YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ለዕሁድ ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ለአስተዳደሩ ስለ ሰልፉ ብናሳውቅም፣ እስካሁን ምላሽ አልተሰጠንም- ብሏል የባላደራው ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ፡፡ ሆኖም በሕጉ መሠረት፣ ዝምታው ዕውቅና እንደመስጠት ስለሚቆጠር ፖሊስ ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ሰልፉ ለሀገራዊ ዲሞክራሲ ነው፤ እናም ሕዝቡ ለሰልፉ ይውጣ ሲል ጥሪ አድርጓል፡፡ ሰልፉ ከተደናቀፈ ባላደራው ወደሚቀጥለው የትግል ምዕራፍ ይሄዳል፡፡ መግለጫው በተሰጠበት ግቢ አቅራቢያ ወጣቶች ባላደራው ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

ምንጭ: ዋዜማ
@YensTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፓሊስ የደስታ መግለጫ ለጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ።

@YeneTube @Fikerassefa
በልምምድ ላይ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።

አውሮፕላኑ ዛሬ ጠዋት ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአየር ሃይል ካምፕ በመነሳት በልምምድ ላይ እያለ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ኡኬ ደንካካ በተሰኘ ቦታ መከስከሱን የምስራቅ ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበራ ያሚ ለዶቸ ቨለ አረጋግጠዋል።

በአደጋው የሁለት አብራሪዎች ህይወት ማለፉንም አቶ አበራ ገልጸዋል። ከሟቾች መካከል የአንደኛው አስክሬን አውሮፕላኑ ከተከሰከሰበት ከ100 ሜትር በላይ ርቆ መገኘቱንም ተናግረዋል። የአደጋው መንስኤ ገና በመጣራት ላይ መሆኑንም ነው አቶ አበራ የተናገሩት።

« በደረሰን መረጃ መሰረት የተከሰከሰው አውሮፕላን የጦር መለማመጃ አውሮፕላን ነው። ሁለት ሰዎች በልምምድ ላይ እንደነበሩም ነው ያጣራነው። ከሁለቱ ሰዎች የአንደኛው አስክሬን ሲገኝ የሌላኛው ከአውሮፕላኑ ጋር ቃጠሎ ደርሶበታል። አደጋው የደረሰው ከምሳ ሰአት በፊት ሲሆን እስካሁን የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ነው የምናውቀው።»

የጦር አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት በዚሁ በአደአ ወረዳ፣ከጥቂት አመታት በፊት በጦር ሂሊኮፕተር ላይ በደረሰ ተመሳሳይ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ይታወሳል።የ157 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የመጋቢት 2011ዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ የደረሰውም በዚሁ አካባቢ ነበር።

Via:- DW
@YeneTube @Fikeeassefa
ሰኔ መጀመሪያ አካባቢ የተጀመሩት የአልማ ትምህርት ቤቶች ነገ ይመረቃሉ።

የአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር (አልማ) የክልሉን የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል እንቅስቃሴ አካል የሆኑ ሦስት ትምህርት ቤቶች ነገ ይመረቃሉ።የአልማ ስትራተጅያዊ ዕቅድ የሙከራ ትግበራ ፕሮጀክት ለቀጣይ አፈፃፀም አቅም በሚፈጥር መንገድ መጠናቀቁንም ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልጸዋል፡፡ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መላኩ ፋንታ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በምሥራቅ በለሳ ጉሀላ ከተማ ሰኔ 04/2011 ዓ.ም ተጀምረው ነገ የሚመረቁት ሦስት የትምህርት ቤት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ገንዘብ መጠናቀቃቸው ለቀጣይ ዕቅድ አፈፃፀም ትምህርት ተቀስሞባቸዋል፡፡

ነገ ተመርቀው አገልግሎት የሚጀምሩት ትምህርት ቤቶች መንግሥት፣ አልማና ሕዝቡ በቀጣይ ሦስት ዓመታት የክልሉን የትምህርት ቤቶች ደረጃ ከሚገኝበት 16 በመቶ ወደ 50 በመቶ ለማሳደግ የታለመው ስትራቴጂያዊ የለውጥ ዕቅድ አካል መሆኑን አቶ መላኩ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አልማ/አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢዜማ መሪ ፕ/ር ብርሓኑ ነጋ ዶ/ር አብይ አህመድ የኖቤል ሽልማት በመሸለማቸው ያስተላለፉት የደስታ መልእክት።

@YeneTube @Fikerassefa
ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ የቤተሰብ ጨዋታ አዘጋጅ በመሆን ነፃነት ወርቅነህን እንደሚተካ ለማወቅ ችለናል።

#YeneTube
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከፕሬዚዳንት ሲሲ ጋር በስልክ ተወያዩ!

መሪዎቹ በውይይታቸው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተደረገ ባለው ድርድር ላይ አተኩረው መነጋራቸው ነው የተመለከተው።
በዚህም ወቅት ግድቡን በተመለከተ የሚደረገውን ድርድር መቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ተሸላ በመሆናቸው ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ ኤል ሲሲ ላስተላለፉት የደስታ መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅረበዋል። ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ዙሪያ ያነሳችው አቋም የኢትዮጵያን ቀይ መስመር የሚያልፍ በመሆኑ ከመግባባት ላይ መድረስ እየተቻለ አለመሆኑን ኢትዮጵያ መግለጿ ይታወቃል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከአዲስ አበባ ወደ ለገዳዲ ሰንዳፋ የሚወስደው መንገድ ተዘግቷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ይዤ እመለሳለሁ
@YeneTube @Fikerassefa
በቀጣዩ ዓመት የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ካፒቴኖች ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊያን ይሆናሉ
ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ኢትዮ- ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያዊያን ካፒቴኖች እንደሚያዝ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ጥላሁን ሳርካ አስታወቁ።

Via:- Addis maleda
@YeneTube @Fikeeassefa
እስክንድር ነጋ የጠራው ሰልፍ ⬆️

ነገ አዲስ አበባ ይካሄዳል ስለተባለው ሰላማዊ ሰልፍ

በጋዜጠኛ አስክንድር ነጋ የሚመራው እራሱን የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት እያለ የሚጠራው ለነገ ጥቅምት 02 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።

ይሁንን በሰልፉ ጉዳይ የተለያዩ መረጃዎች በመውጣት ላይ ናቸው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባንድ በኩል በሰልፉ ምክንያት የሚዘጉ መንገዶች ዝርዝር ይፋ አደረገ በሌላ በኩል ደግሞ ነገ በመስቀል አደባባይ ስብሰባም ሆነ ሰልፍ አይኖርም አለ የሚሉ መረጃዎች በማህበራዊ መገናኛዎች እየተሰራጩ ይገኛል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት በጉዳዩ ዙሪያ ስለ ሰልፉ ትክክለኛውን መረጃ ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም መረጃ ሊሰጡን አልቻሉም።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
ኪፕቾጌ በቃሉ መሰረት ከሁለት ሰዐት በታች ማራቶን ጨረሰ!!

1:59:40 በሆነ ሰዐት በመግባት የማራቶን ታሪክን ቀፕሯል።
@YeneTube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነገ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሰልፍ የለም አለ።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ነገ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ሰልፍ እንደሚደረግ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሰልፉ ምክንያት የሚዘጉ መንገዶችን መኖራቸውን ገለፀ በሚል የኮሚሽኑን ሎጎና የኃላፊዎችን ስም በመጠቀም የተላለፈው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ነገ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ በመስቀል አደባባይ የሌለና ምንም የሚዘጋ መንገድ አለመኖሩን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ መደበኛ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡መሰል ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎች በህብረተሰቡ የእለት ከእለት እንስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚሳድሩ መሆኑን ኮሚሽኑ በማስታወስ ህብረተሰቡ ከተሳሳተ መረጃ ራሱን መጠበቅ እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
በሰቆጣ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ትናንት ከቀኑ 11፡30 አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ በርካቶችም ቆስለዋል፡፡የሰቆጣ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደጀን ወዳጅ ለአብመድ እንደገለጹት ከወልደያ ወደ ሰቆጣ ይጓዝ የነበረ መለስተኛ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከጭነቱ ልክ በላይ በርካታ ሰዎችን እንደጫነ አደጋው ደርሷል፡፡በወረዳው ዲብርሳይል (07) ቀበሌ ላይ በተከሰተው አደጋ 17 ሰዎች መሞታቸውን ያስታወቁት ኢንስፔክተር ደጀን ‹‹አራት እናቶች ከነልጆቻቸው፣ አንዲት እናት ከሦስት ልጆቻቸው፤ አባት ከልጆቹ ጋር ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ባልና ሚስትም የነበሩ ሲሆን ባል ከነልጁ ሕይወቱ አልፏል፤ ሚስት ከአንድ ልጇ ጋር ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ይገኛሉ›› ብለዋል፡፡

በአደጋው የተጎዱ ሰባት ሰዎች በተፈራ ኃይሉ ሆስፒታል ገብተው ሕክምና እንዲያገኙ መደረጉን ጠቅሰው ‹‹አሁን ላይ አንደኛዋ ጉዳቱ የከፋ በመሆኑ ወደ መቀሌ ሪፈራል ሆስፒታል ተልካለች›› ነው ያሉት፡፡ከወልደያ ወደ ሰቆጣ ከመጠን በላይ ጭኖ እንደመጣ የተገለጸው ተሽከርካሪ መጫን የነበረበት እስከ 12 ሰው ቢሆንም አሳፍሮ የነበረው ከእጥፍ በላይ 25 ሰዎችን እንደነበር አስታውቀዋል፡፡ቦታው ዳገት በመሆኑ ወደ ኋላ በመመለስ ከመስመር ወጥቶ ሦስት ሜትር ገደል ውስጥ መውደቁንም አመልክተዋል፡፡የመኪናው ሾፌር በሕይወት መኖሩንና በሕግ ጥላ ሥር እንደሚገኝ ያመለከቱት ኢንስፔክተር ደጀን ፖሊስ መታወቂያ የያዙ ሟቾችን አስከሬን ለቤተሰብ ማስረከቡን ገልጸዋል፡፡

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የጎጃም አዲስ አበባ መንገድ አልተዘጋም ብሏል፡፡

ከትናንት ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ግን መንገዱ ዝግ እንደሆነ እየተነገረ ነው። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ‹‹ወቅታዊ የፀጥታ ስጋቶችን መነሻ በማድረግ ፍተሻ እየተካሄደ ነበር፤ በዚህ ምክንያት መኪኖቹ ወረፋ ሲበዛባቸው ተመልሰዋል እንጅ መንገድ ስለመዘጋቱ መረጃ የለንም፤ እንዲዘጋም አላዘዝንም፡፡ ፍተሻውን ላለመጠበቅ የተመለሱ ካልሆኑ በስተቀር መንገድ አልተዘጋም›› ብለዋል፡፡ "ተጨማሪ ጥያቄዎችን ለማመስመለስ ብንፈልግም ስልካቸው በመዘጋቱ አልቻልንም፡፡" አብመድ

የደጀን ወረዳ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሳ አስፋው ዛሬ ከቀኑ 6፡30 ላይ በስልክ እንደገለጹት መንገዱ አሁንም እንደተዘጋ ነው፡፡ ‹‹ወደ ኦሮሚያ ክልል የሚመለከታቸው አካላት ስልክ ስንደውል ከትናንት ጀምሮ ‹አልተዘጋም› እያሉን ነው፤ በተጨባጭ የሚያልፉ መኪኖች ግን የሉም፡፡ ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልልም መኪኖች እየመጡ አይደለም፤ ድብብቆሹን ትቶ የሕዝቡን ችግር ለመፍታት ቢሠራ መልካም ነው›› ብለዋል፡፡

ወደ ኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም ያገኘኛቸው የሥራ ኃላፊ ‹‹ከአዲስ አበባ ውጭ ነኝ፤ ስለጉዳዩ በቂ መረጃ የለኝም›› በማለት ከፌዴራል ፖሊስ ይመለከታቸዋል የተባሉ ኃላፊን ስልክ ቁጥር ብቻ ሰጥተውናል፡፡ ከፌዴራል ፖሊስ የደወልንላቸው ግለሰብ ግን ‹‹ጉዳዩ እኔን አይመለከትም፤ ማንን እንደሚመለከትም አላውቅም፡፡ መንገድ ተዘጋ ሲባል እንዲሁ ነው የሰማሁት›› ብለዋል፡፡
በመንገዱ መዘጋት እየተጉላ ከሚገኙት ውስጥ ብዙዎቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ተማሪዎቹ የምዝገባ ጊዜ በማለፉ ለሚገጥማቸው ችግር ኃላፊነት የሚወስድ አካል ባለማግኘታቸው እየተቸገሩ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ለማነጋገር ጥረት እያደረግን ነው፡፡ የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ‹‹ስለጉዳዩ በቂ መረጃ አላገኘንም፤ ሁኔታውን አጣርተን ከሰዓት በኋላ የሚኖረውን ምላሽ እናሳውቃለን›› ብለዋል፡፡

Via አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
ከባህር ዳር አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ዛሬም አልተከፈተም።

የደጀን ወረዳ አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሳ አስፋውም በአሁኑ ሰዓት ኦሮሚያ ክልል ያለው መንገድ ስላልተከፈተ ደጀን ከተማ ላይ በርካታ መኪኖችና መንገደኞች በከተማዋ እንዳሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ኃላፊ አቶ ለማ ሆርዶፋ በበኩላቸው ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ የተዘጋበትን ምክንያት ለማጣራት አመራሮችን ወደ ሥፍራው እንደላኩ ገልፀው፤ ዛሬ ጠዋትም በጉዳዩ ላይ ተነጋግረውበት አንድም መኪና መቆም እንደማይችል አቅጣጫ አስቀምጠን መኪና በሰላማዊ መልኩ እያለፈ እንደሆነ መረጃ እንዳላቸው ነግረውናል።

ምንጭ:BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ደብረ ብርሀን በአሁኑ ሰዓት ወጣቱ ስላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል ስሞኑን በሚደረገው መገድ መዝጋት በጣም ነዋሪዎች መማረራቸውን ለየኔቲዩብ ገልፀዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእጩ ሰልጣኞች ምልመላንና ቅበላ ፖሊሲን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ!

Via Elias Meseret/Ethiopian Airlines
@YeneTube @FikerAssefa
"በርካታ ወጣቶች ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮ ታስረዋል"--- እስክንድር ነጋ በስልክ ከነገረኝ
እስክንድር እንዳለው ዛሬ ጠዋት የመጨረሻ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበሩበት ወቅት በተለይ መርካቶ አካባቢ በርካታ ወጣቶች ታስረዋል። "አሁን አንተን ሳወራህ ፖሊስ ጣብያዎች እየዞርኩ ልጆቹን ለማስፈታት እየሞከርኩ እያለ ነው። ቁጥራቸው ብዙ ነው፣ ስንት እንደሆነ እንኳን አላውቅም። ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሀላፊዎች ጋር ትንሽ ቆይቼ በአጠቃላይ ጉዳዮች ላይ አወራለሁ።


የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነገ ጥቅምት 2 ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ በመስቀል አደባባይ የለም ብሎ ዛሬ ጠዋት አሳውቆ ነበር።

Via:- Elias Meseret
@YeneTube @Fikerassefa
አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሁሉም መነኃርያዎች እና ኤርፓርቶች ተማሪዎችን እየተቀበለ መሆኑን የተማሪዎች ፕሬዝዳንት ናትናኤል ለየኔቲዩብ አስታውቋዋል።

@YeneTube @Fikerassefa