YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Audio
በሐረሪ ክልል የሚገኝ የማኅበረሰብ የትምህርት ተቋም በይዞታው ውስጥ በሚፈፀም ህገወጥ የመሬት ወረራ የተነሳ የመማር ማስተማር ሥራ መጀመር አልቻልኩም አለ።

እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንም በህገወጥ መሬት ወረራው እየተቸገርኩ ነው ብላለች። የክልሉ ፀጥታ ምክር ቤት ችግሮቹን ለመፍታት ዝርዝር መርኃ ግብር አውጥቼ እየተንቀሳቀስኩ ነው ብሏል።

Via:- VOA
@YeneTube @Fikerassefa
ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱትና በምዕራብ ወለጋ አይራ ወረዳ ሰሞኑን አሰቃቂ ጥቃት የተፈጸመበት መሆኑን ምስሉ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሲታይ የነበረ አንድ ወጣት ወንድማቸው መሆኑን ያመለከቱ ግለሰብ ወጣቱ “በፀጥታ ኃይሎች ነው የተገደለው” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።የአይራ ወረዳ ፀጥታና አስተዳደር በበኩሉ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው መግለጫ ወጣቱ በወንጀል ተጠርጥሮ የሚፈለግ የነበርና በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ለማምለጥ ሙከራ ሲያደርግ መገደሉን አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት ምሽት በአሶሳ ከተማ መካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን (ከመናኸረያ ወረድ ብሎ) ባልታወቁ ሰዎች ቦንብ ተወርዉሮ በሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ፖሊስ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ሰምተናል::

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ሕዝቦች የሰገን ዞን እንዲፈርስ የተወሰደውን ወሳኔ ተከተሎ የዞኑ ሰራተኞች መበተናቸውንና የደመወዝ ክፍያም ተነፈግን ሲሉ አማረሩ።የክልሉ የሰው ኃብት ልማት ቢሮ በበኩሉ የ610 ሰራተኞችን ምደባ በተመለከተ የማስተባበር ላይ ይዣለሁ፤ የደሞዝ ክፍያው ይፈፀም ግን በቅድሚያ የስራ መደብ ልሰጣቸው ይገባል እያለ ነው። ቅሬታቸው ተገቢ ነው። ወደ ሥራቸው የሚመለሱበትም ጥረት ተጀምሯል ነው የተባለው።

ምንጭ:VOA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያዊቷ ሎዛ አበራ ለማልታው ቢርኪርካራ የእግር ኳስ ክለብ በቋሚነት ፈረመች።

ክለቡ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የፊት አጥቂ ሎዛ አበራ ከክለቡ ተጫዋቾች ጋር ለሳምንታት የቆየ አስደናቂ ብቃቷን ያሳየችበት ልምምድ ካደረገች በኋላ በይፋ የቡድኑ አባል ሆናለች ነው ያለው። በክለቡ በሚኖራት ቆይታም መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማት ምኞቱን ገልጿል። የ21 ዓመቷ ሎዛ ለክለቡ ፊርማዋን ባኖረችበት ወቅት “ላለፉት ዓመታት የሊጉ አሸናፊ የሆነውን ክለብ በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ፤ እንደ አንድ የስኬት እርምጃ እወስደዋለሁ” ብላለች።

እንደ ማንኛውም የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ግብ ማስቆጠር ቢኖርብኝም፥ በተለይ ቡድኔ የሊጉ አሸናፊ እንዲሆን እና በአውሮፓ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር እንዲሳተፍ ውጤታማ ጥረት አደርጋለሁ ነው ያለችው።ሎዛ የቢርኪርካራ ክለብ ተጫዋች መሆኗ በማልታ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እውቅና ያገኘ ሲሆን፥ ተጫዋቿ በመጪው የፈረንጆቹ ጥቅምት 9 ቀን ከሄበርኒያንስ ክለብ ጋር በሚደረገው ጨዋታ እንደምትሰለፍ ክለቡ በይፋዊ ድረገፁ አስነብቧል።

ምንጭ: ዋልታ
@YeneTube @FikerAssefa
አውስትራሊያ ፅንስ ማስወረድን ከለከለች!!

ከአውስትራሊያ ይሄን ፅንስ ማስወረድን የሚከለክለውን ህግ ያላፀደቀችው ግዛት ኒው ሳውዝ ዌልስ ነበረች፡፡ አሁን ረቂቁ ድምፅ ተሰጥቶበት አፅድቃለች፡፡

ረቂቁ የጸደቀው የ 119 አመት ዕድሜ ያለውን ህግ ገልብጦ ነው፡፡ ይሄ ህግ በተቃዋሚዎች ያረጀ፣ ጊዜ ያለፈበት ተብሎ ይተች ነበር፡፡
ይሄ አዲስ ህግ ለሳምንታት የፈጀ ንትርክ ተደርጎበት ነበር፡፡ በመንግስት መዋቅር ውስጥም ክፍፍል ፈጥሯል፡፡

ከዚህ በፊት ማስወረድ ይቻል የነበረው ዶክተር ለሴቷ ጤና አደጋ ስላለው ፅንሱ መውረድ አለበት ካለ ብቻ ነበር፡፡

አዲሱ ህግ ፤ ፅንስ ለማስወረድ የሚሞክሩ ሴቶችና ዶክተሮች የ 10 አመት እስር ይጠብቃቸዋል ሲል ቢቢሲ የአገሪቱን የጤና ሚኒስቴር ጠቅሶ ዘግቧል።

Via:- EthioFM
@YeneTube @Fikerassefa
የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን አስመለክቶ ከ48 ቀናት በኋላ ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክቶች ይፋ ሆኑ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን በማስመልከት ለማካሄድ ላቀደው ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።

Via:- Ethio Fm
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ አማራጭ ሃሳቦችና የሚወከሉበት ምልክቶችን ይፋ አደረገ። በዚህም መሰረት፡-

(ጎጆ )“ሲዳማ በደ/ብ/ብ/ህ ክልል ውስጥ እንዲቆይ እፈልጋለሁ” ለሚለው አማራጭ የጎጆ ቤት ምልክት።

(ሻፌታ) ሲዳማ እራሱ ችሎ እንዲያስተዳድር እፈልጋለሁ ለሚለሁ አማራጭ ሻፌታ ምልክት።

Via:- ELU
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ክብረ በዓል ልዩ ትራንስፖርት አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡

አየር መንገዱ ይህ ልዩ ትራንስፖርት ከዚህ ቀደም ያልነበረኝ ነው ብሏል፡፡ ከአዲስ አበባ ኮምቦልቻ ድረስ በአየር አድርሼ ከኮምቦልቻ ግሸን ማርያም ድረስ ደግሞ ከወሎ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን በየብስ አጓጉዛለሁ ማለቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አስራት በጋሻው ለሸገር ነግረዋል፡፡ከመስከረም 19 ጀምሮም ለተከታታይ 4 ቀናት በረራዎቹን እጥፍ እንደሚያደረጉ ሰምተናል፡፡ አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ግሸን ማርያም ስፍራው ድረስም 4 ሺ 999 ብር እጠይቃለሁ ብሏል፡፡

Via Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ያዘጋጀው ውል «የተሳከረ» ከአገሪቱ ሕግጋት የሚጣረስ መሆኑን አንድ የሕግ ባለሞያ ተናገሩ። በ2012 ዓ.ም. በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የሚጀምሩ 142 ሺሕ ገደማ ወጣቶችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች «በግልም ይሁን በቡድን በሚፈጠሩ ግጭቶችና ጥፋቶች ተሳታፊ ወይም ተባባሪ» እንዳይሆኑ ለመጠበቅ በተማሪዎች፣ በወላጆች እና በወረዳ የትምህርት ጽሕፈት ቤቶች የሚፈረም ውል ተዘጋጅቷል።

በሰነዱ ወላጆች ልጆቻቸው «በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በማንኛውም መነሻ በሚፈጠሩ ግጭቶችና ጥፋቶች በግልም ይሁን በቡድን እንዳይሳተፍ፣ ተባባሪም እንዳይሆን» መምከራቸውን ተስማምተው እንዲፈርሙ ያስገድዳል።

በወላጅ ወይም በአሳዳጊ እንዲሞላ በተዘጋጀው ቅጽ ልጅ በዩኒቨርሲቲ «በጥፋቶች ተሳታፊና ተባባሪ በመሆን ለሚያደርሰው ጥፋትና ጉዳት ለሚወሰድበት ርምጃ በሕግ ተጠያቂ» እንደሚሆን ማስገንዘባቸውን ተስማምተው ወላጆች ይፈርማሉ።

በዚያው ሰነድ የወረዳ የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲፈርሙበት በተዘጋጀው ክፍል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለሚያጠፉት ጥፋት ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ተጠያቂ እንደሚሆኑ ያትታል። በሰነዱ መሰረት ልጅ «በዩኒቨርሲቲ ቆይታው በማንኛውም ምክንያት በግልም ይሁን በቡድን በሚፈጠሩ ግጭቶችና ጥፋቶች ተሳታፊ ወይም ተባባሪ እንዳይሆን ስልጠና የወሰደ ሲሆን ይህንን ተላልፎ ችግር ቢፈጥር ለሚደርሰው ጥፋት ሁሉ እሱም ሆነ ወላጆቹ/አሳዳጊዎቹ ተጠያቂ» ይሆናሉ።

የሕግ ባለሞያው አቶ አብዱረዛቅ ነስሮ ይኸ እርስ በርሱ የሚጋጭ ሆኖ አግኝተውታል። «የወላጆችን ስታየው ወላጆች እንደማይጠየቁ፤ ግዴታቸው ማስገንዘብ እንደሆነ የሚያወራ ይመስላል። ለወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀውን ስታየው ደግሞ ወላጅ ተጠያቂ ሊሆን እንደሚችል፤ በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን ያወራል። ይኸ አንድም እርስ በርሱ የተጋጨ፤ የተሳከረ ነው» ሲሉ ተችተዋል።

via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
የመተከል ግጭት እየተረጋጋ ባለበት ቢሆንም ማክሰኞ መስከርም 13 ቀን በዳንጉር ወረዳ ሁለት የከብት እረኞች ተገለዋል:: ትናንት ደግሞ አንድ ሰው ሞቷል። አሁን መከላከያ ሠራዊት አከባቢዉን እንደተቆጣጠረውና እያረጋጋ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀውልናል::

@YeneTube @FikerAssefa
"አዲስ አበባችንን እንደስሟ አዲስና አበባ ለማድረግ ያቀድነው ዕቅድ በእርግጠኝነት ይሳካል።አጠቃላይ ስፋቱ 13.9 ሔክታር በዛሬው ዕለት ሦስት ፓርኮችን እናስመርቃለን።"

-ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌📌📌 አስተውሉ
📖 ማንበብ ህይወትን ይቀይራል

  TOP BOOK  ፤ መፅሀፍት ጥቆማ

🔺የመፅሀፍት ጥቆማዎች
🔺በተለያዩ ዘርፍ አዳዲስ መፅሀፍት እናቀርባለን ጥቆማዎች
🔺ትምህርታዊ መርጃ ፣ ታሪክ ፣ የሳይኮሎጂ ፣ ቋንቋ
🔺የድሮ ማለትም የቆዩ መፅሀፍት ጥቆማ

ጆይን ያድርጉ መጀመርያ↙️↙️↙️

@TOPBOOkSERIES
@TOPBOOkSERIES

  * ኤደን መፅሀፍት ቤት * *ሜክሲኮ ቡና እና ሻይ አጠገብ
📞 0912732493
         📞  0911340536
 
የኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን ነገ በሚከበረው የደመራ በዓል "ግጭት ቀስቃሽ፣ አንዱን የሚያሞግስ ሌላውን የሚያንቆሽሽ፣ ብዙሀነታችንን የማይገልፁ ፅሁፎች፣ በሕገ መንግስቱ ከተፈቀደው #ሰንደቅ_ዓላማ ውጪና የተለያዩ አርማዎችን" መያዝን ከለከለ።

Via:- Eshete bekele
@YeneTube @Fikerassefa
የ63 ሚሊዮን ዶላር የብድር ግምገማ ተፈረመ

ለአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን የከተማ አውቶቡስ B6 ኮሪደር ፕሮጀክት የሚውል የ63 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የብድር ግምገማ ዛሬ በገንዘብ ሚኒስቴር አዳራሽ ተፈራርመዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዘመናዊ ገመድ አልባ የምድር ለምድር የራዲዮ ግንኙነት በአዲስ አበባና ዙሪያዋ በስራ ላይ አዋለ፡፡

በስራ ላይ የዋለው አዲሱ የገመድ አልባ የራዲዮ አገልግሎት ሥርዓት የተቋሙ የጥገናና የዝርጋታ ሰራተኞች ደህንነት ይበልጥ እንዲረጋገጥ ይረዳል ተብሏል፡፡ የተቋሙ የስራ ጥራትና የሚሰጠውን አገልግሎት ከፍ እንደሚያደርገውም ተነግሯል፡፡ግንኙነቶቹ በማንኛውም ሰዓት እንዳይቋረጡ መጠባበቂያ የሀይል አማራጭ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡ “አስትሮ 25” የተባለው ይኸው ዘመናዊ የምድር ለምድር ገመድ አልባ የራዲዮ ግንኙነት ስሪቱ “ሞቶሮላ ሶሉሽንስ” የተባለው የእስራኤል ኩባንያ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ተሊላ ተቋሙ ለሰራተኞቹ ደህንነት የሰጠው ትኩረት በአለም በስፋት ጥቅም ላይ የዋለውን የግንኙነት ሥርዓት እንዲመርጥ አድርጎታል ብለዋል፡፡የሞቶሮላ ሶሉሽንስ የምስራቅ አፍሪካ ማናጀር ዩቫል አናን በበኩላቸው ኩባንያቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥራት ያለው አገልግሎት ለደንበኞቹ በማቅረብ የጀመረውን ጥረት በማገዙ ደስተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

Via Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssefa
በ2009 ከተመደበው የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ 419 ሚሊዮን ብር የደረሰው የአዲስ አበባ አስተዳዳር ሙሉውን ገንዘብ ለወጣቶች ሰጥቻለሁ አለ፡፡

በወቅቱ የፖለቲካው አለመረጋጋት ሲፈትነው የነበረው መንግሥት 10 ቢሊዮን ብርን ለወጣቶች ሥራ እድል ፈጠራ በሚል መመደቡ ይታወሳል፡፡ ከፌዴራል መንግስት የተዘዋዋሪ ፈንድ 419 ሚሊዮን ብር የደረሰው የከተማዋ አስተዳደር በመዲናዋ ለሚገኙ ስራ አጥ ወጣቶች ብሩን ሙሉ በሙሉ ማበደሩን ለአሐዱ ተናግሯል፡፡ብድሩን የሰጠው አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ያበደርኩት ገንዘብ ደንበኞቼን ትርፋማ አድርጎልኝ ከጠበኩት በላይ ብድራቸውን እየመለሱ ነውም ብሏል፡፡

ብድሩን የወሰዱ ወጣቶች እዳቸውን በአግባቡ መክፈል መጀመራቸው ተቋሙን እንዳነሳሳው ጠቅሶ፣ በያዝነው 2012ም ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ለማበደር መዘጋጀቱን ጠቁሟል፡፡ይሁንና የአሐዱ ቴሌቪዥን ምንጮች እንደሚሉት ከብድር ተቋሙ ከ1997 ጀምሮ ብድር የወሰዱ በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች ብድራቸውን መክፈል ባለመቻላቸው ተቋሙ እያፈላለጋቸው ነው፡፡የፌደራሉ መንግሥት ተዘዋዋሪ ፈንድ በምን አግባብ ለወጣቶች እንደተሰጠና ምን ያክሉ ብድርስ እየተመለሰ ነው የሚለው መረጃ ባለመታወቁ መንግሥት እንዲጣራ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

Via Ahadu Radio & Television
@YeneTube @FikerAssefa
Happening Now!

የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ንግግራቸውን በአማርኛ እያደረጉ ነው።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የቅማንት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቅዴፓ) የአማራ ክልል ልዩ ሃይል በህዝባችን ላይ ጥቃት እየፈጸመ ነው ሲል ከሷል፡፡ ኅብረተሰቡንም ያንገላታሉ፤ ያስፈራራሉ- ብሏል ባሰራጨው መግለጫ፡፡ ጳጉሜ 4 በጭልጋ ወረዳ አርሶ አደሮች ላይ ተኩስ ከፍተው ሦስት ሰዎች ሞተዋል፡፡ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች በርካታ ሰዎችንም አቁስለዋል ብሏል፡፡ ክልሉ ልዩ ሃይሉን ከቅማንት ወረዳዎች እንዲያስወጣ ፓርቲው ጠይቋል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ፌደራል ፖሊስ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ደመራ በዓል ወቅት ከሀገሪቱ #ሰንደቅ_ዐላማ ውጭ ሌሎች አርማዎችን መያዝን ከልክሏል፡፡

ፋና ብሮድካስት በዘገበው የኮሚሽኑ መግለጫ፣ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን መያዝ አይቻልም፡፡ አንዳንድ አካላት የቤተ ክርስቲያኗን ተገቢ ጥያቄ ሽፋን በማድረግ ነገሮችን ወዳላስፈላጊ አቅጣጫ ለመውሰድ እየሞከሩ መሆኑን ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa