TIKVAH-ETHIOPIA
" ዋና ኃላፊዋ በሀገር ውስጥ የሉም። ነገር ግን ደብዳቤያችን ከደረሳቸው በኃላ ነው የወጡት " - የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ2015 /2016 በጀት አመት የፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በተመለከተ የተከናወነ የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት…
" ዜጎች ምን ያህል እንደሚንገላቱ የአይን ምስክር ነኝ !! " - የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር)
ዛሬ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት #የፓስፖርት_አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ በተካሄደው የ2015/2016 የክዋኔ እና ኦዲት ሪፖርት ስብሰባ ላይ በመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኩል ስለ ሰራተኞች ስነምግባር ፤ ስለ ዜጎች እንግልት ተነስቷል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺእመቤት ደምሴ (ዶ/ር) መ/ቤቱን " ሁላችንም የምንረግጠው በር ነው ያላችሁ " ሲሉ ገልጸዋል።
" ነገር ግን ሁላችንም ተጠቂ / Victim የሆንበት ጉዳይ ነው እውነቱን ለመናገር " ሲሉ ተናግረዋል። ይህንን ያሉት ስለ ሰራተኞች ስነምግባር እና ስለ ተገልጋይ እንግልት ባነሱት ሃሳብ ነው።
በጉዳዩ ላይ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ኃላፊዎች ለምክር ቤቱ " አጃቢዎቻቸው ፣ በቋንቋ ፣ ቦታ ባለማወቅ ... በተለያዩ ምክንያቶች አጅበዋቸው የሚመጡት እንጂ አገልግሎት ፈላጊዎቻችን አይደለም የሚንገላቱት " ብለዋል።
የምክር ቤት አባልና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ግን " እኔ ምስክር ነኝ እኔ ተንገላትቻለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።
" እኔ ተንገላትቻለሁ ፤ እኔ ተገፍቼ ወጥቻለሁ ያውም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መታወቂያ እያሳየሁ ፤ ተጎትቼ ወጥቻለሁ ይህንን ከማንም አይን እማኝ አይደለም እኔ ላይ የደረሰ ነው። እኔ ይሄንን የምለው እኔ ተበድያለሁና እኔ ለምን ተበደልኩ ብዬ አይደለም " ብለዋል።
" እኔ ይህን ሃሳብ እያቀረብኩ ያለሁት ከኃላዬ ያለው ዜጋ ምን ያህል እንደሚንገላታ የአይን ምስክር ነኝ ለማለት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
" ይህንን ፈትሹት ፤ ሩቅ አይደለም የሩቅ ጊዜ ትዝታ አይደለም እየናገርኳችሁ ያለሁት ዛሬ ላይ እየተፈጸመ ያለ ነው " ብለዋል።
" አገልግሎት ፈላጊው ወረቀት ይዞ ፣ የሞላውን ፕሪንት አድርጎ ይዞ በጣም እየተንገላታ ፤ እየተገፋ ያለበት ሰዓት ነው ያ መሆን የለበትም " ሲሉም አሳስበዋል።
አክለው " ለዜጎቻችን መስጠት የምንችለውን አቅማችን የፈቀደውን አገልግሎት በአግባቡና በስርዓት ልንሰጥ ይገባል እንጂ ከዛም አልፎ መንገላታትን ልንጨምርበት አይገባም " ብለዋል።
መ/ቤቱ ያሉትን ቅርንጫፎች አቅም እንዲያጠናክር እና ዜጎችን ከሚያንገላታ አሰራር እንዲታረም በጥብቅ አሳስበዋል።
በሌላ በኩል ይህ መ/ቤት ህዝብ ክፉኛ የሚማረርበት እንደሆነ ዜጎች በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፤ አሁንም እያሰሙ ይገኛሉ።
በተለይ አዲስ አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት ለማሳደስ ያለው ስቃይ ከፍተኛ መሆኑ እንዲሁም ከውጭ በደላሎች እና እዛው መ/ቤቱ ውስጥ ባሉ አንዳንድ ሰዎች መካከል ያለው የጥቅም ትስስርና ሙስና እጅጉን የከፋ እንደሆነ ነው የሚያስረዱት።
በተለይም በአዲስ አበባ ከኦንላይን ሲስተም ጋር ያለው ስራ በጥቅም የተተበተበ ነው።
ሲስተሙ አይሰራም ይባላል ወይም ተገልጋዩ ሊጠቀም ሲሞክር አይሰራም ነገር ግን ውጭ ያሉ የጥቅም ተጋሪዎች ሲሰተሙ ሰርቶላቸው 25 ሺህ ብር የነበረውን ክፍያ 5ሺህ ብር ጨምረው 30 ሺህ ብር ተቀብለው ይሰራሉ ፤ ከዛም በላይ የሚጠይቁ አሉ።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች ይህ አደገኛ የጥቅም ስራና ግልጽ የሆነ የዜጎች ገንዘብ ብዝበዛና ሙስና በአደባባይ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ መፍትሄ እንዳልተሰጠው በምሬት ገልጸዋል።
#TikvahEthiopia
#Passport
@tikvahethiopia

❤1.55K👏578🙏168😡66😢32😭27🥰21🤔18🕊15😱7
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Passport
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለአዲስ አበባ አስቸኳይ ፓስፖርት አመልካቾች ባሰራጨው መልዕክት የአስቸኳይ ፖስፖርት ኦንላይን ሲስተም የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበት ስራ መጀመሩን ገልጿል።
ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ሁሉም አመልካች በኦንላይን በማመልከት በቀጠሮ ቀኑ ብቻ ወደ ተቋሙ መሄድ መስተናገድ እንደሚችል አሳውቋል።
በኦን ላይን መሙላት ያልቻሉ አስቸኳይ ጉዳይ ያላቸው አመልካቾች በአካል መጥተው መስተናገድ እንደሚችሉ ገልጿል።
በተጨማሪ አገልግሎቱ ፥ " ከግንቦት 6/ 2017 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ የፓስፖርት አገልግሎት ከጠዋቱ 12:00 - 8:00 ሰአት ድረስ የአስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት ደግሞ ከ9:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4:00 ሰአት በሁለት ፈረቃ እንሰጣለን በቀጠሮ ቀናችሁ በፕሮግራሙ መሰረት ወደተቋማችን በመምጣት ተስተናገዱ " ብሏል።
" ከቀጠሮ ቀን ውጭ በተቋሙ አካባቢ መቆምም ሆነ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው " ሲልም አሳስቧል።
#ICS

👏367❤100😡61🙏31😢21🕊13😭12🤔10🥰2😱2