ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
Forwarded from እውነት አርነት ያወጣል (ቴዎድሮስ)
"እውነት አርነት ያወጣል":
የቤተ ክርስቲን መጻሕፍት ለማሳየት ከሚጥሩት ‹‹የመዳኛ መንገዶች›› ውስጥ አንዱ በቅዱሳኑ መካነ መቃብር መቀበር ወይም መሳለም የሚለውን ነው፡፡ ‹‹አጽራረ ጽድቅ መናፍቃን… የማይለውን እንደሚል የሚለውን ደግሞ እንደማይል እያስመሰሉ በማሳየት ለማስጠላትና ለማስነወር ጥረት…›› ያደርጋሉ የሚለው ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ በቅዱሳን መቃብር አማካይነት መዳን አለ የሚለውን ሐሳብ ለማስተባበል ይረዳኛል በሚል ቀጣዩን ጽሑፍ አስነብቧል፤ "በቅዱሳናት መካናት ዐጽድ መቀበር ለመዳን የሚያስፈልጉ ነገሮችን (ከላይ በክፍል አንድ የተገለጹትን) ሳይፈጸሙ ሌላ የመዳኛ መንገድ ነው ብላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምራ አታውቅም፤ አታስተምርምም፡፡ ሆኖም የተቀደሱ ቦታዎችን መሳለምም ሆነ እንዲህ ባሉ ቦታዎች መቀበር የራሱ የሆነ በቊዔት አለው፡፡ ሆኖም የተሐድሶዎች መሠረታዊ ችግር ስለ በረከትና መንፈሳዊ በቊዔት የማያውቁና የማይምኑ መሆናቸው ነው"፡፡

በርግጥ ግን ዲያቆኑ እንዳለው ‹‹…የማይለውን እንደሚል የሚለውን ደግሞ እንደማይል…›› በማስመሰል የሚያቀርቡ ሰዎች የማይለውን ለማለት ‹‹…የመዳኛ መንገድ ነው…›› ብለው ያቀረቡት ትምህርት ይሆን? ዲያቆን ያረጋል ‹‹…በክፍል አንድ የተገለጹትን…›› ያላቸው ‹‹የመዳኛ መንገዶች›› ከጥምቀት ጀምሮ በተዋረድ ያድናሉ ተብለው የሚታመኑትን ነው፡፡

1. የመድሎተ ጽድቅ ጸሐፊ እንዳሰፈረው ይሄኛው ‹‹የመዳኛ መንገድ›› ከሌሎች ጋር ተደምሮ ነው የሚያድነው ወይስ ራሱን ችሎ?
2. ዲያቆኑ ‹‹የለም›› ለማለት የሞከረው ትምህርት በቤተ ክርስቲን መጻሕፍት ውስጥ የለም ወይ የሚሉትን ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ ገድለ ክርስቶስ ሠምራን እንካቹ "መታሰቢያዬን እያደረገ ስሜን እየጠራ በስሜ በታነጸው ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ የሚቀበረውን እስከ ስንት ትውልድ ድረስ ትምርልኛለህ? አለችው፡፡ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ አላት"፡፡

ትውልድ ማዳን ይቻላል በሚል በሚሳለቀው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለመዳን ዲያቆኑ በክፍል አንድ የገለጽኳቸው ካልተሟሉ መዳን ሙሉ አይሆንም ከሚለው ውስጥ አንዱም እንኳ የለም፡፡ ከዚያ ይልቅ የክርስቶስ ሠምራን መታሰቢያ ማድረግና #ስሟን_እየጠራ_መቀበር ለሟቹ ብቻ ሳይሆን እስከ ዐሥር ትውልድ የሚያድን ዋስትና ሆኖ ነው የሰፈረው፡፡ ዲያቆኑ ይሄን እያየ ‹‹…የማይለውን እንደሚል የሚለውን ደግሞ እንደማይል እያስመሰሉ በማሳየት ለማስጠላትና ለማስነወር…›› የተደረገ ጥረት ነው በሚል ይከራከር ይሆን?

https://tttttt.me/tewoderosdemelash/904