ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸነፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡
ዘንድሮ ለዘርፉ ከቀረቡ እጩዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የ16 ዓመቷ ስዊድናዊት የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ግሪታ ተንበርግ በሰፊው ያሸንፋሉ የሚል ግምት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከ20 ዓመት በፊት ደም አፋሳሽ የነበረውንና በርካታ ሰዎች ያለቁበትን የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ አድርገው ሰላም በማውረዳቸውና ምስራቅ አፍሪካ የትብብር ቀጠና እንዲሆን ያደረጉት ድፕሎማሲያዊ ጥረት የኖቤል ሽልማቱን እንዲያሸንፉ ጉልህ ሚና ተጫውቷል ተብሏል፡፡
በተለይም ወደ ደም መፋሰስ እየገባች የነበረችው የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች ተደራድረው የስልጣን ክፍፍል በማድረግ ወደ ሰላም መመለሳቸውም ትልቅ ዋጋ የሚያሰጥ ስኬት ተደርጎም ተወስዷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአንድ ቀን 350 ሚሊዮን ችግኝ ማስተከላቸውና በእርሳቸው አመራር የካቢኔያቸውን ግማሹ በሴቶች እንዲያዝ ማድረጋቸውም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲቸራቸው ያደረገ መሆኑን የፖለቲካ ጠበብቶች ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በተለያዩ መስኮች ጉልህ ተግባራቶችን ያከናወኑ ግለሰቦችን ተቋማት በየዓመቱ የሚሸለሙበት የኖቤል ሽልማት በአለማችን ከሚሰጡ ሽልማቶች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡
የኖቤል የሰላም ሽልማት እስካሁን ለ133 ግለሰቦችና ተቋማቶች ተሰጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ 1938 ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ለኖቤል ሽልማት መታጨታቸው የቢቢሲ መረጃ ያሳያል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማትን በማሸነፋቸው 9 መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም 9 ሚሊዮን የስዊድን ክሮነር ይበረከትላቸዋል፡፡
Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa

አዲስ አበባን ከባህርዳርና ጎንደር የሚያገናኘው መንገድ ዛሬ ረፋድ ጀምሮ ጎሃ ጺዮን ከተማ ላይ ተዘግቷል።
ጎሃ ጺዮን በአባይ በርሃ አፋፋ ላይ የምትገኝ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች አዋሳኝ ከተማ ናት።
@YeneTube @Fikerassefa
ጎሃ ጺዮን በአባይ በርሃ አፋፋ ላይ የምትገኝ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች አዋሳኝ ከተማ ናት።
@YeneTube @Fikerassefa
⬆️ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ ከተማ የሚሄዱ ተጓዦች ለእንግልት እየተዳረጉ መሆናቸውን አስታውቀዋል!
በደጀን እና ጎሃ ፅዮን መሥመር ወደ አዲስ አበባ ተጓዦችን አሳፍረው ሲሄዱ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉንም የዓይን እማኞች ለአብመድ በስልክ ተናግረዋል፡፡
ተጓዦቹ ከረፋዱ 3:00 ገደማ ጀምሮ በጎሃ ፅዮንና አካባቢው እንዳያልፉ ተደርገዋል፡፡ ከ60 በላይ ተሽከርካሪዎችም ወደ ደጀን ከተማ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ነው ያስረዱት፡፡
ክልከላው ‹‹በመጭው እሑድ አዲስ አበባ ላይ በተጠራው ሰልፍ ልትሳተፉ ነው›› በሚል እንደሆነም ነው ተጓዦች የጠቆሙት፡፡ ለአብመድ አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል በአማራ ክልል የሚገኙ መንፈሳዊ ቦታዎችን ጎብኝተው ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ የነበሩም ይገኙበታል፡፡ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚሔዱ ተማሪዎች እና ለሕክምና ክትትል ቀጠሮ ወደ አዲስ አበባ የሚሂዱ ተጓዦችም እንደንዳሉ ታውቋል፡፡ ጉዳዩ የሚመለከተው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የሚገቡ ተሽከርካሪዎች በሠላም እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ እየሄዱ የነበሩ ተጓዦች ግን እንዳያልፉ መደረጉንና ወደ ደጀን እየተመለሱ መሆኑንም ኮሚሽኑ ከተሳፋሪዎች አገኘሁት ባለው መረጃ አረጋግጧል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ኮማንድ ፖስት ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የተጣራ መረጃ እንዳልደረሰው አስረድቷል፡፡
ከአስተያየት ሰጭዎቹ ያገኘነው መረጃ የሚያሳየው ግን ከረፋዱ 3:00 ጀምሮ ችግሩ እንደተፈጠረ ነው የተናገሩት፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ጉዳዩን ለማጣራትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሠራ መሆኑን አስረድቷል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ መረጃው እንደደረሰው ገልጾ ዝርዝር ምክንያቱን እያጣራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
Via አብመድ

ዶክተር አብይ እንዲያሸንፉ የረዳን ኢትዮጵያዊ ወንድማችን
አንድ ግለሰብ የኖቤል ተሸላሚ ይሆን ዘንድ ከመስፈርቶቹ አንደኛው በታዋቂ አለም አቀፍ ዩኒቨርስቲ በሚያስተምሩ ምሁራን መጠቆም ይኖርበታል። ዶክተር አብይ የኖቤል ተሸላሚ እንዲሆኑ ጥቆማ ያደረጉት የኖርዌዩ University of South Eastern Norway አሶሽዬት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ግሩም ዘለቀ ናቸው። ዶክተር ግሩም ያላቸውን ሃላፊነት በመጠቀም ስለጠቅላይ ሚኒስትራችን 61 ገፅ ፅሁፍ በማዘጋጀት ለኖቤል ሽልማት ያጯቸው ሲሆን የኖቤል ፕራይዝ አዘጋጆችም እጩነታቸውን ተቀብለው በመጨረሻ ሽልማቱ የዶክተር አብይ ሆኗል።
Via:- Ermias Tokuma

የትግራይ ክልል ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈ!
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የሰላም የኖቤል ሽልማት በማሸነፋቸው የእንኳን ደስ አልዎት መልእክት አስተላልፏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተሸለሙት የኖቤል የሰላም ሽልማት ሀገሪቱ የጀመረችው የሰላም ጉዞን አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚያስችል እምነቱን ገልጿል።
Via FANA
@YeneTube @FikerAssefa

Best brand frames❤️ Gucci👌 Boss🤓 and many more....The price includes delivery to any destination in addis and it includes😁 photo solar and anti glare lenses😎 call +251912894364
Or inbox via @ZenachBrands1
Or inbox via @ZenachBrands1
Forwarded from YeneTube
Buy and Order Quality clothes we will bring any orders from USA 🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 in 8 to 15 days
for more info: @order_us1_inbox
☎0911073577 (abrsh)
👉tops 👚
👉Demin👖
👉Dress 👗
👉underwear 👙
👉T- shirt 👕
For more 👇🏾👇🏾👇🏾join the chanal
👉🏻 https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFeEeXHsZxR6KmWVxA
🏠location: medihanialem mall, 3rd floor , 306

Forwarded from YeneTube via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ፍርድ ቤቱ የነአቶ በረከት ስምዖንን የክስ መዝገብ መርምሮ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ፡፡
በነአቶ በረከት ስምዖን የክስ መዝገብ ዛሬ በድጋሜ ከሰዓት በኋላ የተሰየመው ችሎት ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ተጨማሪ ሰነድ መርምሮ የሰነዱ አካል እንዲሆን ብይን ሰጥቷል፡፡ከፍርድ በፊት የሚቀርብ ማንኛውም ማስረጃ መርምሮ ትክክለኛ ብይን ለመስጠት አጋዥ ስለሚሆን ዐቃቤ ሕግ እንዲያዝለት ያቀረበውን 141 ገፅ ማስረጃ ከዚህ ቀደም የቀረበው የሰነድ ማስረጃ አካል እንዲሆን ሊያያዝ ይገባል ብሏል ፍርድ ቤቱ፡፡ፍርድ ቤቱ ሰነዱን መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለጥቅምት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
Via AMMA

የቀድሞው የዞን 9 ጦማሪዎች ቡድን አባል በፍቃዱ ኃይሉ ለጸሃፊያን የሚሰጠው የፔን ፒንተር “International Writer of Courage” ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሸላሚው ድርጅት የፔን ኢንተርናሽናል አጋር የሆነው የእንግሊዙ ፔን ነው፡፡ በፍቃዱ ሽልማቱን ትናንት በለንደኑ ብሪትሽ ላይበራሪ እንደተቀበለ ድርጅቱ በትዊተር ገጹ አስታውቋል፡፡ በፍቃዱ ባሁኑ ሰዓት የአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ም/አዘጋጅ እና ለአማርኛው DW ሬዲዮ ጽሁፍ አቅራቢ ነው፡፡
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ለዕሁድ ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ለአስተዳደሩ ስለ ሰልፉ ብናሳውቅም፣ እስካሁን ምላሽ አልተሰጠንም- ብሏል የባላደራው ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ፡፡ ሆኖም በሕጉ መሠረት፣ ዝምታው ዕውቅና እንደመስጠት ስለሚቆጠር ፖሊስ ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ሰልፉ ለሀገራዊ ዲሞክራሲ ነው፤ እናም ሕዝቡ ለሰልፉ ይውጣ ሲል ጥሪ አድርጓል፡፡ ሰልፉ ከተደናቀፈ ባላደራው ወደሚቀጥለው የትግል ምዕራፍ ይሄዳል፡፡ መግለጫው በተሰጠበት ግቢ አቅራቢያ ወጣቶች ባላደራው ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡
ምንጭ: ዋዜማ
@YensTube @FikerAssefa

በልምምድ ላይ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።
አውሮፕላኑ ዛሬ ጠዋት ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአየር ሃይል ካምፕ በመነሳት በልምምድ ላይ እያለ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ኡኬ ደንካካ በተሰኘ ቦታ መከስከሱን የምስራቅ ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበራ ያሚ ለዶቸ ቨለ አረጋግጠዋል።
በአደጋው የሁለት አብራሪዎች ህይወት ማለፉንም አቶ አበራ ገልጸዋል። ከሟቾች መካከል የአንደኛው አስክሬን አውሮፕላኑ ከተከሰከሰበት ከ100 ሜትር በላይ ርቆ መገኘቱንም ተናግረዋል። የአደጋው መንስኤ ገና በመጣራት ላይ መሆኑንም ነው አቶ አበራ የተናገሩት።
« በደረሰን መረጃ መሰረት የተከሰከሰው አውሮፕላን የጦር መለማመጃ አውሮፕላን ነው። ሁለት ሰዎች በልምምድ ላይ እንደነበሩም ነው ያጣራነው። ከሁለቱ ሰዎች የአንደኛው አስክሬን ሲገኝ የሌላኛው ከአውሮፕላኑ ጋር ቃጠሎ ደርሶበታል። አደጋው የደረሰው ከምሳ ሰአት በፊት ሲሆን እስካሁን የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ነው የምናውቀው።»
የጦር አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት በዚሁ በአደአ ወረዳ፣ከጥቂት አመታት በፊት በጦር ሂሊኮፕተር ላይ በደረሰ ተመሳሳይ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ይታወሳል።የ157 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የመጋቢት 2011ዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ የደረሰውም በዚሁ አካባቢ ነበር።
Via:- DW
@YeneTube @Fikeeassefa

ሰኔ መጀመሪያ አካባቢ የተጀመሩት የአልማ ትምህርት ቤቶች ነገ ይመረቃሉ።
የአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር (አልማ) የክልሉን የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል እንቅስቃሴ አካል የሆኑ ሦስት ትምህርት ቤቶች ነገ ይመረቃሉ።የአልማ ስትራተጅያዊ ዕቅድ የሙከራ ትግበራ ፕሮጀክት ለቀጣይ አፈፃፀም አቅም በሚፈጥር መንገድ መጠናቀቁንም ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልጸዋል፡፡ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መላኩ ፋንታ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በምሥራቅ በለሳ ጉሀላ ከተማ ሰኔ 04/2011 ዓ.ም ተጀምረው ነገ የሚመረቁት ሦስት የትምህርት ቤት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ገንዘብ መጠናቀቃቸው ለቀጣይ ዕቅድ አፈፃፀም ትምህርት ተቀስሞባቸዋል፡፡
ነገ ተመርቀው አገልግሎት የሚጀምሩት ትምህርት ቤቶች መንግሥት፣ አልማና ሕዝቡ በቀጣይ ሦስት ዓመታት የክልሉን የትምህርት ቤቶች ደረጃ ከሚገኝበት 16 በመቶ ወደ 50 በመቶ ለማሳደግ የታለመው ስትራቴጂያዊ የለውጥ ዕቅድ አካል መሆኑን አቶ መላኩ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፦ አልማ/አብመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከፕሬዚዳንት ሲሲ ጋር በስልክ ተወያዩ!
መሪዎቹ በውይይታቸው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተደረገ ባለው ድርድር ላይ አተኩረው መነጋራቸው ነው የተመለከተው።
በዚህም ወቅት ግድቡን በተመለከተ የሚደረገውን ድርድር መቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ተሸላ በመሆናቸው ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ ኤል ሲሲ ላስተላለፉት የደስታ መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና አቅረበዋል። ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ዙሪያ ያነሳችው አቋም የኢትዮጵያን ቀይ መስመር የሚያልፍ በመሆኑ ከመግባባት ላይ መድረስ እየተቻለ አለመሆኑን ኢትዮጵያ መግለጿ ይታወቃል።
Via FBC