✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.21K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
በቤተክርስቲያናችን ስርአት መሰረት 7 ጊዜ እንፀልያለን የእነሱም ትርጉም
እንደሚከተለው ቀርቦአል ።ካነበቡ በኃላ ሼር ማድረግዎን እንዳይረሱ።
ጠዋት 12 አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔርን አምላክን በፀሎት
የሚያመሰግንበት ምክንያት (ሚስጥር)
1 እግዚአብሔር አምላክ ሌሊቱንና ጨለማውን አሳልፎ ብርሀን እንድናይ
ስላበቃን በዚህ ሰአት እግዚአብሔር አምላካችንን እንድናመሰግን ታዝዝዋል
አንድም በዚህ ሰአት ጌታችን ለክስ ከጲላጦ ፊት ቆሞ የተወቀሰበት ሰአት ስለሆነ
አንድም በዚ ሰአት አባታችን አዳም ያልተፈቀደለትን እፅ በልቶ ከገነት የተባረረበት
ሰአት ስለሆነ ነው አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እያሰበ ወደ አምላኩ እንዲፀልይ
ታዝዋል
ሰልቱ ሰአት ከጠዋቱ 3 ሰአት አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ የታዘዘበት
ምክንያት (ሚስጥር)
1 በዚህ ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብስራተ ገብርኤልን
የሰማችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም በዚህ ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ጌታችንን የፀነሰችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም ጌታችን መድሀኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የተገረፈበት ሰአት ስለሆነ ዮሐ 19 ፥1
ሐዋ ስራ 2፥15 እያንዳንዱ ክርስቲያን ይሔንን የመሳሰሉ ሁሉ እያሰበ
እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግን ታዝዋል
6:00 አንድ ክርስቱያን እኩለ ቀን (ከ ቀኑ 6ሰአት) ሲሆን እንዲፀልይ
የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር )
1 ጌታችን በቀራኔዎ አደባባይ በመስቀል ተሰቅሎበታልና አንድም ልብሱን
ተገፎበታል አንድም ሳዶር አላዶር ዳናት ሮዳስ በተባሉ ችንካሮች ተቸንክሮበታል
አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እያሰበ በዚህ ሰአት እንዲፀልይ ታዞበታል
ተስአተ ከ ቀኑ 9:00 ሰአት ሲሆን አንድ ክርስቲያን የሚፀልይበት
ምክንያት (ሚስጥር)
1 አይሁዶች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየ�ሱስ ክርስቶስን መራራ ሐሞት
አጠጥተውበታል አንድም ቅድስት ነፍሱን ከ ክቡር ስጋው የለየበት ሰአት ነውና
አንድም በመስቀል እንዳለ 7ቱን አፅርሀ መስቀል የተናገረበት ማር 15፥34 ማቴ
27፥50 አንድ በዚህ ሰአት ይህንን እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል
የሰርክ ሰአት ከቀኑ 11፡00 ሰአት አንድ ክር�ቲያን እንዲፀልይበት
የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር)
1 ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ከርሰ መቃብር የወረደበት ሰአት
ስለሆነ አንድም ቀኑን በሰላም አሳልፎ ወደ ምሽት በሰላም ያደረሰን አምላክ
ምስጋ ስለሚገባው ነው ይህንን የመሳሰሉ ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያን እንዲያስቡ
ታዘዋል
6 ከምሽቱ 3 ሰአት በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን እንዲያመሰግን
የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)
1 በዚህ ሰአት እራሱ ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስርአተ ፀሎት
አሳይቶበታል አንድም በዚህ ሰአት ጌታችንን አይሁድ በይሁዳ ጠቁዋሚነት
ተረበርበው የያዙበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን
ከመተኛቱ በፊት በሰላም ያዋለንንና ያስመሸንን አምላክ አመስግኖ መተኛት
አለበት ይህን ሁሉ እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል
መንፈቀ ሌሊት ከሌሊቱ 6ሰአት በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን
እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግንበት የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)
1 በዚህ ሰአት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶበታልና ነው
አንድም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ድል
አድርጎበታልና(ተነስቶበታል) በመዝሙረ ዳዊት አመሰግንህ ዘንድ በመንፈቀ
ሌሊት እነሳለው ባለው መሰረት ጳውሎስ ሲላስ በእስር ቤት ሆነው ወደ
እግዚአብሔር የፀለዩበት ስለሆነ ነው አንድም የሰው ልጅ የሚመጣበት ጊዜ ማታ
ይሁን መንፈቀ ሌሊት ይሁን ዶሮ ሲጮህም ይሁን ሲነጋም ቢሆን አይታወቅምና
ባለው አምላካዊ ቀል መሰረት በመንፈቀ ሌሊት አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ
ታዝዋል
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክብር

#join
@embtee
@embtee

Inbox ይላኩልን @yitayal123bot
*መቼ ነው* እውነተኛ ክርስቲያኖች የምንሆነው?
*መቼ ነው* እግዚአብሔር በፈጠራቸው ነግሮች የምንማረከው?
*መቼ ነው* እግዚአብሔር ለምን እንደፈጠርን የምንረዳው?
*መቼ ነው* እግዚአብሔር እንደሚፈልገው መኖር የምንጀምረው?
*መቼ ነው* ስለ ሀይማኖታችን በሙሉ ልብ እምንናገረው?
*መቼ ነው* እማይጠቅም ንግግር ከመናገር የምንቆጠበው?
*መቼ ነው* ለመልካም ስራ ምሳሌ የምንሆነው?
*መቼ ነው* በስግደታችን በፆማችን የምንጠቀመው?
*መቼ ነው* ጾለታችን ተሰሚነት የሚያገኝው?
*
*መቼ ነው* ውሎና አዳራችን በቅዱስ ቃሉ ሚሆነው?
*መቼ ነው* ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ የምንመካው?
@embtee
*መቼ ነው* ያአለምን ትልቅነት ከልባችን የምናወጣው?
*መቼ ነው* ቤታችን ውስጥ ያለው የተበላሸ ሂዎት የሚስተካከለው?
*መቼ ነው* ቤታችን ውስጥ መጸሐፍ ቅዱስ ውዳሴ ማሪያም የሚወራው?
@embtee
*መቼ ነው* ውሽት እምናቆመው?
*መቼ ነው* የእግዚያአብሔርን ውሳኔ መቃውም እምናቆመው?
*መቼ ነው* እኔ እኔ ማለት ትተን ውንደሜ እህቴ ማለት እምንጀምረው?
*መቼ ነው* ለሰዎች ከክርስቶስ ውጪ ጌታ እንደሌለ እምንናገረው?
*መቼ ነው* ጥሩና ለጋሽ መልካም ሰው የምንሆነው?
*መቼ ነው። ክርስቲያንነታችንን የምናስተዋውቀው?
*መቼ ነው* ለድሃ እምናዝነው?.
*መቼ ነው* ትዳራችን ስላም ሚያገኝው?
*መቼ ነው* የጋብቻን ጥቅም ተገንዝበት ለትዳር የምንቻኮለው?
*መቼ ነው* ከሀሜት; ስውን ከመበድል; ከማስቀየምና ከማማት እምንላቀቀው?
*መቼ ነው* ወላጆቻችንን እምናስደስተውና እምንታዝዝው?
*መቼ ነው* ያልተጣራ ውሬ ካማውራት እምንቆጠበው?
*መቼ ነው* እምንዋደደው?
*መቼ ነው* እግዚአብሔር በሰጠን ነገር ደስተኞች የምንሆነው?
*መቼ ነው* ስግደት ፆም ፆለት የምንላመደው?
*መቼ ነው* የበድለንን ይቅር የመንለው?
*መቼ ነው* ከራስ ወዳድነት እምንላቀቀው?
*መቼ ነው* ከሞት ቡኃላ ላለው ሂወት ስንቅ እምናዘጋጀው?
*መቼ ነው* አባቶችን እምናከብረው?
*መቼ ነው* ለእውቅት ጊዜ የምንሰጠው?
*መቼ ነው* ባወቅነው የምንሰራው?
*መቼ ነው* የ ምንሞትበትን ቀንም ይሁን ስፍራ እንደማናውቅ ተገንዝበን
በተጠንቀቅ የምንቆመው?
*መቼ እረ መቼ ነው* ክርስትናን የምንኖረው?
*መቼ ነው* ለእነዚህ ተግባራዊ መልስ የምንመልሰው
እግዚአብሔር ይርዳን
አሜን።
ውስብሃት ለእግዚአብሔር
ወወላዲትድንግል
ወለመስቀሉ ክብር

#join @embtee

👇👇
Comment @yitayal123bot