳ (4.0)

7) ጁቡቲ (2.2)

8) ሲሼልስ (1.6)

9)ኤርትራ (1.3)

10) ቡሩንዲ (0.5)

@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮ ቴሌኮም ለአራት ሺ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች የኪስ ገንዘብ ደጎመ።

ኢትዮ ቴሌኮም ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጋር ባመተባበር በ13 ዩንቨርስቲ ለሚገኙ ስምንት መቶ ተማሪዎች በየወሩ ሲያቀርብ የነበረውን የኪስ ገንዘብ ድጋፍ ድጎማ በሁሉም አገሪቱ የንቨርስቲዎች በማስፋፋት ለአራት ሺሕ ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግ ሊጀምር ነው።

የመጭው ማክሰኞ በሀያት ሪኤጀንሲ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የከፍተኛ የመንግስት ተቋማቱ ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት ይፋ ይደረጋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ የወጣ!!

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ በሳውዲ አረቢያ

የኤጀንሲው ስም :- ነጂድ የውጪ ሀገር እና ሰራተኛ አገናኝ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የኤጀንሲው ፍቃድ ቁጥር 763193/2010

ኤጀንሲው ፍቃድ ያገኘበት ሀገር ሳውዲ አረቢያ

የሚፈለገው የሰራተኛ አይነት
100 ሹፌር እና 600 #የቤት_አያያዝ ደሞዝ
1000 ሳውዲ ሪያል ለሁለቱም ስራ።

መስፈርት 8ክፍል ያጠናቀቀች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላት / ያለው።
@yenetube @Fikerassefa
የትህምርት ሚኒስትሩ ስራቸውን የለቀቁት በጤና እክል ምክንያት ነው

"የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌጤ ኃላፊነታቸውን በፍቃዳቸው ለቀዋል ።የለቀቁበትም ምክንያት ያገጣማቸው የጤና እክል ስራቸውን በአግባቡ መስራት ስላላስቻላቸው እንጂ ሌላ ምንም አይነት ፓለቲካዊ ወይም አስተዳደራዊ ምክንያት የለውም "
ሲሉ የቅርብ ወዳጃቸው በስልክ ነግረውኛል ሲል ጋዜጠኛ ተስፌዬ ጌትነት አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎችና ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው መግባታቸው ውጥረት ፈጥሯል!

የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎችና 10 ሺህ የሚገመቱ ስደተኞች 200 ኪሎ ሜትር ዘልቀው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባታቸው በደቡብ ክልል ሱርማ ወረዳ ውጥረት መፍጠሩ ተጠቁሟል፡፡ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ታጣቂዎች በሱርማ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች ተበታትነው፣ የሱርማ አርብቶ አደሮች ላይ ዘረፋና ጥቃት እየፈፀሙ መሆኑንና ለአካባቢው ጸጥታም ስጋት መደቀናቸውን የምዕራብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ለውጭ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ አስታውቋል።ቁጥራቸው 10 ሺህ የተገመቱና ከታጣቂዎች ጋር አብረው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የዘለቁ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችም በአካባቢው ተበታትነው ሰፍረው እንደሚገኙ የአካባቢው አስተዳደር ጠቁሟል፡፡ድንበሩን ጥሰው 200 ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የዘለቁት ስደተኞችና ታጣቂዎች ወደ ኋላ እንዲመለሱ ማሳሰቢያ እየተሰጠ ሲሆን የመከላከያ ሰራዊት እርምጃ ለመውሰድ ወደ አካባቢ የሚያስገቡ መንገዶች አለመሰራታቸው እንቅፋት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ በቀጣይ መንገዱ ተሰርቶ ታጣቂዎችና ስደተኞቹ ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ይደረጋል ተብሏል፡፡

Via Addis Admas
@YeneTube @FikerAssefa
ፈረንሳይ የዜጎቿን የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ በመፈተሽ ግብር ሰዋሪዎችን ልትለይ እንደሆነ ተገለፀ፡፡

ይህም ባለፈው ሳምንት ከግብር ክፍያ ጋር በተያያዘ የወጣው ሕግ አካል ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በገፃቸው ላይ የሚለጥፉትን  የግል መረጃ ዝርዝር  በማየት  ነው ግብር የከፈለ እና ያልከፈለ የሚለየው፡፡እርምጃው የዜጎች ራስን በነፃነት የመግለጽ እና የግላዊነት መብት ላይ ጫና ሊያሳድር ቢችልም ድንጋጌው የሚተገበርበት ቅድመ ሁኔታዎች አሉ ተብሏል።ከቅድመ ሁኔታዎቹ አንዱ በሚስጥራዊ ይለፍ ቃል የተቆለፉ ገጾችን ሰብሮ አለመግባት ነው፡፡

ከዚህ ባለፈ ግን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለሕዝብ ይፋ የተደረጉ መረጃዎችን መጠቀም እንደሚችል ነው የተነገረው። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የፈረንሳይ የመረጃ ደህንነት ክፍል ሕጉ እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል።የበጀት ሚንስትሩ ጄራልድ ዳርማኒን በበኩላቸው አጭበርባሪዎችን የምንገታበት አንድ መንገድ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ/ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ዛሬ ጠዋት በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ! ጥቃቱ የትራፊክ እንቅስቃሴ በሚበዛበት የፍተሻ ጣቢያ አካባቢ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ የተፈጸመ ነው። ፖሊስ በበኩሉ ጥቃቱ በከተማዋ የሚገኝን የግብር መሰብሰቢያ ማዕከል ኢላማ ያደረገ መሆኑን አስታውቋል። በጥቃቱ ከሞቱት በተጨማሪም ከ100 በላይ ሰዎች ሆስፒታል ገብተዋል ነው የተባለው። ለጥቃቱ እስካሁን…
ዛሬ ጠዋት በሞቃዲሾ በደረሰው ጥቃት ቢያንስ 76 ሰዎች ሞቱ!

ከሰዓት በፊት በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃት በትንሹ 76 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። ዛሬ ጠዋት በርካታ ሰዎች ወደ ሥራ በሚሄዱበት ሰዓት ደረሰ በተባለው በዚህ የቦምብ ጥቃት ከሟቾች በተጨማሪ በርካቶች ቆስለዋል።አደጋው የደረሰበት ይህ የሞቃዲሾ ክፍል ፍተሻ የሚደረግበትና በርካታ ሰዎች የሚንቀሳቀሱበት ነው።

የፖሊስ መኮንኑ ኢብራሂም ሞሐመድ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ፍንዳታው እጅግ አደገኛ ነበር።የመዲና ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ሞሐመድ የሱፍ ለአሶሽየትድ ፕረስ እንደተናገሩት 73 አስክሬኖች ተቀብለዋል።ሳካሪ አብዱልቃድር የተባለ የአይንም ምስክር በበኩሉ "ማየት የቻልኩት እዛም እዚም የተበጣጠሰ የሰው አካል ነው፤ የአንዳንዱ ሰው ሬሳ በእሳት በመቃጠሉ መለየትም አይቻልም ነበር" ብሏል።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም። ዘግይተው እየወጡ ባሉ መረጃዎች ደግሞ የሟቾች ቁጥር ከተገለጸውም እጥፍ ሊደርስ እንደሚችል ይጠቁማሉ። መሐመድ አብዱራዛቅ ተባሉ የምክር ቤት አባል የሟቾቹ ቁጥር 90 እንደደረሰ ያልተረጋገጠ አሀዝ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
- Engineering Art -

የወዳጅ ዘመድዎን ፎቶዎች ከፈለጉት ፅሁፎች እና የተለያዩ ዲዛይኖች ጋር፣ ሳቢና ማራኪ በሆነ የእንጨት ስራ ቀርፀው ያስቀሩ።

ለሚኖሮዎት ጥያቄ @marsengraving ብለው ቴሌግራም ላይ ያግኙን።


ብዙ የተሰሩ ሥራዎች አሉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ⬇️
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFXiDfCeA__IVLJ7PA
Forwarded from YeneTube
እንኳን አደረሳችሁ

በ አዲስ አበባ የተለያዩ እቃዎች አስመጪ
ብራንድ የወንድና የሴት ሰዓቶች
የሴት ቦራሳዎች
የመዋቢያ እቃዎች
አልባሳት

የምናስመጣቸው እቃዎች ጥራት እና በቀላሉ ገበያ ላይ አለመገኘት እንዲሁም ወደ ክልል ከተሞች መላክ መቻላችን ለየት ያደርገናል ።

ቦሌ መዳንአለም ሞል
+251993014846

ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይጎብኙን ይምረጡ ይዘዙን

👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
Forwarded from YeneTube
🎄🎄ታላቅ ቅናሽ 🎄🎄
እንኳን አደረሳቹሁ በአሉን አስመልክቶ ታላቅ ቅናሽ በየቲ ኮስሞቲክስ እንዳያመልጣችሁ አሁኑኑ ሊንኩን በመጫን ቻናላችን ጆይን ያድርጉ

https://tttttt.me/yeticosmo

Yeticosmotics is glad to announce its #holiday discount

1. Apple cider with only 850 br

2. Zara perfume with only 1200 br

2. Tresemme shampoo and
conditioner 1100

3. 1 literJohnson wash and shampoo with only 650 br and we have discount for so many products

Join our telegram channel using

https://tttttt.me/yeticosmo
https://tttttt.me/yeticosmo
በድሬዳዋ ዩኒቭርሲቲ ትናንት ታህሳስ 18/2012 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 አካባቢ የባንኪንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል የ3ኛ አመት ተማሪ ይሁን አለማየሁ ከፎቅ ላይ ተወርውሮ ህይወቱ አልፏል:: ዩኒቨርሲቲው የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን እንደሚመኝ በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል::

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በድሬዳዋ ዩኒቭርሲቲ ትናንት ታህሳስ 18/2012 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 አካባቢ የባንኪንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል የ3ኛ አመት ተማሪ ይሁን አለማየሁ ከፎቅ ላይ ተወርውሮ ህይወቱ አልፏል:: ዩኒቨርሲቲው የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን እንደሚመኝ በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል:: @YeneTube @FikerAssefa
ከዚው ጋር በተያያዘ ዩኒቨርሲቲው ለጊዜው ትምህርት ማቋረጡን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ሰኞ ታህሳስ 20/2012 ዓ/ም ሊጀመር የነበረው ትምህርት አጋጠመኝ ባለው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በዩኒቨርሲቲው ትምህርት ማስቀጠል የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን ተረድቷል::ስለሆነም የመማር ማስተማር ሂደቱ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ የዩኒቨርሲቲ ሴኔት ወስኗል:: ስለሆነም ዩኒቨርሲቲው ከታህሳስ 20/2012 ዓ/ም በኋላ ምንም አይነት አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን ገልጾ የተማሪዎችን የመልሶ መቀበያ ጊዜ ወደ ፊት በሚዲያ የሚገልጽ መሆኑን አሳውቋል::

@YeneTube @FikerAssefa