TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶክተር ደብረፂዮን🔝

የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ዛሬ በሰጡት መግለጫ፦

"መንግስት በሙስናና የሰብኣዊ መብቶች ጥሰት ስም የጀመረው እንቅስቃሴ አቅጣጫውን ስቶ የትግራይ ህዝብ #ለማንበርከክ የሚደረግ ጥረት ስለሆነ አንቀበለውም" ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፕሬዝደንቱ ዘመቻው #የውጭ ጣልቃ ገብነት አለበት ብለን እናምናለን ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

በህግ የበላይነት ላይ አንደራደርም፡፡ ነገር ግን ሁሉም መጠየቅ አለበት፡፡ ለሌላ ፖለቲካዊ አላማ መጠቀሚያ መሆን የለበትም፡፡ ሜቴክ ይሁን ደህንነት ሀገርን የሚመለከት እንጂ እኛን የሚመለከት አይደለም፡፡ የኛ ሰው ለምን ታሰረ አንልም ነገር ግን ህግ እየተጣሰ ነው፡፡ ትግራይን ለማዳከም የውጪ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት እየታየ ነው፡፡ በትግራይ ህዝብ ላይ አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል፡፡ ኢህአዴግ ከገመገመው ውጪ ነው እየተደረገ ያለው፡፡" ብለዋል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን፣ ኡትዮ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት!

‹‹ዩኒቨርሲቲዎች የሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት መጠናከሪያ እንጂ #የነውጥ እና #የጥላቻ መነሻ መሆን #አይገባቸውም፡፡›› የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

‹‹ማኅበረሰቡ፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገረ ሽማግሌዎች የተቋሙን #ሰላም ለማስጠበቅ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመቀናጀት እየተሠሩ ነው›› የደሴ ከተማ ነዋሪዎች

‹‹ዩኒቨርሲቲውን እየፈተኑ ያሉት በውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሆኑ #የውጭ ተፅዕኖዎች ናቸው፡፡›› የወሎ ዩኒቨርሲቲ

https://telegra.ph/ውሎ-ዩኒቨርሲቲ-01-10
የአሸንድዬ ጨዋታ አከባበር በላልይበላ!

በአሸንድዬ በዓል #የሀገር ውስጥ እና #የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች እየታደሙ ነው። የአሸንድዬ በዓል "የባህል እሴቶቻችን የአብሮነታችን መሠረት ናቸው" በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ነው።

የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የላልይበላና አካባቢው ነዋሪዎች በበዓሉ እየታደሙ ነው። የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኝዎችም ተገኝተዋል። ይህም በዓሉን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለማስተዋዎቅ እና ተጠቃሚ ለመሆን ያስችላል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦዴፓ

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ልኮልናል።

ፓርቲው በላከልን መግለጫ እስካሁን ትጥቃቸውን ያልፈቱ የጉህዴን ታጣቂዎች በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ግልገል በለስ ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ/ም በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ንፁኃን ዜጎች መገደላቸውና በርካቶች መቁሰላቸውን ገልጿል።

ድረጊቱ በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለለው አስነዋሪና አሳፋሪ መሆኑን በመግለፅ አውግዟል።

በንፁሀን ዜጎች  ላይ ይህን የመሰለ ወንጀል የፈጸሙ አካላት በአፋጣኝ ለህግ እንዲቀርቡ ፓርቲው አጥብቆ ጠይቋል።
 
ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ የታጣቂ  ቡድን አባላት በመተከል እና ከማሽ ዞኖች  ትጥቅ ሳይፈቱ በከተሞችና በገጠር ቀበሌዎች በመንግስት ሎጀስትክስ  እየተንቀሳቀሱ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ስጋት እየፈጠሩ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል።

ፓርቲው ወቅታዊ የሆነውን ክልላዊ ሁኔታን በማስመልከት ፦

- የመተከልን ህዝብ ማህበራዊ  እረፍት በመንሳት ቀጠናውን የጦረነት ማዕከል ለማድረግ የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸው እንድቆጠቡ ፤ አረሶ አደሩን ለማስራብ በማለም የእርሻና የምርት ወቅት በመጠበቅ የሚደረግ አመራር ፈጠር  ግድያ በእጅጉ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

- ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ከጉህዴን ጋር የክልሉ መንግስት በደረሰው ስምምነት መሰረት የታጠቁ የጉህዴን ኃይሎች ተሃድሶ ስልጠና ከወሰዱ በኃላ ትጥቅ ፈተው ወደ ህብረተሰቡ ይቀላቀላሉ ቢባልም ትጥቅ ሳይፈቱ ማህበረሰቡ ውስጥ የሚያደረጉት እንቅስቃሴ በተለይም የመንግስት የፀጥታ አካላትን ሚና #ተክተው የሚያደረጉት እንቅስቀሴ በአስቸኳይ እንዲቆምና ትጥቅ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስቧል።

- በመተከል ዞን ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አጀንዳቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚታትሩ #የውስጥ እና #የውጭ ሃይሎች ከድረጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

- ሰሞኑን በግልገል በለስ ከተማ በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ግድያና ከድርጊቱ ጀርባ ያሉ አካላትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የክልሉና  የፌደራል ፖሊስ በማጣራት አጥፊዎችን ለህግ እንዲያቀርቡና ለህዝቡ ይፋ እንዲያደረጉ ጠይቋል።

- የክልሉ መንግስት በሰላም ውስጥ ልማትን ማሰብና መፈፀም የማይችሉ፣ በግጭት ውስጥ በህዝብ ደም በስልጣን ላይ ለመኖር የሚፈልጉ ሀሳብና ውጤት አልባ ጊዜ ያለፈባቸው አመራሮችን በአስቸኴይ በማጥራት እንዲያስተካክል ፓርቲው አሳስቧል።

(ከቦዴፓ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
👍45873😢15👎11🙏7🕊4🥰1👏1