YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዛሬ ከመሸ የየኔቲዩብ የዩቲዩብ ቻናላችን ላይ የለቀቅነው ቪዲዮ ይመልከቱ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን አስቂኝ ጥያቄዎች ጠይቀናቸው ግራ አጋብተናቸዋል

https://www.youtube.com/watch?v=2JYkxikyNMw
የጅማ ዩንቨርስቲ

ምዝገባ አከናዉነዉ ወደ ትምህርት እንዳይመለሱ በማህበራዊ ሚዲያ የማስፈራርያ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ሙከራ የሚያደርጉ አካላት መኖራቸዉ ተደርሶበታል

ዛሬ አርብ ህዳር 12/2012 ዓ.ም. በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ካምፓሶች የዩኒቨርሲቲዉ ሴኔት ባስተላለፈዉ ዉሳኔ መሰረት ምዝገባ ተካሂዷል፡፡ ምዝገባዉ ነገ ቅዳሜ ህዳር 13/2012 እና እሁድ ህዳር 14/2012 ዓ.ም. ቀጥሎ የሚከናወን ሲሆን፣ በታቀደዉ መሰረት ሰኞ ህዳር 15/2012 ዓ.ም. የመማር-ማስተማር ሂደቱ ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ ይቀጥላል፡፡

ይሁን እንጂ ተማሪዎች እንዳይረጋጉና ምዝገባ አከናዉነዉ ወደ ትምህርት እንዳይመለሱ በማህበራዊ ሚዲያ የማስፈራርያ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ሙከራ የሚያደርጉ አካላት መኖራቸዉ ተደርሶበታል፡፡ ይህን የሚያደርጉ አካላት ላይ ዩኒቨርሲቲዉ ጥብቅ ክትትል እያደረገ ሲሆን በግቢ ዉስጥ የተጠናከረ የጸጥታና ህግ-ማስከበር ስራ በተጠናከረ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

በመሆኑም፣ ዉድ ተማሪዎቻችን አስተማማኝ የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን አዉቃችሁ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሳሳች መልእክቶች አብዛኛዉን ትምህርት ፈላጊ ተማሪዎችን ለማደናገር የሚደረጉ ሙከራዎች መሆናቸዉን በመገንዘብ ዩኒቨርሲቲዉ ቀደም ብሎ ባወጣዉ ማስታወቂያ መሰረት ተመዝግባችሁ ትምህርታችሁን እንድትቀጥሉ እናሳስባለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ሰላምና መረጋገት ሰፍኖ ትምህርት እንዲጀመር ጉልህ ሚና እያበረከታችሁ ለምትገኙ የግቢ ዉስጥና ዉጭ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ
@Yenetube @Fikerassefa
ደባርቅ ዩንቨርስቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ስለሆኑት ፕሮፌሰር ተሰማ ዘውዱ ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ ስለተሰራጨው ወሬ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

👇👇👇👇👇👇👇

https://telegra.ph/Debark-11-22
Forwarded from YeneTube
ለወንዶች!!!!
የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን
RJ FASHION
ለውድ ደንበኞቹ ጥራት ያላቸውን የወንዶች ብራንድ እና አዲስ Style
➡️ሹራቦች
➡️ጃኬቶች
➡️ቱታዎች
➡️ጫማዎችን
በቅናሽ ዋጋ አቅርበናል:
ሾው ሩም አድራሻ:
ገርጂ መብራት ሀይል (ዊዝደም ህንፃ ፊት ለፊት)
ስልክ:-+251900628132
:-011-6296465
የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ያለውን ሊነክ በመጫን ያገኙናል
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
🤜🏾መኪናዎትን ከሌባ ለመጠበቅ የሚረዳ 🚔🚔🚔 ኣዲስ ምርት ኣስመጥተናል🚔🚔🚔
🤜🏾•ሰሞኑን እየተበራከተ የመጣው የመኪናዎች ስርቆት ሀሳብ ሆኖቦታል እንግዲያውስ ሀሳብ አይግባዎ አስተማማኝ መሪ መቆለፊያ አምጥተንሎታል
🤜🏾የመኪናዎን መሪ ጥርቅም ኣርጎ በመቆለፍ ቁልፍ የያዝን ሌባ ጨምሮ መሪውን እንዳያዞረው በማድርግ መኪናውን ክስርቆት ይጠብቀዋል::
+251912894364

• Made of hardened iron material to resist cutting and durable in using.
• Comes with anti-theft security lock and 2 keys.
• Can be adjustable to fit for most steering wheels.
• Highly visible deterrent, can frighten the thieves to avoid being stolen.
• Weight 2kg
ለበለጠ መረጃ እና ለተለያዩ አዳዲስ እቃዎች ቻናላቸንን ጆይን ያድርጉ
@ZenachBrands
ከጎንደር ዩንቨርስቲ የተላለፈ ማሳሰቢያ!

ውድ ተማሪዎቻችን ፣ በዚህ ሳምንት በተወሰኑ ግቢዎቻችን እየተቆራረጠ ሲሰጥ የቆየው መማር ማስተማር ዛሬ በሁሉም ኮሌጆች ተጀምሯል።ነገር ግን የተወሰኑ ተማሪዎቻችን ከግቢ መውጣታቸው ይታወቃል፡፡ስለሆነም በዚህ ሰዓት መማር ማስተማሩን የሚያስተጓጉልና ስጋት የሌለ በመሆኑ ከግቢ የወጣችሁ ተማሪዎቻችን ከመጭው ሰኞ ህዳር 15/2012ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ገበታችሁ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ
@YeneTube @FikerAssefa
የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ እስከ 20 ብር ሊቀንስ ይችላል ተባለ!

ለረጅም አመታት ቀረጥ ሲጣልበት ከነበረው የቅንጦት እቃዎች ዝርዝር በመውጣት ከመድሃኒት ጤና አገልግሎት ዘርፍ እንዲካተት የጤና ሚኒስቴር በወሰነው መሰረት የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ወደተግባር ሲገባ በአንድ እጅግ ምርት ላይ እስከ ግማሽ ድረስ የዋጋ ቅናሽ ሊያሳይ እንደሚችል ተገልጿል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@YeneTube @FikerAssefa
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ማሳወቂያ ጋዜጣዊ መግለጫ በሃዋሳ ሃይሌ ሪዞርት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰአት ይሰጣል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የአየር ብክለትን የሚለኩ መሳሪያዎች ተተከሉ::በዚህም የተለያዩ አካባቢዎች በፒያሳ፣ በመርካቶ፣ በቆሼ አካባቢ፣ እና በሜክሲኮ የአየር ብክለትን የሚለኩና ለሚከታተለው አካል የሚያሳውቁ መሳሪያዎች ተተክለዋል።

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
ጉግል ምርቶቹ ላይ ስህተት ላገኘ ሰው 1.5 ሚሊዮን ዶላር ሊከፍል ነው!

ጉግል በአንድሮይድ ስልኮቹ ላይ ስህተት ለሚያገኝ ሰው የሚከፍለውን ገንዘብ ከ200,000 ዶላር ወደ 1.5 ሚሊዮን ዶላር አሳደገ።ጉግል በአንድሮይድ ምርቶቹ ላይ በተገጠመው ካሜራ ላይ ከደህንነት ጥበቃ ጋር የተያያዘ ክፍተት ላገኘ ሰው ገንዘቡን እንደሚያበረክት አስታውቋል። ድርጅቱ እንደ ጎርጎሮሳውኑ አቆጣጠር ከ2015 ወዲህ ለደህንነት ጥበቃ ተመራማሪዎች አራት ሚሊየን ዶላር መክፈሉንም ይፋ አድርጓል።

አፕል፣ በዝፊድ፣ ፌስቡክና ሳምሰንግም በምርቶቻቸው ላይ ከደህንት ጥበቃ ጋር የተያያዘ ክፍተት ለሚጠቁም ሰው ገንዘብ ይሰጣሉ። ክፍተቶች ከተጠቆሙ በኋላ ምርቶቹን እንደሚያስተካክሉም ድርጅቶቹ ይናገራሉ።'ቲታም ኤም' የተባለው መሣሪያ ስልክ የሚከፈትበት መረጃ የሚከማችበትና የስልኩን ደህንነት የሚጠብቅም ነው። አንድ ተመራማሪ የዚህን መሣሪያ ክፍተት ማሳየት ከቻለ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ያገኛል ማለት ነው።

ምንጭ:BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በወር ለ90 ሰዎች የስነ ልቦና እና የሚዲካል ነፃ ህክምና የሚሰጥ ክሊኒክ ተከፈተ።

በአሜሪካ ለረጅም አመት የኖሩት ኢትዮጰያዊው ፓስተር ዮሴፍ የቤተሰባቸውን ቤት ወደ ክልኒክ በመቀየር ቀበና አካባቢ የሚገኝ "ራፋ" የተባለ ክሊኒክ ከፍተዋል። ክሊኑኩ በየወሩ አቅም ለሌላቸውና ከሚኖሩበት ወረዳ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ለሚችሉ 90 ሰዎች የነፃ የስነ ልቦና እና የሚዲካል ነፃ ህክምና በየወሩ በተገጓዳኝነት ለአንድ አመት ያክል ይሰጣል ሲሉ ፓስተር ዮሴፍ ነግረውኛል።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
CSO-observer-Preliminary Report -sidama REFRENDUM-22.pdf
143.1 KB
ሕዳር 10 ቀን 2012 ዓም የተካሔደውን የሲዳማ ህዘብ ወሳኔ በተመለከተ ከየኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ለምርጫ የተሰጠ መግለጫ

@Yenetube @FikerAssefa
የሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶች ጥምረት የሲዳማ ረፈረንደምን በተመለከተ ካወጣሁ መግለጫ ላይ #ጠንካራ_ጎኖች እና #የተስተዋሉ_ክፍተቶች ከላይ ባላው ፎቶ ላይ ተገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
በተሽከርካሪ አደጋ ስድስት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ህይወት ጠፋ!

በደቡብ ክልል ከንባታ ጠምባሮ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ወረዳ ትናንት በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የስድስት ሰዎችን ህይወት ማጥፋቱን ፖሊስ አስታወቀ።የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ማቲዎስ አደጎ እንደገለጹት፥ አደጋው የየደረሰው ከማለዳው 12 ሰዓት አከባቢ በሀደሮ ጡንጦ ወረዳ በተለምዶ ሌሾ ማዞሪያ ነው።ኤፍኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ ከዶዮገና ወደ አረካ በመጓዝ ላይ እያለ ነፍሰ ጡር ይዞ ወደ ጤና ጣቢያ በመጓዝ ላይ ከነበረ ባለ ሶስት እግር ባጃጅ ጋር በመጋጨቱ አደጋው ሊደርስ ችሏል።በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ገልጸው፤ አስክሬናቸው ቤተሰብ መረከቡን አስታውቀዋል።

አንድ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባት የቤተሰቡ አባል በዱቦ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑንም ጠቁመዋል።የኤፍኤስ አር አሽከርካሪ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝም ኮማንደር ማቲዎስ አስረድተዋል፡፡የአደጋው መንስኤ ለጊዜው ባይታወቅም ሲጥል የነበረው ዝናብ ጋር ተያይዞ በመጋረድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል የፖሊስ አዛዡ ገምተዋል።አሁን ላይ ወቅቱ ያልጠበቀ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን በመቆጣጣር ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አዛዡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫ ቦርድ የሲዳማን ሪፈረንደም አስመልክቶ የመጀመሪያው መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።
በቀጥታ በEtv እየተላለፈ ይገኛል።
#Breaking

"ሲዳማ ክልል ሆኖ ለመደራጀት የሚያስችለውን ድምፅ አግኝቷል" ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

በሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጤት መሰረት ሲዳማ ክልል ሆኖ ለመደራጀት የሚያስችለውን ድምፅ ማግኘቱን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን ለማስፈፀም ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የምርጫ ካርዶች እና ቁሳቁሶች ተመድበዋል ሂደቱም ሙሉ ለሙሉ ሰላማዊ እንደነበር ምርጫ ቦርዱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጠት ሂደት ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንደተከናወነ ይታወቃል፡፡

በድምጽ መስጫው ቀን ማምሻ ላይ ቆጠራው ተጠናቆ የህዝበ ውሳኔው ውጤት በምርጫ ጣቢያዎች ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡

Via:-EBC

@Yenetube @Fikerassefa
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ በፐርሰንት ሲሰላ! !

98.51% ለክልልነት ጥያቄው #የድጋፍ ድምፅ የሰጠ እንዲሁም 1.48% ለክልልነት ጥያቄው #የተቃውሞ ድምፅ የሰጠ መሆኑ ታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
ዛሬ ከመሸ የየኔቲዩብ የዩቲዩብ ቻናላችን ላይ የለቀቅነው ቪዲዮ ይመልከቱ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን አስቂኝ ጥያቄዎች ጠይቀናቸው ግራ አጋብተናቸዋል

https://www.youtube.com/watch?v=2JYkxikyNMw
Forwarded from YeneTube
ለወንዶች!!!!
የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን
RJ FASHION
ለውድ ደንበኞቹ ጥራት ያላቸውን የወንዶች ብራንድ እና አዲስ Style
➡️ሹራቦች
➡️ጃኬቶች
➡️ቱታዎች
➡️ጫማዎችን
በቅናሽ ዋጋ አቅርበናል:
ሾው ሩም አድራሻ:
ገርጂ መብራት ሀይል (ዊዝደም ህንፃ ፊት ለፊት)
ስልክ:-+251900628132
:-011-6296465
የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ያለውን ሊነክ በመጫን ያገኙናል
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA