✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.21K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
~ አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ !
የመሰከረም 4ቱ ሰላማዊ ሰልፍ
ዝርዝር መርሃ ግብር ወጥቷል
*★★★*

★ ★ ይህን መልእክት በየፔጁ #SHARE አድርጉታ ?።

★ ወደ ቀደመ ኦርቶዶክሳዊ ማንነታችን በቶሎ እንመለስ።

#ETHIOPIA | ~ ኦርቶዶክስ ሀገር መሆኗን ለዓለሙ ሁሉ የምታሳውቅበት ዕለት መጥቷል። አንተ የተኛህ ሁሉ ንቃ።

• ሰልፉ ከኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጉዳይ ጋር ምንም የሚያይዘው ጉዳይ የለም። የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የሚባለው አጀንዳ የሚፈታው በተጀመረበት በቅድስ ሲኖዶስና በራሷ በቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ነው። ይህን በተመለከተ የሚጻፍ መፈክርም ሆነ ባነር መኖር የለበትም። እንዲህ ዓይነት ባነር ጽፈው የሚወጡ ካሉ እነጃዋር የሚልኳቸውና የሰልፉን መንፈስ ለፖለቲካቸው ማራገቢያ የሚያውሉ ሰዎች ሴራ ነውና ወዲያውኑ እንደታዩ ለሕግ አስከባሪዎች በመጠቆም ማስረከብ ይገባል። በመስከረም 4 ቱ ዓለም አቀፍ ሰልፍ ኦሮሞ፣ ዐማራ፣ ትግሬ፣ ደቡብ፣ ነጭ፣ ጥቁር የለም። እስላም ጴንጤ፣ ካቶሊክ የለም። ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን የሚወዱ ሁሉ አደባባይ ይወጣሉ። በደሏን፣ ችግሯን፣ ብሶቷን አብረው ያሰማሉ። መሆን ያለበት ይኼ ነው። ይሠመርበት።

የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም፡፡
*** እንደ አምለከ አበው መድኀኔ ዓለም ፈቃድ #ለመስከረም_፬/ ፳፻፲፪ ዓ.ም. #የሚካሄደውን_ሰልፍ_በተመለከተ_የወጣ_መርሐ_ግብር_

••
ሰልፉ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት መስከረም ፬ በአደባባዮች ይካሄዳል፡፡ በዕለቱም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሰልፉ ላይ ይገኛሉ፡፡

•••
የሰልፉ አስተባባሪዎች ሁሉም ምዕመን በኀላፊነት የሚያስተባብሩት ሲሆን፤ በግንባር ቀደምትነት ግን
• የሰ/ት/ቤቶች አንድነት፤

• የመንፈሳዊ ኰሌጅ ተማሪዎችና ምሩቃን፤

• በሰ/ት/ቤቶችማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን፤

• የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት፤

• የሠለስቱ ምዕት ማኅበራት ኅብረት፤

• የአእላፋት ድምፅ የካህናትና ምእመናን ተናሥኦት ኅብረት፤

• የጽዋ ማኅበራት ሙሴና ደርገ ሙሴዎች ናቸው፡፡

የሰልፉ ይህን መስሎ ይካሄዳል።

• መስከረም 4 ጠዋት 2.30-3፡30 ሰዓት ሁሉም የአዲስ አበባ ነዋሪ ነጭ ልብሱን ለብሶ ሌሊት ቅዳሴ ያስቀድሷል። ቅዳሴው እንዳበቃ ከየአብያተ ክርስቲያናቱ እስከ ተመደበላቸው መሰባሰቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በሚከተለው ሁናቴ ጉዞ ወደ መስቀል አደባባይ ይሆናል።

★ ለምሳሌ ከሰሜን አቅጣጫ የሚመጡ የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ መገናኛቸው ገነተ ጽጌ ላይ ይሆናል። የደቡቦቹም፣ የምሥራቆቹም፣ የምዕራቦቹም እንዲሁ የመገናኛ ስፍራ ይነገራል።

★ ሰልፉ መንግሥትን ለመለመን፣ እግሩ ስር ለመደፋት አይደለም። ሰልፉ ዝም ስላልን ለናቁን፣ ቁጥራቸውም ትንሽ ነው ብለው ለተገዳደሩን ተዉን ትንሽ አይደለንም። ከመቻቻል ወደ መከባበር እንሸጋገር ለማለትና በዚያውም በኢትዮጵያ አየር ላይ የነገሰውንና ደም አፍሳሽ ዲያብሎስን በመስቀሉ፣ በዕጣኑ ማዕጠንት፣ በዝማሬ፣ በምህላ ለማስታገስ፣ ለማሰርም ጭምር ነው።

የሰልፉ ሥዕል ይህን ይመስላል።

• ባለ መለከቶችና ባለ ጥሩንባዎች ድምፅ እያሰሙ ባንዲራን እያውለበለቡ ከፊት ይመራሉ፤

• በመከተልም የበገና ዝማሬ የሚያቀርቡ በገናቸውን እየደረደሩ፣ ተው ስማኝ ሀገሬ፣ እርግብና ዋኔ፣ ኪራላይሶ፣ ስማነ አምላክነ ወመድኃኒነ እያሉ ይከተላሉ፡፡

• ማዕጠንት የያዙ ካህናት እያጠኑ፣ በመስቀላቸውም እየባረኩ፣ አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ ኪዳን፣ ጸሎተ ማርያም፣ መልክአ ማርያምና መልክአ ኢየሱስ፣ ዳዊቱንም ፍካሬ ዘጻድቃንን እየጸለዩ ይመራሉ፤

• የየሰንበት ትምህርት ቤት መለያ ልብስ(ዩኒፎርም)ና ጥንግ ድርብ የለበሱ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ተማሪዎች በዝማሬ ጭምር አባቶችን ይከተላሉ፤ /የሰ/ትቤቶች አመራር ያስተባብራሉ/

• የጽዋ ማኅበራት በነጭ ልብስ (በማኅበራቸው መለያ ልብስ) ይከተላሉ /የየማኅበሩ ሙሴና ደርገ ሙሴ ያስተባብራሉ/

• ጥንግ ድርብ የለበሱ መዘምራን ማኅሌታውያን ይከተላሉ /አጋፊሪና መጨኔ ያስተባብራሉ/

• መስቀል የያዙ ዲያቆናትና ካህናት፤ ልብሰ ተክህኖ የለበሱ፥ ጥላና ድባብ የያዙ ካህናት ይከተላሉ፤ /ሊቀ ዲያቆንና ቄሰ ገበዝ ያስተባብራሉ/

• ምዕመናን ነጭ ልብስ፣ ነጠላ (ቲሸርት) በመልበስ ይከተላሉ፡፡ /የሰባካ ጕባኤ አባላት ያስተባብራሉ/


• በተመደበልን ቤተ ክርስቲያን ከተገኘን በኋላ ጠዋት ከ3፡30-4፡30 በሊቃነ ጳጳሳት እየተመራን ወደ መስቀል አደባበይ ጕዞ ይካሄዳል፤

• ከረፋዱ 4፡30-7፡30 በመስቀል አደባባይ ሰልፉ ይካሄዳል፡፡

• የመንፈሳዊ ኰሌጅ ተማሪዎችና ምሩቃን ጥቋቁሩን ቀሚሳቸውን እንደለበሱ /አስተባባሪዎሆነው ያስተባብራሉ/

• የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ተማሪዎችም /የተመደቡላቸው አስተባባሪዎች ያስተባብራሉ፡፡/

★ ስለ ጽዮን ዝም አንልም።

#ልዩ_ማስታወሻ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ምእመናን ተቃውሟቸውን በድጋሚ መስከረም 16 በደመራ ዕለት በትርዒቶቻቸው እንደ የሁኔታው ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ ተቃውሞው ሁሉ ግን በዝማሬ፣ በምስጋና እንጂ ፉጨት፣ ግርግር፣ የለውም። ስንዱዋ እመቤት የሥርዓት ሁሉ ምንጭ ናትና ልጆቿ ምን ያህል ሥርዓት እንዳላቸው በዐይናቸው ይመለከቱታል።

• ተጨማሪ የሰልፉን ማብራሪያዎች በተመለከተ ነገ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ይሰጣልና ይጠብቁ፡፡

•••
¶ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች። አራት ነጥብ።

•••
" እኔ ግን እላለሁ! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት፣ ቅድስት፣ ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜ ትርሳኝ። ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሟገትልሽ ባልሞትልሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ። ይህን ባላደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።

"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ።" አሜን !

"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጳጉሜን 4/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።