ወግ ብቻ
17.9K subscribers
513 photos
11 videos
21 files
51 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch
@zefenbicha

Creator @leul_mekonnen1
Download Telegram
ማሪታ ሎሬንዝ

ዘመድ አይጥፋ ባለፈው ዙምባቤ ሐረሬ ዞር ዞር ስል ትንሽ ሃገሬ ብትናፍቀኝም ጓድ መንግስቱም እንኳን ተወለዱ ለማለት  እቤታቸው ጎራ አልኩኝ ።

ፍልቅልቋ ባለቤታቸው ወ/ሮ ውብባንቺ ቡና  አፍልተው እያጫጫሱ ሳለ በአይኔ የፊደል ካስትሮን እና  የጓድ መንግስቱ  ፎቶ ስቀላውጥ አይተው "ጥቁር ነብር " ሚላቸው በአሉ ግርማ  ጓድ መንግስቱ ፊታቸውን ጠቆር አርገው የማየውን ካጤኑ በኃላ

ይገርምሃል  ያኔ ሁለታችንም የበዛ የሃገር ፍቅራችን እራሳችን ላይ ወቶ ካቲካላ እንደጠጣ ሰው በሰከርንበት ጊዜ ነበር ይሄን ፎቶ የተነሳነው ብለው ላፍታ ትክዝ አሉ።

እንግዲ ወዳጄም አይደል እቺ ሰዓት ምን እያወራን መሰለክ ብለው የትዝታ ፈገግታ ብልጭ አረጉና ጉሮሮዋቸውን ጠራርገው እንዲ ሲሉ ጀመሩ ....

ስለ ሴት እያወራን ነበር ለዛውም ስለ ጉደኛ ሴት ...

ካስትሮ ሞት በቃኝ ካንተ ጋር ትግል ደከመኝ ስለተባለለት ከ600 በላይ ጊዜ የግድያ ሙከራ ስለተደረገበት የኔ ወዳጅ ፣ የህፃናት አንባ ልጆች አጎት፣ የኤርኔስቱ ቼ ጉቬራ የትግል ጎደኛ  ፣  ፣የሶሻሊስት አጥማቂ፣ የአሜሪካ ራስ ምታት ፣ ከከበርቴ ቤተሰብ የተገኘው የበኩር ልጅ ፣ የውቧ ኩባ ባላባት፣የራሁል ወንድም ፣ ፊደል ካስትሮ እንዴት ከሞት አፋፍ ስንት ጊዜ እንዳመለጠ አጫውትሃለሁ አሉኝ በኩራት ።

  በተለይ ደሞ ከሴት ወጥመድ እንዴት እንዳመለጠ ብታይ ብለው ወደጣሪያው እያዩ ወገባቸውን ወደ መደገፊያው አሳረፋ።

ነገር ጎንጓኟ አሜሪካ ልታስገድለው ያልቆፈረችው ጉድጓድ አልነበርምና

በEisenhower 38 ጊዜ፣በKennedy 42 ጊዜ፣በJohnson ፣በNixon፣በReagan ፣እንዲሁም በBush እና በClinton ጊዜ ጨምሮ ከ635 ጊዜ ሚሆን የግድያ ሙከራ የተደረገበት ብርቱው ሶሻሊት ነበር ፊደል ካስትሮ የኃላ ኃላ አሜሪካ ሴት ላከችበት!

አሉና ወደባለቤታቸው ዞር ብለው የፍቅር አዪዋት

ወ/ሮ ውብባንቺ አሄሄሄሄ ስለዛች ጉደኛ ስለ"ማሪታ" ልታወጋው ነው አሉ ፊታቸው ሙሉ እየሳቀ ።

"marita lorenz" እቺ ሴት  የጀምስ ቦንድን ሴቶች ምታስንቅ ቆንጆና በ25 ዓመታት የስለላ ታሪኳ ገዳዬ ገዳዬ ተብሎ የተዘፈነላት ቀላች እንጂ የሙት መንፍስ ስጋ ለብሶ በላት ።

ከጀርመን አባቷና ከአሜሪክዊት እናት የተወለደች የCIA ግርፍ ነች ብለው አከሉበት ።

ማሪታ ሎሬንዝ ምንትስ በተባለ መርስ ልትገለው ባንድ ክፍል ውስጥ እራሷን ከቁመተ ለግላጋው ከፊደል ካስትሮ ጋር ተገናኘች ቀድሞውኑ ቀልቡ የነገረው ፊደል ካስትሮ ቁልቁል እያያት እንድትገይኝ  ነው አይደል የላኩሽ አላት ፀጉሩዋን እየደባበሰ ።

" ቼ" አለችው በስፖኒች ቋንቋ "የኔ" ማለት ነው አሉ ጓድ መንግስቱ በእንክሮት ቃሉን ረገጥ አርገው ።

ማሪታ ሎሬንዝ ተንሰፈሰፈች ልገልህ አልችል   አለችው
( Quiero esta noche contigo un gastado papi ) አለችው

ትንሽ ማስተካከያ ታክሎበት

"ካንተ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት"

ማለቷ ነው ብላ ከደረቱ ተለጥፋ ትኩስ እንባ በጉንጮቿ አወረደች ።

ጓድ መንግስቱ ወደኔ እየተጠጉና ሚስታቸውን አፈር እያሉ  "የኩባ ሴቶች በደንብ ካረካቸው እና የልባቸውን ካደረሱ
የእርካተ ጣሪያ ላይ ሲወጡ በነሱ ቋንቋ  "Carico papi"  ይላሉ አሉኝ ይህም ነጮቹ Am coming ሚሉት ነው ብለው በሳቅ ፈነዱ ።

እትዬ ውብአንቺም አንቱ !

ዘንድሮም አላረጁ አሉ በባላቸው ቅብጥብጥነት አየሳቁ።

ከነዚህ ሁላ የግድያ ሙከራዎች መክሸፍ ምን እንዳዳነው ገምት እስኪ ጃል ? አሉኝ

አይናቸውን አጨንቁረው መልሴን በመጠባበቅ።

እኔም የግል ጠባቂዎቻቸው ብርቱና ንቁ ናቸው ብዬ አስባለሁ አልኩ ጥርጣሬ ባዘለ ድምፅ

ልክ ነክ አሉ ጓድ መንግስቱ ፈገግ እያሉ አንዱ እሱ ሲሆን ግን ዋነኛው የሱ ደመ ነፍስ ነበር ።

ደመ ነፍስ ? አልኩ ጥያቄ ባላው ድምፀት

ጓድ መግስቱም ቀጠል አረገው ፊደል ካስትሮ ቡና ይወዳል እሱን ካልጠጣ እና ያንን ግንድ ሚያክል ወይራ ወይራ ሚል ሲጋሩን(Cigar)አፋ ላይ ካላረገ ስራ አይሰራም ።

አይኑም አይገለጥለትም አሉ ጥቁሩ ነብር ።

የነሱ ቡና እ'ንደኛ እንዳይመስልህ ቦንብ ነው ፣ቦንብ ሚጠጣው እራሱ ባረቄ መለኪያ ነው ።

አንዴ እሷን ቋ  ካረገ ሁሉ ነገር ወገግ ብሎ ይታየኛል ይላል ፤ አሉ ጓድ መንግስቱ  አይናቸውን ወደ ፎቶው ቡዝዝ አርገው ።

እናሳ በምን ተቋጨ የሲቲቱ ጉዳይ አልኩ መጨረሻውን ለመስማት ጓጉቼ

በዚህ ሰዓት ሁሉ ነገሬ ጆሮ ሆኖ ነበር ።

ሳትገለው የፍቅሩን አዙሪት አልቻልኩም ብላ ወደ ሃገሯ አሜሪካ ሄደች ።

ማሪታ ሎፔዝ ልገለው አልቻልኩም ብላ CIA ን ግን ዋሸች ።

አንድ ልጅ ወልዳለታለች ይባላል አሉ እሱ ግን ውሸት ነው ይላል አሉ ጥቁሩ ነብር ።

የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው የለው ብለው ሚስታቸው ውብባንቺ በነገር ጎሸም አርጓቸው ።

ጓድ መንግስቱም ዞር ብለው ሚስታቸውን እስቲ ተይ ...ተይው ዓለሜ አሏትና በረጅሙ ተነፈሱ ።

የራሳቸው ትዝ ሳይላቸው አልቀረም

ብቻ አሜሪካም ልትገለው እንደቋመጠች በ90 ዓመቱ ዓረፈ አሉኝ ጥቁሩ ነብር ደግመው ፎቶውን እያዩ።

እኔም ፎቶውን ደግሜ ሳየው ፊደል ካስትሮ

"ገደገድኩባት " ሚሉ ነው ሚመስሉት ።

By Ermias frew

@wegoch
@wegoch
@paappii
54👏5👍4🔥2😱1
መፈቀር ደስ ይላል

ለስለስ አርጌ ነው ማልወደውን ተይ የምላት በትህትና እሺ ትለኛለች እሺታዋ ውስጥ መብትህ ነው ስልጣን አለህ ስትለኝ የሚሰማኝ ስሜት ጥልቀቱን እወድላታለሁ ::

አስሬ እየደወለች እንደልጅ እየተፍነከነከች  ሲያሻትም እያጉረመረምች እየተበሳጨች ያጋጠማትን ነገር ትኩስ ዜና ደውላ ስትነግረኝ ድምፆ ላይ ያለው ቃና እውነተኛ ስለሆነ በፍፁም ልቤ ነበር ምቀበላት ::

ማታ ማታ

ጀንበር ከመሰለው ከንፈሯ መንፈስን ቀላቅላ እፍፍፍ ትልብኛለች እንደ ቡችላላ ስፍስፍ ትላለች ከነብሴ ትጣበቃለች እኔ ደሞ እፉዬ ገላ እሆናለሁ ፍፍፍ ባለችኝ ቁጥር ወደሰማይ በነፍሴ እቃትታለሁ::


እንደምትወደኝ ስለምታሳየኝ የሚሰማኝ ሰላም ወደር አልነበረውም አንዳንድ ቀንማ ስትንከባከበኝ "ከክሽ ክሽ”በኃላ ቢሆንም ንጉስ ባልጋው ሳለ ሚጎማለለውን ምተውን ይመስለኛል ::

ስትጨነቅልኝ ደሞ ደበረኝ ካልኳት አመመህ እንዴ ብላ ፊቷ  ላይ ያለው መረበሽ አንጀቴን ይበላዋል እንደ ታናሽ ወንድሟ ስትሳሳልኛለች እንደ ቆሎ ጓደኛዋ ስታሾፍብኛለች እንደ እናቷ (አባቷ )  ስትሰማኝ አይይይይይ... እላለሁ እናቴ የመረቀችኝ ምርቃት ደርሶ እንጂ እንደኔ አመል እንደኔ መደመር መቀነስ ሚጢሚጣ በቃሪያ የሆነች ልጅ ነበር ሚገባኝ ።

የሆነው ሆኖ መፈቀር ደስ ይላል ::

By ኤርምያስ ፍሬው

@wegoch
@wegoch
@paappii
88🔥8👏3🥰2
"እናቴ ሁልጊዜ 'ደህና ነህ? ደህና ነህ?' ማለት ታበዛለች" አለኝ። ገና ከመግባቱ ። ጓደኛየ ነው፣ አብረን እንሰራለን። እናቱ ጋር አውርቶ ገና ስልክ መዝጋቱ ነበር። ሁልጊዜ ጧት ጧት ያወራሉ።

"እናት አይደሉ" ከማለቴ ፈጠን ብሎ
"ኖ ኖ ከኖርማሉ በዛ ይላል የሷ! በኋላ ስትነግረኝ በተወለድኩ በሁለት ወሬ አንዲት ደንቃፋ ሰራተኛ ትልቁ ባለአበባው የቡና ስኒ ታውቀዋለህ? ያ ስኒ አምልጧት ጭንቅላቴን ነርቶኝ ነበር። እና እናቴ የሆነ የአዕምሮ ችግር ይፈጠርብኛል ብላ ስትጨነቅ ነው የኖረችው። እንደምታየኝ ተርፊያለሁ! እሷ ግን እስከአሁን አታምንም። አለና ተሳሳቅን።

ወደቡና ማሽኑ ሄዶ ሁለት ቡና ይዞ መጣ ...አንዱን ዘረጋልኝ። ቡና ማቆሜን ለሃያኛ ጊዜ ትላንት ነግሬው ነበር። እንደገና ሳስታውሰው ሳቀና "እናቴ እውነቷን ነው መሰል አንተ?" አለ።

"እንደገና ደውልላቸውና ሰራተኛዋ የቡና ስኒ ነው ወይስ ዘነዘና የጣለችብኝ ብለህ ጠይቅ" ዝም አለ። የመልስ ምት እያሰበ ነው። ሲያስብ ትንሽ ይዘገያል ስኒው መሰለኝ። ቆይቶ

"ሰራተኛ ነበራችሁ" አለኝ
የለንም
ስኒስ ?
የለንም
ዘነዘናስ?
የለንም
በቃ አንተ ራስህ ሲያቅፉህ አምልጠህ በጭንቅላትህ መሬት ላይ ወድቀህ ነበር። 😁

By alex abrham


@wegoch
@wegoch
@paappii
😁7019👍1
ገደልኩት

ወሎ መስታወትን "መታዘቢያ" ይለዋል።

ራስን መመልከቻ፣ እድፍን ጉድፍን ማያ፣ ከራስ ጋር ማውጊያ መሆኑን አይቶ።

እውነት ነው !

ወርሃ ግንቦት  ከረጅምና አሰልቺ ቀን በኃላ
እቤቴ ውስጥ ካለው ሙሉ ገፅታዬን ከሚያሳየው መስታወት ፊት እርቃኔን በትካዜ ቆምኩ ፍዝዝ ብዬ እራሴን በእዝነት ተመለከትኩት ።

እኔ ለእኔ አዘንኩ መስታወቱ ውስጥ ያለው የራሴው ምስል አይኑ እንባ አቅርሮ ታየኝ በአይኑ የሆነ ነገር ይለኛል መናገር ማይቻል ቡቡ ልጅ ፊት እያሳየ ሆዴን ያባባኛል::


መስታወቱ:- እባክህ ዛሬም በዛ ባማይረባ ፍቅር በሚሉት ዝባዝንኬ ወሬ እኔንም ልብህንም ማሰልቸት ተውና ስለ ካሳኖቫ እናውራ ስለቬነስ ፈገግ እያልክ አጫውተኝ አለኝ ? ..........
ደሞ መጪው ክረምት ነው ፊትህን አታዝንበው !

እኔ :-የኔና የሲፈን የፍቅር ህይወት እራሱ እኮ ሃምራዊ ቀለም ነው ስለሱ እናውራ አልኩት::

መስታወቱ :-እንዴት አንድ ሰው  ጥንካሬም ድክመትም ይሆናል ?
ሲልህ ትልፈሰፈሳለህ ሲልህ ዘራፍ አርበኛው አያቴ ተጉሉት ምናምን ትላለህ ምንድነው ችግርህ ?

እኔ:- እኔ አላውቅም ....ብቻ እኔ ማውቀው የማትደራደርባቸው ነገሮች ተብዬ ብጠየቅ ከመልሶቼ መሃል  አንዱ እሷ ነበረች።

ሲፈን  እንዴት እወዳት ነበር መተው በማልችልበት ልክ እወዳት እደ'ነበር አተም ታውቃለህ !

እራስ ወዳድ እንዳልባል እየፈራው እንጂ አሁንም ድረስ እኮ እወዳታለሁ የእኔ እንድትሆን እፈልጋለሁ !
ለዘግ ላለ አመታትም አብረን ብንቆይ ሳልጠግባት ነው የተለያየነው::

መስታወቱ:-ምን ለያችሁ ታዲያ ?

እኔ:- ሁኔታዎች ድንግት ኑሮ ሚሉት ደራሽ ወንዝ ወሰደብኝ አልኩ እያቀረቀርኩ::

ከውጪ ሚሰማው ዝናብ የኔን ሃዘን የሚስደርስ የቅርብ ወዳጄ ነው ሚመስለው ሰማዩ ያነባዋል  ያንዠቀዥቀዋል !


መስታወቱ :- አንዳንዴ መለያየት ሳይኖርብህ ሁኔታዎች ይለዩሃል" እጣ ፍንታ ነው ምርጫ"የሚያስብሉ የህይወት መንታ መንገድ ጋር ትቆማለህ !

እሱን መረዳት አለብህ !

ከልክ እና ከስህተት ባሻገር አንድ ሜዳ አለ - እዛ እንገናኝ ትልሃለች  ዓለም ዱላዋ ይሰብርሃል ::
 
ስለዚህ እውነታውን መቀበል ነው ያለብህ ብትሸሽም ሲከተልህ ይኖራል እንጂ አታመልጠውም አለኝ ጎርነን ባለ ድምፅ ::

መብረቁ ተስረቀረቀ  የራሴው የሳግ ድምፅ መሰለኝ ።

ሳለላስበው በጉንጮቼ እንባ እየወረደ ነበር የአለም ዱላ ልቤን ቀጠቀጠው ::

መስታወቱ:-በአሽሙር አፉን አጣሞ ፈገግ አለ ደስ አለው ይህን ቀን እንደሚመጣ ነግሬህ ነበር አልሰማኽኝም ነበር አለኝ ::

ይሁን አሁንም ዋናው ምክር መስማትህ ነው እ'ውስጥህ ያለውን አንተነትህን ግደለው መሞት ይፋልጋል ፣ሸኘው አለኝ ...

እኔ:- በመስኮት አሻግሬ ተመለከትኩ ያንን ብዙአየሁን ከውስጤ ልገለው ተመኘው !


ዛሬዬ የተሰራው በእሷ ትላንትናዬ ውስጥ በመኖር ነው :: 

እንዴት ላርግ ያኛው ቡዙአየሁ እኮ መልካም ሰው ነው ፈገግታ ከፊቱ ማይጠፋ እምነት ፣ተስፍ ፣ፍቅር አብረው ፀንተው ይኖራሉ የሚል ደግ ሰው ነው አልኩት ::

መስታወቱ:- አየኽው ያኛው ብዙአየሁ ምን እንደሰህ?

ለማንም አልሆነም ላንተም አልበጀህም  እሷንም ለሰቀቀን እና እራሷን እንድትጠላ ነው ያረካት  ::

መስታወቱ:-ተዋታ በቃ ትቅርብህ

እኔ:- እንዴት ልተዋት

መስታወቱ:- ወንድ ልጅ አይደለህ ?
ቁረጥ ምድነው ገብርዬን ያጣ ካሳ ምትሆነው ቆፍጠን በል !

የነገን ማን ያውቃል ምን ይዞልህ እንደሚመጣ ?

እኔ:- አቤት እ/ር ግን ማኖር ሲያውቅበት !

ተመስገን🤲 በረጅሙ ተነፈስኩ::

እኔ:-አብቅቷል ካልኩ በኃላ ወጣልኝ ባልኩ ማግስት የትዝታ ፈረስ የኃሊት እያስጋለበ ከተጓዝኩት መንገድ ዳዴ እያስባለ ይመልሰኛል

አብረን የሆነው ሁሉ ይናፍቀኛል

መስታወቱ:-ብትመጣስ  ?

እኔ:- አላውቅም ግራ ያጋባል ግን ሲመስለኝ እንደዛ የሚል ተስፋ አይደል የሚያኖረኝ አንዳንዴ ህይወት የምታምረው ፣እንደ ሲፈን ጡት ምታጓጓው ከፊት ተስፋ ከኃላ ትዝታ ሲኖራት ነው ::

መስታውቱ:- ተስፋ እና ህልም ብቻውን እኮ እንደቆመ ውሃ ነው ይሸታል!


በልብህ ያለው ፍቅር የማይሞት ህልም ቢመስልህ ፣ ብትውተረተርም፥ የሚጨበጥ ያለ መስሎህ ብትዋትትም ፥ ምናልባትም እሷ ቆይታ ይሆናል ከገደለችህ ፤

ውስጥህ ያለው ፍቅር እኮ እድትገለው እየቃተተ ነው  ! አለኝ ለመተንፈስ መቸገሬን አይቶ ...


እኔ :-

ተለያየለን ፣ገደልኩት ፤መስታወቱን ሰበርኩት።

ከዚህ ቀን በኃላ የዚህ የህይወቴ ገፅ እንደመስታወቱ ፊቴንም ቆንጥሬ እንደማይበት ሁሉ የሲፈንም ታሪክ ቁንፅል ነው ታሪኳ፣ሽርፍራፊ ነው ትዝታዋ፣የደበዘዘ ነው መልኳ።

ጊዜ የዳበሰው ትዝታ !

ከኤርምያስ ፍሬው

@wegoch
@wegoch
@paappii
62😢1
ቦግ እልም!
(አሌክስ አብርሃም)

በደርጉ ዘመን «ዕድገት በህብረት » የሚባል ዘመቻ ታውጆ ነበር አሉ። በየዩኒቨርስቲው ያለው ተማሪ በየገጠሩ እየሄደ ህዝቡን እንዲያስተምር፣ እንዲያነቃ ነበር ዘመቻው! ከዘማቾቹ ፍልስፍና ቢጤ ያነበበ ተማሪ ይሄድና አንዱን በሰላም የሚኖር አርሶ አደር "ፈጣሪ የሚባል ነገር የለም አጉል እምነት ነው» ይለዋል! ማለት ብቻ አይደለም የተማረ የሚታመንበት ዘመን ነበርና በመረጃና በማስረጃ ያንን ሚስኪን ገበሬ ራሱን አዙሮ አሳመነው! ገበሬው «በቃ ፈጣሪ የሚባል ነገር የለም » አለና ከቤተክርስቲያን ጠፋ! ለሌለ ሲኦል በከንቱ ነው ስፈራና ስጋየን ስጨቁን የኖርኩት አለና ጠጁን እየጠጣ፣የስጋ ነገሩን እንዳማረው እየፈፀመና እርሻውን እያረሰ ሲኖር ሲኖር ሲኖር ዘመቻው አልቆ ልማት የሚያለሙ ሚሽነሪዎች እዛው ገጠር ሄደው ያንኑ ሰው አገኙት «ፈጣሪ አለ፣ እንደውም ለአንተ ብሎ ሙቶ ተሰቅሎ . . . » ብለው ክፉኛ ሰበኩት፣ አመነ! ቤተክርስቲያን በስንት ጊዜው ሲሄድ «ምነው ከግዚሃር ቤት ጠፋህ» ቢሉት
«እኔማ ምን መጥፊያ አለኝ፣ እግዜሩ ራሱ በየተራ ሰው እየላከ ቦግ እልም ያደርጉብኛ እንጅ» አለ አሉ!

By Alex abrham

@wegoch
@wegoch
@paappii
😁8623👍7🔥2😢1
እንደቆመብኝ ዓለም አይቶኝ ቢሆንስ ?
(አሌክስ አብርሃም)

ይሄ የተረገመ ኮሮና ሳያጠፋፋን በፊት አንድ ሶሪያዊ ጓደኛ ነበረኝ …ከመሬት ተነስቶ ኢትዮጲያን ይወዳል …በተገናኘን ቁጥር ግብፅን ተባብረን እንረግማለን እናማለን ! አገሩ የዩኒቨርስቲ መምህር ነበር ፣ወሬን እሱ ያውራት! ስንትና ስንት መከራ አልፎ ነው አሜሪካ የገባው ግን ሁልጊዜ ሳቅ ከፊቱ ላይ አይጠፋም አወራሩ ራሱ የሆነ ድራማ ነው የሚመስለው ….

‹‹ሚስቴ ጋር የተለያየነው የጋብቻችን ቀን ማታ ነው ›› አለኝ

‹‹አግብተህ ነበር ?››

‹‹ታዲያ! ያውም አይኖቿ እንደዳይመንድ የሚያንፀባርቁ ….ሳቋ ልብህን እንደሳሙና አኩረፍርፎ የሚጨርስ …የእጆቿ ጣቶች እንደባህር እንጉዳይ የሚስልከለኩ ….ከንፈሯ …የሚሳም ሳይሆን እንደአቮካዶ ጁስ በወፍራሙ ፉት የሚባል ዓይነት ….››
አገላለፁ አማሎኝ ‹‹እህት አላት ?›› ልል አስቤ ከአፌ ላይ መለስኩትና

‹‹እድለኛ ነህ ›› አልኩት

‹‹አይደለሁም ባክህ !››

‹‹ምነው? ››

‹‹የጋብቻችን ቀን ማታ … ከተማችን ውስጥ አለ ወደሚባል ኢንተርናሽናል ሆቴል ነበር የሄድነው …እዛ ነው ክፍል የተያዘልን …ሰፊ ይሄን አዳራሽ የሚያክል ክፍል ! በአበባ በተሞላ ክፍላችን ውስጥ ገብተን …የጓጓሁለትን ሰውነቷን በምኞት እየተቃጠልኩ አያለሁ !ጫማወቿን ስታወልቅ በሂና የተዋቡ በወርቅ አልቦ ተተሸቆጠቆጡ ከአንተ የእጅ ጣት የረዛዘሙ ውብ የእግር ጣቶቿ ….ሽፍንፍኗን ከፀጉሯ ላይ ስታነሳው ወገቧ ላይ የሚገማሸር ከክረምት ጨለማ የጠቆረ ውብ ፀጉሯ ….የሙሽራ ቀሚሷን ስትከፍተው የወርቅ ሃብል የሚጫወትበት የብርሃን ሜዳ የመሰለ ሰፊ ደረቷ ….ግራና ቀኝ ሙሉ ጨረቃቃ የመሳሰሉ ክብ ጡቶቿ …ከተፈጠረች እህል ቀምሳ ታውቃለች ወይ የሚያስብል እንዲህ በአንድ አጅ መዳፍህ የምትከበው ውብ ሽንጥ ….ወረድ ስትል በእቅፍ የማትደርሰው ኩርት ያለ ዳሌ ….

ምራቄን ዋጥኩና ‹‹እና ምን ተፈጠረ ?›› አልኩት

‹‹በቃ ያደረገችውን የወርቅ ጌጣጌጥ ሁሉ አወላልቃ ራቁቷን ስትሆን …ወርቅኮ ውበት ይቀንሳል አልኩ …ወርቁን ስታወላልቅ ውበቷ ወጣ ….በቃ እሷን ፈዝዠ ስመለከት የራሴን ልብስ ማውለቅ ረስቸ ነበር ….ወላሂ ! ስልምልም እያለች ‹‹አውልቅ እንጅ ›› ስትለኝ የድምፅዋ ፍስስስ ማለትና መለስለስ እንኳን ልብስ ቆዳን ማውለቅ ያስመኛል .... የአልጋ ልብስና አንሶላውን ገለጥ ሳደርገው የገነት በር የተከፈተ ነበር የሚመስለው …ሽቶው …በቃ በሽቶ የታጠበ አንሶላ በለው ….በባህላችን እንደዛ ነው ….ቀስ ብላ በነዛ ረዣዥምና ውብ እግሮቿ ወደአልጋው ሳብ ሳብ ሳብ እያለች …ስትመጣ በቃ እንደዚህና እንደዛ ጠረጴዛ …ነበር ርቀታችን ….. ፈገግ ብየ ስመለከታት ጅስሜ ሁሉ እንደእሳት እየነደደ ወንድነቴ ሁሉ ከተፈጠረ እንደዛ ቁሞ አያውቅም …እንኳን ሌላ ጆሮየ ቁሞ ነበር …ፀጉሬ ቁሞ ነበር ….

ድንገት አልጋው ጋ ልትደርስ አንድ ሁለት እርምጃ ሲቀር ያለንበት ሆቴል ምድር በሚያናጋ ፍንዳታ ወደፍርስራሽነት ተቀየረ …. የማስታውሰው እነዛ ውብ አበቦች በአየር ላይ ሲንሳፈፉ ነው .... ክፍሉ በአቧራ ብናኝና በሚፈነጣጠር እቃ ሲሞላ ነው …በቃ !!›› ብሎ ትክዝ አለ

‹‹ምን ተፈጠረ ከዛ …ባለቤትህ ….?››

‹‹እኔጃ ! የነቃሁት ከምንኖርበት ከተማ ውጭ ቃሬዛ ላይ ተሸክመውኝ ሲሮጡ ነበር …ከተማችን በጦርነት እየተናጠች ነው …ከሳምንት በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካምፕ ገባን …ሚስቴ ትኑርም ትሙትም አላወቁም አላገኟትም …ከሶስት ዓመት በኋላ እዚህ ያሉ ቤተሰቦቸ ጋር መጣሁ …ፈለኩ አስፈለኩ በቃ አልተገኘችም …. የአላህ ....ህልም ነበር የምትመስለው ! ከሁሉም ግን እስካሁን ሳስበው የሚያስቀኝ ....›› ወዲያው ከትካዜው ወጥቶ መሳቅ ጀመረ

‹‹የሚያስቀኝ ምን መሰለህ? …ከፍንዳታው በኋላ ሲያገኙኝ …እንደዛ እንደቆመብኝ ይሆን ?….እያልኩ እስቃለሁ …ሃሃሃሃሃሃሃሃ ›› ጎርናና ሳቁ አካባቢውን ሞላው ...የነበርንበት ኮፊሾፕ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ዙረው አዩን ...ማን ያምናል ያሳቀውን ነገር ቢሰማ …

‹‹…አስበኸዋል ? አልጀዚራ ፍንዳታውን ሲዘግብ እኔ ራቁቴን ከፍርስራሽ ውስጥ እንትኔን ሚሳኤል አስመስየ ተጎትቸ ስወጣ ….የአላህ ! ጦርነት ክፉ ነው ...አገርህንም አንተንም ከነገመናህ ነው ለአለም የሚያሰጣህ ››

@wegoch
@wegoch
@paappii
😁10357😢15👍7👏1
ጫካ ውስጥ አንዱ ዝንጀሮ ዛፍ ላይ ሆኖ ቅንዝርርር ይልበታል; እናም ካቅሙ በላይ ሲሆንበት ታች ያለው አንበሳ ጀርባ ላይ ጉብ ብሎ ፀጉሩን እንቅ አርጎ ይሰርረዋል …

አንበሳው ከጀርባው ለማውረድ በዚህ በዛ ሲታገል ዝንጀሮ እንቅ እንዳረገ ይጨርስና ወርዶ ላጥ ይላል …
አንበሳውም ተደፈርኩ ብሎ ሲያባርረው ዝንጀሮ ሆዬ በሆነች ቅያስ እጥፍ ብሎ ሌላ ዝንጀሮ በመምሰል ዱቅ ብሎ ጋዜጣ ማንበብ ይጀምራል፦

አንበሳው ይደርስና "የሆነ ዝንጀሮ በዚህ ሮጦ ሲያልፍ አይተሃል" ሲለው

"አንበሳውን የነፋው?" ይለዋል …

ይሄኔ አንበሳው ድንግጥ ብሎ ፦

"ከመቼው ጋዜጣ ላይ አወጡት? 🤔"

By hasen enjamo

@wegoch
@wegoch
@paappii
😁67👎2012👍1
ሰውዬው በድመቱ ይበሳጭና አውጥቶ ይጥላታል። ምሽት ላይ ድመቷ ወደ ቤት ትመለሳለች።በማግስቱ እንደገና ራቅ ወዳለ ስፍራ ወስዶ ይጥላታል። ይሁንና እሱ እቤቱ ሳይደርስ ድመቷ ቀድማው ደርሳ አገኛት። ንዴቱ የባሰ ጨመረ፣ ደሙ ፈላ። ከዚያ በጆኒያ አድርጎ እርሱ ራሱ ወደማያውቀው ሌላ ከተማ ወስዶ በጣም ውስብስብ ባለ ሰፈር ውስጥ አዙሮ፣ አሽከርክሮ ጣላት። ይሁንና  ይህን እርምጃ ከወሰደ በኋላ እሱ ራሱ እንዴት ወደ ቤቱ ይመለስ? ቢዞር፣ ቢሽከረከር መንገዱ ጠፍቶት ወደ ቤቱ መመለስ አቃተው። የመጨረሻ ሲጨንቀው ወደ ቤቱ ስልክ ደወለና ባለቤቱ ስልኩን አነሳች   ....
ባል: ሄሎ ሃኒ

ሚስት: ሄሎ የት ጠፋህ የኔ ማር?

ባል: ትንሽ ለጉዳይ ወጣ ብዬ ነው። ድመቷ አለች?

ሚስት: አዎ  ምነው?

ባል: አንዴ አቅርቢልኝ  😅

By hasan enjamo

@wegoch
@wegoch
@paappii
😁11613🥰4🔥1
"አንድ ሽበት ታያለህ ፀጉሬ ላይ?" አለኝ አንገቱን ጎንበስ አድርጎ

"አይይይ..." አልኩ አንገቴን ከግራ ወደቀኝ እየነቀነኩ

"አየህ... የእኔ ሚስት እናት በላት። ያኖረችኝ እንደ እናት ነው። ተግሳፅዋም፣ ፍቅሯም፣ እንክብካቤዋም፣ አሳቢነቷም ልክ እንደ እናት...ይገርምሀል ሳገባት ለብዙ ሰው መሳለቂያ ሆኜ ነበር...የሆነ ማዕበል ነው የተነሳብኝ..."

ለምን?

"በእኔና በእሷ መካከል ያለው የዕድሜ ልዩነት የተለመደ አልነበረም። 13 ዓመት ትበልጠኝ ነበር። እኔ የ27 ዓመት እያለሁ እሷ 40 ዓመቷ ላይ ነበረች። ይህ ነገር ብዙ ሰውን አስገረመ፣ ቤተሰብ ተንጫጫ (እናቴን ጨምሮ)፣ ጓደኞቼ በሙሉ አሽሟጠጡ አሾፉ፤ በሄድኩበት ሁሉ "ምነው ምነው አንተ?፤ ምነው ብጤህን ብትፈልግ?" እያለ አሸማቃቂው በዛ፤ ደግነቱ እኔ ላመንኩበት ነገር ምድር ከፍ ሰማይ ዝቅ ቢል አንድም ለውጥ አላደርግም። እናም እሷ ትበልጥብኛለች ብዬ 'አዲዮስ' አልኳቸው። አኮረፉ... ፍጡር የተባለ ሁላ ነው ያኮረፈኝ ከሚስቴ ውጪ፤ ርቀን ብቻችንን መኖር ጀመርን። በሄድንበት ሁሉ ባለትዳር መሆናችንን አይቶ ተገራሚው ቢበዛም 'ወይ ፍንክች' አልን፤ ኃላ ኃላ ነገሩን ተላመድነው። በዓመቱ መንታ ልጆች ወለድን ሁለት ወንድ፤ እነሱ በተወለዱ በሁለተኛው አመት አንድ ሴት ልጅ ደሞ ደገምን።

በስመአብ እንዴት ደስ ይላል...አሁን ስንት ዓመትህ ነው?" አልኩት ነገሩ እያስገረመኝ።

"አሁን 50 አለፍኩ...ልጆቼም ጎርምሰዋል"

"ኦ አትመስልም ግን...ልጆችህ አብረውህ ነው የሚኖሩት"

"ሴቷ ከእኔው ጋ ነች ወንዶቹ ውጪ ሀገር ሄደዋል።...ባለቤቴ የተረጋጋ ህይወት ነበር ያኖረችኝ...በጣም ነው የምወዳት፤ እሷ ደሞ ስትወደኝ የእኔን ሺ እጥፍ አይበቃውም፤ ብዙ እንክብካቤ ነበረኝ። እኔም በሁሉም ነገር እጅግ እታመንላታለሁ (ታምነኛለች) ፣ ከሰው ሀሜታ ሁሉ በፍቅር እሸፍናታለሁ...ቅንጣት እንዲከፋት አልፈልግም። ለነገሩ ቀስ በቀስ ሰዉም ስለእኛ ማውራቱን እርግፍ አድርጎ ተወ...ያው ተረቱ "ጉድ አንድ ሰሞን ነው" ይባል የለ። የሚገርምህ ያኔ ሲስቁብኝ የነበሩ ጓደኞቼ ዛሬ ከፊሎቹ በህይወታቸው የተረጋጉ አይደሉም...አንዳንዱ ቤተሰቡን በትኖ ጤና የማይሰማው አለ...አንዳንዱ ኑሮ እና ሚስቱ አቃጥለው ጠብሰውት ዕድሜው ትንሽ ሆኖ ግርጅፍ ያለ አለ... አንዳንዱ ያለ ትዳርም የሚኖር አለ። ብቻ ምን ልበልህ..."

"ይገርማል ...ባለቤትህስ ታድያ?"
"አልፋለች። ሁለት ዓመት ሊሞላት ነው ካለፈች።"

ይቅርታ

"የጤና ረዳት ነበረች። ክፍለ ሀገር ለስራ እንደሄደች በወባ ምክንያት ታማ ነው የሞተችው።የሚገርምህ ስትሄድ ውስጤን ብዙም ደስ አላለውም ነበር።ያው የስራ ነገር ሆነና ሄደች በህይወት አልተመለሰችም።" ትክዝ አለ። ፊቱ ላይ ጥልቅ የሆነ ሀዘን አ ሳየኝ

"ይቅርታ...መጥፎ ትዝታ ጣልኩብህ " አልኩ

"አይ ምንም አይደል...ባይገርምህ አሁን ጎኔ እንዳለች ነው የሚሰማኝ...ከህልፈቷ በኃላ የመጀመሪያ ዓመት ላይ እጅግ ከብዶኝ ነበር። ኋላ በልጆቼ ተፅናናሁ በተለይ ሴቷ ልጄ የእናቷን መልክ ከነ ልቧ ነው የወረሰችው...ይመስገን በእነሱ ተፅናናሁ።...ትዳር ውስጥ ስትገባ አብዛኛው የሚስማማበትን ሳይሆን...ለአንተ የምትስማማህ ላይ ወስን...ያኔ ምንም መናወጥ የሌለበት ባህር ላይ ታንኳህን እንዳሳረፍክ ይገባሀል። ምክንያቱም ከታደልክ የዘላለም ህይወትህ ነው።" ቀና ብሎ አየኝ። ባለ ሙሉ ልብነቱ ከአወራሩ ያስታውቃል። ስልኩ ጠራ "ህምምም ...አየህ እቺ የእናቷ ቢጤ ደወለች..." ፈገግ እያለ ስልኩን አንስቶ ስፒከር ላይ አደረገና በዓይኑ ስማት ብሎ ምልክት አሳየኝ
"ሄሎ አባቢ...የት ነህ?"
"አለሁ...እዚሁ መናፈሻው አካባቢ ቁጭ ብዬ ነው..." ልክ በዓይኑ እንደሚመለከታት ነው ድምፅዋን በስስት ነው የሚሰማው

"አይ ይሁን ...አትገባም ወደ ቤት ንፋስ እንዳይመታህ... ምግብም አስቀምጬልሀለሁ ቡና ከፈለክ አለልህ ሞቅ አድርገህ መጠጣት ነው...ወይ በዛው ሳልፍ ላግኝህ እንዴ?"አለች። ስታወራ በፍጥነት ነው መልስ እስኪመልስላት አትጠብቅም
"ነይ እሺ...ትላንት የጠየቅሽኝንም ትወስጃለሽ በዛው"
"መጣሁ እሺ..."ብላ ስልኩ ተዘጋ።
"ተመለከትክልኝ በዚህ ሁሉ ፍቅር መሀል ሆኜ እርጅና ከየት ይመጣል ብለህ? ሀ ሀ ሀ ሀ😊... እስካሁን ግን እኮ አልተዋወቅንም...ስምህን ማን ልበል?" አለኝ። ለካ ድንገት እራሴን ላናፍስ ብዬ በገባሁበት መናፈሻ ቦታ ነው ድንገት ከዚህ ሰው ጋር አብረን ተቀምጠን ወግ የጀመርነው።

"አብርሃም እባላለሁ...እኔስ ማን ልበል?"

"እኔ አድማሱ እባላለው። እዚህ አካባቢ አይቼህ ግን አላውቅም... እዚህ ነዋሪ ነህ?" በደንብ ልብ ብሎ እያየኝ ጠየቀኝ...
"አይ እኔ እንኳን ለዘመድ ጥየቃ ከዝዋይ ነው የመጣሁት በዛውም አንድ ጉዳይ ነበረኝ...እዚህ ፀሀዩም ከረር ሲልና ቦታውን ሳልፍ ስለወደድኩት ገብቼ ቁጭ አልኩና ተገጣጠምን። "
"ግሩም ነው።እኔም ቦታውን እጅግ ነው የምወደው ለቤቴም ቅርብ ነው።ብዙ ጥሩ ጥሩ ተጨዋወትን!...ያቿትልህ አበባዬ መጣች..." ቀና አልኩኝ... እውነትም አበባ እየተራመደ መጣ። ከቁመቷ ዘልግ ማለት፣ከመልኳ ጥራት፣ከዓይኗ፣ከጥርሷ፣ከአፍንጫዋ ምኗንም ጥንቅቅ አድርጎ ነው የሰራት...ቅልጥፍናዋ ከአረማመዷ ያስታውቃል። ደነገጥኩ።
አባቷን አቅፋ ሳመች። ወደ እኔ እጇን ዘረጋች "አብርሃም ይባላል። የዝዋይ ልጅ ነው።" አላት አባቷ ትከሻዬን ነካ አድርጎ እያስተዋወቃት። እኔ ዝም ብዬ እጄን ዘረጋሁ። ከአባቷ ጋ የረጅም ግዜ ግንኙነት እንጂ፤ ፈፅሞ ዛሬ የተገናኘን አንመስልም።
"አበባ..." አለችኝ። ውበቷ በጣም ነው ያስደነገጠኝ። አባቷ ሳይታዘበኝ አይቀርም። በራሴ አፈርኩ።"ታድያ እቤት ይዘኸው አትመጣም ነበር? ከአንድ ሰዓት በፊት ብትመጡ እኮ ቡና አፈላላችሁ ነበር።ደሞ ምግብም አብ ስዬ ነበር። ቅድም በስልክ አልኩህ አ? አስቀምጬልሀለው። ቡናውንም እንዳልኩ" አለች ሁለታችንንም እያየች...ስታወራ ምንም መልስ እንደማትጠብቅ አሁን ይበልጥ ተረዳሁ።

"እሱም ተፈጥሮ ወዳጅ እኔም ተፈጥሮ ወዳጅ...ጨዋታ ይዘን ከዚህ ቦታ መነሳቱ እንዴት ይሁንልን ብለሽ ..." ብሎ በዓይኑ ተመለከተኝ። ጭንቅላቴን በአዎንታ ነቀነኩ...

"እሺ ይሁን በቃ ሌላ ቀን ...አሁን ስጠኝና ልሂዳ ረፈደ...ጓደኛዬም እየጠበቀችኝ ነው።"አለች። ብር አውጥቶ ሰጣት ወይ የትራንስፖርት ይሆናል፣ ወይ የትምህርት ቤት አልያም ለሌላ ይሆን ይሆናል።ከተቀበለችው በኃላ ተሰናብታን በፍጥነት ሄደች። ከዓይናችን እስክትሰወር በዓይኑ ተከተላት።ዓይኑ ላይ ጥልቅ ትዝታ አለ።
"...እና መች ነው ወደ ከተማህ የምትመለሰው?" አለኝ ከዓይናችን ከተሰወረች በኃላ ወደእኔ ተመልሶ

"አይ ትንሽ መቆየቴ እንኳን አይቀርም። የምጨርሳቸው ጉዳዮች አሉኝ።" አልኩ

"የምረዳህ ነገር ካለ አለሁ፤ ብዙ ግዜ ከዚህ ቦታ አልጠፋም። እሁድ እንደውም ቤት ብትመጣ ደስ ይለኛል።በዚህ አቅጣጫ 100 ሜትር ሄደህ በግራ ስትዞር አንድ ሱቅ አለ፤ ከእሱ ቀጥሎ ያለው ሰማያዊ በር የኔ ነው።እንዳትቀር አጠብቅሀለው።በል ሰላም ሁን ልሂድ" ብሎ ከመቀመጫው ተነሳ።
"እሺ...መልካም ቀን..." ብዬ ቆሜ ተሰናበትኩትና ቁጭ ብዬ ከዓይኔ እስኪሰወር ከጀርባው አስተዋልኩት። ተክለ ሰውነቱ በእርጅና አንድም ንክች አላለም። የሚመስለው ገና የ 40 ዓመት ወጣት ነው።ለካ ዙሪያችን አድርገን የምንሸከማቸው ሰዎች ናቸው የሚያጎብጡንም፤ የሚያቃኑንም።

by Abrham. F Yekedas

@wegoch
@paappii
158👍18🥰8
የደራሲ ቅጣት ...

የሆነ ሰውዬ ይሞትና ገነትንም፣ ሲዖልንም ይጎበኛል፡፡ ገነት ሲደርስ በጎ ምግባሮች እንደቀጠሉ ናቸው። መልካም ሰርተው የፀደቁትንም አስተዋለ፡፡ ይልቅ የገረመው አንዲት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ የሚፅፍ ሰው ተመለከተ። ገረመውና ምን እንደሆነ ቢጠይቅ "ደራሲ ነው" አሉት። እየተደነቀ “አይ ደራሲ ፀድቆም አያርፍ፣ አሁኑም ይፅፋል” ሲል ተደመመ።

ከሚንቀለቀል የእሳት እቶትን ውስጥ የሲዖልም ሕይወት ቀጥላለች። አመፅ፣ ግርግሩ፣ ጦርነቱ…ኃጥያቱ አናት ባናቱ ይደራረባል። አሁንም አንድ ሰውዬ ከእሳት ዛፍ ስር አረፍ ብሎ በእሳት ብዕር፣ በእሳት ወረቀት ይቸከችካል። ተመልካቹ ሰውዬ ግራ ተጋባም ምን ሊሆን ይችላል ሲል እያሰበ ጠየቀ "ደራሲ ነው፣ ይከትባል" አሉት።

እየተገረመ፣ እየተደነቀ መልዓኩን "ቆይ ደራሲ እዚህም ሲፅፍ አይቼዋለሁ… እዛም ሲቸከችክ ተመልክቼዋለሁ ካዲያ ገነትም ገባ፣ ሲዖልም ወረደ ምን ቀረበት? ምንድነው ቅጣቱ? ምን ተጎዳ?" ሲል ጠየቀው።

መልዓኩም መለሰለት “ገነት ያሉት ይታተምላቸዋል"

By Alemayew Gelagay

@wegoch
@wegoch
@paappii
😁9527👏4🤔4
አስፈሪወቹ ሌሊቶች!

የሆነ ጊዜ የሚከራይ ቤት ስፈልግ አንድ ክልፍልፍ ደላላ "ግራውንድ ፕላስ 2 " ቪላ አጠገብ ያለች ቆንጆ የብሎኬት ቤት አሳየኝ። ለታክሲ ቅርብ፣ ፅድት ያለች በዚያ ላይ ዋጋዋ የማይታመን ርካሽ! ቤት። እድሌን አመስግኘ ወዲያው ተስማማሁ። መስኮቷን ስከፍት ፊት ለፊት የተንጣለለው ውብ ቤት ይታየኛል። መሀል አዲስ አበባ እንደዛ ሰፊ ግቢ ውብ ህንፃ...ዙሪያውን ያለ ደካማ መንደርተኛ እያየሁ "ወይ አዲስ አባባ የኑሮ ልዮነት..." እያልኩ እሁድ ገብቸ እስከማክሰኞ አለሜን ቀጨሁ።

ማክሰኞ እኩለ ሌሊት አካባቢ ነበር ድንገት ከአልጋየ የሚያነጥር ድምፅ እንደሰፌድ ቆሎ አንቀርቅቦ ያስነሳኝ። መድፍ ነበር የመሰለኝ። ደንግጨ ብነሳ ሀድራው ደርቷል ጭብጨባው፣ ጉሪያው፣ ከበሮው.... ሌላ ነገር ነው። በተለይ ከበሮው የአደዋ ዘማችን ነጋሪት ያስንቃል...ይነዝራል!
ድዝዝ ድዝዝ ድዝዝ ...
ጨብ ጨብ ጨብ
እሰይ እስይ እሰይ እሰይ
ሁርርርርር፣ ሁይይይ፣ አሀይ ..... እህህህህህህ !
ግርጭው ብርጭው አፍከኸከት ግራጭገት
አጉዛራ
ቀወዢራ
ጆቢጃራ
እሁይይይይ ....ደግሞ በጎች በመሀል ይጮሃሉ! ባኣኣኣኣ! ዜማውን ሁሉ እስካሁን አስታውሰዋለሁ።

መስኮቴን በቀስታ ከፍቸ ባጮልቅ ያ ቪላ ቤት ዙሪያውን በቆሙ የቤት መኪኖች ተጥለቅልቆ ሰፈሩ በከርቤ ጭስ ታፍኗል። በሩ ላይ ነጠላ ያደገደጉ ሰወች ቁመዋል፣ መብራቱ ፀሐይ ይመስላል። እንዳለ በሩ ቄጤማ ተጎዝጉዞበታል። ህልም ነበር የሚመስለው። በኋላ ስሰማ የታዋቂ ጠንቋይ ቤት ሆኖ ተገኘ። የተከራየሁት ቤት ለሰባት ወር ባዶውን እንደከረመ አንዲት ያለሁበት ግቢ ልብስ የምታጥብ ልጅ ነገረችኝ።

ድምጿን ቀንሳ በፍርሃት "ጥሩ አይደለም የገባው ሁሉ ተጥመልምሎ ነው የሚወጣው ቶሎ ልቀቅ ይሄን ቤት...ከአንተ በፊት ተከራይቶ የነበረው ልጅ፣ ሌሊት አያለሁ ብሎ በመስኮት ብቅ ሲል አፉ ወደግራ አፍንጫው ወደቀኝ ተጠነጋግሮ እግሩም ተጥመልምሎ ቁጭ! " አለችኝ....። አንች ለምን አልተጥመለመልሽም ልላት ፈልጌ ከአፌ መለስኩት። ውስጤ ቢፈራም "ሳለ መድሃኒያለም ለጠንቋይማ ርስቴን አለቅም" ብየ ጧት ጧት አፌና አፍንጫየ አለመጣመሙን በእጀ እየዳሰስኩ መኖሬን ቀጠልኩ። አንድ ቀን ጧት ቁርሴን ስበላ በአጋጣሚ ወደአፌ የላኩት ማንኪያ አፌን ሳተው። የደነገጥኩት መደንገጥ። መስተዋት ፊት ቁሜ ሳይግን አልተጣመምኩም። ነፍሴ መለስ አለች።

እና ማክሰኞና ሐሙስ "ላይቭ ባንድ በሚያቀርበው ጭፈራ እየተዝናናሁ መኖር አዝናኝ ሆነልኝ። አንድ ሐሙስ እንደውም ፀጥ ብሎብኝ ማዛጋት ጀምሮኝ ማንን ልጠይቅ ስል? ያችው ልብስ አጣቢ "ግንቦት ገባ፣ በዚህ ወር ሁልጊዜ ሰውየው የሆነ ቦታ ስለሚሄድ ሰላም እናድራለን" አለችኝ። እውነትም ጠንቋዮ ሙሉ ግንቦትን ጠፍቶ ሰኔ ላይ ተመለሰ። ሰፈሩም ትንሽ ዘና ብሎ ከረመ። በሳምንትም በወርም ከመንደርተኛው አንዱ ጠንቋዮን የተሳፈጠ ይጣመማል የሚል ወሬ ስለነበር እነዛ ሌሊቶች አስጨናቂ ነበሩ። ጠንቋይ እንዲህ ተፈሪ መሆኑን ያኔ ነው ያወኩት። በሹክሹክታ በሚደርሰን ስጋት ብዙ አስፈሪ ሌሊቶች የምናሳልፍ ህዝቦች ነን።

እንግዲህ በሳምንት ሁለት ቀን ማክሰኞና ሐሙስ ሌሊት እንዲቹ ሲቀወጥ ያድራል። የገረመኝ ይሄ አይደለም! ብዙ ባለሀብትና ታዋቂ ሰው የሚሰግድለትን፣ ስንቱን ሐብት በሐብት ያደረገ ነው የሚባለው ይሄ ጠንቋይ ለማየት ስመኝ አንድ ቀን በሁለት ሰወች ታጅቦ ሲወጣ አየሁት! ...(ጠንቋይ ከዛ በፊት አይቸ ስለማላውቅ ፤ የሆነ ፍጥረት ነበር የጠበኩት) ....ምን ገጠመኝ? መናኛ ሙሉ ልብስ ለብሶና ከዘራውን ይዞ የሚያዘግም ሽማግሌ። ያችው ወሬ ወዳድ ልብስ አጣቢ እየተጣደፈች መጥታ ነበር "ወጣልህ ና እየው" ያለችኝ። ...እና ምን አለችኝ?
"ጡረታውን ሊቀበል እየሄደኮ ነው"
ጡረታ?
"አወ ...ወታደር ነበር...ቢሞት ጡረታውን አያሳልፍም ከቤት የሚወጣውም በዚቹ ቀን ነው" 😀

By Alex abrham

@wegoch
@wegoch
@paappii
😁7829🤔4👍2🔥1
እውነት ሁሉም ነገር 'upgrade' ያረጋል! ህይወት፣ ኑሮው፣ ሳሩ፣ ቅጠሉ፣ ሰፈሩ፣ መንደሩ፣ ሰዉ ሁሉ  'upgrade' ያረጋል!

እብድ ነው። ከሰፈሬ ሁለት አቋራጭ ራቅ ብሎ የሚኖር። በልጅነቴ ወደትምህርት ቤት ስሄድ ነው ማየው።  በጫት ገረባ የተሞላው አፉ፣ ያገኘውን ከብስኩት ልጣጭ እስከ አፉን እስካስጌጠባት ገረባ ድረስ እጁ ለመያዝ ከልካይ የለውም። በተለይም ከተማውን በእርቃኑ ማካለሉ የሱ ትልቁ መለያ ነው። ወንዱን ሴቱን አዛውንት ጨቅላ ሳይለይ ያለከልካይ  ያስኮመኩመናል።  ወንዶቹ በሱ ባዶ ገላነት ደስተኛ እንዳልሆኑ አውቃለው (እኔስ እንደው ልጅ ነኝ)  ይህ ነገራቸው ለሱ ከማዘን የመነጨ ሳይሆን በእንትኑ ምክንያት ነው። ረዥም ነው ከረዥምም ረዥም። በምን ይሉኛል ብሂል  አቀርቅሮ  ከማለፍና በእጆቻቸው አይናቸውን ከመከለል በዘለለ ለአፍታ እንኳ ቢሆን ድንገት በእይታ ይህንን በረከት የተቋደሱ ሴቶች የከተማውን ወንድ በዛ ልክ ይጠብቁታል የሚለው ስጋት እንጂ።

 ጊዜያት ነጎዱ። እኔም አደኩ ወደ ወንዶቹ ጎራ። ከብዙ ጊዜያት በኋላ ያንን እብድ አየሁት። ተለውጧል። መላ መላውን የማውቀው  አሁን ላይ ከላይ እስከታች ታጥቋል። ቲሸርት ሱሪ አልቀረው። ከአንዴም ሁለቴ ለብሶ  አየሁት። ያ በእጁ የሚይዛት በአፉ የሚያጣጥማት ገረባው ግን አሁንም የሱ ነች። upgrade መሆኑ ነው። ወንድ ነኝ ያልኩት እኔ እራሴን አየሁት። በዘመኑ ኑሮና ህይወት እየተራቆትኩኝ ነው። የፊተኞች ኋለኞች የኋለኞች ፊተኞች ነው መሰል ነገሩ። እኔንስ የሚያሳስበኝ  ግን እንደው ውል ብሎኝ ብራቆትስ? በብዙ እብዶች መሀል ያለው አንድ ጤነኛ ነኝ ሚሉትን ቅኔ ብቀኝስ? የኔውን እንደሆነ በማይዳሰሱ ቅርፆች UNESCO ላይ አስመዝግቤዋለው። የከተማው ወንዶች ነን ባዮችንስ አስገምት ይሆን?  አቤ...ት! በሰላም ማይታበድባት ሀገር ...

By 乃丨丂尺卂ㄒ

@wegoch
@wegoch
@paappii
😁4028👎4🔥1
የማባልጋት ባለትዳር ነበረች ።

ዋና ተግባራችን ወሲብ ነው ። የምንቀጣጠረው ለወሲብ ብቻ ነው ። የምናወራው ስለ ወሲብ ነው ። አንዳችን አንዳችንን የምንፈልገው ወሲብ ሲያምረን ነው ።

አጠገቤ ሆና ባሏ ደውሎ ያውቃል: "ሰውዬሽ ደወለ" ብዬ ስልኳን አቀብያት አቃለሁ ። ምንም እንዳልተፈጠረ ስታወራው እርቃኗን አትመስልም ነበር። ይገርመኛል ድድብናችን ።

ነውራችን ስለተደጋገመ ተግባራችን ብልግና መሆኑ ተሰወረብን ።

ቢሮዋ እሄዳለሁ፣ ቢሮዬ ትመጣለች ። ጓደኛዬ ቤት፣ እኔ ቤት፣ የሆነ ኮስመን ያለ ሰዋራ ቦታ ፣የሆነ ድብቅ ፅድት ያለ ስፍራ ፣ መኪና ውስጥ ... ብዙ ብዙ ቦታ ትመጣለች እንዋሰባለን ። የታሪካችን መነሻ እና መድረሻው ወሲብ ነው ።
አንድ ቀን በደነገጠ: ተስፋ በቆረጠ ድምፅ "ባሌ አወቀብን" አለችኝ .....ደነገጥኩ ።

ጠፋሁኝ ...ጠፋች

ከአስራ ሰባት ቀን በኋላ ጓደኞቼ "ገኒ ሃዘን ላይ ነች፣ ሙሉ ከላይ እሰከታች ጥቁር ለብሳለች፣ ከስታለች" አሉኝ

"ምን ሆነች?" አልኩ

"ባሏ ሞቶባት ነው፤ ራሱን አጥፍቶ ነው የሞተው" አሉ።

ስደነግጥ፣ ፊቴ ሲቀያየር ፣ እምባዬ ሲያመልጠኝ አዝኜለት ነው የመሰላቸው ። እኔ እንደገደልኩት አልጠረጠሩም ።

የጥፋተኝነት ስሜት ሊገለኝ ሲል ማምለጫ መፅሃፍ ቅዱስ ገለጥኩ።

"ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል " የሚለው ከሁሉም ጎልቶ ተነበበኝ ።
..
ሰው ይዞ መውደቅ ፤ ማስተካከል የማይቻል አወዳደቅ ፣ ሲያስታውሱት የሚያስነክስ አይነት አወዳደቅ፣ እነሳለሁ የማይሉት አወዳደቅ ፣ ወድቄ ነበር የማይሉት አወዳደቅ። በግዜ ምክንያት የማይደበዘዝ አወዳደቅ ...
እንደዚህ አይነት መውደቅ ሲ..ያ...ስ..ጠ..ላ !! !

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
😢5330👎10👍6🔥3😁2