✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.21K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
የእመቤታችን የስሟ ክብር!

በቀሲስ መምህር ሄኖክ ወልደ-ማርያም

በአንድ ወቅት ወደ ወሎ አካባቢ ሁለት የቆሎ ተማሪዎች ሲከራከሩ አንድ አባት የይሰማሉ፡፡ መከራከሪያ ነጥባቸው አንዱ የቆሎ ተማሪ ማርያምን ብሎ ሲምል ይሰማዋል፡፡ ይህን የሰማው ተሜም ‹‹ማርያምን ብለህ፣ በሙሉ አፍህ ጠርተህ መማል ቀርቶ ስሟን መጥራት አይገባህም›› ይለዋል፡፡ ምላሽ ሰጪ ተሜ ደግሞ ‹‹እናቴ ናት ስሟን ብጠራ፣ በስሟ ብምል ምን ገዶህ››ይለዋል፡፡ ተከራካሪ ተሜም ‹‹ትሰማለህ ውዳሴዋን ሳታደርስ፣ ፍቅሯን በልቦናህ ሳታሳድር ማርያም ስትል አታፍርም? አባቶች እመቤታችን ድንግል ማርያም ብለው ቢጠሯት ውዳሴዋን አድረሰውላት፣ በፍቅሯ ብዙ ሆነውላት ነው የከበረ ስሟን የሚጠሩት›› ይለዋል፡፡

ለመሸነፍ የዳዳ ተሜ የራሱን ባዶነት የእመቤታችንን የስሟን አክብሮት በመገንዘብ ‹‹ታዲያ በስሟ ካልጠራኋት ምን ብዬ ልጥራት›› ይለዋል፡፡ አዛኜ ብለህ ጥራት ይለዋ፡፡ የእነዚህን የፍቅር ክርክር የሰሙት አባት በመሃላቸው በመግባት ‹‹ትሰማለህ ተሜ አንተም ስሟን መጥራት ፈርተህ አዛኜ ብትላት የከበረ ስሟን አክብረህላት ነው፡፡ አንተም እመቤቴ ማርያም ብትላት የከበረ ስሟን ወደህላት ነው፡፡ ስለዚህ ሁለታችሁም ልክ ናችሁ›› ብለው ሃሳባቸውን በማስታረቅ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡

ለብቻቸው እየሄዱ ‹‹አይ እመቤቴ እንኳን ለምስጋናሽ ለከበረው ስም አጠራርሽ የማልበቃ ኃጢአተኛ ነኝ›› ብለው የእመቤታችንን የሥም አጠራር ተረድተው በተማሪው ትህትና ተገርመዋል፡፡ የእመቤታችን ስም የክርስቶስን ፍርድ የሚያራራ ነው፡፡ ኃጥአን በምድር በሥጋ በሠሩት በደል፣ ጌታችን በሰማይ በነፍስ ብድራቸውን ሲከፍል፣ እነዛ በእሳት ዙፋን ፊት የቆሙ ምስኪን ነፍሳት ጌታችንን ‹‹እባክህን ስለ እናትህ ብለህ ማረን ይቅር በለን፡፡ ስለ ስሟ ተለመነን›› ይሉታል፡፡ ጌታችንም ስለ ስሟ ፍርዱን ያቀላል፡፡ በእሷ ጸጋ ያጸድቃል፡፡

ጌታችን እንኳን ለሙሉ ክብሯ፣ ለስም አጠራሯ ልዩ ቦታ አለው፡፡ የእመቤታችን ስሟ መድኃኒት ነው፡፡ አባቶቻችን እናቶቻችን ለፍቅሯ ለስም አጠራሯ ከመሳሳታቸው የተነሳ አዛኜ፣ ወለላይቱ፣ እማዋይሽ፣ ወይኒቱ ወዘተ… በማለት
ይጠሯታል፡፡

እመቤታችን እንኳን ያደረባት የመለኮት ጸጋ ቀርቶ፣ስሟ የአጋንንት መዶሻ፣ የሰይጣን ድል መንሻ፣ የዲያብሎስ ማሸሻ፣ ነው፡፡ ስሟ ሲጠራ አጋንንት ረአድ፣ በድንጋጤ መርበድበድ ስለሚይዛቸው ስም አጠራሯን ይፈሩታል፡፡

እናውቃለን ዛሬ በዘመናችን ድንቅ ሠሪ፣ አጋንንት አባራሪ የሆነችው ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ስሟ ሲጠራ አጋንንት ይቃጠላሉ፣ መሄጃ መሮጫ ያጣሉ፣ በድንጋጤ ባህር ገደል ይገባሉ፡፡ እመቤታችን በወለደችው በክርስቶስ ስም መከራ እና በአንገቷ ካራ የተቀበለችው የቅድስት አርሴማ ስም ተዓምር ከሠራ የቅድስት አርሴማን አምላክ የወለደችው የእመቤታችን ስሟ ምን ይሠራ ይሆን?

እመቤታችን በሥጋ አርፋ ቅዱሳን ሐዋርያት ለቀብር ወደ ቤቴሴማኔኒ ይዘዋት በሄዱበት ሰዓት በትዕቢት የደነዘዘ፣ የአልጋዋን ሸንኮር ለመጣል እጁን የመዘዘ ታውፋንያ በቅዱስ ገብርኤል የእሳት ሰይፍ እጁ ተጎምዶ ነበር፡፡ የእመቤታችንን የስሟ ክብር ያወቀው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ግን የታውፋንያን እጅ በልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብቻ በተአምራት ሊገጥምለት አላሰበም፡፡ ይልቁኑም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በድንግል ማርያም ስም በማለት ወደ ነበረበት ቦታ መልሶለታል፡፡ ቅዱስ ጴጥረስ በጌታችን ስም ሙት እያስነሳ፣ ድውያንን እየፈወሰ ድንቆችን የሚያደርግ ሊቀ ሐዋርያት ነው፡፡ ነገር ግን ከጌታው ስም በተጨማሪ የእናቱ ስም ተአምር እንደሚያደርግ ስላወቀ በተግባር አሳይቶናል፡፡

የበላዔ ሰብዕ የመዳን ምክንያት፣ የእመቤታችን የስሟ መጠራት ነው፡፡ በላዔ ሰብዕ በስሟ ተለመነ ጥሪኘ ውሃ ሠጠ፣ ከሰባ ስምንት ነፍስ ዕዳ አመለጠ፡፡ ጌታችን ለቅዱሳን ቃል ኪዳን ሲገባ የመጀመሪያው ‹‹ስማችሁን የጠራ፣ በስማችሁ የተማጸነ›› በማለት ነው፡፡ ለካ ስም መጥራት ያስገባል መንግስተ ሰማያት፡፡

በአገራችንም በውጭም ያሉ ቅዱሳኖች የተትረፈረፈ የጸና ቃል ኪዳን ከፈጣሪያቸው ተቀብለዋል፡፡ ከተቀበሉት ውስጥ አንዱ ‹‹ስማችሁን የጠራ፣ በስማችሁ የተማጸነ፣ ስሙን በስመማችሁ የሰየመ›› የሚል ነው፡፡ ጌታችንም እመቤታችንን ‹‹ስሙን /ስሟን/ በስምሽ የሰየሙ በመላእክት ፊት የከበሩ፣ በመንግስቴ ለዘላለም የሚኖሩ ናቸው›› ብሎ በስሟ ብቻ ቃል-ኪዳን ገቶላታል፡፡ ወገኔ አማላጅነቷ አይድነቀን ስሟ ብቻ መጽደቂያችን ነው፡፡ በእርግጥ ለመጽደቅ ሥራ ያስፈልጋታል፡፡ ግን ብዙዎች በስሟ ገነት ገብተዋል፡፡

ማርያም የሚለው ስሟ ብዙ ትርጓሜ ቢኖረውም እንደ አባቶቻችን አስተምህሮ ማርያም የሚለውን ስሟን በሁለት ከፍለው ትረጉሙን ይነግሩናል፡፡ ማር እና ያም!፡፡

ማር ፡- በምድር ካሉ ጣፋጭ ምግቦች አንዱ ነው፡፡ ማር በጣፋጭነቱ ብቻ ሳይሆን በመድሃኒትነቱም ይታወቃል፡፡

ያም፡- በሰማይ ያሉ ቅዱሳን የሚመገቡት እጅግ ጣፋጭ ምግብ ነው፡፡

ስለዚህ የእመቤታችን ስም በምድርም በሰማይም ላሉት ሁሉ እንደ ምግብ ጣፋጭ እና መድሃኒት ነው፡፡ ማርያም የሚለውን ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ከእመቤታችን በፊት እና በኋላ የተጠሩበት ሴቶች አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡-

1/ ማርያም፡- የሙሴ እህት - ዘፀ. 15-20

2/ ማርያም፡- የዮቶር ልጅ የእዝራ የልጅ ልጅ 1 ዜና.መ 4÷17

3/ ማርያም፡- የማርታና የአልዓዛር እህት - ዮሐ. 11÷1

4/ ማርያም መግደላዊት፡-ሰበት አጋንንት የወጣላት ሉቃ. 8÷2,፣ ማር. 15÷40-41

5/ ማርያም፡- የታናሹ የያዕቆብና የዮሳም እናት ማር.16÷1፣ ሉቃ. 24÷10

6/ ማርያም፡- የቀለዮጳ ሚስት- ዮሐ. 19÷25

7/ማርያም፡- የማርቆስ እናት - ሐዋ.ሥራ 12÷12

እነዚህ ከላይ ያሉት በማርያም የተጠሩ ቢሆንም የእመቤታችን የድንግል ማርያም ስም ግን ግብሯን ይጠቅሳል፡፡ ያ ማለት ቅድስናዋን ንጽህናዋን፣ መድኃኒትነቷን፣ በምድርም በሰማይም የከበረች መሆንዋን ስለሚገልጽ ልዩ ያደርጋታል፡፡

ውድ የእመቤታችን ልጆች እኛም ስሟን ልናከብር እንጂ በሆነውም ባልሆነውም ስሟን መጥራት አልያም በስሟ መማልና መገዘት የለብንም፡፡ ማርያም የሚለው ስም ለእኛ ለልጆቿ እንደ ማርዳ በአንገታችን የሚጠለቅ ጌጣችን፣ እንደ ቅቤ ከሰውነታችን የሚዋኃድ፣ ኋላም የሚያድን ከፍርድ ነው፡፡ ስለዚህ የከበረ ስሟን በአግባቡ ጠርተን አክብረን ለመክበር ያብቃን፡፡

‹‹በስምሽ ያመነውን ማን ያስፈራዋል፡፡ በልጅሽስ ያመነውን ማን የስፈራዋል፡፡ የአንበሳም ጩኸት እንደ ውሻ ጩኸት ይመስለዋል፡፡ የነብሮችም ኃይል እንደ ድመት ደካማ ነው›› አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ይቺን ቅድስት እናት እናክብር፣ እንውደዳት በፍቅር!
‹‹ስለ እመቤታችን ክብር፣ያላስተዋልነው ነገር›› ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ፡፡

መስከረም 6/1/12 ዓ.ም
አዲስ አበባ
•እንኳን ደስ አላችሁ የዳዊት ዜማ ተደራሽነቱን ለማስፋት በዩቲዩብ መምጣቱን ሰምተዋል!

«ተጀምሯል»

መንፈስን አዳሽ የሆኑ ዝማሬዎችን እንዲሁም በተጨማሪ አውደ ስብከቶችን ግጥሞች በምስል እና በቪዲዬ በታገዘ ወቅታዊ የሆኑ ዝግጅቶችን ዜናዎችን ይዘን እንቀርባለን እንዳያመልጦ ከስር የተቀመጠው ሊንኩን ከፍተው SUBSCRIBE 🔻 ያድርጉት የደወል 🔔 ምልክቱንም ይጫኑ በየእለቱ ወደናንተ የምንለቀው ይደርሶታል እናመሰግናለን .

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://m.youtube.com/channel/UCuzDApz9RTu02VXXFRnwQtg
https://m.youtube.com/channel/UCuzDApz9RTu02VXXFRnwQtg
https://m.youtube.com/channel/UCuzDApz9RTu02VXXFRnwQtg
👆👆👆👆ይክፈቱት👇👇👇👇👇
✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞ pinned «•እንኳን ደስ አላችሁ የዳዊት ዜማ ተደራሽነቱን ለማስፋት በዩቲዩብ መምጣቱን ሰምተዋል! «ተጀምሯል» መንፈስን አዳሽ የሆኑ ዝማሬዎችን እንዲሁም በተጨማሪ አውደ ስብከቶችን ግጥሞች በምስል እና በቪዲዬ በታገዘ ወቅታዊ የሆኑ ዝግጅቶችን ዜናዎችን ይዘን እንቀርባለን እንዳያመልጦ ከስር የተቀመጠው ሊንኩን ከፍተው SUBSCRIBE 🔻 ያድርጉት የደወል 🔔 ምልክቱንም ይጫኑ በየእለቱ ወደናንተ…»
✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞ pinned «ክፍል 3 እነሆ ብለናል https://youtu.be/7n0ZD843RaM https://youtu.be/7n0ZD843RaM https://youtu.be/7n0ZD843RaM»
መታደል ማለት ባለሃብት ወይም ዝነኛ መሆን አይደለም

መታደልስ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ሆኖ መፈጠር ነው

ኦርቶዶክስ ያረከኝ አምላክ ስምህ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን ( አሜን )

በስተመጨረሻ የድንግል ማርያም ልጆች በተለይ ወጣቶች የአባቶችን ቃል ጠብቁ ሀይማኖታቹን ጠብቁ ያሉንን አንርሳ በመንግስት የሚደገፈው አቶ ዮናታን የሚባለው ለስም መልካም ወጣት ብለው የመሰረቱት አላማው ወደ ጴንጤነት ማስኮብለል ነውና ወጣት ሆይ ንቃ በመሪአችን እውቅና የተሰጠው ያለምክንያት አይደለም በቲቪ መምጣቱ ያለምክንያት አይደለም ካስታወሳቹ የበግ ለምድ ለብሰው ይመጣሉ የሚለውን አስታወሳቹ ንቁ ንቁ ንቁ ንቁ ተዋህዶ ከነክብሯ ለዘላለም ትኑር እመብርሀን ምልጃዋ ጥበቃዋ አይለየን አሜን።

@zemaryan
ለሁሉም ይድረስ አጋሩ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን።

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለምንድን ነው ለመስቀል ክብር የምትሰጠው?

መስቀል
"መስቀል ኃይላችን ነው
ኃይላችን መስቀል ነው
የሚያፀናን መስቀል ነው
መስቀል ቤዛችን ነው
መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው
አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነው እኛም በመስቀሉ
እንድናለን ድነናልም።" /የዘወትር ጸሎት/

በብሉይ ኪዳን መስቀል የእርግማን ምልክት ና የወንጀለኞች መቀጫ ነበር::(ዘዳ 21:23)
ክርስቶስ በደሙ ስለቀደሰው ግን ቅዱስ መስቀል ተብሏል። በመስቀል ድህነትን አግኝተናል።(1ኛ. ጴጥ 2: 24-25)
ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለሙን ከኃጢአትና ከሞት ለማዳን በቀራኒዮ የተሰቀለበት ቤዛችን ነው።
መስቀል የነጻነታችን ግርማ: የድህነታችን መገኛ: ጠላትን ድል የምንነሣበት መሳሪያችን ነው።
ሰውን በመስቀል ላይ መቅጣት የተጀመረው በጥንቱ ፋርስ በዛሬዋ ኢራን /ከክርስቶስ ልደት በፊት/339-33/ ዓመት ነው።

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለምንድን ነው ለመስቀል ክብርን የምትሰጠው?

1. ክርስቶስ መስዋዕት ሆኖ ራሱን የሠዋበት እውነተኛ መንበር በመሆኑ፤
2. የክርስቶስ ደም የፈሰሰበት: እኛ የዳንበት የነጻነት አርማችን ስለሆነ፤
3. የአምላካችን መለኮታዊ ፍቅር የተገለጠበት መሳሪያ በመሆኑ፤

የመስቀል ዓይነቶች
___

1. የመጾር መስቀል:-
±±±±±±±±±±±±±
በቅዳሴ እና በማዕጠንት ጊዜ ሠራዒው ዲያቆን የሚይዘው ነው።

2. የእጅ መስቀል:-
±±±±±±±±±±±±±±±
ካህናት ምእመናንን የሚባርኩበት በእጅ የምትያዝ የመስቀል ዓይነት ናት።
3. የአንገት መስቀል:-
±±±±±±±±±±±±±±±±
ምእመናን ለአምላካቸው ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ ከማዕተባቸው ጋር በአንገታቸው የሚያደርጉት ነው።

4. እርፈ መስቀል:-
±±±±±±±±±±±±±±
በማንኪያ ቅርጽ ተሠርቶ በእጅታው ላይ የመስቀል ምልክት ያለበት ነው። ሠራዒው ዲያቆን በቅዳሴ ጊዜ የአምላካችንን ክቡር ደሙን ለምእመናን የሚያቀብልበት ነው። እንዲሁም ጌታችን በእለተ አርብ የተወጋበት ጦር ምሳሌ ነው።
መስቀል ከተለያዩ ማዕድናት ይሰራል

መስቀል ከተለያዩ ማዕድናት ሊሰራ ይችላል: መስቀሉ የሚሰራባቸው ማዕድናት የራሳቸውን ባህርያት እንዳላቸው ሁሉ ምሳሌውን ለመግለጽ ብቁ ናቸው ብለው አባቶች ያስቀመጡትን እንደሚከተለው እንመለከታለን፦

1. የእንጨት መስቀል:-
----------------------------
ጌታችን የተሰቀለው በዕጽ በእንጨት ላይ መሆኑን ለማመልከት ነው።
+ ለምን ኢየሱስ ክርስቶስ በእንጨት ተሰቀለ? አዳም ዕጽ/ እንጨትን በልቶ ሞትን በማምጣቱ ክርስቶስም በእንጨት ተሰቀሎ ህይወትን ሊሰጠን በእንጨት መስቀል ተሰቀለ።
2. የብረት መስቀል:-
-------------------------'-'
ጌታችን በአምስቱ ቅንዋተ ለመቸንከሩ ምሳሌ ነው።

3. የብር መስቀል:-
---------------------------
ይሁዳ በሠላሳ ብር አሳልፎ ስለመስጠቱ። በተጨማሪም ከብር ቢሰራ ተስፋን: ዕድልን ያመለክታል። ይኸውም እርሱ ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ ሊሆን በደሙ ዋጋ ከፍሏልና ከእርሱ ተስፋ እንድናደርግ ያመለክተናል።
4. የወርቅ መስቀል፦
---------------------------
ከወርቅ ቢሰራ ወርቅ ንጹህ እንደሆነ ንጹሀ ባህርይ እድፈት የሌለው
ጽኑ አንተ ነህ ብሎ ለመመስከር ነው።

5. የመዳብ መስቀል:-
------------------------------
መዳብ ቀለሙ ቀይ ይመስላል: ጌታችን ለእኛ ብሎ ያፈሰሰው ደም ምሳሌ ነው።

ብዙዎች የመስቀል ጣላት ሆነው መስቀልን ጣኦት ነው ይላሉ ጣኦት ማለት ግን የሠይጣን ስም የሚጠራበት ፣የሚመለክበት ነው።
መስቀል ደግሞ የመድኃኒዓለም ስም የሚጠራበት ህማሙን የሚድኑበት አርማችን፣ ኃይላችን ነው እንጂ መስቀል አምላክ አይደለም። በመስቀል የተሠቀለው ግን አምላክ ነው።
ምሳሌ: ሰው አልጋ ላይ ሲተኛ አልጋ ላይ ተኛ ይባላል እንጂ እንጨቱ ላይ ተኛ አይባልም: ሰው የቤቱን በር ሲዘጋ እጨቴን ልዝጋ አይልም በሩን ልዝጋ ይላል እንጂ: አልጋ አልጋ ይባላል የተሰራው ከእንጨት ሊሆን ይችላል ነገር ግን እንጨት ተብሎ አይጠራም: በርም በር ይባላል እንጂ እንጨት ተብሎ አይጠራም። እንዲሁም ጌታ የተሰቀለበትን መስቀል መስቀል ይባላል ፤እንጂ እንጨት አይባልም።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሏል:
"ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ።
መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።
(ፊልጵ 3÷18-19)

" ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ
ይራቅ።" ( ገላ 6:14)
@Zemaryan
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።
የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ ተብሎ ተጽፎአልና።
(1ኛ ቆሮ 1÷18-19)

ጌታ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፡፡
@Zemaryan
መስከረም 16ቀን 2013ዓ.ም

መልካም በዓል
@Zemaryan @Zemaryan
፨ ሲኦል ይሻለኛል ፨
እነ አባ ኤፍሬም ውዳሴ ማርያምን ፅፈው እውነት ካልፀደቁ እነ አባ ህርያቆስ ቅዳሴ ማርያምን ፅፈው እውነት ካልፀደቁ እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አርጋኖንን ሰዓታትን ደርሰው እውነት ካልፀደቁ እነ ቅዱስ ያሬድ አንቀፀ ብርሀንን ድጓን ደርሰው እውነት ካልፀደቁ እነ ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ መፅሀፍትን እንደዛ አመስጥረው እውነት ካልፀደቁ እነሱ ከሌሉበት ገነት ይልቅ እነሱ ያሉበት ሲኦል ይሻለኛል ። የሚያረጅ እምነት ስለሌለን የሚታደሰ ሀይማኖት የለንም ። እኛ በሀጥያት ስናረጅ ቤተክርስቲያን እኛን በንስሀ እና በስጋ ወደሙ ታድሰናለች እንጂ እሷ አትታደስም ። አባቶቻችን የቀደሱትን ቅዳሴ እንቀድሳለን ፡ እነሱ የደገሙትን ውዳሴማርያምና ዳዊት እንደግማለን ። እነሱ የቆሙትን ሰዓታትና ማህሌት እንቆማለን ። እነሱ የተቀበሉትን ስጋና ደም እንቀበላለን ። ከዛስ ? እነሱ የገቡበት እንገባለን ። እምነታችን ይህ ነው ።
@Sihela_adhno
@Sihela_adhno
#ከማኅበረ_ሥላሴ_አንድነት_ገዳም_የተላከ_መልዕክት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቢያንስ ለ 15 የተዋህዶ ልጆች Share በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ።


#በኢትዮጵያና_በመላው_ዓለም_ለምትገኙ_ኦርቶዶክስ
_ክርስቲያኖች_በሙሉ_ከጥቅምት_24_እስከ_30_ከ
ህፃናት_እስከ_ሽማግሌ_ማንም_ሳይቀር_በማህበረ_መ
ነኮሳቱ_አማካኝነት_ፆም_ታውጇል::
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱአምላክ አሜን
በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኛችሁና በደሙ የዋጃችሁ በኢትዮጵያ
የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ በቤታችሁም ያላችሁ
በህመም ምክንያት በሆስፒታል ያላችሁ በማረሚያ ቤት ያላችሁ
በጦር ሜዳም ያለችሁ እንዲሁም በተለያየ ስፍራ የምትገኙ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የከበረ ሰላምታችንን
በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡
እኛ ማኅበረ ስላሴ እንድነት ገዳም የምንገኝ ማኅበረ መነኩሳት
በሀገራችን ሰላም መታጣት ምክንያት ከሀዘናችን ጋር አምላክ
አበው ክብር ምስጋና ይግባዉ ደኅና ነን፡፡
እግዚአብሔር ገና ሃያ ሁለቱን ስነ-ፍጥረት ፈጥሮ ሳያበቃ
ሳጥናኤል በዓለተ ረቡዕ በሶስተኛዉ ሰማይ በጌታ ላይ በማመጽ
በጀመረዉ ጸብ ምክንያት ከመላዕክቱ ጋር ተዋግቶ ተሸንፎ ወደ
ምድር ተጥሎ እነሆ ያለ እረፍት ለሰባ ሺ አምስት መቶ አመታት
በመላዉ ዓለም ደም ሲያፈስ ቆይቷል፡፡ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ፡፡
ጌታ የተሰጠዉ የቀጠሮ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ታግሶታል፡፡
አሁን ግን ከወትሮዉ ለየት ያለዉ ነገር የእግዚአብሔር ቤተ -
መቅደስ በሆነችዉና የቅዱሳን የአስራት ሀገር በተሰኘችው
በኢትዮጵያ ሀገራችን የሳጥናኤል ጭፍሮች ክተት ሰራዊት ምታ
ነጋሪት ብለዉ ዘምተዉ በታሪክም ያልሰማነዉ በዘመናችንማ
አይተን የማናቀዉ የአርስ በአርስ እልቂት እንኳን ከክርስቲያን
ከሰብአዊ ፍጡር የማይጠበቅ ድርጊት ተፈጽሟል እየተፈጸመም
ነዉ፡፡
ሰይጣን ብቻዉን ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ከሰዉ ጋር ሆኖ
በሰዉ ልብ አድሮ ግን ምንም የሚቀረዉ የሀጢያት ሥራ የለም፡፡
በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፡፲፭ ላይ ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ
ያለዉ የጌታ ቃል ተጥሷል፡፡
ቀድሞ አንድ ሰዉ ለሥራም ሆነ ለንግድ ወይም ለተለያየ
ጉዳይ ወደ ማያዉቀዉ ወደ ሚያዉቀዉም በኢትዮጵያ ክፍላተ
ሀገር ወይም ክልል ሲዘዋወር ለሀገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ነኝ
ብሎ አይጨነቅም፡፡ የእግዚአብሔር እንግዳ ተብሎ ከመሸበት
ገብቶ እግሩን ታጥቦ ቤት ያፈራውን በልቶ ጠጥቶ ከመልካም
ምንጣፍ ተኝቶ አድሮ ሲነጋ ተነስቶ መርቆ ቀሪዉን ምንገድ
ይጓዛል፡፡
ዛሬ ግን ያ ቀረና የእግዚአብሔር እንግዳ እራቱ ጥይትና ገጀራ
መጠጡ ደም ሆኗል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ ፳፭፥፵፪ ላይ
የተጠቀሰዉ እንግዳ ሆኜ ብመጣ አልተቀበላችሁኝም ብራብ
አላበላችሁኝም የሚለዉ የጌታ ቃል ትዉልዱን እየተዋቀሰዉ ነዉ፡፡
በእርግጥም በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ ብሎ ዮሐንስ
ወንጌላዊ እንደተናገረዉ እንግዶች የሰላም ተጓዦች መሆን
ይጠበቅባቸዋል፡፡ነገር ግን የሰላም ሰዎችም አብረዉ
ተጨፍልቀዉ የጥፋት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነ
እግዚአብሔር አሁንም ታግሶናል፡፡እኛ አሁን ከሞት የተረፍነዉ
ከጥላ ያረፍነዉ በጽድቃችን አይደለም በቸርነቱ ለንስሐ ጊዜ
ተሰጥቶን ነዉ እንጅ፡፡
ነቢያት ስለ ጥፋት ሲተነብዩ በሰዉ ልጅ ሐጥያት ከእግዚአብሔር
የሚታዘዘዉን መቅሰፍት ማስገንዘባቸዉን እንጅ ጥፋት ዝም ብሎ
ደርሶ የሚታዘዝ አይደለም፡፡
አሁን በኃጢያታችን ምክንያት እየተጎነጨነዉ ያለዉ መከራ ከዚህ
በፊት ብዙ የተነገረ ቢሆንም በትንቢተ ዮናስ ታሪካቸዉ
እንደተጠቀሰዉ እንደ ሰብዓዊ ነነዌ ወደ እግዚአብሔር በጾም
በጸሎት ሆኖ በመለመን በማልቀስ መከራዉን ማስቀረት
እንዲቻል ቅዱሳን በመጽሐፍት አስተምረዉናል፡፡
በኖህ ዘመን ምድር በዉሃ ሙላት የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት
ነዉ፡፡ በሎጥ ዘመን በሰዶም ሀገር የተቃጠለችዉና ከምድረ ገጽ
የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት ነዉ፡፡
ዛሬስ እየተሰራ ያለዉ ኃጢያት በዚያ ዘመን ከነበረዉ ያንሳልን ?
ያን ጊዜስ በንስሀ ላልተመለሱ ሰዎች ፈርዶ ያጠፋቸዉ አምላክ
ዛሬስ ፈርዶ ማጥፋቱ ይሳነዋል ወይ ? አይሳነዉም
እንዲያዉም እንደ ዘመናችን ኃጢያት ብዛትና ክብደት
ላልፈረደብን እግዚብሔር እያመሰገንን ይህን መልዕክት
በያላችሁበት ሲነበብላችሁ ከሰማችሁት በኋላ ወደ ልባችሁ
ተመለሱ ከእንግዲህ ወዲህ በዘር ፣ በጎሳ ፣ በቋንቋ ፣ በሀገር ፣
በብሔር መለያየት ይብቃ ፣ መገዳደል ይብቃ ፣ መዘራረፍ ይብቃ
፣መሰደድም ይብቃ አጠቃላይ የጥፋት ዘመቻ ይብቃ፡፡ ወደ
ቀድሞ ኢትዮጵያዊ አንድነታቸን እንመለስ በኅብረት ተቻችለን
እንኑር፡፡
የኃጢያታችንን ካባ አዉልቀን በነብስም በሥጋም የሚያድነንን
የንስሐ ካባ እንልበስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፥፲፪ ላይ እኔ
እንደወደድኳችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ብሎ ጌታችን ባዘዘብ
መሰረት ጥላቻን አስወግደን የዘር ፣የጎሳ፣ የቋንቋ ፣ የክልል
ልዩነት ሳይኖረን እርረ በእርሳችን እንዋደድ፡፡
በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፬፥፳፯ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ያለዉ ጌታ
ቃሉ አይለወጥም እና ይህ ከሆነ ብቻ እዉነተኛዉን ሰላም
ማግኘት ይቻላል፡፡
የተከበራችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ነብዩ ኢሳያስ በትንቢቱ ምዕ
፩፥፲፱ ላይ ‹‹ እሺ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት
ትበላላችሁ እምቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኃለች
የእግዚአብሔር አፍ ይህንን ተናግሯልና›› የሚለዉን የትንቢት ቃል
ዛሬም በእኛ ኢትዮጵዊያን ላይ እንዳይደርስብን ለእግዚአብሔር
ቃል እንታዘዝ እና ክፋትን ሁሉ ትተን ንስሀ ገብተን የምድርና
በረከት እንብላ፡፡ አለበዚያ ግን ምሕረት በእጁ የሆነ አምላክ
መዓተም በእጁ ነዉና ምርጫዉ ግን የእናንተ ነዉ፡፡ በሀገራችን
ሰላም ይሰፍን ዘንድ ማንኛዉም ክርስቲያን የተጣላ ታርቆ ፣
የበደለ ክሶ ፣ ይቅር ተባብሎ ፤ ከጥቅምት ፳፬ እስከ ጥቅምት ፴
ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም ድረስ ልጅ አዋቂ ሳይለይ እስከ ዘጠኝ ሰዓት
እየጾማችሁ በሀዘን በለቅሶ ምህላ በመያዝ ከእግዚአብሔር
ምህረትና ይቅርታ በጋራ እንድንለምን እኛ የማኅበረ ሥላሴ
አንድነት ገዳም ማኅበረ መነኮሳት ሁሉን በፈጠሩ በቅድስት
ሥላሴ ስም አምላክን በወለደች በእናታችን በቅድስት ድንግል
ማርያም ስም በታላቅ አክብሮት መልዕክታችንን ለመላዉ ሕዝበ
ክርስቲያን አስተላልፈናል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ሰላም ይስጥልኝ
የሞቱትን ሁሉ ነብስ ይማርልን
የጠፋዉን የተቃጠለዉን የወደመዉን ንብረት ሆሉ ይተካላችሁ
አሜን ይሁን ይደረግልን
መምህር አባ ወልደ ሰንበት ነጋሽ
የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም አበመኔት
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Share share share share share share

1 ሰው ለ 15 ምዕመን
╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
ሰላም የቻናላችን ተከታታዩች
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስብከተ ወንጌል የተለያዩ መፃፀፎች መንፈሳዊ ዜናዎች
እንደሚያቀርብ ይታወቃል ያሎትን ሀሳብ አስተያየት ቢቀነስ ቢጨመር የምትሉትን ይፃፉል አስተያየታቹ ያበረታታናልና

እናም በዚ ቻናል ለማገልገል ፍላጎት ያሎት 👉 https://tttttt.me/maryamn111bot