✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.21K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
#የካቲት_11_ፆመ_ነነዌ_ይጀምራል
"#ምነው_ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን እንደ ሆነ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ" አለው። ትንቢተ ዮናስ 1:6 ።
#የዚህ ፆም ጊዜ ሶስት ( 3 ) ቀን ብቻ ነው ። ቀኖቹም በየዓመቱ ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ናቸው ። የነነዌ ፆም በመባጃ ሐሙስ( አቆጣጠር ) ከፍ እና ዝቅ ስለሚል አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል ።
የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህን ፆም የወሰኑት ልትጠፋ የነበረች ነነዌን በፆም ምክንያት እግዚአብሔር ይቅር ስላላት ይህን አምላካዊ ይቅርታውን ለዘለዓለም ለማሰብና ዛሬም በዚህ ዓለም ከነነዌ የከፋ ርኩሰትንና ኃጢያትን ስላለ የነነዌ ሕዝብ ይቅር ያልክ አምላክ ዛሬን ይቅር በለን ለማለት ነው

++ የነነዌ ሰዎችም እግዚአብሔርን አመኑ ለፆም አዋጅ ነገሩ
ከትልቁም ጀምሮ እስከ ትንሾቹም ማቅ ለበሱ ወሬውም ለነነዌ ንጉስ ደረሰ። እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናፀፊያውን አውልቆ ማቅንም ለበሰ። አመድ ላይም ተቀመጠ አዋጅንም አስነገረ።

++ በነነዌም ውስጥ የንጉሱንና የመኳንቱን ትእዛዝ አሳወጀ እንድህም አለ ሰዎችም እንስሶችም አንዳችም እንዳይቀምሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ። ሰወችና እንስሳትም በማቅ ይከደኑ። ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩሁ። ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይፀፀት እንደሄነ ከፅኑ ቁጣውስ ይመለስ እንደሆነ ምን ያውቃል በማለትም አሳሳበ።

++ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸውም እንደተመለሱ በስራቸውም አየ። እግዚአብሔር አምላክም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተፀፀቶ አላደረገውም
ት ዮናስ ( ፫ ፤ ፭-፲ )
የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ ቸር አባት ለሀገራችንም ለህዝባችንም ምህረትና ቸርነቱን ያብዛልን ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን አሜን ፫
ለመንፈሳዊነት ቅድሚያ እንስጥና የእግዚአብሔርን ብድራት እንጠብቅ፡ እግዚአብሔር ጾማችንን ጾመ ድህነት ጾመ ስርየት ሰይጣንን ድል መንሻ ፣የኃጥያት መደምሰሻ ፣ መንግስተ
ሰማያትን መውረሻ ያድርግልን
ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን