ለመንፈሳዊ ልምምድ ጠቃሚ ምክሮች
++++++++++++++++++++++
በመጀመሪያ ምን ያህል አዋቂዎች ብንሆን ማወቃችን ብቻ ሊያስደስትን እና ሊያረካን አይገባም፡፡ ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ያወቅነውን በስራ ለምንተረጉምበትና ትእዛዛትን መፈፀም ለምንችልበት ሕይዎት ነው፡፡
ጌታችን የተራራው ስብከቱን ሲያጠቃልል የተናገረው ቃል ይህን ነው፡፡ ‹‹ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በአለት ላይ የሰራ ልባምን ሰው ይመስላል፣ ይህንንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሰራ ሰነፍን ሰው ይመስላል፡፡›› (ማቴ 7፣24-6) ስለዚህ እንደሰማን ለመስራት ለምግባራችን ትልቅ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል፡፡ ይህንንም ሲያረጋግጥልን ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡›› ብሏል ካህኑም በፀሎተ ቅዳሴ (ቅድመ ወንጌል) ወንጌልን ለመስማት፣ እንደሰማንም ለመስራት በቅዱሳን ፀሎት የበቃን አድርገን›› እያለ የሚጸልየው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ ትእዛዙ ለመኖር እና ቃለ ወንጌሉን ለመፈፀም ራሳችንን እናለማምድ፡፡
መንፈሳዊ ልምምድ አንድ ሰው ለነፍሱ ድህነት ያለውን ተስፋ ያመለክታል፡፡ ስሕተቶቹን፣ ድክመቶቹን ሁሉ ለይቶ አውቆ ለማስወገድ እየጣረ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ አንተም ወንድሜ ስህተቶችህን ሌሎች
አይተው እስከሚነግርህ ድረስ መጠበቅ ሳይኖርብህ በራስህ ለይተህ እወቃቸው፡፡ምክንያቱም ያለብህን ችግር ሳታውቀው ለመንፈሳዊ ልምምድ መነሳት ስለማትችል ነው፡፡ ‹‹በሽታውን የደበቀ መድሃኒት አይገኝለትም›› ይባል የለ፡፡ ‹‹ህምምተኞች እንጂ ባለጤናዎች ባለመድሃኒት አያስፈልጋቸውም›› (ማቴ 9፤12)
ባንተ ያለውን ችግር ሌሎች ማወቃቸውም ቢሆን አያበሳጭህ፡፡ ይልቁንም በየትኛው መንፈሳዊ
መስክ ልምምድ ማድረግ እንደሚገባህ አደረርገህ ተቀበለው፡፡
በእግዚአብሔር ህግ ብርሃንነት ራስህን እየመረመርክ ድክመቶችህን ፈልግ፡፡ ትንንሽ ድክመቶች እንኳ ቢሆኑ አትናቃቸው፤ምክንያቱም
ያድጋሉና፡፡ ‹‹ወይናችን አብቧል ኑ የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮዎች፣ ጥቃቅን ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙ፡፡››(መኃ 2፣15)
#ራስህን ከማፅደቅ ተቆጠብ ለስህተቶችህም ማስተባበያ አትፈልግ ራሱን የሚያፀድቅ ሰው ዘወትር ባለበት መሔድ እንጂ የሚያሻሽለው አንድም ነገር የለምና፡፡ ምክንያቱም ባይኑ ፊት ከእርሱ በላይ ሰው የለም ለራሱ እንከን የለሽ ነው፡፡ለችግሮች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ይህን ያደረኩት በዚህ ምክንያት ነው እያለ ሲያስተባብል ወድቆ ይቀራል፡፡ለራሱ ትክክለኛ ግምት ያለው የማይመፃደቅ ሰው ግን ድክመቱን መናዘዝ ብሎም ማስወገጃውን መንገድ መለማመድ ይችላል፡፡ ችግሮችህ ስር ሰደው ሰውች ሊገልጡብህ የሚችሉበት ደረጃ ሲደርሱ የሚሰማህ መሸማቀቅ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ቀደምብለህ እራስህ ገልጠሐቸው ለመፍትሔው ልምምድ ብታደርግ ይህ ሁሉ ነገር ባንተ ላይ አይከሰትም፡፡
#ሁሌም ራስህን ሁነህ ተገኝ፡፡በሕይወትህ ቅንነት የሚነበብብህ ሰው ሁን፡፡ መጽሃፍትን ስታነብም ሆነ ስብከት ስታዳምጥ ጉድለቶችህን እየፈለክ ይሁን፡፡ ሰምተህ ለማድረግም ተነሳሳ፡፡
#የኃጢያት ስሩ አንድ ነው፡፡ ብዙ መንገዶች ቢኖሩትም እርስ በራሳቸው የተያያዙ መሆናቸውንም እርግጠኛ ሁን፡፡ አንድ የተወሰነ የሀጢያት አይነትን ለመቅረፍ ስትነሳ ሳታውቀው
ሌሎችንም እየበጣጠስክ መሆኑን እወቅ፡፡እንዲሁም አንድ በጎ ሥነ ምግባርን ለማዳበር ስትለማመድም ቢሆን ሌሎች ብዙ ሥነ ምግባራትን እያተረፍክ መሆኑን ልብ በል፡፡ ሥነ ምግባራቱም በአንድ ሠንሰለት የተያያዙ ናቸው
┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛