✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.2K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
¤የኔታ እንዲህ አሉኝ:-
@embtee
" የራስህ ልብ ጠላት እንዳይሆንብህ አጥብቀህ
ቆልፈው:: ግን ልብህን በባዶው አትቆልፈው:: ፈጣሪህን
ክርስቶስን : ድንግል እመቤትህን : ቅዱሳን ወዳጆችህን
ካስገባህ በሁዋላ ነው እንጂ . . .
. . . ለምን ትለኝ እንደሁ . . . ዓለም ብትናወጽ : ተራራው
ቢነቀል : ማዕበላት ቢማቱ . . . በሰላም ልብህ ከታተመ
ምንም አይመስልህም::
. . . 3ቱ ሰላሞች ደግሞ የክርስቶስ ሰላም (ዮሐ. ፲፬:፳፯) :
የድንግል ማርያም ሰላም (ሉቃ. ፩:፵፩) የቅዱሳን ሰላም (ማቴ. ፲:፲፫)
ናቸው::
. . . ይህ ካልሆነ ግን . . . ልብህን በባዶው ብትቆልፈው
ከልካይ ያጣ ሰባሪ (ሰይጣን) ገብቶ ይመላብሃል:: ወዲህ
ደግሞ 'የክርስቶስ ሰላም ብቻ ይበቃኛል' ብለህ ብትናገር
የቅዱስ መጽሐፍ ተቃዋሚና ግብዝ መሆንህ ነው::
. . . እና ደግሞ የትኛውንም ጠላት ትሸሸዋለህ:: ግን
ጠላትህ ልብህ ከሆነ (ልብህ ውስጥ ካደረ) የትም
ሸሽተህ አታመልጠውምና ልጄ ሆይ! ልብህን ለሚገባቸው
ከፍተህ : ለማይገባቸው ቆልፍ::"
"' አባቶቻችን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን:: '"

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
@embtee 👈👉 @embtee
@embtee 👈👉 @embtee
💢 የተዋህዶ ስርአት የተከተሉ የኦርቶዶክስ ቻናሎችን እነሆ💢
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
#ቃለ_ዘተዋህዶ
💢ስለ ድንግል ማርያም ክብር ዝም አንልም! አማላጅነቷን ለአለም እንሰብካለን።
ቤተክርስቲያን አትታደስም መታደስ ያለባቸው ትታደስ ብለው የሚያወሩት ናቸው ምክንያቱም መንገድ ጠፍቷቸው መንገድ ስተዋልና።
👉 @kaleze 👈
👉 @kaleze 👈

#ዝማሬ_ዳዊት
💢የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙሮች እና ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት
"እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።ሃሌ ሉያ። "
👉 @ortodoxmezmur 👈
👉 @ortodoxmezmur 👈

#ትምህር_ሃይማኖት
💢ኑ ትምህርተ ሃይማኖትን እንማር፣ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትን እንዘምር ቅዱሳት መጻሕፍትን እናንብብ።

ፈጥነው ይቀላቀሉንና ሃይማኖቶን ይወቁ፣ በሥነ ምግባር ያጊጡ።

ካልተማሩ አያውቁ ካላወቁ አይጸድቁ እንዲሉ አበው።
👉 @thaymanot 👈
👉 @thaymanot 👈

#ውዳሴ_ማርያም
💢የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮትን በተመለከተ፤ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ስለ ሥርአተ ቤተክርስቲያን፤ትምሕርተ ሐይማኖት ወ.ዘ.ተ ።"
👉 @wdasemariyam 👈
👉 @wdasemariyam 👈
#ግሩፕ
👉 @wdaselemariyam👈

#ጉዞ_ድንግልን_ይዞ
💢ያለ ድንግል ማርያም ምልጃ ዓለም አይድንም ስንል እኮ ማረጋገጫው ወላዲተ አምላክ መሆኖ ብቻ ሰለሚበቃ ነው።
👉 @GuzoDinglnYizo 👈
👉 @GuzoDinglnYizo 👈

#ዜና_ቤተክርስቲያን
💢 በቅድስት ቤተክርስቲያን የተከናወኑ መልካም እንዲሁም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በማቅረብ መረጃና ሀሳብ ለመለዋወጥ።
👉 @zenaTewahedo16 👈
👉 @zenaTewahedo16 👈

#የመዝሙር_ግጥሞች
💢 አጥንት በሥጋ ተሰውሮ እንዲኖር በሥጋ ተሰውራ የምትኖር ነፍሳችን በደስታ በሀሴት የሚሞላ የመላእክትን ዝማሬ...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የመዝሙሮችን ግጥሞችን እንደየጊዜአቸው በ አይነት ዓይነቱ ማግኘት ይፈልጋሉ?? እንግዲያውስ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👉 @yamazemur_getemoche👈
👉 @yamazemur_getemoche👈

#የድንግል_ማርያም...
💢 የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች ማኅበርተኞች ቻናል👇👇የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አስተምሮ የጠበቀ መንፈሳዊ ጥያቄና መልሶችን ለማግኘት👇
ተጨማሪ ከምንመናን የመጡ ጥያቄ መልሶችና ሌሎች መንፈሳዊ ጥያቄና መልሶችን በፁህፍ በድምፅ ለማግኘት ሊንኩን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ👆🏻
👉 @Teyakaenamels 👈
👉 @Teyakaenamels 👈


#የመፅሀፍ_ቅዱስ_ጥያቄ...
💢የመፅሀፍ ቅዱስ ጥያቄና መልስ የመፅሀፍ ቅዱስ እውቀቶን የሚገመግሙበት የሚያዳብሩበት እንዲሁም ያላወቁትን ነገር የሚያውቁበት ቻናል
👉 @reknowbible 👈
👉 @reknowbible 👈

#ደጓ_እናቴ_ማርያም
💢የኢ/ኦ/ተ/ቤ አስተምህሮትን የጠበቀ
💢ስለ ቅዱሳን መላእክት
💢ስለ ሥርአተ ቤተክርስቲያን
💢ትምሕርተ ሐይማኖት እንማራለን
#ኦርቶዶክስ_አትታደስም
ወጣት☝️ታሪክህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ።
ይ ቀ👇 ላ ቀ ሉ
👉 @embtee👈
👉 @embtee👈

#መፅሐፍ_ቅዱስ
💢 እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ ያገኘኸውን ብላ፤ ይህን መጽሐፍ ብላ፥ ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር አለኝ።
፤ አፌንም ከፈትሁ መጽሐፉንም አጐረሰኝ።
፤የሰው ልጅ ሆይ፥ አፍህ ይብላ፥ በምሰጥህም በዚህ መጽሐፍ ሆድህን ሙላ አለኝ። እኔም በላሁት፥ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ።
ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ፤3፥-3
👉 @mesehafkidus 👈
👉 @mesehafkidus 👈

#ቅዱስ
💢 የአብይ ፆም እስከ ምናጠናቅቅ የንስሀና የበገና መዝሙሮችን እናጠናለን መንፈሳዊ ግጥሞች ትረካዎች መነባንብቦችን እየተከታተል እንማማራለን !!!!
👉 @kidus_God 👈
👉 @kidus_God 👈
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
እንኳን ለአምላካችን ለጌታችን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ክብረ በዓል
በሰላም አደረሰን።
አምላካችን መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው እንደ እብራውያን
አቆጣጠር በስድስተኛው ዓ.ዓ ማብቂያ ላይ ነበር።
የሔሮድስ ሞት በ4 ዓ.ዓ ከኒሳን(ከመጋቢት)1 በኋላ ነበር።የመጥምቁ ዮሐንስ
አገልግሎት የተጀመረው በ26 ዓ.ም ነበር። የክርስቶስ አገልግሎት የተጀመረው
በ 26 ዓ.ም በዓመቱ መጨረሻ ላይ ነበር።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ሦስተኛው ፋሲካ ኒሳን 14 በ 29 ዓ/ም
ነበር።
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው በ 30 ዓ/ም በመጋቢት
ወር በ 14ኛው ቀን ነበር።
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለውጥ
ከድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ማረን ይቅር በለን።
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለውጥ
በዮርዳኖስ የተጠመቀ በመስቀል የተሰቀለ አቤቱ ማረን ይቅር በለን።
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለውጥ
በሶስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሳ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ያረገ
በአባቱም ቀኝ የተቀመጠ አቤቱ ራራልን ይቅር በለን አሜን።
ክብር ምስጋና ኃይልና ባለጠግነት ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን
ለዘለዓለሙ አሜን።
🌟🌟 @Embtee 🌟
🌟🌟 @embtee 🌟
🌟🌟 @embtee 🌟
የሚያሸንፍ ፍቅር። " ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት "
አንድ ሰርግ ውስጥ አንድ ሽማግሌ ሙሽሮቹን ሊመርቁ ቆሙና «አጣልቶ
የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ» ብለው ሲመርቁ ሰማሁ፡፡
እስካሁን ብዙ ሠርግ ተገኝቼ ምርቃት ሰምቻለሁ እንዲህ ያለ ምርቃት ሰምቼ
አላውቅም፡፡ ምን ማለታቸው ይሆን? እያልኩ በኅሊናዬ ሳብሰለስለው ቆየሁ፡፡
«አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር? ደጋግሜ አሰብኩት፡፡ ይህንን
ሳወጣ እና ሳወርድ እንዳጋጣሚ ሽማግሌው ምርቃታቸውን ፈጽመው እኔ
የነበርኩበት ጠረጲዛ ጋ መጡና ተቀመጡ፡፡ መጠየቅ አለብኝ አልኩና አንገቴን
በጠረጲዛው ላይ ሰገግ አድርጌ
«ደኅና ዋሉ አባቴ» አልኳቸው፡፡
«ይመስገነው ደኅና ነኝ» አሉኝ፡፡
«ቅድም የመረቁት ምርቃት ሰምቼው ስለማላውቅ ገረመኝ» አልኩ ወሬ
ለመወጠን ብዬ፡፡
«አንተ ብቻ አይደለህም ብዙዎች ይገርማቸዋል» አሉ ፈገግ ብለው፡፡
«ምን ማለትዎ ነው ግን»
«መጀመርያ አንድ ታሪክ ልንገርህ» አሉኝ ጃኖአቸውን ወደ ቀኝ መለስ እያደረጉ፡፡
እኔም ወንበር ቀየርኩና አጠገባቸው ተደላድዬ ተቀመጥኩ፡፡
«አንድ ጊዜ አንዲት እኅት ምክር ልትጠይቀኝ መጣች፡፡ እናም እንዲህ ስትል
አጫወተችኝ፡፡ እኔ እና ባለቤቴ ከተጋባን ስምንት ዓመታችን ነው ሁለት ልጆችንም
ወልደናል፡፡ የራሳችን ቤት እና መኪና አለን፡፡ ሁለታችንም የየራሳችን በቂ ደመወዝ
የሚገኝበት ሥራ አለን፡፡ ይህንን ያህል ዓመት በትዳር ስንኖር ተጋጭተን ወይንም
ተጣልተን አናውቅም፡፡ እንኳን ለመጣላት ለመፋቀረም ጊዜ አልነበረንም፡፡
ጭቅጨቅ፣ ንዝንዝ፣ በዚህ ወጣ፣ በዚህ ወረደ የሚባል ነገር በቤታችን ታይቶም
ተሰምቶም አያውቅም፡፡ ጎረቤቶቻችን እና የሚያውቁን ሁሉ በኛ ይቀናሉ፡፡ እርሱን
ምን የመሰለች ሚስት አለችህ ይሉታል፤ እኔንም ምን የመሰለ ባል አለሽ
ይሉኛል፡፡ አንድ ጊዜ ጓደኛዬን ለማየት እና በዚያውም ለመዝናናት ብዬ ናይሮቢ
ሄድኩ፡፡ ባለቤቴ ሥራ ስለነበረው አልሄደም፡፡ ጓደኛዬ ትዳር ከያዘች አምስት
ዓመቷ ነው፡፡ ባለቤቷ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ስለሚሠራ ነው
@embtee @embtee
@embtee @embtee
ኬንያ የሄዱት፡፡ እነርሱ ቤት አንድ ሳምንት ተቀመጥኩ፡፡ ያን ጊዜ ታድያ የኔን ትዳር
ትዳር መሆኑን ተጠራጠርኩት፡፡ ጓደኛዬ ባለቤቷን በስሙ አትጠራውም፤ እርሱም
እንዲሁ፡፡ ደክሞት ከመጣ እግሩን ታጥባላች፣ እርሱም እንዲሁ፡፡ ምግብ ሲበሉ
እንደተጎራረሱ ነው የሚጨርሱት፡፡ ልጆቹን፣ቤቱን ሌላውንም አብረው ነው
የሚያደርጉት፡፡ አንዳንድ ጊዜ በኃይል ይከራከራሉ፤ ሊደባደቡ ነው ብዬ ስፈራ
ለጥቂት ጊዜ ይኳረፉና ግን መልሰው ይፋቀራሉ፡፡ አንድ ቀን ታድያ ጓደኛዬን
«ለመሆኑ ተጣልታችሁ ታውቃላችሁ?» ስል ጠየቅኳት፡፡ «በጣም እንጂ እኛ
መጣላትንም መፋቀርንም እናውቅበታለን፡፡ ተጣልተን ተጣልተን ወጥቶልናል፡፡
ከጠብ በኋላ የሚኖረን ፍቅር ሁልጊዜ ምነው በተጣላን ያሰኘኛል» አለችኝ፡፡
ከዚያም ወደራሴ ተመልሼ አሰብኩ፡፡ እኔ እና ባለቤቴ ተጣልተን አናውቅም፡፡
አያድርሰውና አንድ ቀን ብንጣላ እንዴት እንደ ምንታረቅ የምናውቅበት
አይመስለኝም፡፡ ክፉን አርቅ አልኩ ለራሴ፡፡ ግን እኛ ተጠባብቀን ነው ወይስ
ተፈቃቅረን ነው የምንኖረው ብዬም ራሴን ጠይቄዋለሁ፡፡ ሳስበው ግን
በመጠባበቀ እንጂ በመነፋፈቅ የምንኖር አይመስለኝም፡፡ እናም ትዳሬን
ጠላሁት» አለችኝ፡፡ ችግሯ ገብቶኛል፡፡ አንድ ጥያቄ ጠየቅኳት፡፡ «ላንቺ ፍቅር
ማለት የጠብ አለመኖር ነው? ወይስ ጠብን ማሸነፍ? አልኳት፡፡ ቀና ብላ አየችኝ፡፡
አልመለሰችልኝም፡፡ ዝም ብላ አሰበች፡፡
«ለመሆኑ ለምን እንደማትጣሉ ታውቂያለሽ?» አልኳት፡፡
«ለምን ይመስልዎታል?» ብላ እኔኑ መልሳ ጠየቀችኝ፡፡
«የማትጣሉት ስለማትገናኙ ይመስለኛል፡፡ የት ተገናኝታችሁ፣ የት ተነጋግራችሁ፣
የት ተከራክራችሁ፣ የት ተቀራርባችሁ ትጣላላችሁ፡፡ መጋጨትኮ ከመቀራረብ
የሚመጣ ነው፡፡ እናንተ ጠብን አይደለም ያሸነፋችሁት፤ ጠብን ነው የሸሻችሁት፡፡
አለመሞት እና ሞትን ማሸነፍ ይለያያል፡፡ አለመጣላትና ጠብን ማሸነፍም
እንዲሁ፡፡ «ሐኪሞች ለምን ክትባት እንደሚወጉን ታውቂያለሽ አይደል፡፡ ክትባቱ
የሚሠራው ከሞተ ቫይረስ ነው፡፡ ለምን? ያ የተዳከመ ቫይረስ ወደ ሰውነታችን
ሲገባ ሰውነታችን ጦርነት ተከፈተብኝ ብሎ ራሱን ያዘጋጃል፡፡ መድኃኒት
ያመረታል፡፡ ራሱን በሽታ ለመከላከል ዝግጁ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ ልምድ
አዳበረ፤ በሽታውን እንዴት እንደ ሚያሸንፍ ኃይል እና ዐቅም ገንዘብ አደረገ ማለት
ነው፡፡ ትዳርም ይኼ ክትባት ያስፈልገዋል፡፡ ወደፊት ከባዱ የትዳር ቫይረስ መጥቶ
በበሽታ እናንተን ጠራርጎ ከመውሰዱ በፊት ደካማውን ቫይረስ መከተብ
ያስፈልጋችኋል፡፡ ኃይል እና ዐቅም መፍጠር ያስፈልጋችኋል፡፡ ያልተከተበ ልጅ እና
የተከተበ ልጅ ልዩነታቸው የሚታወቀው በሰላሙ ጊዜ አይደለም፡፡ ወረርሽኙ ሲገባ
ነው፡፡ ያን ጊዜ ማን መቋቋም እንደሚችል ይታያል፡፡ ሁለታችሁም በየፊናችሁ
ትውላላችሁ፡፡ ከዚያ ወደቤት ትገባላችሁ፡፡ ራት ትበላላችሁ፡፡ ይቀጥላል፡፡ ቤትም
ውስጥ ብትሆኑ አንቺ ጓዳ ነሽ፤ እርሱም ቴሌቭዥን እያየ ነው፡፡ ልቅሶ ስትሄዱ
እርሱ ከወንዶች ጋር ነው አንቺ ከሴቶች ጋር ነሽ፡፡ ዓመት በዓል ሲመጣ እርሱ በግ
ይገዛል፣ አንቺ ዶሮ ትገዣለሽ፡፡ እርሱ በቱታ ጎምለል ጎምለል ይላል፤ አንቺ
በሐበሻ ቀሚስ ጉድጉድ ትያለሽ፡፡ ይቀርባል ትበላላችሁ፡፡ በቃ፡፡
@embtee @embtee
@embtee @embtee
ወዳጄ የማይፈስ ውኃ ከድንጋይ ጋር አይጋጭም፡፡ የረጋ ውኃ ይሻግታል እንጂ
ግጭት የለበትም፡፡ ወንዝ ሆኖ ሲወርድ ግን አረኹ ገደሉ፣ ዐለቱ ቋጥኙ
ይላተመዋል፡፡ ለመላተም አይሄድም፡፡ ሲሄድ ግን ይላተማል፡፡ ከመኖር ብዛት
ታድያ ፈለግ ይሠራል፡፡ ከዚህ ብኋላ ኩልል ብሎ መፍሰስ ነው፡፡ እዚያ ደረጃ
ለመድረስ ግን ስንት ትግል፣ ስንት ልትሚያ፣ ስንት ውጣ ውረድ አለ፡፡ ይኼ ሁሉ
ወንዝ ማን ቦይ ቀድዶለት መሰለሽ የሚፈስሰው፡፡ በዘመናት እየታገለ በጠረገው
መንገድ እኮ ነው እንዲህ አምሮ ሲፈስስ የምታይው፡፡ ትዳርም እንዲሁ ነው፡፡
እድገት ካለው፡፡ ሕይወት ካለው ይፈስሳል፡፡ ሲፈስስ ታድያ መላተም፣ መጋጨት
ያጋጥማል፡፡ ይህ ግን እየተፈታ ይሄድና በኋላ የትዳር ፈለግ ይሠራል፡፡ ከዚያ በኋላ
ኩልል እያለ መውረድ ነው፡፡ ፏፏቴ ይኖረዋል፡፡ ዳግላስ የሚወርድ ውኃ
ይኖረዋል፡፡ ከዐለቱ ጋር ሲጋጭ ሕመም መሆኑ ቀርቶ ውበት ይሆነዋል፡፡
አንዳንዶቹኮ ከተጋቡ በኋላ ወንድም እና እኅት ብቻ ሆነዋል፡፡ አንዳንዶቹ አብሮ
ሠሪ «ባለ አክሲዮን»፡፡ አንዳንዱ ባል ገንዘብ መስጠት አይቸግረውም፤ ሃሳብ
መስጠት ግን አይሆንለትም፡፡ አንዳንዷ ሚስት ቤቷን ማስተዳደር አያቅታትም፤
ባሏን ማስተዳደር ግን አይሆንላትም፡፡ ብዙዎቹ «እኛኮ አንድ ነን» ብለው
የሚፎክሩት ልዩነቶቻቸውን የሚያዩበት አጋጣሚ ስለሌላቸው ነው፡፡ መች
ተወያይተው፣ መች ተከራክረው፣ መች ተገዳድረው ያውቃሉ፡፡
ሦስት ዓይነት ባል እና ሚስት አሉ፡፡ የሚገጥሙ፣ የሚገጥሙ የሚመስላቸው ግን
የማይገጥሙ፤ ፈጽመው የማይገጥሙ፡፡ የሚገጥሙ ባል እና ሚስት
እየተገዳደሩ፣ እየተጋጩ፣ እየተስማሙ፤ እየተቸገሩ፣ ችግር እየፈቱ፤ በሃሳብ
እየተለያዩ፣ እየተቀራረቡ፤ እየተዋወቁ ሄደው በሂደት አንድ የሚሆኑ ናቸው፡፡
የሚገጥሙ የሚመስላቸው የማይገጥሙ የሚባሉት ደግሞ ሲታዩ የተስማሙ፣
የተፋቀሩ፣ አንድ የሆኑ፣ ጠብ እና ልዩነት የሌለባቸው የሚመስሉ፤ በውስጥ ግን
የተከደኑ፣ በጊዜ የሚፈነዱ፣ ያልተዳሰሱ ቁስሎች ያሉባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ
በአማርኛ «ይጠጌ አይነኬ» ይባላሉ፡፡ በሂሳብ asy
mptote የሚባሉት ናቸው፡፡
የሚገጥሙ የሚመስላቸው፤ ሰውም ሲያያቸው የሚገጥሙ የሚመስሉ፤
በእውነታው ግን መቼም የማይገጥሙ ናቸው፡፡ ሦስተኛዎቹ ጎን ለጎን የሚሄዱ
ናቸው፡፡ parallelÝÝ ምናቸውም የማይገጥም፡፡ አለመግጠማቸውም
የሚታወቅ፡፡ ያልተፋቱት ለልጆቻቸው፣ ለሕግ ጉዳዮች፣ ለቤተሰቦቻቸው ሲሉ እንጂ
በጋብቻ ውስጥ በፍቺ የሞኖሩ ናቸው፡፡
አሁን ልጄ ራሳችሁን እዩ፡፡ መጣላት ለጋብቻ አስፈላጊ ነው እያልኩሽ አይደለም፡፡
በትዳር ውስጥ መጋጨት ብቻውን የመጠላላት ምልክት እንዳልሆነ ሁሉ፣
አለመጋጨት ብቻውንም ግን የፍቅር ምልክት አይደለም ነው የምልሽ፡፡ ለመሆኑ
ለመጣላት ጊዜ አላችሁ? አንድ ወንበር ላይ መቀመጥና አብሮ መቀመጥ፤ አንድ
አልጋ ላይ መተኛትና አብሮ መተኛት፤ አንድ ቤት ውስጥ መኖርና አብሮ መኖርኮ
ይለያያሉ፡፡» ከዚህ ውይይታችን በኋላ ወደ ባልዋ ሄዳ ለትዳር ጊዜ ስለመስጠት፤
በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ስለመነጋገር፤ የቤት ሥራን ለሥራነቱ ብቻ ሳይሆን ለደስታ
መፍጠርያነቱ አብሮ ስለ መሥራት ማንሣት ስትጀምር ነገር መጣ፡፡ ጭቅጭቅ
ጀመርሽ ይላት ጀመር፡፡ የማይስማሙባቸው ነገሮች እየታወቁ መጡ፡፡
ይገርምሃል፡፡ በልቶ የማያውቅ ሰው ሲበላ እንደሚያመው ሁሉ፣ ተጋጭቶ
የማያውቅ ሰው ሲጋጭ አያድርስብህ፡፡ አንድ ጋሪ ጠጠር በየቅንጣቱ ቢወረወር
ከሚጎዳህ በላይ ጋሪውን እንደሞላ ቢደፋብህ የሚጎዳህ ይበልጣል፡፡ «ተጋጭተን
አናውቅም» የሚሉ ሰዎችም ሲጋጩ እንደዚያው ነው፡፡ ለዚህ ነው «አጣልቶ
የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ» ብዬ መመረቅ
የጀመርኩት፡፡ ጠብን የሚያሸንፍ ፍቅር፣ ጦርነትን የሚያሸንፍ ሰላም፣ ጨለማን
የሚያሸንፍ ብርሃን ነው የሚያስፈልገን ብዬ፡፡
ጉልበት ስሜ ተነሣሁ፡፡
→ → ከ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እይታዎች የተወሰደ
@embtee @embtee
@embtee @embtee
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👇👇👇👇👇👇👇
💦 @Zemaryan 💧
💦 @Zemaryan 💧 #ይቀላቀሉ
💦 @Zemaryan 💧 👈👈👈👈
💦 @Zemaryan 💧
❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️

እንክዋን ለመጥምቁ አመታዊ በዓል አደረሰን
የካቲት 30 ተረክቦተ ርዕስ ትባላለች
የመጥምቁ ዮሐንስ የተቆረጠች አንገት በሸክላ ውጪት የተገኘችበት በዓሉ
በምስጋና በሰአታት በማህሌት በቅዳሴ በዝክር እናከብረዋለን ክብሩ ለኛው
ነውና ፊት አይቶ የማያዳላው ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ ከቀሳፊ ነገር ይሰውረን
አሜን
@embtee @embtee
@embtee
❖__________ደብረ ዘይት__________❖
የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት ይባላል፡፡
ደብረ ዘይት የስሙ ትርጉም የዘይት ተራራ ማለት ሲሆን ስያሜውን ያገኘው
በቦታው ብዙ ወይራ ተክል ይበቅልበት ስለሆነ ነው፡፡ ጌታ በደብረ ዘይት የዳግም
ምጽአቱን ነገር ማስተማሩ ይነገርበታል፡፡ ‹‹ እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ
ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ‹ይህ መቼ ይሆናል የመምጣትህና
የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድነው አሉት›› መቴ 24፡3
ስለ ጌታ መምጣት ት.ዘካ 14፡5 ፣ ሐዋ ሥራ 1፡11 ፣ 1ኛ ተሰ 4፡16 እና ራዕ
22፡7 ይመልከቱ
አመጣጡስ እንዴት ነው?
ጌታ ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ለሁሉም እንደ ሥራው ለመክፈል በግርማ መለኮቱ
በክበበ ትስብዕቱ ይመጣል፡፡
ጊዜው ዘመነ ዮሐንስ ወርኃ መጋቢት ዕለተ እሑድ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ
ሊቃውንት ተናግረዋል፡፡ ምነው ‹‹ የሚያውቀው የለም ይል የለም; ቢሉ እዉነት
ነው የሚያውቀው የለም ብዙ የዮሐንስ ዘመን ብዙ የመጋቢት ወር ብዙ የእሑድ
ዕለት አለና ለይቶ የሚያውቅ የለም፡፡
ሞት ለማንም አይቀርምና ሁሉም ይሞታል፡፡ ዘፍ 3÷19
በዕለተ ምጽአት ቅዱስ ገብርኤል ስምንቱን ነፋሳተ መዓት
ከየመዛግብታቸው ያወጣቸዋል፡፡ ዛፍን ነቅለው ድንጊያውን ፈንቅለው ምድርን
እንደብራና ይዳምጧታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ነጋሪቱን ይመታል 1ኛ መቃብ 9÷8
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ዘያነቅሖሙ ለሙታን ሲል በዱር በገደል በባሕር
በየብስ በመቃብር ውስጥ ያሉት በአውሬ ሆድ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡
በሁለተኛው ነጋሪት ሲመታ አጥንትና ሥጋ አንድ ሆነው ፍጹም በድን
የሆናሉ፡፡ @embtee
ሦስተኛው ነጋሪቱን መቶ /ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው
ዘኢይመውት /ንቃሕመዋቲ ዘትነውም ባለ ጊዜ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ
ፍቱልኝ ሳይል ደጉ ደግነቱን ክፋውም ክፋቱነቱን ይዞ ይነሣል፡፡
ወንዱ የ30 ዓመት ሴቲቱ የ15 ዓመት ሆነው ጻድቃን ብርሃን ለብሰው
ብርሃን ተጎናጽፈው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ማቴ 13÷43 ኃጥአን ጨለማ
ለብሰው ፍጹም ዲያብሎስን መስለው ይነሣሉ፡፡ ጻድቃን ስለሠሩት መልካም
ሥራ ኑ የአባቴ ብሩካን ብሎ መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸዋል፡፡ ኃጥአንን
ስለክፋ ሥራቸው /ከኔ ሂዱ/ ብሎ ገሃነም ይሰዳቸዋል፡፡ ጻድቃን ደስ ይላቸዋል
ኃጥአን ግን ያዝናሉ ዋይ ዋይ እያሉ ደረት ይደቃሉ እንባቸውን ያፈሳሉ፡፡
የማይጠቅም ለቅሶ የማይረባ ኃዘን ነው ሰቅለው የገደሉትም አይሁድ ክብሩን
አይተው ላይጠቀሙ ይጸጸታሉ፡፡
ምልክቱስ ምንድን?
ምልክቱስ ምንድን ነው ብለው ጌታ ሲጠይቁት ‹‹ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ
አላቸወ፡- ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ @embtee @embtee
ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ
በስሜ ይመጣሉ፤ብዙዎችንም ያስታሉ፡፡ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ
አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፡ አትደንግጡ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና
ነው፡፡ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፡ ረሀብም
ቸነፈርም የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር
መጀመሪያ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል
ይገድሉአችሁማል፡ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላቸሁ››
አላቸው፡፡
በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ከቅዱሳኑና ከሰማዕታቱ ጋር ለመቆም ያብቃን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፡- የማቴዎስ ወንጌል 24÷1 ትርጓሜ
መዝገበ ታሪክ 2
@embtee

@embtee
@embtee
@embtee
እንኳን ለአባታችን ለፃድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ በዓለ እረፍት አደረሳችሁ ።
"ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም::"
Watch "Ethiopia: ዶ/ር ፓስተር ወዳጄነህ ነብያቶች ዘንደዉን እንደ ሚያመልኩ አጋለጠ" on YouTube
https://youtu.be/vqONAmpWhsI
Watch "ዶ/ር ፓስተር ወዳጄነህ :ድንግል ማርያምን እናታችን እመቤታችን መባል ሲያንሳት ነው" on YouTube
https://youtu.be/xaC8cP2Htx8
Watch "Ethiopian: ዶ/ር ዘበነ ለማ ስለ ዶ/ር ወዳጄነህ እና ቤቲ ያላቸዉን አድናቆት እና ምክር ለገሱ" on YouTube
https://youtu.be/VcJUcV4fW9U
Watch "እራስህን አድን ወደ ኃላ አትይ (ኦሪት ዘፍጥረት 19፥22) -- new Memhir Mehreteab Asefa sebket" on YouTube
https://youtu.be/yONOlTBHACU
Video ተመልከቱት 2 ሰዓት ምስክርነት
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
የዶክተር ፓስተር ወዳጄነህ ምስክር እውነትና ተገቢ ነው!
.
ሰሞኑን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆነው ፓስተር ወዳጄነህ
በኤክሶደስ ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ ከቤቴልሄም ታፈሰ ጋር ውይይት አድርጎ
ነበር፡፡ ውይይቱን ደጋግሜ ተመለከትኩት፡፡ ፓስተር ወዳጄነህ በውይይቱ
ውስጥ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችም በተለይም “ነብያትን” እና
“ፓስተሮቹ” ላይ በሰላና በበሰለ መንገድ ትችቱን አቅርቧል፡፡ አዳዲስና
ከቀድሞዋ ፕሮቴስታንት አስተምህሮ ወጣ እያለ የመጣውን መጥፎና
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አሰራር በጣም በድፍረት እንዲሁም በእውቀት
ድባቅ መቶታል፡፡
.
በተቃራኒው ደግሞ ስለ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በብዙ ፕሮቴስታንቶች
ላይ ያለውን ሸወራራ አተያይ ለማጥራትና ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
ባልዋለችበት ላዋሏት፤ ያላለችውን አለች፤ ያላደረገችውን አደረገች እያሉ
ሲከሷት ለከረሙት እንደ ፓስተር ዳዊት ሞላልኝና መሰሎቹ ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን ምን እንደምትመስል ከ'ዴቭና ቤተሰቦቹ' በተቃራኒና እውነት
ላይ ቆሞ የኦርቶዶክስን እውነተኛ አስተምህሮ ገልጧል፡፡
.
ይህን ድርጊቱን በብዙ ኦርቶዶክሶች ዘንድ ከበሬታንና አድናቆትን
ሲያተርፍለት፤ ጥቂት በማይባሉና ኦርቶዶክስንና አስተምህሮዋን በሚያውቁ
መምህራኖች ዘንድ "መስካሪ አያስፈልገንም" ተብሏል፡፡ ነገር ግን በዚህ
ትችት እኔ አልስማም፡፡ ምክንያቱም ከፕሮቴታስታንት ቤተክርስቲያን አካባቢ
ለቁጥር የሚታክቱ፤ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ስድብና ትችቶች ተሰምተዋል
ተነበዋል፡፡ በዚህም ብዙ የኦርቶዶክስ ምእመን ተቀይሟልም ምላሽም
ለመስጠት ተሞክሯል።
.
ፓስተር ወዳጄነህ በተቃራኒው ቆሞ “ኦርቶዶክሰ ኢየሱስን አታውቅም
ማለት ስህተት ነው፤ ቅድስት ድንግል ማርያም በህቱም ድንግልና ቅድመና
ድህረ ውልደት ድንግልናዋ አልተለወጠም፤ ቅድስት ድንግል ማርያም
ቅደስናዋንና ለእኔም እናቴ መሆኗን አምናለሁ እቀበላለሁ፤ ኦርቶዶክሶች
እሮብና አርብ ሲጾሙ ኢየሱስን እያሰቡ ነው፤ ከኦርቶዶክሶች ዘጠኝ በአሎች
ስምንቱ ኢየሱስን የሚያስቡ ናቸው፤ አብይ ጾም ኢየሱስ ክርስቶስ
ስለጾመው ነው የሚጾሙት፤ መላእከትን በጣም እውደቸዋለሁ
አከብራቸዋለሁ፤ መላእክት እኔ እልካለሁ ለሚሉ ፓስተሮችም መላእክት
ለሰው በፍጹም አይላኩም የጎረምሶች ድፍረት….” ማለቱ ስህተቱ ምኑ
ላይ ነው? ምስክርነቱ ለኦርቶዶክስ ምእመናን አስተምህሮ ወይም ማባበያ
ታስቦም አይመስልም፡፡
.
ይልቁንስ ይህ ንግግሩ በፕሮቴስታንቱ አካባቢ ያለውን ሽወራራ እይታ
ለማጥራት የተደረገ የዶክተር ፓስተር ወዳጄነህ ጥረት ሆኖ ነው የታየኝ፡፡
ይህ ጥረቱ ይበል ያሰኘዋል እንጂ ኩርኩም አያስፈልገውም፡፡ ንግግሩ
በተለይ ለፕሮቴስታንቱ ምእመናን ጥሩ መስታወት ነው ብዬ እምናለሁ፡፡
.
መሰደባችንን ያልሆነውን ናችሁ ተባልን ብለን ቅር ካለን፤ የሆነውንና
ያደረግነው ሲታወቅልን ሲከበር ቢቻል ማመሰግን ካልተቻለ ደግሞ ዝምታ
መልካም ይመስለኛል፡፡
.
የዶክተሩ ንግግር ከዚያኛው አካባቢ ግርግር አስነስቶ ዳግም እንደ አዲስ
የዶክተንሩ የግል ጉዳይ እያነሱ የራሳቸውን ግንድ ትተው የዶክተሩን ጉድፍ
የሚጠነቁሉ ብዙዎች ተስተውለዋል። ስለዚህም ዶክተሩን አለንልህ ልክ
ልንለው ይገልባል።
.
ተሃድሶ ተፋፋመብን ከማለት ተዋህዶን ማፋፋም
.
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተሃድሶ እንቅስቃሴ በገሃድ
እየተፋፋማ መሆኑ ለፕሮቴስታንቱም ለኦርቶዶክሱም ምእመን ገሀድ የሆነ
ሀቅ ነው፡፡ ተሃድሶውን የሚያፋፍሙት በጥንቃቄ እንደጦርነት እቅድ ነድፈው
አካሄዳውቸ አስልተው የሚጓዙ ናቸው።
.
እነዚህ አካላት ከሚጠቀሙት አካሄድ አንዱ የፕሮቴስታንታዊ
አስተምህሮዎችን አንሸራታው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሚያስገቡ ሰዎችን
ከሚገባውን ከተባለው በላይ ማድነቅና ማደናነቅ፤ እንኳን የእነሱን ሃሳብ
ደግፈው አይደለም ኦርቶዶክስን ብቻ ስለነቀፉ ታላቅ አድቅቆትና ክብር
ይቸራቸዋል። ይህ አንዱና ዋነኛው የተሃድሶው አካሄድ ነው፡፡ በዚህም
ቀላል የማይባል ውጤትና ስኬት አስመዝገበዋል፡፡ @embtee
.
መጽሐፍ ቅዱስ “እንደ እርግብ የዋህ እንድ እባብ ብልህ ሁኑ” ይላል፡፡
ስለዚህም የዶክተር ወዳጄነህን ንግግር ይበልጣ ማጎልበት ማድነቅ፤
ዶክተር ወዳጄነህ ውስጥ ያለውን እውነትና ብዙ ሊናገር የፈለጋቸውንና
ፈርቶ ያላወጣቸው እውነቶች ካሉ በማድነቅና ሀሳቡን በማክበር
በማበረታት ማስወጣት ይገባል እንጂ ማሳቀቅና ምን አገባህ ብሎ ኩም
ማድረግ አይገባም።
.
ይህ በጋዜጠኞች አካሄድ ስፓይራል ኦፍ ሳይለንስ (Spiral of silence)
ከሚባለው የንድፈ ሀሳብ አካሄድ ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ምን ማለት ነው
ሰው እውነት ይኖረውና ግን ብዙ የሚጮኽውና አየሩን የተቆጣጠረው ወሬ
ከእሱ እውነት ተቃራኒ ሲሆን በብዙሃኑ ላለመገለል ሲል ዝምታን
ይመርጣል፡፡
.
ስዚህም ዶክተር ወዳጄነህ የዚህ የንድፈ ሀሳብ ተጠቂ እንዳይሆን አይዞህ
ማለት፤ እንዲሁም ሌሎች እውነቶችን እንዲናገር ማበረታታትና አለሁልህ
እያሉ ማድነቅ አስፈላጊና የጸረ ተሃድሶ አካሄዱ አንድ አካል ሊሆን ይገባል፡፡
በዚህም ብዙ በጎ ነገር እንደሚገኝ ባለ ብዙ ተስፋ ነኝ።
.
እንዲህ ካደረግን ተሀድሶ ተፋፋመብን ብሎ ከመብከንከን ተዋሕዶን
በሌሎች አብያተ ክርቲያናት እያፋፋሙ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መምታት
ይቻላል፡፡
.
ዘመኑ እውነት ብቻ ሳይሆን ውበትን፤ መረጃ ብቻ ሳይሆን ጥበብንም፤
ጉልበት ብቻ ሳይሆን አእምሮን፤ ልፋትን ብቻ ሳይሆን ብልሀትንም
ይጠይቃል፡፡ ጸረ ተሃድሶ ትግሉ ለተነሱ ጥያቆዎች ሁሉ መልስ እየሰጡ
መሄድ ብቻ በቂ አይደለም፤ ጉባኤን እየዘረጉ የራስ አስተምህሮ ብቻ
ማስተማሩ ብቻ ከጥቃቱ አያድንም፤ ከዚያም ከፍ ብሎ ለመጣብን ብቻ
መከላከል ሳይሆን ገፋ ብሎ ሄዶ መነሻውን መቆጣጠር፤ የተሃድሶውን
አስኳል በጥያቄና በእውነት መምታት ግድ ይላል፡፡
.
እንደ ዶክተር ወዳጄነህ አይነት ሀሳብ የያዘ ሰው ሲመጣ ደግሞ ማድነቅና
ማንቆለጳጰስ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚያ ወገን ሌሎች ያልሆኑትን “የወንጌል
አርበኛ፤ ኢየሱስን ያፈነዳ…” የመሳሰሉትን አድናቆቶች ዞር አድርጎ እንደ
ዶክተር ላሉ ሰዎች “እውነትን የተናገረ፤ በወንጌላውያን መሀል የተዋህዶው
ሰው…” የመሳሰሉትን አድናቆቶቹ ከግብሩ ጋር የሚመሳሉ አክብሮቶች
መስጠቱ መልካም ይመስለኛል፡፡ እንዲህ ከሆነ ከመከላከል ወደ መልሶ
ማጥቃት ተሄደ ማለት ነው፡፡ መጽሐፍም ዘመኑን ዋጁት ይላል፡፡
@embtee @embtee
ለ any comment 👉
@maryamn123bot
@bezaale
የከበሮ እና የመቋሚያ ምሳሌያዊ ትርጉም
(በሶሎሞን አያሌው)
👉💯 ከበሮ 💯
ከበሮ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ግራና ቀኝ ሲመታ ስንመለከልት ጌታችን በአይሁድ እጅ በጥፊ መመታቱን ያስታውሰናል።
ሰፊው የከበሮው አፍ፡- የመለኮት ምሳሌ ነው።ይህ የከበሮ አፍ የጌታችንን የባህሪ አምላክነት ምሉዕ በኵለሄ መሆኑን አስልጣኑ ወሰን ድንበር እንደሌለው የሚያስታውሰን ነው። የአፉን መስፋት ስንመለከት በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ በህልውና በመለኮት ባሕርይ አባቱ ከአብ ባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተስተካከለ ሁሉን የያዘ ሁሉን የሚገዛ መሆኑን እናስባለን።
ጠባቡ የከበሮው አፍ፡- የትስብእት ምሳሌ ነው በመዝሙር ጊዜ እየተቁረቁረ ድምጽ የሚሰጠው ጠባቡ የከበሮ አፍ የወልድ እግዚአብሔርን በጠባብ ደረት በ አጭር ቁመት ተወስኖ መገለጥ የሚያመለክተን ነው።ፍጥረታትን ሁሉ የሚገዛ እሱ በስልጣኑ ሽረት በመለኮቱ ኅልፈት የሌለበት ቢሆንም ስጋን ተዋህዶ ተገልጧል።ይህንን ጠባብ የከበሮ አፍ ስንመለከት ሁሉን የሚገዛ እሱ በ አጭር ቁመት በጠባብ ደረት መወሰኑን እናስባለን። ሐ፤ ፩፡፩- ፩፬ @embtee
ከበሮው የሚለብሰው ጨርቅ፡- ከበሮ የጌታችን ምሳሌ እንደሆነ ከላይ አይተናል። ከዚህ አንጻር የለበሰው ጨርቅ ደግሞ በዕለተ ዓርብ አይሁድ ጌታችንን ያለበሱት ጨርቅ (ቀይ ከለሜዳ) ምሳሌ ነው። ''ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት'' ማቴ 26:28
በከበሮው ላይ የተለጠፈው ጠፍር፡- በጌታችን ጀርባ ላይ የታየው የግርፋት ሰንበር ምሳሌ ነው። ጠፍሩን በከበሮው ላይ ስንመለከት በጌታችን ጀርባ ላይ የታየውን ሰንበር እናስታውሳለን። ''እጆቼን እና እግሮቼን ቸነከሩኝ አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ'' መዝ 21(22):16 እንዲል ጌታችን አጥንቱ እስኪቆጠር ጀርባው እስኪቆስል ተገርፏልና የዚያ ምሳሌ ነው።
የከበሮው ማንገቻ፡- የከበሮውን መምታት ስናስብ በ አንገታችን የምናስገባው ማንገቻ ጌታችንን አስረው የጎተቱበት ገመድ ምሳሌ ነው። አይሁድ ጌታችንን ወደ ቀራኒዮ ሲወስዱት የእጁ መጋፊያና መጋፊያ እስኪገጥም ድረስ በገመድ የእንግርግሪት አስረው ጎትተውታል መንገቻውን ከበሮው ላይ ስናይ ይኽንን ጌታችን የታሰረበትን ገመድ እናስታውሳለን።
👉♻️♻️መቋሚያ፡-♻️♻️ @embtee
መቋሚያ ብዙውን ጊዜ ከእንጨት የሚዘጋጅ እንደ በትር ዘለግ ያለ ከወደ ጫፉ የመስቀል ቅርፅ ወይም የ 'ፐ' ቅርፅ ያለው ነው፡፡ አገልግሎቱም ለመደግፊያ ፣ ለመመርኮዣ እና ለመዘመሚያ ነው። ከፅናፅል እና ከበሮ ጋር እንዲሁም ብቻውን በማህሌት ላይ በዝማሬ እና በሽብሸባ ያገለግላል፡፡
ምስጢሩ፡- መቋሚያ ከአዳም ተስፋ እና ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በእፀ መስቀል ላይ የተሰቀለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው።
መቋሚያ ያዕቆብ ትምህርተ መስቀል ያለበትን በትር በፊቱ እያቆመ ይሰግድና ይፀልይ የነበረበት ምሳሌ ነው።
መቋሚያ በትከሻቸው ላይ አድርገው ወዲያ እና ወዲህ ማለታቸው አይሁድ ጌታን በእለተ አርብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ መውሰዳቸውን ።
ካህናቱ መቋሚያውን ከዜማ ጋር አስማምተው ከመሬት ላይ መጣል እና መደሰቃቸው አይሁድ ጌታን ማነው የመታህ እያሉ ተራ በተራ በዘንግ መምታታቸውን ለማስታወስ ነው።
መቋሚያውን ከትከሻቸው አንስተው ወደ መሬት ማሳረፋቸው ሌላ ሰው መቀበሉ (መሰብሰቡ) እና ማስቀመጡ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ሲጓዝ ስለነበር ሳንሰቅለው እና የልባችንን ሳናደርስ ህይወቱ ያልፍብናል በማለት መስቀሉን ለሌላ ሰው ማሸከማቸውን ለማስታወስ ነው ።
ወስብሃት ለእግዚአብሔር
@embtee @embtee
@embtee @embtee