YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮ ቴለኮም ለአንድነት ፓርክ የመግቢያ ቲኬት ከውጭ ሀገር በኦንላይን መግዛት የሚያስችል አሠራር ተግባራዊ አደረገ።
@Yenetube @Fikerassefa
የኔቲዩብ እለታዊ ዜና አቅርበንላችዋል ⬇️


https://www.youtube.com/watch?v=DGyY-s67HFM
ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ማምረቱን ከጥር ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማቆሙን አስታወቀ። ከኢትዮጵያው አደጋ በኋላ የታገደው 737 ማክስ በአሜሪካ ፌድራል የበረራ መቆጣጠሪያ ባለሥልጣንና ዓለም አቀፍ ተቋማት የደህንነት ማረጋገጫ እየጠበቀ ነው።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡ምክር ቤቱ ዛሬ በሚያደርገው ውይይት የኢንቨስትመንት፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደግል ስለማዛወር እና የኤክሳይዝ ታክስ ላይ የቀረቡ ሶስት ረቂቅ አዋጆች መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
የዛምቢያው ፕሬዝዳንት በሀገራቸው ያሉት የአሜሪካ አምባሰደር ግብረሰዶማውያንን በመደገፋቸው ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አደረጉ

ባለፈው ወር በዛምቢያ በግብረ ሰዶም ወንጀል ተከስው ወደወህኔ ያመሩትን ሁለት ወንዶች ፍርድን በመቃወም " ፍርዱን ስሰማ ደንግጫለው ፣ዛምቢያ በግብረሰዶም ላይ ያላትን ህግ ልትፈትሽ ይገባል" ያሉትን በዛምቢያ የአሜሪካ አምባደርን ዳንኤል ፉትን የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ኤድጋር ቻጋር ሉውንጉ ከስካይ ቲቪ ጋር ባለፈው እሁድ ባደረጉት ቃለ ምልልስ "ሀገራችንን ለቆ እንዲወጣ አዘነዋል ።እንዲህ አይነት ሰው በሀገራችን እንዲኖር አንፈቅድም" ብለዋል።

Via :- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር የህብረተሰቡ ትብብር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ብዛቱ 250፣4753 የብሬን ጥይት፣32 ክላሽ ፣ 2053 የክላሽ ጥይት በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብራሃጅራ ከተማ በትላንትናው ዕለት የተያዘ ሲሆን የጸጥታ ኃይላችን ቁርጠኝነት የተሞላበት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

ምንጭ: ከአማራ ክልል የሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በስድስት ወራት ውስጥ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በስርቆት እንደወደመበት ገለፀ

ከግንቦት 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች በትራንፎርመር፣በኤሌክትረክ ገመድ እና በታውሮች ላይ በተፈፀመበት ስርቆት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ እንደተዘረፈ የአገልግሎቱ የኮርፖሬት ከሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለአሐዱ ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና ዙሪያው በተከሰተው የኤሌክትሪክ መስመር ወይም ኬብል ስርቆት ሀገሪቱ ከ6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ማጣቷንም አቶ መላኩ ተናግረዋል፡፡

ይህ የስርቆት ተግባር በመላው ሀገሪቱ ተስፋፍቶ ከ38 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ለኪሳራ እንደተዳረገ አቶ መላኩ ይገልፃሉ፡፡

በመንግስት ላይ ከሚደርሰው የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ የኃይል አቅርቦት እንዲስተጓጎል እንዲሁም በኢንዱስትሪዎች ላይም ከፍተኛ ኪሳራ እየተፈጠረ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

Via:- አሐዱ ሬዲዮ
@Yenetube @Fikerassefa
አሰሪዋን የገደለችው የቤት ሰራተኛ በፈፀመችው ወንጀል ጽኑ እስራት ተፈረደባት!

ገርጂ ኮንዶሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ አሰሪዋን በመግደል እና በስርቆት ወንጀል የተከሰሰችው የቤት ሰራተኛ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ሁለት ክስ በጽኑ እስራት ተቀጣች፡፡በ1ኛ ክስ ተከሳሽ መሰረት ነገሰ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 540 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ከምሽቱ 4 አካባቢ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው ገርጂ ኮንዶሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው ሉዋም ሱቅ ውስጥ ሟች እርግብ ገ/ክርስቶስ ቤት ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ እየሰራች በነበረችበት ወቅት ለጊዜው ያልተያዘው ግብረአበሯ በተደጋጋሚ ጊዜ ስልክ በመደወል ሟችን በተኛችበት ግደያት በማለት ሲነግራት እሷም በእለቱ ሟች ወደ ተኛችበት ክፍል በመሄድ በብርድ ልብስ አፍና የጉሮሮዋ ቧንቧ እንዲደፈን በማድረግ ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጓ በፈጸመችው የሰው ግድያ ወንጀል ተከሳለች፡፡

በ2ኛ ክስ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ለ) እና 669 (2) (መ) በመተላለፍ ተከሳሽ በ1ኛ ክስ ላይ በተጠቀሰው ቦታ ሟችን ከገደለቻት በኋላ ያልተያዘውን ግብረአበሯ ስልክ በመደወል ጠርታ ወደ ሟች ሱቅ በመግባት 6000 ብር እና ግምቱ ያልታወቀ ገንዘብ እንዲሁም የዋጋ ግምቱ ብር 1650 ብር የሆነ ስልክ ከወሰዱ በኋላ ግብረ አበሯ ለተከሳሽ 2000 እና የሟችን የእጅ ስልክ የሰጣት የወሰደች በመሆኑ በፈጸመችው የግድያና ከባድ ስርቆት ወንጀል ተከሳለች፡፡ተከሳሽ የዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ተነቦላት እንድትረዳው ከተደረገ በኃላ በ2ቱም ክስ ላይ የተጠቀሱትን ድርጊቶች አልፈፀምኩም በማለት የእምነት ክህደት ቃሏን ሰጥታለች፡፡

ዐቃቤ ሕግም እንደክሱ አቀራረብ የምስክሮች ቃል እንዲሳማ ለፍርድ ቤቱ ያመለከተ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሽ በቀረበባት 2 ክስ ጥፋተኛ ተባለች::በመጨረሻም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽን የዘወትር ፀባይ መልካም እንደነበር እና የቤተስብን የምትረዳ መሆኑን በማቅለያ በመያዝ በ2ቱ ክስ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል፡፡

Via Attorney General
@YeneTube @FikerAssefa
የሰው ፀጉር፣ ውዳቂ ዊግ፣ የውሸት ጢም፣ የውሸት ቅንድብ፣ የውሸት ሽፋል እና ሌሎችም አርቴፊሸል ማጌጫዎች ደግሞ 40 በመቶ ቀረጥ እንዲጣልባቸው ተደንግጓል!

ተሻሽሎ ረቂቁ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይዝ ታክስ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍ ያለ ቀረጥ እንዲከፈልባቸው ደንግጓል፡፡
ይህም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ለመለዋወጫ አገሪቱን ከሚያስወጧት የውጪ ምንዛሬ ባሻገር ለህብረተሰብ ጤና እክል ይፈጥራሉ፣ ለትራፊክ አደጋም ምክንያት ይሆናሉ በሚል በገፍ ከውጪ እየገቡ ያሉ ያረጁ ተሽከርካሪዎችን ለመግታት ያለመ ነው ተብሏል፡፡የቪዲዮ መቅረጫ፣ ቴሌቪዥን፣ ካሜራ፣ ድምፅ መቅረጫና የሬዲዮ የድምፅ ስርጭት መቀበያ መሳሪያዎች ላይም 10 በመቶ ቀረጥ ተጥሏል፡፡

የሰው ፀጉር፣ ውዳቂ ዊግ፣ የውሸት ጢም፣ የውሸት ቅንድብ፣ የውሸት ሽፋል እና ሌሎችም አርቴፊሸል ማጌጫዎች ደግሞ 40 በመቶ ቀረጥ እንዲጣልባቸው ተደንግጓል፡፡የቅንጦት ዕቃ ተብለውና ለህብረተሰብ ጤናም ጉዳት እንደሚያስከትሉ ታምኖባቸው በተሻሻለው የኤክሳይዝ ታክስ ከተካተቱት መካከል ቴሌቪዥን፣ ስኳር፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ሽቶዎች፣ ወርቅና አልማዝን ጨምሮ ከከበሩ ማዕድናት የተመረቱ ማጌጫዎች፣ ትንባሆ፣ የሲሊንደር ዘይት እና ሌሎችም ተካትተውበታል፡፡ረቂቅ ሕጉ ከመፅደቁ በፊት በዝርዝር እንዲፈተሽ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
አዲሱ ኤክሳይስ ታክስ ንድፈ መመርያ በመኪኖች ላይ እሰከ 500 %በምግብና መጦች ላይ ደግሞ እሰከ 50% ታክስ ለመጣል አቅዷል።

ለተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት የቀረበው አዲሱ ኤክሳይስ ታክስ ከሰባት አመት በላይ ያገለገሉ መኪኖችን 500% ፣ ከአንድ አስከ አራት አመት ያገለገሉትን መኪኖች ከ 100 አስከ 150 % ፣መገጣጠሚያቸው ከውጭ የሚመጣ ወይንም እዚህ የሆነ መኪኖችን 100% ታክስ ለመጣል አቅዷል። በለስላሳና መጠጦች ላይ 25% በታሸጉና በጣፋጭ ብስኩቶችና ምግቦች ላይ ከ20 አስከ 50 % ኤክሳይስ ታክስ ለመጣል አቅዷል።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በዚህ ዓመት የሚሰጠው 12ኛ ክፍል ላይ ብቻ ነው | EBC

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና እንደማይሰጥ አስቀድሞ ቢነገርም አንዳንድ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለ10ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎችን እያዘጋጁ መሆኑን መረጃ እየደረሰው ነው፡፡

የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ለኢቲቪ እንደገለፁት ለአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ዝግጅት ማድረግ እንደማይገባ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች መደበኛ የክፍል ፈተና ብቻ እንደሚፈተኑ ለማስታወስ ለሁሉም ክልሎች ተቋሙ ድብዳቤ ፅፏል ብለዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ብሄራዊ ፈተና የሚወስደው 12ኛ ክፍል ላይ መሆኑን ተማሪዎችም ወላጆችም ሆነ ትምህርት ቤቶች ሊያውቁት እንደሚገባ አቶ አርአያ ተናግረዋል።

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን ከቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና ከወዳደቁ የፕላስቲክ ዕቃዎች ጋር በማደባለቅ ከገብረ ጉራቻ ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት የሞከሩ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

(አብመድ)
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ለኹለት የሥራ ኃላፊዎች የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ ሰጠ። የሥራ ኃላፊዎቹ በማረሚያ ቤት ፖሊስነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሲሆኑ ማረሚያ ቤት ኮሚሽኑ ለምክትል ኮሚሽነር ውቤ ወንዴ እና ለኮማንደር አማረ ወርቁ ነው የረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ የተሰጠው።

ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የተለያዩ የባህር ዳር ዩንቨርስቲ የፓሊ ከምፓስ ተማሪዎች የግቢው በር ዝግ በመሆኑ መቸገራቸውን ለየኔቲዩብ አቤቱታቸውን ገልፀዋል።

ነገሩ እንዲህ ነው ዛሬ በዩንቨርስቲው የምግብ አገልግሎት እንዳልነበረ እንዲሁም የግቢው መግቢያ እና መውጪያ በሮች ዝግ መሆናቸውን በተጨማሪ ግቢ ውስጥ ያሉ አገልግሎት የሚሰጡ የATM ማሽኖች ዝግ መሆናቸው የተማሪዎች ብር አውጥተው ለመመገብም እንደተቸገሩ ገልፀዋል ለ የኔቲዩብ።

ሆኖም ግን ከ11 ሰዐት ብኃል በሮች ተከፍተው ተማሪዎች መግባት መውጣት ችለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ታስረው የነበሩ 1 ሺህ 443 ስደተኞችን ከሀገሪቱ ሊመልስ መሆኑን በፉስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡ ለዚሁ ተግባር አውሮፓ ኅብረት የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የደቡብ ሱዳን መሪ ሳልቫ ኪር እና የተቀዋሚዎች መሪ ሬክ ማቻር የአንድነት ሽግግር መንግሥት ለማቋቋም ዛሬ መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በሚያለያዩዋቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ግን አሁንም ከስምምነት አልደረሱም፡፡ ቀደም ሲል የኅዳሩን ቀነ ገደብ በ100 ቀናት አራዝመውት ነበር፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ገርጂ ኮንዶሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ አሰሪዋን በመግደል እና በስርቆት ወንጀል የተከሰሰችው የቤት ሰራተኛ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ኹለት ክስ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣች፡፡

Via:- አዲስ ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa
ለ90 ሺህ ኢትዮጵያዊያን እና ስደተኞች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለመፍጠር እንዲሁም ለ20 ሺህ ስደተኞች እና ኢትዮጵያዊያን ጥራት እና ተቀባይነት ያለው የክህሎት ስልጠና ለመስጠት መታቀዱን የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

Via:- ፋና ብሮድካስቲንግ
@Yenetube @Fikerassefa