YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ለሚገኙና የህክምና እርዳታ ማግኘት ለማይችሉ ዜጎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ማዕከል መከፈቱ ተነገረ፡፡

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ በአዲስ አበባ በሚገኙ ጎዳናዎች ላይ ያሉ ዜጎችን ለመርዳት ተቋቁሟል የተባለው ክሊኒክ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት የተቸገሩ በጎዳና ላይ ላሉ ዜጎች የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ነው ሲሉ የነገሩን የሆስፒታሉ ዋና ፕሮቮስት ዶ/ር ወንድምአገኝ ገዛኸኝ ናቸው፡፡

ተጨማሪ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ከሆነም ከአዲስ አበባ የጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ወደ ሆስፒታሎች ሪፈር እንዲፃፍላቸው በማድረግ አገልግሎቱ እንዲሰጥእና በተጨማሪም በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ዜጎችም በተመሳሳይ አገልግሎቱ እየተሰጠ እንደሆነ ዶ/ር ወንድማገኝ ነግረውናል፡፡የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በተጨማሪም በማህበራዊ አገልግሎት የካንሰር ህክምና ለመከታተል ከተለያዩ ሀገሪቱ ክፍሎች ለሚመጡ ህሙማን የሚያርፉበት እና የምገባ አገልግሎት የሚያገኙበት ማዕከል መክፈቱንም ሰምተናል፡፡

Via Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssefa
(ሕወሓት) እና (አዴፓ) ቅራኔን በተመለከተ “በአዲሱ ዓመት ችግሮቻችን በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀመጠን ተወያይተንና ተግባብተን ለመፍታት ዝግጁ ነን” ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስሀን ጥሩነህ ተናገሩ።

አቶ ተመስገን ይህን ያሉት አዲሱን 2012 ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመላው ብሔር ብሄሰቦችና በተለይም ለአማራ ክልል ህዝብ የመልካም ምኞት መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት ነዉ። እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ ችግሮችንን ለመፍታት ዝግጁ ነን ያሉት አቶ ተመስገን ፤ ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከ(ሕወሓት) ወገንም ተመሳሳይ ፍላጎት ይኖራል ብለው እንደሚያምም ገልፀዋል፡፡ በአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር መኖሩን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳደሩ በአዲሱ ዓመት ለአንድ ሚሊዮን ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን ይፋ አድርገዋል። አዲሱ ዓመት ለመላው ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ በተለይ ለአማራ ክልል ህዝብ የሰላም፣ የብልፅግናና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የቻይናው ኩባንያ የቤተ መንግሥቱን የመኪና ማቆሚያ 1.5 ቢሊዮን ብር ሊገነባ ነው።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሻሽነት ወደ ሙዝየም በመቀየር ላይ ላለው ብሔራዊ ቤተመንግሥት የመኪና ማቆሚያ ለመገንባት ከተወዳዳሩት ኹለት የቻይና ግንባታ ኩባንያዎች መካከል ቻይና ጂያንግ ሱ ኮንስትራክሽን በ1.5 ቢሊዮን ብር ውል ፈፀመ።የአዲስ ኣበባ ኮንሰትራክሽን ቢሮ በቤተ መንግሥቱ ግቢ ውሰጥ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ሙዚየም ለመጎብኘት ለሚመጡ ጎብኚዎች ከቤተ መንግሥቱ ፊት ለፊት የሚገነባው ይህ የመኪና ማቆሚያ ግንባታ ወጪ የሚሸፍን ይሆናል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
መስከረም 4፤2012 ዓ.ም የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመለክተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት መግለጫ ሰጡ፡፡

መግለጫውን የሰጡት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በቤተክርስቲያን እየደረሰ ያለውን የመቃጠል፣ የካህናት መገደልና ሌሎች በቤተክርስቲያንቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን አስታውቋል፡፡ሰልፉን በማስመልከት ዝርዝር መግለጫዎችን በመስከረም 2፤2012 ዓ.ም እንደሚሰጥ የገለጹት ኮሚቴዎች፣ የነበራቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ከመንግስት አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሆነና በውይይቱ አጥጋቢ መልስ ካገኙ ሰልፉ ሊቀር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ማህበራቱ የሰላማዊ ሰልፍ መካሄድ አለመካሄዱንም በቀጣይ መስከረም 2 በሚኖረው ድጋሚ መግለጫ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል ሰልፉ ከኦሮሚያ ክልል ቤተክህነት ምስረታ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ በመጠቆም ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምስረታ ጋር በተያያዘ በጉዳዩ ዙሪያ በቅርቡ ሲኖዶሱ የሰጠው መግለጫ በቂ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ሰልፉን ለማዘጋጀት ከባለፈው አንድ ወር ጀምሮ እየተንቀሳቀሱ እንደቆዩም የጠቆሙ ሲሆን፤ የሰልፉ አላማም በሰላማዊ መንገድ በቤተክርስቲያኒቷ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የታቀደው ሰልፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሆንና ህዝበ ክርስቲያኑ ከቤተክርስቲያንቷ ጎን እንዲቆሙም ጠይቀዋል፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የአፍሪካ የፖለቲካ አማካሪዎች ማኅበር ሽልማት አበረከተላቸው።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ኬሂንዳ ባሚግቤታን ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ማሻሻያ አድርገዋል።በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችና እስረኞች እንዲፈቱና በውጭ የሚኖሩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ወደ አገራቸው በነጻነት እንዲመለሱ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።ወደ አገራቸው ከመጡ በኋላም ከፖለቲከኞቹ ጋር ተቀራርበው መስራታቸውንና ከምሁራን ጋርም የፖለቲካ ከባቢ መፍጠራቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።ማኅበሩ ከዚህ ቀደም ለሁለት ናይጄሪያዊ ፖለቲከኞች ተመሳሳይ ሽልማት ሰጥቷል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ይህንን ሽልማት ሲቀበሉም ሦስተኛ ግለሰብ ናቸው ብለዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነባር የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት መስከረም 8 ቀን እንደሚጀምር አስታወቀ።

ዩንቨርሲቲው በማህበራዊ ድረገጹ እንዳስታወቀው የ2012 ዓ.ም ቅድመ ምረቃ ነባር ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 5 እና መስከረም 6 ይካሄዳል።እንዲሁም ነባር የድህረምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑንም አስታውቋል። በተጨማሪም ለነዚሁ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀመረዉ ሐሙስ መስከረም 8 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እወቁልኝ ብሏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2
የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በአዲሱ ዓመት የግብር አከፋፈል ስርዓቱን ዲጂታል ሊያደርግ እንደሆነ አስታዉቋል።

አዲሱ አሰራር የግብር ከፋዩን ጊዜ ከመቆጠብ ባሻገር የመንግስትን ገቢ በማሳደግ ረገድ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል ።ባለስልጣኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 18 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ ከ19 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉንን አስታውቋል።

Via ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ሞስኮ በሚገኘው የሩሲያ ፌደሬሽን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በሁለቱ ሃገራት ሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስገባሁትን የኔትዎርክ መጨናነቅን የሚያቀል ታወር ተክዬ ስራ አስጀምሬአቸዋለሁ አለ፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
#ሰበር_ዜና

የዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል ተብሏል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብ ነገ ረፋድ ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ ከፍተኛ ምግብ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ክልሉ ማስጠንቀቁን ሸገር ዘግቧል፡፡

ለምግብ ዕጥረቱ የሚጋለጡት ግጭትና የሕገ ወጥ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ የታየባቸው አካባቢዎች እንደሆኑ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል ተብሏል፡፡ በደምቢዶሎ፣ ጊምቢ፣ ጉጂና ቦረና የልማት ሥራዎች ዘለግ ላለ ጊዜ ተስተጓጉለዋል፡፡ የወለጋ ገበሬዎች ቡናቸውን መልቀም አልቻሉም፡፡ ባለሃብቶችም ከአካባቢዎቹ ለቀዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሃያላን ሀገራት በጅቡቲ ወታደራዊ ጦር ሠፈር ማቋቋማቸው ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ደኅንነት ስጋት ፈጥሯል- ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ለኢትዮ ኤፍ 107.8 በሰጡት ቃል፡፡ መንግሥት ጉዳዩን ከሌሎች የኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በመሆን እየተከታተለ ነው፡፡ ኢጋድም ሁኔታውን ለመከታተል ግብረ ሃይል አቋቁሟል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 7 ቀናት በገቢና ወጭ ኮንትሮባንድ ግምታዊ ዋጋቸው 34,345,944 ሚሊየን ብር የሚገመት ዕቃ ተያዘ፡፡

ባለፉት ሰባት ቀናት በገቢ ኮንትሮባንድ 23,460,355 ሚሊየን የሚገመት ዕቃ ተይዟል፡፡ከነዚህ መካከል አዳዲስ አልባሳት፣ምግብና መጠጦች፣ሲጋራና ትንባሆ፣ኤሌክትሮኒክስ፣የጦር መሳሪያ እና የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ይገኙበታል፡፡በሰባቱ ቀናት በወጪ ኮንትሮባንድ 10,885,589 ብር የሚገመት ዕቃ ተይዟል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
People living in extreme poverty, as share of world total.

Nigeria: 15.7%
Congo: 10%
India: 8%
Ethiopia: 4.6%
Tanzania: 3%
Bangladesh: 2.3%
South Africa: 2.3%
Indonesia: 2.1%
Yemen: 1.6%
Brazil: 1.1%
China: 0.9%
Pakistan: 0.3%
US: 0.3%
Mexico: 0.3%

(World Poverty Clock)
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2