✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.2K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
"ስለ ቤተክርስቲያን ጸልዩ ከእግራችን የሚተካ እንዲገኝ እግዚአብሔር ተተኪ
እንዳያሳጣን ጸልዩ::"
ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን✞
✞ ✞እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም
በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!✞
👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
. 🗯 የዳዊት ዜማ 🗯
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረባቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት እንዲሁም ከናንተው ተቀድቶ የተዘመሩ ለመስማት
መንፈሶን ያድሱ
👇ቻናላችን
#መዝሙራትን በጊዜያት ከፋፍሎ
#ወረባቶችን
#ልዩ ልዩ የበዓል ዝግጀጅቶች
#ጥንቅቅ ያሉ ከፊደልም ከዜማም ስህተት የራቁ መዝሙራቶችን እናጠናለን
💚💚
💚💚
💛💛💛💛💛💛
💛💛💛💛💛💛
❤️❤️
❤️❤️
❤️❤️
❤️❤️

ለመቀላቀል ከስር ሰማያዊውን ይጫኑ

JOIN OUR CHANNEL
👇👇👇👇👇👇👇

    🔻🔻🔻🔻🔻🔻
🗯 @Zemaryan 🗯
🗯 @Zemaryan 🗯
🗯 @Zemaryan 🗯
🗯 @Zemaryan 🗯
🗯 @Zemaryan 🗯
🔺🔺🔺🔺🔺🔺
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።
መዝሙረ ዳዊት ፻፶፥፮    

ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ
ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን
ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ
ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው)
በማለት መለሰለት፡፡
❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው
ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ”
አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ
እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ
ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ
ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ
ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡
❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ
የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች
እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ
ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም
ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡
❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና
እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም
በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም
የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡
❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን
መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ
ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና
እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው
እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ
ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን
አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡
❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን
ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ
ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም
በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር
ተቀዳጅተዋል።
❖ ጥር ፲፮ ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ዐምስት
መቶ ሦስት በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡
ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“እግዚአብሔር ሤመ ረድኤቶ ለንስእናከ ዐቃቤ
ወስምዖ መጥበቤ
ፍትወ ምግባር ቂርቆስ ወምዑዘ ኂሩት እምከርቤ
ለዘተጽዕረ በምንዳቤ ወለዘቈስለ በጥብጣቤ
ለአባልከ ሰላም እቤ”
(እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ
ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤
በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለኊ) እያለ
ሕፃኑን ሰማዕት ያወድሳል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ፦
“ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ
በልደት ንዑስ፤
ንጹሕ ከመ ዕጣን
ወፍሡሕ ከመ ወይን”፡፡
(በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም
አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል)
❖“ሰላም ለሰማዕታት እለ ምስሌሁ ፭፼ ወ፬፻፤ ፬፼ ወ፪፻፲ወ፬”፡፡
(ከርሱ ጋር ያሉ ፭፼ ከ፬፻፤ ፬፼ከ፪፻፲፬ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባቸዋል) በማለት
አመስግኗል፨
[የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር
አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨
[ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]
👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፍኖስ ወርሃዊ መታሰብያ ክብረ በዓል በሰላም
በጤና አደረሳቹ አደረሰን !!!!
አምላከ እስጢፍኖስ ከሁላችን ጋር ይሁን ከሰማዕቱ ከቅዱስ እስጢፍኖስ
ረድኤት በረከት ያሳድርብን አሜን አሜን አሜን !!!
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
ጥር 18 የቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርዎተ አጽሙ
…ዳግመኛም ያ ከሃዲ ንጉስ ዱድያኖስ ግንድ አምጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስን
በግንዱ ላይ እንዲቸነክሩት አዘዘ፤በላዩም ላይ ሰም አፍስሰው እሳት
እንዲያነዱበት አደረገ ፤ ከዚህም በኋላ እንደመጭመቂያ ሆኖ ከተሰራ የስቃይ
መሳሪያ ላይ አወጡት ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት እንዲጨምቁት አዘዘ፤አንጀቱ ሁሉ
ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረገፍ ድረስ እንዲሁ አደረጉበት ነፍሱ ከስጋው ተለየች
የሰማእቱን ሰጋ አቃጠሉት ፈጩት አመድም ሆነ በቀፎ አድርገው ይድራስ
ወደሚባል ተራራ ላይ በነፋስ ዘሩት ደብረ ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ነው
ወታደሮቹ የታዘዙትን ፈጽመው ተመለሱ። ያንጊዜም መብረቅ ነጎድጓድ ታላቅ
ንውጽውጽታ ሆነ ምድርም ከመሰረቷ እስክትናወጽ ድረስ ከሰማይ ድምጽ ተሰማ
ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ በብሩ ደመና ወረደ
በተራራውም ላይ ተቀመጠ አራቱን የምድር ነፋሳት የሰማእቱን ስጋ እንዲሰበሰቡ
አዘዛቸው ከሞትም አስነሳው ኃይሉን አሳደረበት ባርኮትም ወደ ሰማይ አረገ፤
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስ እየሮጠ ወታደሮቹን ተከተላቸው ወንድሞቼ ቆዩኝ
ከናንተ ጋር ልሂድ እያለ ተጣራ የነዚህ የወታደሮች ቁጥር አራት ነው ስማቸው
ህልቶን፤አግሎሲስ፤ሶሪስና አስፎሪስ ነው፤ ይህንን ታላቅ ተአምራት አይተው
አምነዋል፤ በኋላም በሰማእትነት ሞተዋል፤ ይህ የሆነው ጥር 18 በዛሬዋ ቀን
ነው ይህንንም ቀን " ዝርዎተ አጽሙ " ስትል ቤተክርስቲያን ሰማእቱን አዘክራ
ትውላለች፤ በስሙ በታነጹለት አብያተክርስቲያናት በሙሉ ታቦተ ህጉ ውጥቶ
በደማቁ ተከብሮ ይውላል። አራዳ ጊዮርጊስን የተከሉት ደጉ ንጉስ እምዬ ምኒሊክ
ናቸው ታዲያ የዚህን ታላቅ ደብር መሰረቱን ሲጥሉ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር
ከሚገኝበት ቦታ አፈሩን በመርከብ አጓጉዘው በበቀሎ በፈረስ አስጭነው መሰረት
አድርገውታል፤ይህንን ከአባቶቻችን የሰማነው ነው፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
ምንጭ፦ ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ምዕራፍ 6 ፤ 15 - 18
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
ሼር በማድረግ ለሌሎች አሰሙ
እንኳን ለ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም
በጤና አደረሳችሁ አደረሰን አሜን!
ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በአማላጅነቱ በጸሎቱ ለታመኑበት ፈጥኖ
የሚደርስ በብለይ እና በሐዲስ ኪዳን በልዪልዩ ተልኮዎቹ የሠራዊት ጌታ
እግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም የጸና ሰለሆነ ጥበብ በመግለጽ በማጽናት
በማብሰር ከመከራ በማዳን ከእሳት ወላፈን በመታደግ ከአንበሳ መንጋጋ
በማትረፍ እና ትዕቢተኞችን በመቅጣት በመገሰጽ እውነተኛ ታዳጊ መልአክ ነው።
ሰለስቱ ደቂቅን እንደታደጋቸው እንደተራዳቸው ዛሬም በጸሎቱ ለሚታመኑ ዝክሩን
ለሚያደርጉ ድረሳኑን የሚደግሙትን በጸሎት በመዝሙር በቅዳሴ በልዮ ልዮ
መንፈሳዊ ክብረ በዓሉን ብናከብር አማላጅነቱን የተሰጠውን ጸጋ ብንመሰክር
በበደላችን ምክንያት ከተግባረ ጽድቅ ለተሰደድን ስደተኞች ከባሕረ እሳት
ለሰጠምን ኃጥያተኞች የምናመልከው የአባቶቻችን አምላክ መልአኩን ልኮ
የእሳቱን ባሕር እንዲያሻግረን የሊቀ መላእክትየቅዱስ ገብርኤል አማላጅነቱ
የሰለሰቱ ደቂቅ በረከታቸው ይደርብን አሜን!
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ✞
እንኳን ለእመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ድንግል የወርቅ አክሊል
ማርያም እረፍቷ በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!
" አስተርእዮ ማርያም "
በመጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
መንግሥተ ሠማያት ያውርስልን! እኛም ሰምተንና አዳምጠን አንድም
ሠላሳ ስልሳ መቶ ፍሬ እንድናፈራ የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁንልን! አሜን።
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
ጥር 22 የቅዱስ ኡራኤል በዓለ ሲመቱ ነው፤ ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን የመነኮሳት
አባት ታላቁ ጻድቅ አባ እንጦንስ የእረፍት ቀኑ ነው፤ ይህ አባት ወላጆቹ በሀብት
የከበሩ ነበሩ እነርሱ ሲሞቱ ንብረቱን በሙሉ ለድሆች መጽውቶ አናምስት
አናምርት አካይስት አቃርብት ካሉበት፤ ነቀዐ ማይ ልምላሜ እጽ ከሌለበት ፤ ዘር
ተክል ከማይገኝበት ከጽኑ በርሃ ገባ በዚያም በተጋድሎ መኖር ጀመረ ሰይጣናት
በዘንዶ በጊንጥ እጅግ በሚያስፈሩ አውሬዎች እየተመሰሉ ያስፈራሩት ጀመር
“አባቱ አዳም ከገባበት እገባለሁ ብሎ ነው እኮ ከዚህ የመጣው” እያሉ ይስቁበት
ይሳለቁበት ነበር እየደበደቡ ስቃይ አጸኑበት እርሱ ግን በትህትና እናንተ ብዙ እኔ
አንድ እናንተ ኃያላን እኔ ደካማ እናንተ ረቂቃን እኔ ግዙፍ በአምላኬ ኃይል ካልሆነ
እንዴት እችላቹዋለሁ እያለ በትህትና ተዋጋቸው ነገር ግን መከራውን መቋቋም
ሲያቅተው በቃ ወደ ከተማ ልመለስ ብሎ አንድ እግሩን ከውስጥ አንድ እግሩን
ከውጭ አድርጎ ሲያወጣ ሲያወርድ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል የሰሌን ቆብ አድርጎ
የሰሌን ልብስ ለብሶ የሰሌን መቋሚያ ይዞ ከበሩ ፊት ለፊት ጸሎት ሲያደርግ አየ
የዚህን መልአክ ፍጻሜውን ሳላይማ አልሄድም ብሎ ቆመ መልአኩ መጀመሪያ
ለሥላሴ አንድ ስግደት ሰገደ ከዚያም ጸሎት አደረሰ ወንጌል አነበበ
በመጨረሻም አንድ አቡነ ዘበሰማያት ብሎ ሦስት ጊዜ ሰገደ እንደዚህ እያደረገ
12 አቡነዘበሰማያትን አድርሶ 36 ጊዜ ሰገደ በእያንዳንዱ ሶስት ሶስት ጊዜ፤
ከዚያም ቁጭ ብሎ የያዘውን ሰሌን መታታት (መስፋት) ጀመረ፤በ 3፤ በ 6፤ በ 9
እና በ 11 ሰዓትም እንደዚሁ እያደረገ አሳየውና እንጦንስ ከሚመጣብህ
ከሰይጣን ጾር ለመዳን እኔ እንዳደረግሁት ዘወትር አድርግ ብሎ ስርዓተ
ምንኩስናን አስተምሮት ከእርሱ ተሰውሯል፤አባ እንጦንስም መልአኩ እንዳሳየው
ጸሎት እያደረገ ሰሌን እየሰፋ በተጋድሎ ኖሯል፤ ከእለታት በአንዱ ቀን ከአባ
ጳውሊ ጋር ተገናኝተው መጨዋወት ጀመሩ ይህን ቆብ ማን ሰጠህ ይልዋል
ከእግዚያብሔር ነው የተቀበልኩት አለው፤ አባ ጳውሊ አደነቀ “ይልቅስ እስኪ ከኔ
በኃላ እንደዚህ ዓይነት ቆብ የሚያደርግ መኖር አለመኖሩን ወደ እግዚያብሔር
ጸልይሊኝ ይለዋል፤ አባ ጳውሊ ሲጸልይ ነጫጭ ርግቦችን ያያል ደስ አለው ከአንተ
በኃላ ያንተን ፈለግ የሚከተሉ ልጆችህ ይነሳሉ ይለዋል እስኪ እባክህን ደግመህ
ጸልይሊኝ ሁሉም የኔ ልጆች ናቸውን ይለዋል ሲጸልይ አንዳንድ ጥቁር ነገር
የተቀላቀለባቸውን ያያል ገረመው ሁሉም ጻድቃን አይደሉም ጽድቅና ኃጢያትን
የሚቀላቅሉም አሉበት ይለዋል፤ ለሶስተኛ ጊዜ ቢጸልይ ጥቋቁር ቁራዎችን
ይመለከታል ድምጹን አሰምቶ ያለቅሳል ምነው ይለዋል በኃለኛው ዘመን
የሚነሱት መነኮሳት ሹመት ሽልማት ፈላጊ፤ ገንዘብን የሚወዱ፤ ፍቅር የሌላቸው
ትዕቢተኞች ናቸው በፈረስ በበቅሎ ነው የሚሄዱት፤ከመኳንንት ጋር ቁጭ ብለው
ኃጢያትን የሚዶልቱ ናቸው አለው እስኪ እባክህን በንስሃ ይጠራቸው እንደሆነ
ጠይቅሊኝ ይለዋል ይዚህ መልስ አልመጣለትም ይላል መጽሐፈ መነኮሳት 2ኛው
ወይንም ፊሊክስዩስ፤በነገራችን ላይ በፈረስና በብቅሎ ነው የሚሄዱት ያለው ያኔ
በ 3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ስለሆነ ነው ለዚህ ዘመን ስንመነዝረው ሐመርና
ኮብራ መሆኑም አይደል። አባ እንጦንስ የእረፍት ቀኑ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾ ብዙ
ቃል ኪዳን ገብቶለታል ጥር በባተ በ 22ኛው ቀን አርፏል። ከመልአኩ ቅዱስ
ኡራኤል ከአባ እንጦንስ በረከታቸውን ያሳትፈን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
ቅዱስ ኡራኤል ወአባ እንጦንስ
እንኳን አደረሳቹ
👉 @embtee @embtee
እኔን የሚጠብቀኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ እናንተም ከክፉ ነገር ይጠብቃቹ
አሜን
ጥር 24
በዚህች ቀን የኢትዮያዊው ጻድቅ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ስባረ
አፅማቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት አክብራ
የምትውልበት ታላቅ ቀን ነው አባታችን ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ተክለ
ሃይማኖት ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አሰቦ ዋሻ ውስጥ
ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል። ለዓመታት ከቆሙበት
ሳይቀመጡ ከፊት ከኋላ ከጐን እና ከጐን ምንም ሳይደገፉ በአንድ ቦታ በመወሰን
ለ 22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አስቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ
ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል ከዚያም ለ7 ዓመታት በአንድ
እግራቸው ቆመው ፀሎታቸውን ቀጠሉ ስለ ክብራቸውም ከእግዚአብሔር ክንፍ
ተሰጥቷቸዋል በአጠቃላይ ለ29 ዓመታት በጸሎት ቆይተዋል ዕረፍታቸውም
በተወለዱ በ99 ዓመት ሲሆን ቀኑም ነሐሴ 24 ቀን ነው።
በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ለዕረፍታቸው
በእግዚአብሔር ፊት
ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው አባታችን በየዓመቱ
ነሐሴ 24 ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን ታህሳስ 24 ቀን
በዓለ ልደታቸውን ዛሬ ጥር 24 ደግሞ ስባረ አፅማቸውን በታላቅ ድምቀት
ታከብራለች።
የፃድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ጸሎታቸው እና አማላጅነታቸው ቤተ
ክርስቲያናችንን አገራችንን ኢትዮጵያን እና እኛን ህዝቦቿን ከፈተና ይጠብቀን
ዘንድ በቃልኪዳናቸው ያስቧት አሜን!!!
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEzwE8Rx0_ELfmMHsg
†እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት አመታዊ ክብረ በዓል
በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ከጻድቁ አባታችን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት
ረድኤት በረከት ያሳድርብን አምላከ ተክለ ሃይማኖት በቸርነቱ አይለየን
አሜን !
@embtee
@embtee 👈👈