YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ስፖርት!!

የ2019 የፊፋ የዓመቱ ምርጦች በጣልያን ሚላን ይፋ ተደርገዋል!

📌የዓመቱ ምርጥ ወንድ ተጫዋች- ሊዮኔል ሜሲ

📌የዓመቱ ምርጥ ሴት ተጫዋች- ሜጋን ራፒኖ

📌የዓመቱ ምርጥ የወንድ አሰልጣኝ- የርገን ክሎፕ

📌የዓመቱ ምርጥ የሴት አሰልጣኝ- ጂል ኤሊስ

📌የዓመቱ ምርጥ ወንድ ግብ ጠባቂ- አሊሰን ቤከር

📌የዓመቱ ምርጥ ሴት ግብ ጠባቂ- ሳሪ ቫን ቬነንዳል

📌የዓመቱ ምርጥ ግብ/ ፑሽካሽ ሽልማት ዳንዬል ዝሶሪ

📌የዓመቱ ስፖርታዊ ጨዋነት ተሸላሚ- አሰልጣኝ ማርሴሎ ቤልሳ እና ሊድስ ዩናይትድ

📌የዓመቱ ምርጥ ደጋፊዎች- ሲልቫ ግሪኮ ተሸላሚ ሆነዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መርማሪ ፖሊስ ላይ ቅጣት የጣሉት ዳኛ ጥቃት ደረሰባቸው።

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር አርማጨሆ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት አቤሴሎም ተበጀ ነሐሴ 29/ 2011 ለስምንት ተከታታይ ጊዜ የሰጡትን ትዕዛዝ ባለመፈፀም እና ችሎቱን በመድፈር አንድ የፖሊስ አባል ላይ የሰጡትን ፍርድ ተከትሎ፣ ዳኛውን ለማሰር ሙከራ የተደረገ ሲሆን ዳኛው በተፈጠረባቸው የደኅንነት ስጋት ከተማውን ለቀው እንዲወጡ ተደረገ።
በፍትሃብሔር ክርክር መዝገብ ተከሳሽ የሆኑትን አስናቀ አባተን ይዘው እንዲያቀርቡ ስምንት ተከታታይ ትዕዛዝ የተሰጣቸው ምክትል መርማሪ ብርሃኑ እንቁ ማርያም፣ ትዕዛዙን ያልፈፀሙ ሲሆን በችሎት ቀርበውም ምክንያታቸውን ለማስረዳት ፈቃደኛ አልነበሩም።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ሲ ኤም ሲ የሚያመራው የባቡር መስመር ላይ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ ወደ ሃዲዱ በመግባቱ የባቡር ትራንስፖርት ተቋረጠ!

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ወደ ሲኤምሲ የሚያቀናው መስመር ዛሬ ከነጋ ጀምሮ አገልግሎቱ ተቋርጧል። ለአገልግሎቱ መቋረጥ ምክንያት አንድ ኤፍ ኤስ አር አይሱዙ ተሽከርካሪ ለሌት ላይ በመሪና ሲኤም ሲ መካከል የባቡር አጥሩን ጥሶ ወደ ሃዲዱ በመግባቱ ዛሬ ከነጋ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት አልቻለም ሲሉ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ስራሲኪያጅ አቶ ሙሉቀን አሰፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል።

ጉዳቱ የከፋ ባለመሆኑ መኪናውን አንስተን እና ባለሙያዎች ሁኔታውን ፈትሸው በ45 ደቂቃ ውስጥ አገልግሎቱ ይጀምራል ብለዋል ስራሰኪያጁ።አቶ ሙሉቀን አያይዘውም እንዲህ ያሉ አደጋዎች በተለያዩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እንደሚከሰቱ ገልጸው ጉዳቱ ከመሰረተ ልማቱ ባሻገር ደንበኞቻችንን ለእንግልት እየዳረጋቸው ነው ብለዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ የ8ኪሎ ሜትር ተጓዥ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

በአርባ ምንጭ ከተማ ዛሬ ጧት ላይ የተካሄደው የ8ኪሎ ሜትር ተጓዥ የጎዳና ላይ ሩጫ ተተኪዎችን ለማፍራት፣ ከተማዋን ለማስተዋወቅ እና የሰላምና የፍቅር ትስስርን ለማዳበር ያለመ ነው ተብሏል።

በዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ አሊ ቢፍቶ ማላ ከደቡብ ፖሊስ አትሌቲክስ ክለብ 1ኛ ሲወጣ ፣ የግል ተወዳዳሪ የሆነው እርገጤ ኤሌ እና ልኡል ወልዴ ከወላይታ ሶዶ በቅደም ተከተል 2ኛና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

የፓን ኢትዮጵያ መስራችና ስራ አስኪያጅ የሆነችው አትሌት ፋንቱ ሜጌሶ ውድድሩን ማዘጋጀቷ ተመልክቷል፡፡

በሩጫው ላይ አትሌት ፋንቱ ሜጌሶን ጨምሮ የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ እና አትሌት መሃመድ አማን ተገኝተዋል።
የሩጫው መሪ ቃል “ትንሽ ጥላቻ ትልቅ ፍቅርን አያጠፋም” የሚል ነው።

ከሩጫው በመቀጠል በጎፋ ዞን በዛሬው ዕለትም የቋንቋ እና የባህል ሲምፖዚየም ይካሄዳል፡፡
ሪፖርተር᎓- EBC
@YeneTube @Fikerassefa
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በጋሞ ማስቃላ ክብረ-በዓል ላይ ለመታደም አርባ ምንጭ ናቸው፡፡

በወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዳጋቶ ኩምቤ የተመራ ከፍተኛ አመራር በጋሞ "ዩ-ማስቃላ" ክብረ-በዓል ላይ ለመታደም ወደ አርባ ምንጭ አምርተዋል፡፡

አቶ ዳጋቶ የወንድም ወላይታ ህዝብን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለጋሞ ህዝብ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል፡፡
የወላይታ ህዝብ በወንድም የጋሞ ህዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ላይ በመሪው መወከሉ የሁለቱ ህዝቦች ወንድማማችነት ከጉርብትናም በላይ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የአቶ ዳጋቶ ኩምቤ የአርባ ምንጭ ጉብኝት ለቀጣይ የጋሞ እና ወላይታ የህዝብ-ለህዝብ ግንኙነት መጠናከር ዓይነተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

Via:- GMN
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ መሪዎች ሸልማት ተበረከተላቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ፋርማጆ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በጋራ በአፍሪካ ቀንድ አበረከቱት ለተባለ የለውጥና የመልካም ግንኙነት አስተዋጽኦ ሽልማት ተበረከተላቸው።የኮንኮርዲያ ሊደርሽፕ አዋርድ የተባለውን ሽልማት የተቀበሉት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሲሆኑ፤ ሽልማቱ የሚበረከተው ኒው ዮርክ ውስጥ በየዓመቱ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በሚካሄደው የኮንኮርዲያ ስብሰባ ላይ ነው።

የሽልማቱን መበርከት ይፋ ያደረገው የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክትና ፎቶግራፍ ነው።የኮንኮርዲያ ሊደርሽፕ አዋርድ ውጤታማ ሥራን በማከናወን ሌሎችን አነሳስተዋል ተብለው የሚታመኑ፤ ለትርፍ ያልተቋቋሙ የሕዝብና የግል ተቋማት ውስጥ የመሪነት ሚና ለሚጫወቱ መሪዎች እንደሚበረከት የሽልማቱ አዘጋጆች በገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

Via ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
በራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት እና ዛይ ራይድ ሜትር ታክሲ መካከል ከንግድ ስም ባለቤትነት እና ከፈጠራ ባለቤትነት መብቶች ጋር በተያያዘ በተነሳው ውዝግብ ራይድ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት በንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ምርመራ ተጀመረ።

ከአራት ወራት በፊት ራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት የስያሜው የባለቤትነት መብት ይገባኛል በሚል ለኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት እና ለንግድ ውድድር እና ሸማቾች መብት ጥበቃ ባለሥልጣን ማመልከቻ ማስገባቱን ተከትሎ ነው ምርመራው የተጀመረው።
Via:- Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ ለወላይታ ዞን አቻቸው ደማቅ አቀባበል አደረጉላቸው፡፡

ም/አስተዳዳሪ ብርሃኑ ዘውዴ ለወላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ ዳጋቶ ኩምቤ እና ልዑካቸው ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡

አስተዳዳሪዎቹ የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ የተገለፀ ሲሆን በህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ዙሪያ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪ ዳጋቶ ኩምቤ በጋሞዎች ዩ ማሰቃላ በዓል ላይ ለመገኘት አርባ ምንጭ የመጡ ሲሆን የጋሞ ዞን አቻቸው በተመሣሣይ በወላይታ የጊፋታ በዓል ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

Via :- GMN
@YeneTube @Fikerassefa
አራት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በታኅሣሥ መጨረሻ ለባለሀብቶች ይተላለፋሉ

አራት ክልሎች በመገንባት ላይ የሚገኙ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በታኅሣሥ መጨረሻ ለባለሀብቶች እንደሚተላለፉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

«ክልሎች ባልተጠና መልኩ ሕገወጥ የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ መጀመራቸውም አስግቶኛል››ብሏል።
@YeneTube @Fikerassefa
የአሜሪካው ቦይንግ ኩባንያ በቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ተጎጂ ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 144 ሺህ 500 የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑ ተገለፀ።

ድጋፉ ቦይንግ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ከገባው 100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላይ የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ የሚሰጥ መሆኑም ተነግሯል።

ከአውሮፓውያኑ 2020 በፊት ለሚያመለክቱ ለእያንዳንዱ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመዶች ገንዘቡ የሚሰጥ መሆኑንም ነው ኩባንያው ያስታወቀው።

ቦይንግ ኩባንያ ገንዘቡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢንዶኒዢያው ላየን ኤይር ባጋጠመው ሁለት የአውሮፕላን አደጋዎች ህይወታቸውን ላጡ የ346 ሰዎች ቤተሰቦች እና ተፅዕኖ ለደረሰባቸው ማኅበረሰቦች መደገፊያ የሚውል መሆኑም ገልጾ ነበር።

ኩባንያው ከ100 ሚሊየን ዶላሩ ውስጥም ግማሹ ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመዶች በቀጥታ የሚከፈል መሆኑን እና ቀሪው 50 ሚሊየን ዶላር ደግሞ አደጋው ተዕእኖ ለተፈጠረባቸው ማህበረሰቦች ለትምህርት ቤትና ሌሎች የልማት ስራዎች እንደሚውል ነው ያስታወቀው።

ተጨማሪ ለማንበብ⬇️

https://telegra.ph/YYenetube-09-24
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአፍሪካ የሰላም፣ የደህንነትና የልማት ጉዳይ ላይ በመከረው መድረክ ላይ ተሳተፉ።

መድረኩ በጀርመኗ መራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የተመራ ሲሆን፥ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ተሳትፈዋል።

ውይይቱ በዋናነት በሰላም፣ ደህንነትና የልማት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የውይይት መድረኩ በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን የተካሄደ ነው።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
የዘንድሮ ዲቪ ምዝገባ መስከረም 21 ይጀምራል!

አዲስአበባ የሚገኘው የዩናይትድስቴትስ አሜሪካ ኤምባሲ እ.ኤአ. የ2021 የዲቪ ሎተሪ ምዝገባ ፕሮግራም በያዝነው መስከረም ወር እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ ስለፕሮግራሙ ዝርዝር መግለጫ ለመስጠትም ኤምባሲው ለጋዜጠኞች ጥሪ አቅርቧል፡፡ከሌሎች ታማኝ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሠረት የዘንድሮው የዲቪ ምዝገባ ፕሮግራም ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም (ኦክቶበር 2 እስከ ኖቬምበር 5 ቀን 2019 እ.ኤ.አ) ይከናወናል፡፡ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በ2021 እንደተለመደው በኦንላይን ምዝገባ የሚያከናውኑ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች የተፈቀደላቸው ሀገራት ዜጎች በዕጣ በመለየት 55 ሺ ዕድለኞችን ለመቀበል ተዘጋጅታለች፡፡

Via DireTube
@YeneTube @FikerAssefa
የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንና በዛር ዛሬ ተከፍቷል፡፡

በኤግዚቢሽንና በዛሩ ላይ የተለያዩ የኦሮሞ ባህላዊ አልባሳት፣ የባህል እቃዎች፣ ባህላዊ ምግቦችና መጽሐፍት ቀርበዋል፡፡ይህ ኤግዚቢሽንና በዛር እስከ መስከረም 23 ቀን 2012 እንደሚቆይ ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
#update

ከሃያት ጦር ሃይሎች መስመር ተቋርጦ የነበረው የባቡር አገልግሎት ስራውን ጀመረ፡፡

የተባበሩት አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ሀዲድ ውስጥ በገባ ኤፍ.ኤስ.አር ተሽከርካሪ አማካኝነት ዛሬ ማለዳ ላይ ለ2 ሰዓታት ገደማ አገልግሎቱ ተቋርጦ ነበር፡፡የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን አሰፋ ቴክኒሺያኖች ወደ ስፍራው መሄዳቸውን እና ችግሩ በአፋጣኝ እንደሚፈታ በጠዋቱ አሐዱ ልሣን ማለዳ ላይ መናገራቸው ይታወሣል፡፡ሰሚት፣ ሲ.ኤም.ሲ እና ሃያት መስመር ተጓዥ ቤተሰቦቻችንም በመስመሩ ላይ ባጋጠመው ችግር ምክንያት መንገድ በመዘጋቱ መጉላላታቸውን ገልፀውልን የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የባቡር አገልግሎቱ መጀመሩን አሐዱ ሬዲዮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ያለው የኪሎ ሜትር ገደብ ለአጭር ጊዜ ብቻ መነሳቱ ተነገረ፡፡

ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሀገር አቋርጠው የሚሄዱ ተማሪዎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳይገጥማቸው በሚል በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ያለው የኪሎ ሜትር ገደብ ለአጭር ጊዜ መነሳቱን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ተናግሯል፡፡

ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚሄዱበት ወቅት የተለያዩ ህዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚደራረቡበት በመሆኑ በትራንስፖርት አቅርቦቱ እጥረት ሲያጋጥም ነበር ተብሏል፡፡

አሁን ላይም የትራንስፖርት አቅርቦቱ እንዲሻሻል የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ከመስረከም 10/2012 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 30/2012 ድረስ ብቻ በኪሎ ሜትር ሳይገደቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

ተማሪዎች የሚጓዙባቸው የክልልና የከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ተቋማት ባለሙያዎችን በመመደብም ተማሪዎች ባልተቆራረጠ ሁኔታ በቀጥታ ወደ ትምህርት ተቋሞቻቸው እንዲደርሱ ትብብር እንዲያደርጉ ሲልም የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ጠይቋል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተቀመጠና፣ ከዚህ ቀደም ሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ለአነስተኛ ተሽከርካሪዎች 150 ኪሎ ሜትር ለመለስተኛ ከ150 እስከ 250 ኪሎ ሜትር እና ለሀገር አቋራጭ ከፍተኛ ተሽከርካሪዎች ከ250 ኪሎ ሜትር በላይ ገደብ ማስቀመጡን እና በስራ ላይ መሆኑንም ተናግሯል፡፡

በተጨማሪም በመናኸሪያዎች ውስጥ ከሚገኙ ማህበራት ጋር በመተባበር በተለይ ለመስቀል በዓል ወደተለያዩ ክልሎች ለሚጓዙ ዜጎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳይኖር ከመደበኛ ስምሪቶች በተጨማሪ ሌሎች ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚያደርግ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ሰምተናል፡፡

Via:- Shager FM
@YeneTube @Fikerassefa
የአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ከ30 በላይ አሽከርካሪዎችና ሰራተኞች ባደረጉት የስራ ማቆም አድማ ታስረው በዋስ ተለቀዋል።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
የሀዲያ የዘመን መለወጫ “ያሆዴ መስቀላ” በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት በሆሳዕና ከተማ ተከበረ።

በዓሉን ለመታደም ከሀዲያ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና ከተለያዩ አጎራች አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎችም ታድመዋል፡፡የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ “የያዴ መስቀላ” በዓል ከጨለማ ዘመን ወደ ብርሃን መሸጋገሪያ ላይ መደረሱን የሚበሰርበት በመሆኑ የሀድያ ህዝቦች 2012ን በአዲስ ተስፋና ብልፅግና ለመቀበል ስንቅ የሚሰንቅበት ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ማስታወቂያ ⬆️ ሀዋሳ ⬆️

ዩንቨርስቲ ለሚገቡ እና ከዚህ ቀደም ለገቡ ተማሪዎች!!

@YeneTube @Fikerassefa
ሰበር ዜና | የፕሪምየር ሊጉ አዲሱ ፎርማት ውድቅ ሆነ!

ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2012 የውድድር ዘመን 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ከፍሎ እንዲደረግ የወሰነው ውሳኔ ውድቅ ሆነ።
የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን የዘጠኙ የክልልና የ2ቱ ከተማ መስተዳድር እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንቶች፣ የስፖርት ኮሚሽን አመራሮች እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አመራሮች በተገኙበት የውይይት መድረክ ከብዙ ውይይቶች በኋላ ነው ውሳኔው ውድቅ የሆነው።እንደ ምክንያት የቀረበውም ጥናት ያልተጠናበት እና የክለቦችን ይሁንታ ያላገኘ በመሆኑ እንዲሁም ህዝብን ከህዝብ የሚለያይ በመሆኑ እንደሆነ ሰምተናል።በቀጣይ ሊጉ በምን መልኩ ይቀጥላል የሚለው ጉዳይ ክለቦቹ ተመካክረው እንዲወስኑ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

Via Soccer Ethiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በ2011 በጀት ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች የ1 ሺህ 229 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንዳስታወቀው በ2011 በጀት ዓመት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ የ1 ሺህ 229 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤በ1 ሺህ 393 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስ በ19 ሰዎች ላይም የግድያ ሙከራ ተፈጽሞባቸዋል። በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት በተጠቀሰው ዓመት በተፈጠሩ ግጭቶች ላይ በተሳተፉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡

በነዚሁ ግጭቶች ሳቢያም ከሁለት ቢሊየን በላይ ብር የሚገመት የዜጎች ንብረት የወደመ ሲሆን፤1 ነጥብ 2 ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸውና ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል።በዚህ ግጭት የተሳተፉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቶ ከእነዚህ መካከል 645 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ሲሆን 667 ተጠርጣሪዎች እንዳልተያዙ ተገልጿል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል በጃዊ ወረዳና በመተክል ዞን ፤በጎንደርና አካባቢው በተፈጠረ ሁከትና ብጥብጥ፤በሰሜን ሸዋ አስተዳደር እንዲሁም በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ከማሻ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎችና የዚሁ ዞን አጎራባች በሆነው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞን በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ በተፈፀመ ብጥብጥና ሁከት በአሶሳ ዞን አራት ወረዳዎች ውስጥ በኦሮሚያና በበርታ ብሄረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት ተሳታፊ ከነበሩ 1 ሺህ 647 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 185 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

Via Federal Attorney General
@YeneTube @FikerAssefa