✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.21K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
AUD-20181227-WA0005
<unknown>
*እኛ ጡት የሌላት ታናሽ እኅት አለችን ስለ ርሷ በሚናገሩባት ቀን ለእኅታችን ምን እናድርግላት*
*መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ፰፥፰*
በመጋቤ ብሉይ መምህር ኤልያስ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
*ማኅበረ ተዋሕዶ ዘ-ኦርቶዶክስ*

┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
👆👂👂👈
++ በሦስቱ ወጣቶች እምነት የእሳት ኃይል በእሳት ጠፋ ዳን
3÷1-30!! ++

እግዚአብሔርን የካደ በጉልበቱ የተመካ ሥልጣንን ክብርን
ባዕለጠግነትን መፈራትን የሰጠውን ፈጣሪውን የዘነጋ ሰው ንጉሥ
ናቡከደነጾር በባቢሎን ምድር በዱራ ሜዳ ላይ ቁመቱ ስድሳ ክንድ
ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አቁሞ ሕዝቡ በሙሉ
ለእርሱና ለጣዖት ይሰግዱ ዘንድ አዋጅን አወጀ ፡፡ ሕዝቡም
አዋጁን ተከትለው ንጉሥ ላቆመው ጣዖት እንደ ግንድ እየተረበረቡ
እንደ ሻሽ እየተነጠፉ ይሰግዱ ጀመር ፡፡ እግዚአብሔር ሀገርን
ዘመንን ያለ ደጋግ ሰዎች አይተውምና ስቶ በጣዖት ፍቅር ነድዶ
ተጨልጦና ተገርኝቶ በጠፋው ሕዝብ መካከል በእድሜያቸው ለጋ
የነበሩ ሦስቱን ወጣቶች ለምሥክርነት አገኘ ፡፡ ሦስቱ ወጣቶች
እንደተቀረው ሕዝብ ንጉሥ ንጉስ ላቆመው ምስል ሰግደው
ለምን ? ሲባሉ
እምነት በልብ ነው አስመሰልን እንጂ አልሰገድንም
ያለነው በባዕድ ሀገር ያውም በምርኮ ነው በባዕድ ሀገር ያለ
ሰው ደግሞ ቢጭኑት አህያ ቢለጉሙት ፈረስ ነው ስለዚህ
ብንሰግድ ምንም ማለት አይደለም
የሰገድነው ወጣትነታችን አታልሎን አፍላነታችን ገፍትሮን ነው
እንኳን እኛ ሮጠን በልተን ያልጠገብነው ጎልማሶቹ ሽማግሎቹ
አዛውንቱ ሰግደው የለምን ?
ኋላ ንስሐ እንገባለን
ይገድሉናል ብለን ፈርተን ነው የሚሉና ሌሎች ብዙ ሰንካላ
ምክንያቶችን ማቅረብ ይችሉ ነበር፡፡
እነርሱ ግን ለስህተትና ለጥፋት ምክንያት አበጅተው ፈጣሪያቸውን
ክደው ለጣዖት አልሰገዱም ፡፡ በዚህም ታላቅ እምነታቸውና
ተጋድሏቸው ቅዱስ መጽሐፍ ለዘላለም ሲያወሳቸው እውነተኛ
ክርስቲያኖችም ሲመሰክሩላቸው ይኖራሉ ፡፡
+++ የሦስቱ ወጣቶች ታላቅ እምነት +++
በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች እግዚአብሔርን የምናመልከው
የምናገለግለው አስከሞላልን እስከተሳካልን እስከጠገብንና
እስከተመቸን ብቻ እንጂ ከጎደለብን ካጣን ከተቸገርን እርሱን
ለማምለክና ለማገልገል ፈቃደኞች አይደለንም ፡፡ እነዚህ ወጣቶች
በንጉሡና ባነደደው እሳት ፊት ቆመው "ንጉሥ ሆይ አምላካችን
ከሚነደው እሳት ሊያድነን ይቻላል ባያድነን እንኳ አንተ ላቆምከው
ምስል አንሰግድም " ዳን 3÷17-18 በማለት ሲሞላልን ብቻ
ሳይሆን ሲጎድልብንም ፤ ስናገኝ ብቻ ሳይሆን ስናጣም ፤ ጤና
ስንሆን ብቻ ሳይሆን ጤናችን ሲናጋና ስንታመምም ፤ ሲሰጠን ብቻ
ሳይሆን ሲነሣንም ፤ እርሱን በእውነት በሙሉ ልብና በመንፈሳዊ
ደስታ ማምለክ ማመስገን እንደሚገባ አስተማሩን ፡፡ ኢዮባዊ
እምነት ይህ ነውና ፡፡
+++ እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ +++
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጦር ሳይሰብቁ ዝናር ሳይታጠቁ በጦር
አንደበት በፈረስ አንገት ሳይዘምቱ ንጉሥ ናቡከደነጾርንና መኳንንቱን
እግዚአብሔርን ይዘው ድል የነሱ እነዚህን ወጣቶች "እነርሱ
በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ" ዕብ 11÷33 ብሎ
ይመሠክርላቸዋል ፡፡ በዚህም "ዓለምን የሚያሸንፈው እምነታችን
ነው" 1ኛ ዮሐ 5÷4 የሚለውን ቃል አማናዊነት አረጋገጡልን ፡፡
ቤተክርስቲያንም የሐዋርያውን ቃል ቃል አድርጋ ይህን
እምነታቸውንና ተጋድሏቸውን ለዓለም ሁሉ ትመሠክራለች
ቤተክርስቲያን (ምእመናን) በፈተናና በመከራ ያለች ተጋዳይ
(millitant) እንዲሁም ድል አድራጊ መሆኗንም ከእነርሱ
ተጋድሎና ድል አድራጊነት ተምረናልና ፡፡ ዛሬ የመጠጥ ሱስ ߹
የወሬ ሱስ ߹ ሰውና ሰው የማጋጨት ሱስ ሰውነታችንን ድንኳን
ልቡናችንን ዙፋን አድርጎ መንግሥት የሆነብን እንዲሁም የዚህ
ዓለም (ፈጣሪውን የካደ ዓለም) ገዥ የተባለ ዲያብሎስ ከእምነት
ሊያስወጣን ስፍራችንን ሊያስለቅቀን በመጨረሻም እንደ
መንግሥት በራሳችን ላይ ነግሦ ወደ ወረደበት ጥልቅ ሊያወርደን
የሚታገለን ሰዎች ካለን በእምነት ሁሉን ማሸነፍ እንደሚቻል ሦስቱ
ወጣቶች የተግባር መምህራን ይሆኑናል ፡፡
+++ የእሳትን ኃይል አጠፉ +++
ሠለስቱ ደቂቅ ለጣዖት ባለመስገዳቸው ወደ እቶን እሳት
እንዲወረወሩ ተፈረደባቸው ተወረወሩም ፡፡ ያመኑት የታመኑበት
ፈጣሪያቸው መልአኩን ልኮ የእሳቱን ኃይል አጠፋላቸው ፡፡ የእነርሱ
ሰናፊላቸውን እንኳ ሳይለበልብ እነርሱን የጣሉ በእሳቱ ወላፈን
ነድደው ሞቱ ፡፡ ይህን የሚንበለበል እሳት እግዚአብሔር መልአኩ
ቅዱስ ገብርኤል ያጠፋው በእነዚህ ወጣቶች እምነት ምክንያት
እንደሆነ ሐዋርያው ሲመሰክር "በእምነት የእሳትን ኃይል አጠፉ"
ዕብ 11÷ 34 ብሏል :: ክፉዎች ባቀጣጠሉት እሳት ሲነድዱ
በወላፈኑም ሲለበለቡ ደጋጎቹ ግን በእምነት የዘረኝነትን የዕብሪትን
የዝሙትን የጥንቆላን የመተትንና ሌሎች እንደ እሳት የሚፈትኑ
ነገሮችን ሊያጠፉ እንደሚችሉ ሐዋርያት አስተምረውናል 1ጴጥ
4÷12 ፡፡
+++ እሳት የእሳትን ኃይል አጠፋ +++
ቅዱሳን መላእክት እሳታውያን ናቸው ዕብ 1÷7 ፡፡ እሳታውያን
በመሆናቸውም አንድ መልአክ ሲገለጥ ከክብሩ የተነሳ ምድር
እንኳን ይበራል "ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጎናጽፎ ከሰማይ
ሲወርድ አየሁ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት አምዶች
ነበሩ " ራእይ 10÷1 "ከዚያ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ
መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች"
ራእይ 18÷1 ተብሎ እንደተጻፈ ፡፡ ሊቀ መላእክት መጋቤ ሐዲስ
አብሣሬ ትስብዕት የሆነ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚህ እሳታውያን
ቅዱሳን መላእክት አንዱ ነውና ወደ እቶን እሳት ከተወረወሩት
ሦስቱ ወጣቶች ጋር አራተኛ ሆኖ በመግባት እሳቱ እየነደደ
የእሳቱን ኃይል አጠፋ እሳቱ እየነደደ የማቃጠል ኃይሉን አበረደው
፡፡ ይህ እንዴት ያለ ተአምር ነው ? እንግዲህ ምን እንላለን ?
በዚህ ዘመን እንደ እሳት እየነደደ ከሚፈትነን ነገር ሁሉ
የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ያድነን የጌታ መልአክ
በሚፈሩት ዙርያ ይሰፍራል ያድናቸውማልና መዝ 33÷7 ፡፡
የሠለስቱ ደቂቅ በረከታቸው እምነታቸው ይደርብን መልአኩም
ጥበቃ አይለየን !!

በመምህር ቢትወደድ ወርቁ

👉 @Embtee
👉 @Embtee
👉 @Embtee
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሦ ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን አምላክን የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው::

እርሷ የባህርያችን መመኪያ ናትና በእርሷ በእናቱ አማላጅነት ጌታችን ይጠብቀንና ያድነን ዘንድ መታሰቢያዋን እያደረግን ወደርሷ እንለምን ዘንድ ይገባናል::

ዛሬ ዕለት ሰንበት ነው የእመቤታችንም በዓሏ ነው በቃል ኪዳኗ የሚገኘውን በረከት ለማፈስ በዚህ ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን መገስገስ በረከቷን ማፈስ ነው። ለነፍሳችን ስንቅ የሚሆኑትን መልካም ነገር ለመስራት መፋጠንም መባረክ ነው። አዲስም በፀሎታችሁ አስቡት።

የሰንበት ዛቲ
ቤተ ክርስቲያን ስለ እመቤታችን አማላጅነት የምትሰብከው የምታስተምረው ፍጹም በሆነ ሐዋርያዊ ትውፊት ነው::

እመቤታችን ድንግል ማርያም ከሰው ወገን የሰው ችግር ቶሎ የሚገባት ቶሎ የሚታያትና የሚሰማት ርህርህት ናት::

ለምሳሌ በዮሐንስ ወንጌል ያለውን ምንባብ ብንመለከት ሠርግ ደግሰው ተጋባዥ ጠርተው ተጋባዥ ሕዝብ በመጋበዝ ላይ እንዳለ ድጎሳቸው በመቋረጡ ደጋሾቹ አፈሩ::

የሰዎቹ ችግር ቶሎ ገብቷት ለልጅዋ ነገረችው ከዚህም አስከትላ ልጄ ያዘዛችሁን ሁሉ አድርጉ ብላ አሳላፊ ለነበሩ ሰዎች ምክር ሰጠቻቸው ልጅዋም የእናቱን አማላጅነት ተቀብሎ አሳላፊዎችን ውኃ እንዲቀዱ አዘዛቸው።

አሳላፊዎቹም የእመቤታችን ምክር ሰምተው የጌታቸውን ትእዛዝ ስለፈጸሙ የሠርጉ ቤት ከፍርሃት ድኗል::

ይህ አስደናቂ ነገር ሊደረግ የቻለው በእመቤታችን አማላጅነት መሆኑን ቤተ ክርስቲያን ታምናለች::

ምእመናን ከዚህ ሕይወት ሲለዩ በዚህም በሚያልፈው የሕይወታቸው ጉዞ ለሚደርስባቸው ችግር ሁሉ እመቤታችን በአማላጅነት እንደማትለያቸው የታመነ ነው::

በዮሐንስ ወንጌል እንሆ ልጅሽ እንሆ እናትህ ብሎ አደራ በሚሰጥ ሰው ቋንቋ ጌታ የተናገረው ቃል እናቱ ድንግል ማርያም ከእርሱ በቀር ሌላ ልጅ እንዳልነበራት ከማሳየቱም በላይ ምሥጢራዊ አደራው እናቱን ለቤተ ክርስቲያን የተሰጣትን አደራ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ጠብቃ በእመቤታችን ስም እየተማፀነች ሐዋርያዊ ተልእኮዋን ታካሂዳለች::

እመቤታችንም በተሰጣት አደራ የቤተ ክርስቲያን ጉዞ የተሳካ እንዲሆን ልጅዋን በየጊዜው ትለምነዋለች ታስታውሰዋለች::

እርሷን ለሕይወታችን መድኃኒትን አድርጎ ለሰጠን እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን::
መልካም ዕለት ሰንበት ።


┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
👆👂👂👈
AUD-20181229-WA0072.amr
3 MB
*ብርሃንም በጨለማ ይበራል (ዮሐ ፩ ፥ ፭)*
ከመጋቤ ብሉይ መምህር ኤልያስ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
@mbtee
@mbtee
@mbtee
​​#እስከ_መቼ_ነው?

እውነት ቅዱስ ጊዮርጊስን የምንወደው ከሆነ ድምፃችንን እናሰማ እንቃወም፡፡ እስከ መቼ ነው በቅዱሱ አባታችን ስም የሚነገደው? መቼ ነው ታዲያ ስዕሉ የሚከበረው መቼ መቼ? እስከ መቼ ነው ጭፈራ ቤት እና የአህዛብ መቀለጃ ሚያደርጉት፡፡ የቅዱሱ አባታችን ምስል እና ስም ማስነሳት ያቃተን ለምንድነው? ወይስ አንወደውም? ለምን ዝም አልን? መቼስ አያገባኝም አንልም ስለ ዶክተር አብይ እንኳን ስንቱ ነው #ዋ ማንም እንዳይነካዉ እያለ Post የሚያደርገው፡፡ እስቲ ማናችን ነን ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠበቃ የቆምነዉ? እስቲ ማናችን ነን የተከራከርነው? መልሱን እናውቀዋለን፡፡ አሁንም ቢሆን ጊዜው አልረፈደም ሁላችንም FB ላይ post አናድርግ ለሚመለከተው አካል እናድርስ በእርግጥ እኛን ነው የሚመለከተው ነገር ግን መፍትሄ የሚሰጠን አካል ያስፈልገናል። ቅዱስ ስሙ እና ምስሉ ይነሳ ብለን ድምፃችንን እናሰማ መቼም በአባታችን በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ሲነገድ ማየት እሚያስደስተው የለም።
ይህን ያነበበ፣ያየ በሙሉ በተለያዩ ድህረ-ገፅ ላይ POST AND SHARE አድርጉ አደራችሁን።

👉 @embtee
@embtee
ከጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ያገኘነው ምንድን ነው?

ዳግም ልደት
በአዳም በደል ምክንያት አጥተነው የነበረው ልጅነታችንን ክርስቶስ በልደቱ ዳግመኛ እንደመለሰልን ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 1፥12 በማለት ገልጾታል።

ሰላም
በጌታችን ልደት ለዓለም ሁሉ የሚሆን ዘላለማዊ ሰላም ተገኝቷል። ይህም “ክብር እግዚአብሔር በሰማያት ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጐ ፈቃድ” እያሉ ቅዱሳን መላእክት በመዘመራቸው ተረጋግጧል። ሉቃ 2፥14። ስለዚህ በክርስቶስ ያገኘነው እውነተኛ ሰላም በእኛ ጸንቶ እንዲኖር ዘወትር በጾምና በጸሎት እየተጋን ስለሰላም የምንማፀን ሆነን ልንገኝ ይገባል። ሰላም የክርስትና መታወቂያ አርማ ነውና።

ብርሃን
“በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃንን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።” ኢሳ 9፥2። ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ያህል በዲያብሎስ ቁራኝነት ተይዞ የነበረው አዳም ወደሚደነቀው ብርሃን የተሸጋገረው በክርስቶስ ልደት ነው። እኛም በልደቱ ያገኘነውን የጽድቅ ብርሃን ጠብቀን ለመኖር (ብርሃነ ወንጌልን) ፈጽመን ከኃጢአት ርቀን በጽድቅ ሥራ ተወስነን ብርሃን ሆነን ልንኖር ይገባል።

ነጻነት
“በነጻነት እንኖር ዘንድ ክርስቶስ ነጻ አወጣን። ከእንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደገና በባርነት ቀንበር አትያዙ”። ገላ 5፥1። የሰው ልጅ እግዚአብሔርን በነጻነት እያመሰገነ ይኖር ዘንድ ተፈጥሯልና። ኃጢአት በመሥራት የዲያብሎስ ባርያ ሳንሆን በተሰጠን ነጻነት በመጠቀም የጽድቅ አገልጋዮች ሆነን ልንመላለስ ይገባል።

ይቅርታ
በአዳም በደል ምክንያት ከአብራኩ የተከፈሉ በሙሉ በደለኛ ሆነው የነበሩበትን ዘመን ለውጦ አዳምንና የልጅ ልጆቹን በደል ደምስሶ ፍቅርን ይመሰርት ዘንድ ጌታ ተወለደ። በምድርና በሰማይ ላሉት ፍቅርን መሠረተ። እርሱ የሰው ልጆችን በደል ሳይቆጥር ሁሉን ይቅር እንዳለ ክርስቲያንም የበደሉትን ሁሉ ይቅር ይል ዘንድ የፈጣሪው ትዕዛዝ ነውና ዘወትር ሊፈጽማት የምትገባ ከእግዚአብሔር ጸጋ የምታስደምር የልደቱን ብርሃን ለማየት እንደበቁ በዚህም ደስ እንደተሰኙ እንደ ቅዱሳን መላእክት ለእውነተኛ ምስጋና የምታደርስ የጽድቅ መሠረት የበረከት በር ናት። ማቴ 18፥21-23፣ ማቴ 5፥23-25። መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ የሚለው አምላካዊ ቃል ይቅርታ የክርስትና ሕይወት መመሪያ መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልንፈጽማት ይገባል።

ፍቅር
ፍቅር ሰሃቦ ለወልድ ኃያል እም መንበሩ ወአብጽሖ እስከለሞት /ፍቅር ኃያል ወልድን ከዙፋኑ አወረደው እስከ ሞትም አደረሰው።/ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረው እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጅን በደል ሳይቆጥር በዙፋኑ ሆኖ ምሬሃለሁ ማለት ሲችል ፍቅሩን ይገለጽ ዘንድ በከብቶች በረት ተወለደ። እውነተኛ ፍቅሩ ለክርስትናችን መሠረት ለጽድቃችን ፋና እንደሆነ መጻሕፍት ያረጋግጣሉ።

እንግዲህ በልደቱ ያገኘነውን ሰላም፣ ነጻነት፣ ይቅርታ፣ ብርሃንና ፍቅር ዋጋ የተከፈለበት ጸጋ የወረስንበት በመሆኑ ዘወትር በድንቅ ፍቅሩ የሚታደገን አምላካችን እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ እስከ መጨረሻው ድረስ ጸንተን እንድንኖር ክብራችንንና ጸጋችንን አስተውለን ከኃጢአት ርቀን በንሰሐ ታጥበን እራሳችንን ለክርስቶስ የተወደደ መስዋዕት አድርገን እንድናቀርብ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት አይለየን።

አሜን።
🌺🌺🌺
🌺🌺🌺
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
🌺🌺🌺
🌺🌺🌺


@embtee
@embtee
AUD-20190111-WA0026.amr
1.7 MB
*ስለ ልደት በዓል የተሰጠ ትምህርት*
በመጋቤ ሐዲስ ቀሲስ አበበ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰ ማልን
@embtee
@embtee
@embtee

👆🏻👂🏻👂🏻👈🏻
AUD-20190103-WA0008.m4a
14.3 MB
*የቅዱሳን ምልጃ በሰማይ*

💞ዲያቆን ዮርዳኖስ


(የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 6)
----------
9፤ *📖አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።*

10፤ *በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።*

11፤ *ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው።*

*ማኅበረ አትናትዮስ መልስ ለአህዛብ*👆🏼👆🏼👂🏽👂🏽

@embtee
@embtee
@embtee

👆🏻👂🏻👂🏻👈🏻
የትዳር ህይወት የተሳካ እንዲሆን የባል ሀላፊነት ምን መሆን አለበት?ፍቅርስ ምንድነው?ከየት ይጀምራል?…
Gere3025
ፍቅር ምንድነው
💞💞💞💞👏
በመምህር ሕዝቃኤል

🎬 የትዳር ህይወት የተሳካ እንዲሆን የባል ሀላፊነት ምን መሆን አለበት?ፍቅርስ ምንድነው?ከየት ይጀምራል? በምን የገለፃል?+++


መምህር ሕዝቅያስ ማሞ
@embtee
@embtee
@embtee👈
በዓለ ግዝረት

ክብር ምስጋና ይድረሰውና የጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ግዝረት በየዓመቱ ጥር ፮ ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ይከበራል፡፡ ጥር ፮ ቀን በሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር ተጽፎ የሚገኘውን የጌታችንን የግዝረት ታሪክም በሉቃስ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ ከተቀመጠው ትምህርት ጋር በማጣቀስ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፤

ልሳነ ዕፍረት ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ፡፡ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ፤›› በማለት እንደ ተናገረው /ሮሜ.፲፭፥፰/፣ የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጽሟል፡፡ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ በስምንተኛው ቀን እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ግዝረት ይፈጸምለት ዘንድ ሕፃኑ ጌታችንን ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡ ስሙም ገና በሥጋ ሳይፀነስ የእግዚአብሔር መልአክ ባወጣለት ስም ‹‹ኢየሱስ›› ተብሎ ተጠራ /ሉቃ.፪፥፳፩-፳፬/፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ሲገረዝ የሊቀ ካህን ልጅ ነው ብለው ሊገርዙት ወደ እርሱ መጡ፡፡ ጌታችን ግን ወደ ምድር የመጣው ለትሕትና ነው እንጂ ለልዕልና አይደለምና ወሰዱት አለ /ትርጓሜ ወንጌለ ሉቃስ/፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም አረጋዊው ዮሴፍን ‹‹እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የኾነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ፤›› አለችው፡፡ ጻድቁ ዮሴፍም እንዳዘዘችው የሚገርዝ ባለሙያ ይዞ መጣ፡፡ ባለሙያውም በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ ሕፃኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ባየው ጊዜ ‹‹እንድገርዘው በጥንቃቄ ያዙት›› አላቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስም ‹‹ባለሙያ ገራዥ ሆይ! ደሜ ሳይፈስ ልትገርዘኝ ትችላለህን? በዕለተ ዓርብ በመስቀል ስሰቀል ካልኾነ በስተቀር ደሜ አይፈስምና፡፡ ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኀና ደም ይፈሳል፡፡ ይኸውም ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆቹ መድኀኒት ይኾናል፤›› አለው፡፡

የክብር ባለቤት ጌታችን የተናገረውን ይህን ቃል ባለሙያው በሰማ ጊዜም አደነቀ፡፡ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሣና ከጌታችን እግር በታች ወድቆ ሰገደ፡፡ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጁ ላይ እንዳሉ እንደ ውኀ ቀለጡ፡፡ ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም ‹‹ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ፡፡ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ ይህ ልጅሽ ስለ እርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው፤›› አላት፡፡

ጌታችንም ባለሙያውን ‹‹እኔ ነኝ! ትገዝረኛለህን ወይስ ተውክ? ወይስ የአባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ ላድርግ?›› አለው፡፡ ባለሙያውም መልሶ ‹‹የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ጌታችንም አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ የሕዝቡ ዅሉ አባት እንደ ኾኑ ካስገነዘበው በኋላ ‹‹ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው›› በማለት የግዝረትን ሕግ አስረዳው፡፡ ባለሙያውም ይህን ምሥጢር ሲሰማ ‹‹እኔ ከአንተ ጋር እነጋገር ዘንድ አልችልም፡፡ በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና፤›› ብሎ የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት መሰከረ፡፡

በዚህ ጊዜ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ‹‹አባት ሆይ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው፤ ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ›› አለ፡፡ ያንጊዜም ያለ ሰው እጅ በጌታችን ላይ ግዝረት ተገለጠ (የግዝረት ምልክት ታየ)፡፡ ከዚህ ላይ ጌታችን ወደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር አብ ልመና ማድረሱ የለበሰው ሥጋ የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆብ መኾኑንና ጸሎት ማቅረብ የሚስማማው ሥጋን መልበሱን ለማጠየቅ ነው እንጂ በእርሱና በአብ መካከል ልዩነት ኖሮ አይደለም፡፡

ጌታችን ድንግልናዋን ሳያጠፋ ከድንግል ማኅፀን እንደ መውጣቱ ግዝረቱም አይመረመርም፡፡ በተዘጋ ቤት ወደ ሐዋርያት እንደ ገባና እንደ ወጣ ዅሉ እርሱ በሚያውቀው ረቂቅ ጥበብ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቈረጥ፣ ምንም ደም ሳይፈሰው መገረዙ ተገለጠ፡፡

ገራዡም የጌታችንን ቃል ከመስማቱ ባሻገር በሥጋው ላይ የተደረገውን ተአምር ባየ ጊዜ እጅግ አደነቀ፡፡ ከክብር ባለቤት ከጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ወድቆም ሦስት ጊዜ ሰገደና ‹‹በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ!›› በማለት በክርስቶስ አምላክነት አመነ፡፡ ከዚህ በኋላ ያየውንና የሰማውን ዅሉ እየመሰከረ ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡

በዚህች ዕለት ‹‹መሲሑን ሳታይ አትሞትም›› ተብሎ የተነገረለት፤ በንጉሥ በጥሊሞስ መራጭነት መጻሕፍተ ብሉያትን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ከመለሱ ሰባው ሊቃናት አንዱ የኾነውና ትንቢተ ኢሳይያስን ወደ ጽርዕ ቋንቋ የመለሰው ነቢዩ ስምዖን ጌታችንን በታቀፈው ጊዜ ከሽምግልናው ታድሷል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን በማየቱና በተደረገለት ድንቅ ተአምር በመደሰቱም ‹‹አቤቱ ባሪያህን ዛሬ አሰናብተው›› እያለ እግዚአብሔርን ተማጽኗል፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶም የክርስቶስን የዓለም ቤዛነትና ክርስቶስ በሥጋው በሚቀበለው መከራ እመቤታችን መራራ ኀዘን እንደሚደርስባት፤ እንደዚሁም ጌታችን ለሚያምኑበት ድኅነትን፣ ለሚክዱት ደግሞ ሞትን የሚያመጣ አምላክ እንደ ኾነ የሚያስገነዝብ ትንቢት ተናግሯል /ሉቃ.፪፥፳፭-፴፭/፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ነቢዪት ሐናም በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝታ የክርስቶስን ሥራ እያደነቀች ቸርነቱን ለሕዝቡ ዅሉ መስክራለች /ሉቃ.፪፥፴፮-፴፱/፡፡

የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ኅብረት በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ያለ ጥርጥር በፍጹም ልባችን ከምናምን ምእመናን ጋር ይኹን! /፪ኛቆሮ.፲፫፥፲፬/፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት_ክፍል_1_በአቤል_ተፈራMP3_128K.mp3
55.5 MB
ኦርቶዶክሳዊ የፆታ ~~~~ ትምህርት

ክፍል 1 በ ዲ/ን አቤል ተፈራ
👂👂👂👂👂👂

@embtee
@embtee
@embtee👈