✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.21K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ
@embtee
@embtee
ነገ ወይም ማታ እንጀምራለን ትምህርት።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#አስደሳች_ዜና_ለግእዝ_ትምህርት_ፈላጊዎች
በሐገር ውስጥም ከሐገር ውጪም ላላችሁ የግእዝ ሥልጠና ፈላጊዎች ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ሥራችሁን እየሠራችሁ ትምህርታችሁን እየተማራችሁ በኦንላይን በቴሌግራም የልሳነ ግእዝን መሠልጠን ከፈለጉ በ @ASRATEGABRIEL ላይ አሁኑኑ ያነጋግሩን አጠቃላይ ክፍያ 200ብር ብቻ
✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞ pinned «#አስደሳች_ዜና_ለግእዝ_ትምህርት_ፈላጊዎች በሐገር ውስጥም ከሐገር ውጪም ላላችሁ የግእዝ ሥልጠና ፈላጊዎች ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ሥራችሁን እየሠራችሁ ትምህርታችሁን እየተማራችሁ በኦንላይን በቴሌግራም የልሳነ ግእዝን መሠልጠን ከፈለጉ በ @ASRATEGABRIEL ላይ አሁኑኑ ያነጋግሩን አጠቃላይ ክፍያ 200ብር ብቻ»
ውበት ነሽ ለቤቴ.aac
5 MB
✞ ውበት ነሽ ✞

▦ዘማሪት እታፈራሁ ወርቁ▦
╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
እንኳን አደረሳችሁ

"ሀያል ነህ አንተ ሀያል ደጉ መላእክ ገብርኤል
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት አንተ ተራዳን በእውነት..."


#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል 19
✝️✝️✝️

🛑 ሼር
4 More join us👇

╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​የመስቀል አደባባይ ባለቤት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሆኗ ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም ....ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

(ጥር 01 ቀን 2014 ዓ .ም
አዲስ አበባ፥ ኢትዮጵያ)

ዛሬ ጥር 1 ቀን 2014 ዓ.ም 9:00 ሐዋርያ ዘለዓለም የተባለ የወንጌላውያን አማኞች ኅብረት አባል የሆነ ፓስተር መስቀል አደባባይ ላይ ለጠራው የአምልኮ ፕሮግራም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በጽህፈት ቤታቸው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ብፁዕነታቸው የፓስተሩ የመስቀል አደባባይ ፕሮግራም እንዲሰረዝ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን ገልፀው ማሰረዝ ግን አልተቻለም ብለዋል።

እንዲህ ዓይነት ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች ሲኖሩ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት በኩል ተፈቅዶ መሆን ሲገባው ነገር ግን በአንድ ግለሰብ ጥሪ ከሃይማኖት ተቋማት ዕውቅና ውጭ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ጥሪ መተላለፉ አሳዝኖኛል ብለዋል።

ሐዋርያ ዘለዓለም የተባለን ሰው የወንጌላውያን ኅብረትም እንደማያቀው አጣርተው ለዚህ ፕሮግራም መንግሥት ዕውቅና መስጠት የለበትም በሚል ከፍተኛ ጥረት እንዳረጉ አውሰተዋል።

ሆኖም ግን መርሐ ግብሩ ቀድሞ የተያዘና ዓላማውም በጦርነቱ ለተጎዱ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሚል ሽፋን ይዞ በመንቀሳቀሱ ጥረታቸውን ክቡድ እንዳደረገው ተናግረዋል።

ክብርት ከንቲባዋ ጋር በአጭር ቀን ውስጥ ለመነጋገር ቀጠሮ እንዳላቸው የገለፁት ብፁዕነታቸው በስመ ሃይማኖት እኩልነት ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው ድርሻዋን ማጣት የለባትም ብለዋል።

የመስቀል አደባባይ ባለቤት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለመሆኗ ዓለም የመሰከረው በዩኔስኮ የተመዘገበው ከማይዳሰስ ቅርሷ በተጨማሪ ከጥንት ጀምሮ የደመራ በዓልን ማክበሯ እና ለስሙ ያላት አበርክቶዋ ምስክር ነው ብለዋል።

ቀደም ሲል ለባለብዙ አገልግሎት የታደሰው መስቀል አደባባይ ሲታደስ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ጋር የገባነው ውል አድሰው ለቤተክርስቲያን ሊያስረክቡ የነበረ መሆኑን አውሰተው ደብዳቤው በእጃችን ያለ በመሆኑ ይሄው ውል እንዲከበር ለመንግሥት ጥሪ አቅርበዋል።

በመስቀል አደባባይ እንደ የሕዝብ ስፖርት፣ ኮንሰርት እና ሌሎች ኩነቶች ፈቃጁ ሌላ መሆኑን ገልፀው ሃይማኖታዊ ከንዋኔ ሲሆን ግን የሚመለከታት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ብቻ ናት ብለዋል።

ቤተክርስቲያን ለልማት እና ለአብሮነት ያላት አስተዋጽኦ በጽኑዕ አቋም ከቃላት በላይ በተግባር የተገለፀ ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በ2011 ዓ.ም የአዲስ ከተማ አስተዳደር ቤተሰብ ለሌላቸው ተማሪዎች ለምገባ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ በጠየቀን ጊዜ ያለ ሃይማኖት ልዩነት ለሁሉም ተማሪዎች ምግብ የሚሆን 10.000.000 (አስር ሚሊዮን ብር) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መለገሱን የቤተክርስቲያኒቱን ለሁሉ አዛኝ መሆኗንም አስታውሰዋል።
ገንዘቡን ለመመለስ ዝግጁ ነን!
“በህዝብ ገንዘብ ነው የተሰራው፣ ስለዚህ የሁሉም አደባባይ ነው የምትሉ ከሆነ ገንዘቡን ለመመለስ ዝግጁዎች ነን። መስቀል ማክበሪያ ቦታ እርስታችን ነው፣ የተዋህዶ ልጅ ደሞ ለእርስቱ ናቡቴን ነው!

ቀሲስ መምህር ዶክተር ዘበነ ለማ
ከበኩረ ሰባክያን ምህረተአብ አሰፋ የተላከ መልዕክት

ተደዋወል፣ተነጋገር፣ተመካከር፣ይበቃል በል።ሌላው በኛ ቤት እንደልቡ ሲሆን፣ምን ያመጣሉ፣አንድ ሰሞን ተንጫጭተው፣በዛው ይቀራሉ፣እያለ ሲናገር፣አንተ ግን በገዛ ቤትህ መሰብሰብና መፍትሄ ማፈላለግ ካቃተህ፣በእውነት የአቡነ ጴጥሮስ አጽም እሾህ ሆኖ እንዳይወጋህ፣ረቡዕ ጥር 4 በቦሌ መድኃኔዓለም እንገናኝ።

Share አድርጉ!!!! ስልክህ ተዓምር መስራት ይችላል!
ፈዘናል ፈዘናል ፈዘናል!!
ሲጠበቅ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተራዘመ።
(ኢኦተቤ ቴቪ ጥር ፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም
ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር ፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ በቅዱስነታቸው አለመገኘት ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በገጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ስለገቡና ቅዱስነታቸው በመንበራቸው ላይ በሌሉበት ሁኔታ ጉባኤውን ማካሔድ ስለማይቻል የቅዱስ ፓትርያርኩ ጤና እስከሚመለስ ድረስ ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ የተላለፈ መሆኑን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል። እግዚአብሔር ለቅዱስነታቸው ምሕረቱን ሰጥቶ ወደ መንበራቸው ይመለስልን።
ፎቶ:- ከፋይል
“ከሕማሜ ይልቅ የመስቀል ዐደባባይ ነገር ይበልጥ ያሳስበኛል”

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

በእርሳቸው ሆስፒታል መግባት ከከንቲባዋ ይደረጋል የተባለው ስብሰባ ላልተወሠነ ጊዜ መተላለፉን ሲሰሙ የተናገሩት ነው።

፩. በእርሳቸው አለመገኘት ምክንያት ቀኑ ተላልፎ ተረሳስቶ እንዳይቀር ለዚህ ስብሰባ ብቻ ቀኖናው በሚፈቅደው መሠረት ከአረጋዊያኑ ወይም በፓትርያርኩ ውክልና የሲኖዶሱ ጸሐፊ እንዲመሩት ቢደረግ፣

፪. ከንቲባዋ እኔ ቢሮ ወይም ሸራተን እንሰብሰብ ማለታቸው የተሰማ ሲኾን አቡነ ዮሴፍ ግን ወደ መንበረ ፓትርያርክ እርሳቸው መምጣት እንዳለባቸው በጽኑ አሳስበዋል። አበው በዚህ አቋም ቢጸኑ፣

፫. ከከንቲባዋ ጋር የሚደረገው ውይይት ከመስቀል ዐደባባይ ከፍ ያለ ቢኾን።

፬. አሰላለፋቸውን ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለቤተ መንግሥቱ ለማድረግ የሚራወጡ አንድ ጳጳስ ዐርፈው እንዲቀመጡ የመጨረሻ ተግሣጽ ቢሰጣቸው።

የቅዱስነታቸው ጤንነት ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ መኾኑም ታውቋል።
ምንጭ# ከዲ/ን ዓባይነህ ካሤ ገፅ
Watch "አረሳት ኢትዮጵያን // Aresat ethiopian ሊቀ መዘምራን ይልማ ሐይሉ" on YouTube
https://youtu.be/H1Fc8nshWrI
ቋሚ ሲኖዶስ ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያንን መብትለማስከበር ይሰራል ።
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የመስቀል አደባባይ፣የጃንሜዳና ሌሎች የቤተክርስቲያን ይዞታዎች ጉዳይ በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ
አዳነ ች አቤቤ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ጥር 25/2014 ዓ.ም ይዞት በነበረው ቀጠሮ ዙሪያ ባካሔደው ስብሰባ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የሚደረገው ውይይት ቋሚ ሲኖዶስ በሚያስቀምጠው አቅጣጫና ጊዜ ቀጠሮ መሰረት በተለዋጭ ቀጠሮ የሚካሔድ ይሆናል።
የከተማ አስተዳደሩም ቤተክርስቲያን በምታሳውቀው ጊዜ ቀጠሮ ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ዛሬ አስታውቋል።
ቅዱስ ሲኖዶስም ከሚቀጥለው ቀጠሮ ጀምሮ ሕጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያኒቱ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

ኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት