TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Balderas

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕ/ት አቶ እስክንድር ነጋ ፤ በመንግስት ጫና በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው አሳወቁ።
አቶ እስክንድር ሀምሌ 16/2014 ዓ/ም ካሉበት ቦታ ሆነው ፃፉት በተባለውና በፓርቲው የፌስቡክ ገፅ ላይ በተሰራጨ ደብዳቤ በመንግስት ጫና ሳቢያ በፓርቲያቸው በአመራርነትም ሆነ በአባልነት መስራት የማይችሉበት ድረጃ መድረሳቸውን ገልፀዋል።

" ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንድትሻገር ለዓመታት የበኩሌን አስተዋጽዖ ሳደርግ መቆየቴ ይታወሳል። " ያሉት አቶ እስክንድር " በአሁኑ ጊዜ ግን፣ ተረኛው ጨቋኝ መንግስት በባልደራስም ሆነ በሃገር አቀፍ ደረጃ በፈጠረው የለየለት አምባገነናዊ ጫና ሳቢያ፣ በአባልነት ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ። " ብለዋል።

በዚህም " የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ አባላት፣ በየደረጃው ያሉ የፓርቲው አመራር አባላት፣ መላ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ከፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አምሃ ዳኘው ጋር ሙሉ ለሙሉ በመተባበር ስራቸው የተቃና እንዲሆን እንድትተባበሯቸው በትህትና እጠይቃለሁ። " ብለዋል።

በእቅድ ላይ ያለው የባልደራስ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ዝግጅት እንዲከናወን ያላቸው ተስፋ የገለፁት አቶ እስክንድር " ባልደራስ በሃገር አቀፍ ፓርቲነት አድጎ የማየት ተስፋችን ወደ ተግባር ተተርጉሞ ለማየት የፈጣሪ መልካም ፈቃድ ይሁን " ሲሉ መልዕክታቸውን አጠቃለው።

@tikvahethiopia
👍532👎261😢11134👏21🥰5
TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕ/ት አቶ እስክንድር ነጋ ፤ በመንግስት ጫና በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው አሳወቁ። አቶ እስክንድር ሀምሌ 16/2014 ዓ/ም ካሉበት ቦታ ሆነው ፃፉት በተባለውና በፓርቲው የፌስቡክ ገፅ ላይ…
#BALDERAS

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከፕሬዝደንትነታቸው የለቀቁት አቶ እስክንድር ነጋ አሁንም የት እንዳሉ እንደማያውቅ ገልጿል።

የፓርቲው ኃላፊዎች ዛሬ ሰኞ በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ከሐምሌ 16 ቀን 2014 ጀምሮ አቶ እስክንድር ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጽህፈት ቤት እና ከሥራ አስፈጻሚው ጋር ያላቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ገልጸዋል።

የፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አምኃ ዳኘው ከተናገሩት ፦

" አቶ እስክንድር ምንም የነገረን ነገር ባለመኖሩ፤ የት እንደሔደ እና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ባልታወቀበት ሁኔታ አድማጭን የሚያረካ መልስ መስጠት የሚቻልበት ሁኔታ አልነበረም።

በአሜሪካ ሀገር የሚገኙት የአቶ እስክንድር ባለቤት አልደነገጡም ፤ ከፓርቲው ሆነ በውጭ አገር ከሚገኘው የድጋፍ ኮሚቴ ማብራሪያ አልጠየቁም። በዚህ ምክንያት የመታፈን አደጋ እንዳልደረሰበት ገምተናል።

አቶ እስክንድር ያሉበትን ሁኔታ ያሳውቁናል ብለን በመጠባበቅ ላይ ሳለን ነው በአሜሪካ ከሚገኘው የድጋፍ ኮሚቴ በኩል የመልቀቂያ ደብዳቤው ይፋ የሆነው። "

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ቀለብ ሥዩም ፦

" ከሐምሌ 16 ቀን 2014 ወዲህ አቶ እስክንድርን በስልክም ይሁን በአካል አግኝተናቸው አናውቅም።

መንግሥት አቶ እስክንድርን እንዳላፈናቸው እና እንዳላሰራቸው ፓርቲው ያምናል።

ከቤተሰቦቻቸው ደህና መሆናቸው ተገልጾልናል።

ይሁንና አቶ እስክንድር ከአሜሪካ ከተመለሱ በኋላ የተለያዩ የደህንነት መኪናዎች እና የተለያዩ ሰዎች ይከታተሏቸው ነበር። በዚህም ውጥረት እና ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ለመሆናቸው ምልክቶች እንደነበሩ እናውቃለን። "

(ከጀርመኝ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

@tikvahethiopia
👍419👎62😢60😱9👏86🙏5🥰4