የመስቀል በዓል ታሪካዊ አመጣጥ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ሕሙማንን በመፈወሱ ምክንያት በርካታ አሕዛብ ክርስቲያን እንዲሆኑ አስችሏል፡፡
በተአምራዊነቱና በክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የተሰጠው በመሆኑና ይህን የተመለከቱ አይሁድ ቅዱስ መስቀሉን በአንድ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ እንዲቀበር አደረጉ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በየቀኑ ቆሻሻ ስለሚጥሉበት ቦታው ወደ ተራራነት ተቀየረ፡፡ ምንም እንኳን መስቀሉን ለማውጣት ባይችሉም በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች ቦታውን ያውቁት ነበር፡፡ በሰባ ዓመተ ምሕረት በኢየሩሳሌም ላይ በተደረገው ወረራ ኢየሩሳሌም ስለጠፋች በዚያ የነበሩ ክርስቲያኖች ተሰደዱ ፤ የተቀበረበትን ቦታ የሚያውቅ ባለመገኘቱ መስቀሉ ከ300 ዓመታት በላይ ተዳፍኖ /ተቀብሮ/ ኖረ፡፡
https://telegra.ph/MMesekel-09-27

የደቡብ ክልል የሙስና ወንጀሎች የመመርመር እና መክሰስ ስልጣን ለዞን መዋቅር መተላለፉ ተገለጸ።
የሙስና ወንጀሎች የመመርመርና መክሰስ ስልጣን ለዞን መዋቅር ማስተላላፉን የደቡብ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል፡፡በወረዳና በከተማ አስተዳድር ተሿሚዎች፣ በዞን፣ ልዩ ወረዳ እና በወረዳ የመንግሰት ሰራተኞች፣ ህዝባዊ ድርጅት ስራተኞች እና ሌሎች ሰዎች አማካኝነት የሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎችን የመመርመርና መክሰስ ተግባራት በዞን፣ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና በልዩ ወረዳዎች ፖሊስ መምሪያዎች ጽሕፈት ቤቶች እና ዐቃቤ ህግ መምሪያ ጽሕፈት ቤቶች እንዲከናውን ተወስኖ ስልጣኑን የማስተላለፉ ስራ መሰራቱን የደቡብ ክልል ዋና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ኑርዬ ሱሌ ገልጸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዞን የመንግስ ተቋማት በኃላፊ ደረጃ የሚገኙ ተሿሚዎችና በክልል ደረጃ ባሉት የመንግስትና የልማት ድርጅቶች ስራተኞች እና ተሿሚዎች የሚፈፀሙ የሙስና ወንጀሎችን የመመርመርና የመክሰስ ስልጣን ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንና ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዋና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ምንጭ:SRTA
@YeneTube @FikerAssefa

ትላንት መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም በሚዲያ አማካኝነት የተሰራጨው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሷ አርማና ሎጎ መያዝ አትችልም አላልንም እኛ ያልነው የኢትዮጵያ ህዝብ ያልተግባበት የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አርማ ይዞ መምጣት አይቻልም ነው ያልነው።
ምክንያቱም በዓሉ የሀይማኖት መሆኑ ቀርቶ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተጠልፎ የፖለቲካ አጀንዳ መጠቀሚያ ሆኖ ወደ ግጭት እንዳያመራ ነው። ይህንን ታላቅ በዓል በርካታ የዓለም ሚዲያዎች የሚዘግቡት ስለሆነ መንገዱን ስቶ ገጽታችንን ማበላሸት የለበትም ፣ ወደ ግጭት የሚያመሩ ነገሮች ሁሉ ይወገዱ፤ ህዝበ ክርስቲያን ይህንን በዓል በድምቀት አክብሮ አምላኩን አመስግኖ በደስታ ያለምንም የፀጥታ ችግር ወደ ቤቱ እንዲመለስ ነው። ከዚህ ውጭ ምንም የተደበቀ ዓላማ የለውም።
ፖሊስ ለሰላም፤ ሰላም ለሁሉም !!!
Via:- የኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ ኮምሽን
@YeneTube @Fikerassefa

ጥንቃቄ ❗️
በአዲስ አበባ በመንገድ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ሽጉጥና ልዩ ልዩ ድምፅ የሌላቸው መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ/ም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመጣመር በአስሩም ክፍለ ከተሞች በምሽት ክፍለ ጊዜ ባደረገው ድንገተኛ የመንገድ ላይ ፍተሻ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ልዩ ስፍራው ሳሪስ አቦ አካባቢ አይነቱ ካሪና የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2-69099 አ/አ መኪና ውስጥ ብዛታቸው 8 ስታር- ሽጉጦች ከአምስት ተጠርጣሪዎች ጋር የተያዙ ሲሆን በተመሳሳይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከ12 ግለሰቦች ላይ 3 ገጀራ ፣ 12 ጩቤዎች እንዲሁም የሴሌዳ ቁጥር ኮድ 2B-36293 አ/አ ቪትዝ ተሽከርካሪ ውስጥ 1300 የአሜሪካ ዶላር መያዙን አስታውቋል፡፡
በህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችን ጉዳይ እያጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቆ ህብረተሰቡ የፀጥታ ጉዳይ የጋራ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት በፍተሻ ወቅት ላደረገው ክፍተኛ ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቦ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
via:- አዲስ አበባ ፖሊስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛን የገደሉ 3 ተጠርጣሪዎች መያዙን ፓሊስ ገለፀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛን የገደሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ወይዘሮ እፀገነት አንተነህ መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 12 ሰዓት 30 አቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ወደ ስራ ለመሄድ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳለች ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ወንጀል ለመፈፀም አቅደው የትራንስፖረት አገልግሎት የሚሰጡ በማስመሰል ሟችን በባጃጅ ተሽከርካሪ ከሳፈሯት በኋላ አንቀው እንደገደሏት ተጠርጥረዋል፡፡ተጠርጣሪዎቹ የሟችን አስክሬን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ አካባቢ መንገድ ላይ ጥለዋት እንደተሰወሩ ነው ፓሊስ የገለፀው፡፡
ወንጀሉን የፈፀሙ ግለሰቦች አለመታወቁ የፖሊስን ስራ እጅግ አስቸጋሪ ቢያደርገውም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀሉ ከተፈፀመ ጀምሮ ቀንና ሌሊት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ሦስቱን ተጠርጣሪዎች በዘጠነኛው ቀን በትናትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡ተጠርጣሪዎቹ በርካታ የአካባቢው ሰዎችና የሟች ቤተሰቦች በተገኙበት መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ/ም ወንጀሉን እንዴት እንደፈፀሙት መርተው አሳይተዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ፒያሳ አካባቢ በአንድ ግለሰብ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መያዙን አስታውሷል፡፡
ህብረተሰቡም ወንጀለኞችን አጋልጦ በመስጠት እና ምስክር በመሆን እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አድንቆ ይህንኑን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡፡
Via FBC

ቱርክ በኢትዮጵያ ለ19 ሽሕ ተማሪዎች ሙሉ ትምህርት መሳሪያዎችን ለገሰች። ልገሳው የተከናወነው ኢትዮጵያ በሚገኘው የቱርክ ኢምባሲ እና በባቡር ሐዲድ ግንባታ ላይ በተሰማራው ያፒ ማርኪዝ አስተባባሪነት ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች የሚያከብሩት የደመራ በዓል ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ በሰላማዊና ኃይማኖታዊ ሥርዓት እየተከበረ መሆኑን የከተማይቱ ፖሊስ ዐስታወቀ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፈይሳ በተለይ ለዶቸ ቬለ እንደገለጡት ፖሊስ አስቀድሞ ባደረገዉ ዝግጅት መሠረት በዓሉ ሥራዓቱን ጠብቆ እንዲከበር ከፍተኛ ክትትልና ጥበቃ እያደረገ ነዉ። የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ትናንት ባወጣዉ መግለጫ በኃይማኖት ጥያቄ ሽፋን በዓሉን ለማበጥና የተለያዩ የኃይማኖት ተከታዮችን ለማጋጨት የሚያሴሩ እንዳሉ ጠቁሞ ነበር።
በዓለተኛዉ በየበዓሉ ሥፍራዎች ግጭትን የሚቀሰቅሱ መልዕክቶች፣ አርማዎችና በሕገ-መንግሥቱ ከተፈቀደዉ ሰንደቅ ዓላማ ዉጪ ይዞ እንዳይወጣ ፖሊስ አግዶሏም።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፈይሳ እንዳሉት አዲስ አበባ ዉስጥ ዛሬ እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ፖሊስ የከለከላቸዉን ጽሑፎች፣ አርማና ባንዲራዎች ይዞ የወጣ በዓል አክባሪ የለም። አዲስ አበባ የበዓሉ ሥፍራ የሚገኘው ወኪላችን እንደተመለከተው ከሆነ፦ ቀትር ላይ ባንዲራ የሚመስል የአንገት ልብስ ያደረጉ በዓል አክባሪዎችን ፖሊስ ሲከለክል ነበር። የአዲስ አበባ ፖሊስ በዓሉ እንዳጀማመሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ከሰንበት ትምሕርት ቤቶች፣ ከበአሉ አዘጋጅ ኮሚቴና ከአብያተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር ተባብሮ እየሰራ ነዉ።
የዘንድሮዉ የደመረ በዓል የሚከበረዉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በአብያተ ክርስቲያንና በምዕመናን ላይ ይደርሳል ያሉትን ጥቃት መንግስት እንዲያስቆም ባደባባይ ሰልፍ በሚጠይቁበት ወቅት ነዉ። አጠቃላይ የበዓሉን ሒደት በዛሬው የሬድዮ ሥርጭታችን ተከታተሉ።
Via:- DW

በየሰፈሩ #ደመራ ለመደመር እየተዘጋጃችሁ ያላችሁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ሰፈር ውስጥ ያዘጋጃችሁት #ደመራ መለኮስ የሚገባችሁ በየከተማችሁ ላይ የተደመረው ደመራ ሲገባደድ መሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሳስባለች።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
የግብፅ ፖሊስ የርዕሠ-ከተማ ካይሮን የተሕሪር አደባባይን ዛሬ ሙሉ በሙሉ ዘግቶ ዋለ።
እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2011 የተደረገዉ ሕዝባዊ አመፅ ዋና ማዕከል የነበረዉን አደባባይ ፖሊስ የዘጋዉ ፕሬዝደንት አብድል ፈታሕ አስ ሲሲን አገዛዝ የሚቃወመዉ ሕዝብ ተቃዉሞዉን ባደባባይ እንዳያሰማ ለማገድ ነዉ።ፕሬዝደንቱና ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎቻቸዉ በሙስና ተዘፍቀዋል የሚል ዘገባ ከተሰራጨ ወዲሕ ፕሬዝደንቱ ሥልጣን እንዲለቁ የግብፅ ሕዝብ በተለይም ወጣቶች ባደባባይ ሰልፍ እየጠየቁ ነዉ።ባለፈዉ ሳምንት አርብ በሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ በተለያዩ ከተሞች አደባባይ በመዉጣት ፕሬዝደንቱ ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቆ ነበር።
የግብፅ ፀጥታ አስከባሪዎች ሰልፈኛዉን በአስለቃሽ ጢስ በትነዉታል።ፀጥታ አስከባሪዎች በሰልፉ ላይ ተካፍለዋል ያሏቸዉን ከ2000 በላይ ሰዎች ማሰራቸዉንም ጠበቆችና የእስረኞቹ ቤተሰቦች አስታዉቀዋል።የቀድሞዉ ጄኔራል አብደል ፈታሕ አስ ሲሲ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2014 በሕዝብ የተመረጡትን ፕሬዝደንት መሐመድ ሙርሲን በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን አስወገደዉ የመሪነቱን ስልጣን ከያዙ ወዲሕ ሊቃወሟቸዉ በሞከሩ የሐገሪቱ ዜጎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰዱ ነዉ።አስ ሲሲ በሰብአዊ መብት ረጋጭነት ቢወቀሱም የምዕራባዉያን መንግስታት በተለይም የዩናይትድ ስቴትስ እና የአረብ ነግስታት ጠንካራ ድጋፍና ርዳታ አልተለያቸዉም።
Via DW

በግብፅ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰለፍ ተቀሰቀሰ
በግብፅ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰለፍ እየተካሄደ ነው፡፡
ይህንንም ተከትሎም ዋና ከተማዋ ካይሮን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩ ነው እየተነገረ የሚገኘው፡፡
ከዕለተ አርብ ፀሎት በኋሏ ዋራቅ በሚባል አካባቢ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ መልዕክት እያሳሙ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ተቃዋሚዎቹ በሀገሪቱ ያለው የኑሮ መመሰቃቀል እና የሙስና መስፋፋት እንዲቆም መጠየቃቸው ተሰምቷል። የጁምዓ ተቃውሞ በደቡብ ግብፅ በምትገኘው ሉክሰር እና በቁስ አካባቢዎች መቀስቀሱም ተጠቁሟል፡፡
በዋና ከተማዋ ካይሮ ደግሞ የ2011 የተቃውሞ እምብርት የነበረውን የታሂር አደባባይ መግቢያ የፀጥታ አካላት እንደዘጉት ተነግሯል፡፡
ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ በአስተዳደራቸው ላይ የተነሳው ተቃውሞ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለፅ ለተቃውሞ ምንም ምክንያት የለም ያሉ ሲሆን የፀጥታ አካላት በዋና ከተማዋ የፀጥታ ቁጥጥሩን እንዲያጠናከሩ ማዘዛቸው የሚታወስ ነው፡፡
Via:- FBC

በስኬት ተጀምሮ በስኬት የተጠናቀቀ ግሩም በዓል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶኮስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና ልጆቿ በመስቀል አደባባይ ሁልጊዜም ለመስቀል በዓል እንደሚያደርጉት ለአይን በሚያስደምም፣ ለጆሮ በሚጥም፣ መንፈስን በሐሴት በሚያመጥቅ መንፈሳዊ ትርዒት ደምቀው አድምቀዉናል። በዓሉ በታላቅ ስኬት እንዲከበር ሌት ከቀን የለፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን።
በድጋሚ መልካም የመስቀል በዓል።
Via:- ኢንጂነር ታከሉ ኡማ
@YeneTube @Fikerassefa
በድጋሚ መልካም የመስቀል በዓል።
Via:- ኢንጂነር ታከሉ ኡማ
@YeneTube @Fikerassefa
"የአባቶቼን ርስት አልሰጥም
ስለ ጽዮን ዝም አልልም"
እነኚህ የሽሮ ሜዳ ወጣቶች ከላይ የተጠቀሰውን መልዕክት በቲሸርታቸው ላይ አሳትመው ወደ መስቀል አደባባይ ሲጓዙ በቲሸርታቸው ላይ ባሳተሙት #ፅሁፍ ምክንያት ወደ መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ተደርገዋል።