✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.2K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
AUD-20181114-WA0055
<unknown>
*"ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል"ሉቃ 18:14*
*በእንተ ትህትና*
በዲያቆን ሸዋፈራው አለነ
ለመምህራችን እግዚአብሔር የህይወትን ቃል ያሰማልን አሜን...

┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
👆🏻👂🏻👂🏻👈🏻
​​የማይቀር…… ታላቅ የንግስ ክብረ በአል

ርእሰ አድባራት ወገዳማት ዳግሚት ጽዮን አዲስ አለም ማርያም

የታቦተ ጽዮን በአል በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ በተለይ በተለይ ይህን አመታዊ
ታላቅ የእመቤታችን ክብረ በአል
የቻለ አክሱም ጽዮን ያልቻለ ደግሞ ዳግሚት ጽዮን ተብላ ወደምትጠራዉ ወደ
አዲስ አለም ማርያም በመጓዝ በረከት ይዞ ይመለሳል፡፡
የዘንድሮ 2011ዓ.ም የህዳር ጽዮን በአል አርብ ቀን የሚዉል ሲሆን የጾመ ነቢያት
በገባ በሳምንቱ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡

ህዳር 21 ደረሰ /ዉል ዉል አለኝ ደጅሽ(2) በታላቅ ድምቀት ይከብራል
የዚህች ታቦት አመጣጥ ከአክሱም ነዉ፡፡ከእዉነተኛዪቱ የሙሴ ጽላት ጋር በአንድ
ወቅት በአንድነት ይቀደስባቸዉ ነበር፡፡ ይህች ታቦት በንጉስ አብርሀ እና አጽብሀ
ዘመነ መንግስት ወደ ሸዋ ምድር ክርስትናን ለማስፋፋት በተደረገዉ ጉዞ
ከአክሱም ምድር ተንቀሳቅሳለች፡፡ ከዛም በጥፋት ዘመን ከ300 አመታት በላይ
በዋሻ ተደብቃ ስትኖር እንደነበር በመጨረሻም በዳግማዊ ሚንልክ ዘመነ
መንግስት ወደ በአዲስ አለም ምድር ተወስዳ በክብር ትገኛለች፡፡
ይህች ታቦት ባለችበት ስፍራ ተአምራትን እያደረገች ይገኛል፡፡
• ከህንጻ ቤተክርስቲያኑ ግንባታ አንስቶ ንብረቷን ሊሰርቁ እሰከመጡት ሽፍቶች
ድረስ ድንቅ ታአምራቷን እየገለጸች ዘመናት መሀል አልፋለች
• በ2001 ዓ.ም እና በ2008 ዓ.ም በተራራዉ ስር 2 ጸበሎች በእመቤታችን
በራሷ ስም እና በቅዱስ ገብርኤል ስም ፈልቀዉ አይን በማብራት፣ሽባ
በመተርተር፣ የዉስጥ ደዌ ህመምተኞችን እባብ ፣አይጥ፣ አባ ጨጓሬ፣ እና
ጢንዚዛ ከሆዳቸዉ እንዲወጣላቸዉ እያደረገች ይገኛል
• አንድ ታላቅ እናትን(አማሆይ ወለተማርያም) ለአገልግሎት አስነስታ ብዙ
ምዕመናን ልጆቿን ከሰይጣን እስራት እየፈታች እንዲሁም ኩላሊት እና ካንሰር
ሳይቀር ከደዌያቸዉ እየተፈወሱ ይገኛል
• በታሪክ እየጠፋ ያለዉን የአንኮበር ወረብ ለትዉልድ በማቆየት ቦታዉን
በሊቃዉንት ምስጋና እየከበረ እንዲቆይ ሆኗል በተለይም የመስከረም 10፣የ
ዘመነ ጽጌ፣የህዳር 21፣የጥር 11 እና 21 ክብረ በአላት ልዩ የወረብ ጣእመ
ዝማሬዎች የማይረሱ ናቸዉ፡፡
• በተለያዩ ነገስታት እና አንዲሁም ሊቃዉንት የተበረከቱ ቅርሶችን ፣የታሪክ
መዛግብትን እና የዘመኑ የጥበብ አሻራ ያረፈባቸዉን የስዕል እና ኪነ ህንጻ
ዉጤቶች ለትዉልድ በማቆየት እንዲሁም በሙዚዬም ለጎብኚዎች ክፍት
በማድረግ ትዉልድን በመቅረጽ ሰፊ አገልግሎት እየተሰጠባት ይገኛል፡፡
• የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን እና ሊቃዉንተን የሚያፈሩ የአብነት ትምህርት
ቤቶችን ክፍት በማድረግ ተማሪዎች እንዲማሩ በማድረግ ሰፊ አገልግሎት
እየተሰጠባት ያለች ታላቅ ስፍራ እንዳያመልጦ።
💓
ርእሰ አድባራት ወገዳማት ዳግሚት ጽዮን አዲስ አለም ማርያም 🔻መነሻ ከአዲስ አበባ በአንቦ መስመር አቅጣጫ
42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ ደርሶ መልስ ትራንስፖርት 18 + 18
በጥቅሉ 36ብር የሚፈጅ ሲሆን የትራነስፖርት አማራጮች በሰፊዉ የሚገኙ
እንደሆነና ከዋናው አውቶብስ ተራ እና ከአስኮ መናህሪያ ማግኘት የምትችሉ
መሆኑን እያሳሰብኩ ከመኪና መንገድ ወደ ጸበሉ እና ወደ ቤተክርስቲያኒቱ
ለመድረስ የ15 ደቂቃ ብቻ የእግር ጉዞ የሚያስኬድ መሆኑንም ማስታወስ
እወዳለሁ፡፡

Share ማድረግ እንዳይረሳ በ ማርያም

ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለጎ 👉 @yitaya
AUD-20181116-WA0053
<unknown>
*ወደ ግብጽ ሂድ ማቴዎስ 2፥13*
በመጋቤ ብሉይ መምህር ኤልያስ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
👆🏻👂🏻👂🏻👈🏻
✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞:
#ስለ_ቅዱሳን_የሚናገሩ_መጻሕፍት_ያስፈልጉናል

ስለ ቅዱሳት መጻህፍት አለማወቅ ጥልቅ ወደ ሆነ የክህደትና
ስህተት ዐዘቅት ውስጥ ይጥላል፡፡ ጌታችን በወንጌል ‹መጻህፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።›
ማቴ 22፤29 እንዳለ፡፡ የአበው ቅዱሳንን ተጋድሎ የሚነግሩን
አዋልድ መጻህፍት አሥራው መጻህፍትን (መጽሐፍ ቅዱስን) ያብራራሉ ይተረጉማሉ፡፡
ለአንዳንዶች እንደሚመስላቸው ገድላት ወደ ገደል አይከቱም
ከገደል ያወጣሉ እንጂ፡፡ ገድላት የእግዚአብሔርን ቃል ለመፈጸም
እንደ ቃሉ ለመመላለስ ያግዙናል፡፡ ‹የእግዚአብሔርን ቃል
የተናገሩዋችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሩዋቸውንም ፍሬ
እየተመለከታችሁ በእምነታችሁ ምሰሉዋቸው› ዕብ 13፤7
‹እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ።›
ኤፌ 5፤1 ‹በነፍሳችሁ ዝላችሁ እነዳትደክሙ እነዲህ ባለ መቃወም የጸናውን
አስቡ።› ዕብ 12 ፤ 2-5 በማለት ቅዱሳንን እንድንከተል
የሚያዙንን የልዑል ቃላት የቅዱሳኑን ታሪክ ተጋድሎ ሕይወት
የሚተርክልንን ገድላቸውን ሳናነብ እንዴት መፈጸም አንችላለን?
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት ጌትነት ኃያልነት
እንደሚነግረን የቅዱሳንንም ተጋድሎ ታሪክ ተአምር በሁለት
መንገድ ይነግረናል ፡፡
1ኛ ከሌሎች ታሪኮች ጋር አሰናስሎ አያይዞ ምሳሌ በዘፍጥረት
የአብርሃም የይስኃቅ የሔኖክና የሌሎች ቅዱሳን ታሪክ በዘጸዐት
የሙሴ የኢያሱ የካሌብ በመሳፍንት የጌድዮን የዮፍታሔ
በሐዋርያት ሥራ የሐዋርያትን የሳሙኤልን፤ የኤልሳዕን፤የኤልያስን
፤የናቡቴን፤ የዳዊትን ፤ የሰለሞንን ታሪኮች በመጽሐፈ ነገሥት እና
መጽሐፈ ሳሙኤል መጻሕፍት እናገኛለን ፡፡
2ኛ የቅዱሳኑን ታሪክ ለብቻው ምሳሌ መጽሐፈ አስቴር የአስቴርን
ታሪክ ፤ መጽሐፈ ኢዮብ የኢዮብን ታሪክ ፤ መጽሐፈ ሩት የሩትን
ታሪከ ፤ ፤ መጽሐፈ ጦቢት የጦቢትን ታሪክ ይነግረናል
መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱሳንን ታሪክ እንድናነብ አዋልድ መጻሕፍትን
አንድንመለከት ይጋብዘናል ለዚህ አስረጂ የሚሆኑን ጥቂት ኃይለ
ቃላትትን ለማየት ‹የቀረውም የሰለሞንን ነገር ያደረገውም ሁሉ
ጥበቡም እነሆ በሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎዋል።› 1 ነገ 11፤41 ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚከተሉትን ቁምነገሮች
መረዳት እነችላለን
👉የነገረ ቅዱሳን ትምህርት መነሻው መጽሐፍ ቅዱስ ነው ፡፡
ነገረ ማርያም ፤ ነገረ ቅዱሳን እንደምንል ነገረ ሰለሞን አለን።

👉የእግዚአብሔር ቅዱሳን ተአምራት ወ መንክራትን መፈጸም
ይችላሉ ሰለሞን ያደረገውም እንዲል ይኀውም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ‹በእኔ የሚያምን እኔ
የማደርገውን እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።› ዮሐ 14 ፤ 12 ያረጋግጥልናል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ ‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው ፡፡› መዝ 67፤ 35 እያለ ይዘምራል፡፡ በተጨማሪም ቅዱሳኑ ፀሐይን እንዳቆሙ ኢያሱ 10 ፤12 በሥጋ ከሞቱ በኃላ በአጥንታቸው ሙት እንዳስነሱ 2 ነገ 13፤20 በጨርቃቸው በበትራቸው ባሕር
እንደከፈሉ 14 ፤16 2ነገ 2 ፤8 ክፉዎች መናፍስትን አንዳወጡ
የሐዋ 19፤11 በሰውነታቸው ጥላ (Shadow) ድውያንን እንደፈወሱ አጋንንትን አንዳወጡ ተአምራትን እንዳደረጉ የሐዋ 5፤15 መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ ታድያ ገድላት ይህን ሲመሰክሩ ለምን ይተቻሉ?

👉ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሀፍ ቅዱስ ከተተረክው ታሪኩ
በተጨማሪ የራሱን ታሪክ ጥበብ ሕይወት የሚተርክ መጽሐፍ
አለው ፡፡‹በሰለሞን ታሪክ መጽሐፍ › አንዲል ገድለ ሰለሞን ማለት
ነው፡፡ ታዲያ ሰለሞን ስለራሱ ታሪክና ስለሰራቸው ሥራዎች
የሚተርክ መጽሐፍ ካለው ያንንም እንድናነብ መጽሐፍ ቅዱስ
ከጋበዘን የሌሎችን ቅዱሳን ታሪክ ለማንበብና ለመቀበል ሰዎች
ለምን የቸገራሉ?
በሌላም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ‹የንጉሱም የዳዊት የፊተኛውና
የኃለኛው ነገር እነሆ በባለ ራዕዩ በሳሙኤል ታሪክ በነቢዩም
በናታን ታሪክ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፏል።› 1ዜና 29፤29
ተብሎ ተጽፋል፡፡ በዚህ ክፍል ሶስት የቅዱሳን የገድል መጻሕፍት ተጠቅሰውልናል
1ኛ የሳሙኤል
2ኛ የናታን
3ኛ የጋድ
መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ቅዱሳን የታሪክ መጻሕፍት ይመራናል::
የቅዱሳን በረከት ይደርብን!

┏━━° •🌺 ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
👆🌺👆 °
ወንጌል ዘሰንበት
Voice changer with effects (http://thevoicechanger.com)
*ወንጌል ዘሰንበት*
*የዮሐንስ ወንጌል 10 ፤ 25 - 42*
*ኢየሱስም መለሰላቸው እንዲህ ሲል ነገርኳችሁ አታምኑምም እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል።*
በዲያቆን ሳሙኤል አቡኃይ
ለወንድማችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
🌺
@Embtee
@Embtee
@Emmtee
👆👂👈
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ሰላም እግዚአብሔር ይብዛላችሁ ዉድ ምእመናን እንደምን ቆያቹ?

💗 በእመብርሀን ልጆች ማህበር በየሳምቱ እለተ ቅዳሜ እና እሁድ የሚቀርብ መንፈሳዊ ኘሮግራም {ኪነ ጥበብ} ዝግጅት ስላለን በዚ ሰአት እኔም አለኝ ብሳተፍ ለምትሉ ብታናግሩን



📜 ግጥም

📀 መዝሙር

📚 ካነበብኩ

📄 ወጎች

👁‍🗨 እንቆቅልሽ

🎎 ድራማ

🎁 ጥያቄና መልስ

ከነዚ ውስጥ መርጣቹ በሳምንት ሁለቴ ለሚቀርበው አለን ለመስራት እንፈልጋለን!! ክህሎቱ ያላቹ እኔም የበኩሌን አስተዋፀዎ አደርጋለው ለሚል አድሚናትን ያናግሩ የእመብርሀን ምልጃዋና በረከቷ አይለየን አሜን

👉 @yitaya 👈

┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
@embrhan_lijoch
@embrhan_lijoch 👈Join
@embrhan_lijoch
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄
​​የማይቀር…… ታላቅ የንግስ ክብረ በአል

ርእሰ አድባራት ወገዳማት ዳግሚት ጽዮን አዲስ አለም ማርያም

የታቦተ ጽዮን በአል በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ በተለይ በተለይ ይህን አመታዊ
ታላቅ የእመቤታችን ክብረ በአል
የቻለ አክሱም ጽዮን ያልቻለ ደግሞ ዳግሚት ጽዮን ተብላ ወደምትጠራዉ ወደ
አዲስ አለም ማርያም በመጓዝ በረከት ይዞ ይመለሳል፡፡
የዘንድሮ 2011ዓ.ም የህዳር ጽዮን በአል አርብ ቀን የሚዉል ሲሆን የጾመ ነቢያት
በገባ በሳምንቱ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡

ህዳር 21 ደረሰ /ዉል ዉል አለኝ ደጅሽ(2) በታላቅ ድምቀት ይከብራል
የዚህች ታቦት አመጣጥ ከአክሱም ነዉ፡፡ከእዉነተኛዪቱ የሙሴ ጽላት ጋር በአንድ
ወቅት በአንድነት ይቀደስባቸዉ ነበር፡፡ ይህች ታቦት በንጉስ አብርሀ እና አጽብሀ
ዘመነ መንግስት ወደ ሸዋ ምድር ክርስትናን ለማስፋፋት በተደረገዉ ጉዞ
ከአክሱም ምድር ተንቀሳቅሳለች፡፡ ከዛም በጥፋት ዘመን ከ300 አመታት በላይ
በዋሻ ተደብቃ ስትኖር እንደነበር በመጨረሻም በዳግማዊ ሚንልክ ዘመነ
መንግስት ወደ በአዲስ አለም ምድር ተወስዳ በክብር ትገኛለች፡፡
ይህች ታቦት ባለችበት ስፍራ ተአምራትን እያደረገች ይገኛል፡፡
• ከህንጻ ቤተክርስቲያኑ ግንባታ አንስቶ ንብረቷን ሊሰርቁ እሰከመጡት ሽፍቶች
ድረስ ድንቅ ታአምራቷን እየገለጸች ዘመናት መሀል አልፋለች
• በ2001 ዓ.ም እና በ2008 ዓ.ም በተራራዉ ስር 2 ጸበሎች በእመቤታችን
በራሷ ስም እና በቅዱስ ገብርኤል ስም ፈልቀዉ አይን በማብራት፣ሽባ
በመተርተር፣ የዉስጥ ደዌ ህመምተኞችን እባብ ፣አይጥ፣ አባ ጨጓሬ፣ እና
ጢንዚዛ ከሆዳቸዉ እንዲወጣላቸዉ እያደረገች ይገኛል
• አንድ ታላቅ እናትን(አማሆይ ወለተማርያም) ለአገልግሎት አስነስታ ብዙ
ምዕመናን ልጆቿን ከሰይጣን እስራት እየፈታች እንዲሁም ኩላሊት እና ካንሰር
ሳይቀር ከደዌያቸዉ እየተፈወሱ ይገኛል
• በታሪክ እየጠፋ ያለዉን የአንኮበር ወረብ ለትዉልድ በማቆየት ቦታዉን
በሊቃዉንት ምስጋና እየከበረ እንዲቆይ ሆኗል በተለይም የመስከረም 10፣የ
ዘመነ ጽጌ፣የህዳር 21፣የጥር 11 እና 21 ክብረ በአላት ልዩ የወረብ ጣእመ
ዝማሬዎች የማይረሱ ናቸዉ፡፡
• በተለያዩ ነገስታት እና አንዲሁም ሊቃዉንት የተበረከቱ ቅርሶችን ፣የታሪክ
መዛግብትን እና የዘመኑ የጥበብ አሻራ ያረፈባቸዉን የስዕል እና ኪነ ህንጻ
ዉጤቶች ለትዉልድ በማቆየት እንዲሁም በሙዚዬም ለጎብኚዎች ክፍት
በማድረግ ትዉልድን በመቅረጽ ሰፊ አገልግሎት እየተሰጠባት ይገኛል፡፡
• የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን እና ሊቃዉንተን የሚያፈሩ የአብነት ትምህርት
ቤቶችን ክፍት በማድረግ ተማሪዎች እንዲማሩ በማድረግ ሰፊ አገልግሎት
እየተሰጠባት ያለች ታላቅ ስፍራ እንዳያመልጦ።
💓
ርእሰ አድባራት ወገዳማት ዳግሚት ጽዮን አዲስ አለም ማርያም 🔻መነሻ ከአዲስ አበባ በአንቦ መስመር አቅጣጫ
42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ ደርሶ መልስ ትራንስፖርት 18 + 18
በጥቅሉ 36ብር የሚፈጅ ሲሆን የትራነስፖርት አማራጮች በሰፊዉ የሚገኙ
እንደሆነና ከዋናው አውቶብስ ተራ እና ከአስኮ መናህሪያ ማግኘት የምትችሉ
መሆኑን እያሳሰብኩ ከመኪና መንገድ ወደ ጸበሉ እና ወደ ቤተክርስቲያኒቱ
ለመድረስ የ15 ደቂቃ ብቻ የእግር ጉዞ የሚያስኬድ መሆኑንም ማስታወስ
እወዳለሁ፡፡

Share ማድረግ እንዳይረሳ በ ማርያም

ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለጎ 👉 @yitaya
​​አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን

ኅዳር 12-ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ
ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ
ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ዕለት ነው፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፡- ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ'
ካ-ከመ' ኤል-አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ ‹‹መኑ ከመ አምላክ-እንደ
እግዚአብሔር ያለ ማን ነው›› ማለት ነው፡፡ አንድም ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል
አድራጊ የቸርነትና የርህራሄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡
ገናናው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ዲያብሎስን ወደ ጥልቁ ጥሎት በእርሱ ምትክ
ከሁሉ የበላይ ሆኖ በተሾመበት በዚህ ዕለት በበዓሉ መታሰቢያ በኅዳር 12 ቀን
የክብር ባለቤት በሆነ በእግዚአብሔር ፈቃድ ክንፎቹን ወደ ሲኦል ያወርዳል፣
ኃጥአንንም ወደ አዲሲቱ ምድር ያወጣቸዋል ይኸውም የመላእክት አለቃ
የሚካኤል ሠራዊት ይሆናሉ፡፡ ይቅርታ የተደረገላቸውና ምሕረት አግኝተው በአንድ
ጊዜ በክንፉ ያወጣቸው ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በየዓመቱ
በኅዳር 12 ቀን እንዲህ እያደረገ እልፍ ነፍሳትን ያወጣል፡፡ የቤተ ክርስቲያን
ወገኖች የሆኑትን ሁሉ እንደሥራቸው ወደ ምሕረት ቤት ወደ ሰማያዊት
ኢየሩሳሌም ይወስዳቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ አብ መጋረጃ ውስጥ ይገባል፣
በዚህች ዕለት ምድራዊትና ሰማያዊት ስለሆነች ምሕረቱም ከመንበሩ በታች
ይሰግዳል፡፡ ስለውኃ ምንጮች፣ ስለ ወይን ቦታዎች፣ ስለ ምድር ፍሬዎች
በምድርም ላይ ስለሚኖሩ ስለ ሰው ልጆች ነፍስ ሁሉ፣ ስለ እንስሳትም፣ ስለ
ሰማይ ወፎችም፣ ስለ ባሕር ዓሣዎችም፣ በምድር ላይና በባሕር ውስጥ
ስለሚንቀሳቀሱ ሁሉ የምሕረት ባለቤት ከሆነ ከአብ ዙፋን በታች ሁልጊዜ
በማመስገን ይሰግዳል፤ ልመናውንም እስኪሰማውና የምሕረትንም ቃል
እስኪያስተላልፍለት ድረስ ከእግረ መንበሩ ሥር አይነሣም፡፡
ለዚህ ዓለም ምሕረትን የሚለምኑ ቅዱሳን መላእክትም በየዓመቱ ኅዳር 12
ቀንበእግዚአብሔር የዙፋኑ ዓውደ ምሕረት ዙሪያ ተሰብስበው ስለ ሰውና ስለ
እንስሳትም ሁሉ ምሕረትን የሚለምን ቅዱስ ሚካኤል ከአብ መጋረጃ ውስጥ
በወጣ ጊዜ ቸርና መሐሪ አብ ለቅዱስ ሚካኤል የሰጠው ልብሱን እነዚያ
መላእክት ይመለከታሉ፣ ይቅርታን የማግኘት ምልክታቸው ነውና፡፡ ስለዚህ እነዚህ
ቅዱሳን መላእክት በምድር ላይ ምሕረት እንደተደረገ ሰውንም እንስሳትንም
ይቅር እንዳለ በዚህ ዓለምም የሚሆነውን ሁሉ አይተው ቅዱስ ሚካኤል
በለበሰው ልብስ አምሳል ያውቁታል፡፡
ስንክሳሩ እንደሚለው ይህ እጅግ የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል
‹‹ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋራ በመሆን ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ
የሚያጽናናቸውና የዘወትር ጠባቂአቸው ሆኖ የሚራዳቸው እርሱ ነው፡፡››
የብዙዎቹንም ቅዱሳን ገድል ስንመለከት የዘወትር ጠባቂያቸው ቅዱስ ሚካኤል
ነው፡፡
ቅዱሳን በሕይወት ሳሉ ይህ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ረዳትና የዘወትር
ጠባቂ፣ እንደጓደኛም አማካሪ ሆኖ የተበቃቸውን ስንቱን ቅዱሳን ዘርዝረን
እንቸላለን፡፡ እርሱ ያልረዳው ቅዱስ የለም፡፡ መከራውን ያላስታገሰው ሰማዕት
የለም፡፡ ለቅዱሳኑ እንዲህ እንደጓደኛቸው ሆኖ ሲጠብቃቸው ይኖራል፡፡ ነገር ግን
ቅዱስ ሚካኤል ለኃጥአንና አምላካቸውን ለካዱ ሰዎች ደግሞ በቁጣ
ለመቅሰፍት ይመጣባቸዋል፡፡ ሰናክሬም በእግዚብሔር ላይ ክፉ በመናገሩ
በአንዲት ሌሊት ብቻ 185,000 (መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ሠራዊቱን ቅዱስ
ሚካኤል በብርሃን ሰይፉ ፍጅቷቸው አድሯል፡፡ 2ኛ ነገ 19፡35፣ ኢሳ 37፡36፡፡
እግዚአብሔርን ለሚወዱና እርሱንም ለሚያከብሩት መታሰቢያውንም
ለሚያደርጉለት ግን ከሚፈልጉት ነገር ከቶ አያሳጣቸውም፣ ዘወትርም
ይጠብቃቸዋል፣ በኋላም በአማላጅነቱም ከሲኦል እሳት ያድናለቸዋል፡፡ እነሆ ይህ
ገናና ክቡር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡-
‹‹የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡
የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የዚህን የከበረ
መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ
በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ ለቅዱስ ሚካኤልም ለበዓሉ
መታሰቢያ የሚያደርጉትን እስኪያጡ ድረስ ቸገራቸው፡፡ ዱራታዎስም ሸጦ
ለመልአኩ በዓል መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱንና የሚስቱን ልብስ ይዞ
ወጥቶ ሄደ፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ
ተገለጠለትና ወደ ባለጸጎች ሄዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ
እንዲወስድ፣ ሁለተኛም ወደ ባለ ስንዴ ዘንድ ሄዶ በእርሱ ዋስትና ስንዴን
እንዲወስድ ዳግመኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ዘንድ ሄዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ
ነገር ግን ወደቤቱ ሳይርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አዘዘው፡፡ ዱራታዎስም
እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ወደቤቱም በተመለሰ ጊዜ ቤቱ ሁሉ በበረከት ተመልቶ
አገኘው፡፡ እርሱም እጅግ ተደስቶ የዚህን የክበር መልአክ የመታሰቢያውን በዓል
አደረገ፡፡ ጦም አዳሪዎችንና ድኆችን ጠርቶ አጠገባቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው፡፡
ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንድሰነጥቅ አዘው፡፡ በሰነጠቀውም ጊዜ 300
የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ውስጥ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ዱራታዎስንና
ሚስቱን ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ፣
ለባለ ዓሣውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ፡፡ የቀረውም ለፍላጎታችሁ
ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን፣ መሥዋዕታችሁንና
ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፣ በኋለኛውም መንግሥተ
ሰማያትን አጀጋጀላችሁ›› አላቸው፡፡
እነርሱም ይህን ነገር ሲሰሙ ደነገጡ፡፡ የከበረ ገናናው መልአክም ‹‹ከመከራችሁ
ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ፣ መሥዋዕታችሁንና
ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ፡፡ አሁንም በዚህ ዓለም
ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም›› አላቸው፡፡ ይህንንም ከነገራቸው በኋላ
ወደ ሰማያት ወጣ፡፡ እነርሱም በፍርሃትና በክብር ሰገዱለት፡፡››
የመላእክት አለቃ ቅዱስ የሚካኤል ጥበቃው አይለየን! ከበዓሉ በረከት ይክፈለን!
Forwarded from Deleted Account
መምህር ምህረተአብ ስብከት.m4a
1.4 MB
ለመምህራችን በዕውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን በተማርነው ትምህርት ሰላሳ ስልሳ መቶ ያማረ ፍሬ እንድናፈራ አምላካችን ይርዳን
በዕውነት ለመምህር ምህረተአብ ቃለህይወት ያሰማልን ፡፡

┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
👆🏻👂🏻👂🏻👈🏻
AUD-20181127-WA0090
<unknown>
*አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል በተቀደሰው ተራራስ ማን ይኖራል*
*መዝሙር ፲፬፥፩*
በዲያቆን ቤርዜሊ ተስፋዬ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
👆🏻👂🏻👂🏻👈🏻
✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞ pinned «​​አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን ኅዳር 12-ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፡- ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል-አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ ‹‹መኑ ከመ አምላክ…»
Audio
*አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል በተቀደሰው ተራራስ ማን ይኖራል*
*መዝሙር ፲፬፥፩*
በዲያቆን ቤርዜሊ ተስፋዬ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
👆🏻👂🏻👂🏻👈🏻
Forwarded from Deleted Account
AUD-20181214-WA0004.amr
1.8 MB
*እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው ከወዴትስ መጡ*
*ራእይ ዮሐንስ 7፥13*
በጅጅጋ የተሰጠ ትምህርት
በመጋቤ አእላፍ ቀሲስ ገብረ ዮሐንስ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛

👆👂👂👈
Audio
┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
👆🏻👂🏻👂🏻👈🏻
AUD-20181222-WA0028
<unknown>
*መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል*
*1ኛ ጢሞቲዎስ ፮፥፲፪*
ከመጋቤ ሐዲስ ቀሲስ አበበ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
*ማኅበረ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ*
┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
👆👂👂👈
AUD-20181224-WA0032
<unknown>
*ጌታ ሆይ አድነኝ*
*ማቴዎስ ፲፬፥፴*
በመጋቤ ብሉይ መምህር መክብብ
ለመምህራችን የሕይወትን ቃል ያሰማልን

┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
👆👂👂👈