ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
ቅዱስ እውነት ??? #ገድለ ተክለሃይማኖት፥ 48:1- 4 " አንድ ቀን በባሕር ዳር ተቀምጦ ሳለ፥ ሰይጣን ከባሕሩ ወጣ። የአባታችንንም ደቀመዝሙር ያዘው። አንተ ርኩስ መንፈስ ከልጄ ውጣ እያለ በመስቀል ምልክት አማተበ። ሰይጣኑም ዛሩም ደቀመዝሙሩን ትቶ ፈጥኖ ሸሸ። ሊያመልጥም ወደደ። ብፁዕ አባታችንም አማተበበት። ወደ ባሕሩ ሊገባ ባይቻለው በጥልቁ ባሕር ወደብ ቆመ። ብፁዕ አባታችንም ሄዶ #በእጁ…
እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል።

"... የልጁም የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ #ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።" (1.ዮሐ.1:7)

እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን #ያጸድቃል#ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
(ኢሳይያስ.53:10-11)

መዳንም #በሌላ #በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።
(ሐዋ. ሥራ.4:12)

በመጀመሪያ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ሐሰትን አይናገርም።
ልብ አድርገው ያንብቡት ይህ። የተክለ ሃይማኖት ሐሰተኛ ገድል ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ከቶ የማያውቀውን ደግሞ ጨርሶ ያልተናገረውን-

" #እሁድና #ሐሙስ #እባብ #የገደለ #የክርስቲያን #ወገን #ሁሉ #ኃጢያቱ #ይሰረይለታል፤ ብለህ #ለልጆችህ ንገራቸው።" ብሎ ጌታዬ እየሱስ ክርስቶስ የነገረኝን አሁንም እነግራችኋለሁ። በልባችሁ ጠብቁት።
( #ገድለተክለሃይማኖት፥51፥6)
ብሎ መናገሩ ምንኛ ይህ አጋንንት ጎታች ተክለሃይማኖት የድፍረት ኃጢያት እንደተናገረ በግልፅ የሚታይ ነው።

ሐሰትን ይናገር ዘንድ #እግዚአብሔር #ሰው #አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን #አያደርገውምን? የተናገረውንስ #አይፈጽመውምን?
( #ዘኍልቍ.23:17)

ሁለተኛ ያለ #ደም መፍሰስ የኃጢያት ስርየት የለምና የለ ክርስቶስ ደም የኃጢያት ስርየት በጭራሽ የለም።
በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤...
ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ #ከሰበክንላችሁ #ወንጌል #የሚለይ #ወንጌልን #ቢሰብክላችሁ#የተረገመ ይሁን። (ገላትያ.1፤ 6-8)

የኦርቶዶክስ ቤተ እምነት ለፍሬ የሆነ ንስሐ ካልገባችና እነዚህን #ፀረ ክርስቶስ መፃሕፍት ካልጣለች ሕብረትዋ ከሰይጣን ጋር እንጂ ከጌታ ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ሊሆን በጭራሽ አይችልም።
እንደዚህ ዓይነት አሳፋሪ የድፍረት ኃጢያት (መጽሀፍ ቅዱስን ከመበራዟና መንፈስ ቅዱስን ለማደስ ከመሞከሯ ውጪ ታይቶም አይታወቅም።)
መፍትሔው በትህትና በክርስቶስ እየሱስ ዙፋን ስር ወድቆ ለፍሬ የሆነ ንስሐ መግባት ብቻ ነው። እውነትን የሚቃወም እልከኝነት ግን ያስረግማል።
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን #በእምነት #እንቅረብ። (ዕብ.4:18)

የሰይጣን ዋንኛ ዓላማው የሰዎችን ልብ ከመፅሐፍ ቅዱስ በማራቅ የጣኦት ምርኮኛ ማድረግ ቀጥሎም መዳን በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን እንዳያውቁ መንፈሳዊ ዓይኖቻቸውን ማሳወር ነው። ይህ የተረገመው የሰይጣን ዋናኛ የክፋት ዕቅዱ ነው።
እርም የሆኑትን ፀረ ክርስቶስ ልዩ ወንጌል ከሰፈር ውጪ ጥላችሁ፤ መፅሐፍ ቅዱስን ብቻ ተቀባይነት በመስጠት፤ የሕይወትን ራስ፥ ማንም ያልፈታውን መሐተም የፈታ የይሁዳን አንበሳ፤ ይህም ማንም ሊፈፅመው የማይችለውን የማዳንና የምልጃን ታላቅ ገድል ያከናወነና ብቃት ያለው #ዘላለማዊ #ሊቀ ካህን የኦርቶዶክስ ቤተ እምነት የክብርን እንግዳ ጌታ እየሱስ ክርስቶስን ለፍሬ በሆነ ንስሐ ልትጋብዘው ይገባል።

በልጁ የሚያምን የዘላለም
ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም ።
(ዮሐ.3: 33)

@teeod @teeod
@gedlatnadersanat