YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
እስካሁን ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን በጂቡቲ ለማቋቋም የተደረሰ ስምምነት እንደሌለ ተገለጸ።አምባሳደሩ እንዳሉት የኢትዮጵያን የባሕር ኃይል ጂቡቲ ውስጥ ማቋቋምን በሚመለከት ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን ያመላከቱ ሲሆን፤ ነገር ግን "እስከ አሁን የተደረሰ ህጋዊ ስምምነት የለም" ብለዋል።

ተጨማሪ👇👇👇

https://telegra.ph/NAVY-12-04-2
ቅድም ባልነው መሰረት ዛሬ ግንፍሌ አከባቢ በሚገኘው በአብን ዋና ቢሮ ተገኝተን የቀረፅነውን መግለጫ አቀናብረን በቻናላችን ላይ ለቀናል።

ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ አድርጉን!!

https://www.youtube.com/watch?v=AsZ6ColQklU
የብልጽግና ፓርቲ የዕውቅና ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ!

በቅርቡ ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግ እህትና አጋር ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የውህደቱ አካል ለሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት ተሰጥቶ የነበረውን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሰርዝና በአዋጅ አንቀጽ 91(4)ሀ መሰረት በውህደት የተመሰረተውን የብልጽግና ፓርቲን እንዲመዘገብና ዕውቅና እንዲያገኝ የሚያስፈልጉ ሰነዶች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስረክቧል፡፡

Via EPRDF Official
@YeneTube @FikerAssefa
በመቐለ ከተማ ዛሬ በተጀመረው 'አገር ዓቀፍ መድረክ' የፖለቲካ ፓርቲዎችና ግለሰቦች እንዳይሳተፉ "ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ባላቸው ሀይሎች" ጫና ተደርጎባቸዋል ሲሉ የህወሃት ሊቀመንበር ደ/ጺዮን ገ/ሚካዔል ወቀሱ።"ሕገ መንግስትና ህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም ስርዓትን የማዳን አገር ዓቀፍ መድረክ" በሚል መሪ ሀሳብ በተጀመረው ጉባዔ ንግግር ያሰሙት ሊቀመንበሩ "ይህ በህገመንግስቱ የተጎናፀፈውን መብት የረገጠ አፋኝ ተግባር በመሆኑ ስርዓት መያዝ አለበት" ብለዋል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀረቡ። የኤርትራ ማስታወቂያ ምኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው እንደገለጹት አምባሳደር ሬድዋን ጨምሮ 21 አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንቱ አቅርበዋል። ሬድዋን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ባለፈው ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤርትራ ባደረጓቸው ጉብኝቶች አምባሳደሩ ሲያጅቧቸው ታይቷል። ሬድዋን ሑሴን ወደ አስመራ ከመዛወራቸው በፊት በአየርላንድ
የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሰርተዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ሉካንዳ ቤቶች በግብር ምክንያት ባደረጉት አድማ ወደ ቄራ የሚልኳቸውን የእርድ በሬዎች ዛሬ አላኩም።

ዓመታዊ ግብራችን አላግባብ ተተምኗል በሚል ምክንያት አብዛኞቹ የክርስቲያን ስጋ ቤቶች አድማ በማድረግ ወደ ቄራዎች ድርጅት ለእርድ የሚልኳቸውን በሬዎችን እንዳላኩ ከቄራዎች ድርጅት ሰራተኞች አረጋግጫለው።
በዚህ በገና ፆም ወቅት ቢያንስ በቀን 400 በሬ ለእርድ ወደ ቄራ የሚመጣ ሲሆን ዛሬ በአድማው ምክንያት ወደ ቄራ ለእርድ የመጡት በሬዎች ከ50 አይበልጡም።

እስከ ማምሻው ድረስ የሚቆዮት የቄራ ሰራተኞች ዛሬ እምብዛም ስራ ስሌለ ወደ ቤታቸው በግዜ ሄደዋል።

Via:-Tesfay getnet
@Yenetube @Fikerassefa
Breaking....
ቦርዱ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን የመጨረሻ ውጤት ይፋ አደረገ!!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን የመጨረሻ ውጤት ይፋ አደረገ።
ባለፈው ህዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም የህዝበ ውሳኔው የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ይፋ የተደረገ ሲሆን፥ በዛሬው እለት ደግሞ የመጨረሻ ውጤት ይፋ አድርጓል።

በዚህም 97 ነጥብ 7 በመቶ የሆኑት መራጮች ሲዳማ በክልልነት እንዲደራጅ ድምጽ ሲሰጡ፥ 1 ነጥብ 47 በመቶዎቹ ሲዳማ በደቡብ ክልል ለመቆየት ድምጽ ሰጥተዋል።

ቦርዱ የምርጫ ጣቢያዎችን ውጤት በመገምገም፥ የድምር እንዲሁም ሌሎች የምርጫ ውጤት አለመጣጣም ያለባቸውን ጣቢያዎች በማየት ውሳኔ ማሳለፉንም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በመሆኑም በአጠቃላይ ድምጽ ከተሰጠባቸው 1 ሺህ 692 ምርጫ ጣቢያዎች እና ተጨማሪ 169 ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች መካከል በ233ቱ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የድምርና የውጤት አለመጣጣም ችግር ማግኘቱን ገልጿል።
ችግሮቹ አስፈጻሚዎች ቁጥር በሚደምሩበት ወቅት የተገኘ የቁጥር ድምር ችግር እና ድምጽ የሰጡ መራጮች፥ ከተመዘገቡት አንጻር ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
እንዲህ አይነት ችግሮች በሚያጋጥሙበት ወቅት የችግሩን ምንጭ ለማወቅ የድጋሚ ቆጠራ መደረግ ቢኖበትም፥ ቦርዱ በአማራጭ ውጤቶቹ መካከል ያለው የውጤት ልዩነት ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻር በውጤቱ ላይ ለውጥ ስለማያመጣና በሂደቱ ተአማኒነት ላይ ጥያቄ ስለማያስነሳ፥ የድጋሚ ቆጠራ በማዘዝ ውጤት ማሳወቂያ ጊዜው መጓተት የለበትም በሚል የድጋሚ ቆጠራ ማካሄድን አስፈላጊ ሆኖ እንዳለገኘውም ጠቅሷል።
በዚህም መሰረት ዓለም አቀፍ የምርጫ ውጤት አስተዳደር ልምድን፣ የምርጫው አይነት ህዝበ ውሳኔ መሆኑ እና በተወሰኑ ጣቢያዎች የተፈጠረው አለመጣጣም በአጠቃላይ የድምጽ ሰጭዎች ድምጽ ላይ የሚያመጣውን ተጽእኖ ውስንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቦርዱ ችግር የተገኘባቸውን ጣቢያዎች ሁኔታ በማየት ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ከተመዘገበው መራጭ በላይ ድምጽ ተሰጥቶ የተገኘባቸው የ127 ምርጫ ጣቢያዎች ውጤት እንዲሰረዝ እና በቆጠራ እና በድምር ስሌት ስህተት ከተገኘባቸው ጣቢያዎች መካከል የታየው ልዩነት 10 ድምጽ እና ከዚያ በታች የሆኑ ልዩነቶች ዋጋ እንዳላቸው ድምጽ እንዲቆጠሩ ወስኗል።

ከዚህ ባለፈም ከ10 ድምጽ በላይ የድምር ልዩነት የተገኘባቸው ጣቢያዎች ውጤት እንዳይካተት የወሰነ ሲሆን፥ በዚህ መሰረት 37 ምርጫ ጣቢያዎች በከፍተኛ የድምርና የስሌት ስህተት የተነሳ ውጤታቸው ተሰርዟል።

በአጠቃላይ 164 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያሉ ውጤቶች በተጠቀሱት ምክንያቶች የተነሳ እንዲሰረዙ የተደረገ ሲሆን፥ 71 የምርጫ ጣቢያዎች ግን የድምር ልዩነቱ ከ10 ድምጽ በታች በመሆኑ ስህተት ቢኖራቸውም ውጤታቸው ዋጋ ኖሮት እንዲቀጥል ተደርጓል።


ቦርዱ መሰል ችግሮች በሃገር አቀፍ ምርጫ ላይ ቢፈጠሩ ሊኖራቸው ከሚችለው ተፅዕኖ አንጻር ችግሮቹ የተፈጠሩበትን ምክንያት የሚያጣራ የቴክኒክ ቡድን አቋቁሟል፡፡

የቴክኒክ ቡድኑን ውጤት መሰረት አድርጎም ለቀጣዩ ምርጫ አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ስራዎች፣ የአስፈጻሚዎች ስልጠና እና የምርጫ ሂደቱን የማሻሻል ስራዎችን እንደሚሰራም ገልጿል።

በመጨረሻው ውጤት መሰረትም የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር 2 ሚሊየን 304 ሺህ 577 ሲሆኑ ድምጽ የሰጡ መራጮች 2 ሚሊየን 279 ሺህ 22 ናቸው።

ከዚህ ውስጥ 248 ሺህ 97 መሰረዙንም ቦርዱ አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ሃጅ ዑመር እጅግ ተጽእኖ ፈጣሪ ፭ መቶ ሙስሊሞች መካከል አንዱ ሆኑ
.
በየአመቱ የሚወጣው ‘ዘ ሙስሊም 500’ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስን በፈረንጆቹ 2019 ዓመት የአለማችን እጅግ ተጽእኖ ፈጣሪ ፭ መቶ ሙስሊሞች መካከል አንዱ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

መቀመጫውን ኦማን፣ ጆርዳን ያደርገው መንግሥታዊ ያልሆነ እና ከሮያል ኢስላሚክ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ጋር የተቆራኘው ‘ዘ ሙስሊም 500’ በየአመቱ በፖለቲካ፣ በእስላማዊ ምርምር፣ በቢዝነስ፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች አስራ ሦስት በሚደርሱ ዘርፎች ተጽእኖ ፈጥረዋል ያላቸውን ፭ መቶ ሙስሊሞች ከዓለም ዙሪያ ይመርጣሉ፡፡

በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ይነሱ የነበሩ የመብት ጥያቄዎችን ለመፍታት በተደረገው ጥረት እና በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች የመንፈሳዊ መሪነት ሚና በመጫወት በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ አድናቆትን ካተረፉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር በተጨማሪ የሳውዲ ዜግነት ያላቸው ባለሀብቱ ሼክ ሙሐመድ ሑሴን አል-አሙዲንም በዚህ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል፡፡

ባለፈው የትምህርት ዓመት የአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ የክብር ዶክትሬት በመስጠት ላደረጉት ሀገራዊ አስተዋጽኦ እውቅና መስጠቱ ይታወቃል፡፡

Via:- themuslim500.com
@Yenetube @Fikerassefa
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮሪያን በጦር ኃይል ለመደብደብ መዛታቸዉን የፒዮንግዮንግ ጦር አዛዦች አጥብቀዉ አወገዙት።ፕሬዝደንት ትራምፕ፣ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ጉባኤ ትናንት ሲጀመር ሰሜን ኮሪያ ሮኬት ማወንጨፏን ከቀጠለች ዋሽግተን የኃይል እርምጃ ትወስዳለች ብለዉ ነበር።የሰሜን ኮሪያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፓክ ጆንግ ኾን የትራምን ዛቻ «ተስፋ አስቆራጭ» ብለዉታል።ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ አክለዉ እንዳሉት ዋሽግተን እንደ ፎከረችዉ ሰሜን ኮሪያን ካጠቃች ፒዮንግዮንግ ፈጣንና ቆንጣጭ አፀፋ ለመዉሰድ ዝግጁ ነች።የትራምፕ መግለጫ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡንንም ማስቆጣቱን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ አልሸሸጉም።ትራምፕና ኪም ከዓመት ከመንፈቅ በፊት እንደወዳጅ ሲጨባበጡ ፈንጥቆ የነበረዉ ተስፋ ከሰሞናዊ ከበርቻቻ ባለፍ ለሰላም የፈየደዉ ነገር የለም።
@Yenetube @FikerAssefa
የስፓርት ቻናላችን ዛሬ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶትነኃም የሚያካሄዱትን ፍልሚያ በቀጥታ ያስተላልፋል።

ተቀላቀሉት @Yenesport @Yenesport
@Yenesport @Yenesport
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛውን ካምፓስ አዲስ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ገንብቶ ማጠናቀቁን ይፋ አደረገ።

በቡሬና በዋናው ግቢ ከ12ዓመት በላይ የመማር ማስተማር ሂደቱን በስኬት ሲያስጉዘው የነበረው የ2ኛው ትውልድ አካል ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2012ዓ/ም 3ኛውን ግቢ (ጤና ካምፓስ) አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት አድሮጓል። በዚህ አመትም የውሃ ዝርጋታውና የቤተሙከራው ስራ እንደተጠናቀቀ ለጤና ሳይንስ ኮሌጅን እንደሚያስረክብ የቢዝነስና ልማት ምክ/ፕሬዚደንት ዶ/ር ሳይህአለም ካሳው ተናግረዋል።

ጤና ኮሌጅ ከደብረማርቆስ ወደ ባህርዳር መውጫ በኩል በ500ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን የተማሪዎች ካፍቴሪያ፣ ቤተመጽሃፍት፣ ስድስት የተማሪዎች ምኝታ ቤት እያንዳንዱ 80 ምኝታ ክፍል ያላቸው)፣ ቤተሙከራ ባለ ሰባተኛ ፎቅ የአስተዳደር ህንጻ ግንባታዎችን አጠናቋል።የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና ሰራተኞች አዲሱን ጤና ኮሌጅ በጎበኙበት ወቅት በሰጡት አስተያየት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። ለቀሪ ስራዎችም ሃላፊነት ወስደው ለመስራት ተነሳሽነታቸውን ገልጸዋል።ጤና ኮሌጁ የመማር ማስተማር ስራ ጎን ለጎን በሃገራችን ደረጃውን የጠበቀ ከ800በላይ የአልጋ ክፍል ያለው የሪፈራልና ማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ምንጭ:የዩንቨርስቲው ህ/ግ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በኒው አፍሪካን መፅሔት ከ100 አፍሪካውያን ተፅእኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ ሆነው መመረጣቸውን ታውቋል። በዚህም አየርመንገዱ የተሰማውን ልባዊ ደስታ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም የሰብዓዊ መብት ቀን ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ይከበራል።

ኮሚሽኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል በአገር ውስጥ በሲቪል ማህበራት ተደራጅተው ከሚሰሩ ድርጀቶች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገልጿል።‹‹ወጣትነት ለሰላም እና ለሰብዓዊ መብት መከበር›› በሚል መሪ ሐሳብ ለአምስት ቀናት የሚከበረውን የሰብዓዊ መብት ቀንን አስመልክቶ ኮሚሽኑ ከሲቪል ማህበራት ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።በበዓሉ ላይ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትን ለማስከበር ያሉ ተግዳሮቶች፣ ዕድሎችና ስኬቶች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ የመወያያ ዕሁፎች እንደሚቀርቡ በመግለጫው ተጠቅሷል።የመንግስት አካላት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ወጣቶችና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሁም የሲቪል ማህበራት ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ የስለላ እና ደኅንነት ድርጅት በሚል የተቋቋመ ሕገ ወጥ የስለላ ቡድን ነበር ተባለ!

ባሳለፍነው ሳምንት ኅዳር 12/ 2012 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከ ሰኔ 15/2011 ጥቃት ጋር ተያይዞ ከተከሰሱት 13 ግለሰቦች ውስጥ ዘጠኝ ተከሳሾች ከክልሉ መደበኛ የፀጥታ መዋቅር ውጪ የአማራ የስለላ እና ደኅንነት ድርጅት (አሳድ) በሚል ቡድን በማቋቋማቸው ክስ ተመስርቶባቸዋል።የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው፣ በዚህ መዋቅር ጠላት ተብለው የተፈረጁ ኀይሎች በተለይም ህወሐት እና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲን ለመሰለል እና በአስፈላጊው ወቅት መንግሥትን በማዳከም የኀይል እርምጃ ለመውሰድ የስለላ እና መረጃ ደኅንነት ሥልጠና ወስደው ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎችን ያቀፈ እንደነበር ያስረዳል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
"የትራፊክ አደጋ እየገደለን ነው፣ ቀስ ብለን እናሽከርክር፣ #እንደርሳለን"
ባንክ የዘረፉት ተከሳሾች የ12 እና 13 አመት ፅኑ እስራት ተወሰነባቸው።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ሪከርድ ያልቀረበበትና የቤተስብ አስተዳዳሪ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ በማህበራዊ አገልግሎት የሰጠ መሆኑን በቅጣት ማቅለያ በመያዝ 1ኛ ተከሳሽ በ13 ዓመት ከ6 ወር 2ኛ ተከሳሽ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በማለት ወስኗል፡፡

ዝርዝሩ👇👇👇


https://telegra.ph/BankRobing-12-05
ግብረሰዶም የፈጸመዉ ወጣት በ15 አመት ፅኑ በእስራት ተቀጣ ፡፡

ተከሳሽ ክብሮም ገ/ኪዳን የተባለ የ22 ዓመት ታዳጊ ወጣት ለአካለ መጠን ባልደረሰ ልጅ ላይ የግብረሰዶም ወንጀል በመፈጸሙ በዐቃቤ ህግ ተከሶ ክርክር ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ተከሰሹ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 631/1/ለ/ ሥር የተደነገገዉን ተላልፎ በታዳጊዉ ላይ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽሟል፡፡ ወጣቱ ግንቦት 21 ቀን 2011ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 12፡30 ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታዉ ሎቄ ምስራቅ ተብሎ ከሚጠራዉ ስፍራ የ 9 ዓመት ህፃን የሆነዉን የግል ተበዳይ ቤተሰቦቹ ዳቦ እንዲገዛ ሲልኩት ተከሳሹ ህጻኑን ዳቦ ቤት ዉስጥ አስገብቶ በመድፈር ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰበት የየካ ክፍለ ከተማ ዐቃቤ ህግ በማስረጃ አረጋግጦ ክሱን መስርቶበታል፡፡ተከሳሹ ፈፅሞታል ተብሎ የተከሰሰበትን ዝርዝር ምክንያት በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ረዳት ኢንስፔክተር እቴነሽ ወዳጆ ተነቦለት የግል ተበዳዩን ህጻን በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ዳቦ ሊገዛ በመጣበት ጊዜና ቦታ ወሲባዊ ጥቃት ፈጽሜበታለሁ ፡፡ ጥፋተኛ ነኝ በፈጸምኩትም ወንጀል ጸጸት ተሰምቶኛል በማለት የእምነት ክህደት ቃሉን ለመርማሪ ፖሊስ ሰጥቷል፡፡ጉዳዩን የተከታተለዉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎትም ተከሳሽ ወንጀሉን ያመነ በመሆኑና ተጨማሪ ማስረጃዎችን ተመልክቶ የጥፋተኝነት ብይንም ሰጥቷል፡፡በዚህም መሰረት ህዳር 17 ቀን 2012 ዓ.ም ባስቻለዉ ችሎት ተከሳሹን በ15ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

Via Attorney General
@YeneTube @FikerAssefa