✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.21K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
#አ_ል_ሳ_ተ_ፍ_ም!

ለኦርቶዶክሳዊያን እና ለሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በኦሮሞ ባህል ማዕከል የተጠራውን ሕገወጥ መርሐ ግብር ከቤተ ክርስቲያኒቷ ዕውቅና ውጪ የሚደረግ መሆኑን ጠቅሶ ይህንን ሕገ ወጥ ድርጊት መንግሥት እንዲያስቆም ነሐሴ 24 ቀን 2011 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ ቢጠይቅም፤ መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቷን በመናቅ መርሐ ግብሩ እንዲካሄድ ፈቅዷል፡፡

በመሆኑም መላው ኦርቶዶክሳውያን እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁላችን፤ የሀገር ባለውለታ በሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየተቃጣ ያለውን ጥቃትና ሤራ አስመልክቶ በሚደረገው የጥፋት አካሄድ ሁሉ እየተባበረ ያለውን መንግሥት ፥ ይህንን ስህተቱን እንዲያርም እና ሕገ ወጡን ቡድኑን እንዲያስቆም በጳጉሜን ወር ሊያዘጋጀው ባሰበው የመንግሥት መርሐ ግብር ላይ ባለመሳተፍ እንጠይቅ፡፡

ሲጀመር ጀምሮም፤ ለብሔራዊ ኩራትና ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰላምና ብልጽግና፣ ለፍትኅና እኩልነት ከማንም ቀድማ ለታገለችና ሀገር ላቆመች ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋንና ጥያቄዋን በመናቅና ባለማክበር ይህን መርሐ ግብር ለማካሄድ ማሰብም ከፈረሱ ጋሪውን እንደማስቀደምና ለኢትዮጵያና ለሕዝቡ ያበረከተቻቸውን እነኚህን እሴቶች መንግሥት በመናቁ ይህን መርሐ ግብር አልሳተፍም!

#አንሳተፍም #አልሳተፍም

CC፦ #Office_of_the_Prime_Minister-Ethiopia

@zemaryan