#ጾመ ፅጌ ማለት
[ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6]
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" (ት.ሆሴዕ 11፥1 )
🌿❤️ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕግና ስርአትመሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችንን እና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40ው ቀን የእመቤታችንና የጌታችን ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታችን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋናይመሰገናሉ ፡፡
🌿❤️ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አምሥቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስበ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል፡፡ በዚሁ ዘመን ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት ደርሷል፡፡ ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሄድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ሲሆን ይህድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ ወቅት ተለይቶለት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ የሚውለው ግን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና በልጇ የስደት ዘመን ማለትም ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው ዘመን ውስጥ ነው፡፡ በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊቱን በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋርወደ ምድረ ግብፅመሰደድና መንከራተት እየታሰበ በሊቃውንቱ የሚደርስ የምሥጋና ጸሎትም ነው ፡፡ ይህ ድርሰት በግጥም መልክ የተደረሰ ሲሆንበአብዛኛው አምስት ስንኞች ሲኖሩት ብዛቱም 158 ያክል ነው፡፡ እመቤታችን ጣዕሟንና ፍቅሯን እንዲሁም ምስጋናዋን ሲናፍቁ የነበሩትን ቅዱስኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን እንደገለጸችላቸው ሁሉ ለፍቅሯ ሲሳሳ ለነበረውለአባ ጽጌ ድንግል ደግሞ ይህንን የማኅሌተ ጽጌን ድርሰት እንዲደርስ ምስጢርን ገልጻለታልች ።
🌿❤️ በቅድስት ሐገር ሐገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ ወራት ወርኅ ጽጌ (ዘመነ ጽጌ) ናቸው፡፡ ይህም ወቅት ተራሮችበአበባ የሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህም ዘመን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‘’ ስለ ልብስ ስለምንትጨነቃላችሁ ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡ አይደክሙም፣አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ሰሎሞንስ እንኳበክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡እግዚአብሔር፣ ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፣ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፣ እናንተንማይልቁን እንዴት፡፡ እንግዲህ ምን እንበላለን፣ ምንስእንጠጣለን፣ ምንስ እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ‘’ (ማቴ 5÷28-33) በማለት የተናገረውን ቃል በማሰብ መጨነቅ የሚገባን መንግሥተ ሰማያት ለመግባት እንጂ በዚህ ዓለም ስላለው ነገርእንዳልሆነ ተራሮችን በአበባ ያለበሰ አምላክ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረንን እኛን ለኑሮየሚያስፈልገንን ምግብና ልብስ እንደማይነሳን እያሰብን የምንዘክርበት ወቅት ነው፡፡
🌿❤️ የሊቁ ድርሰትም ፍሬ ከአበባ÷ አበባም ከፍሬ እንደሚገኘ ሁሉ ማኅሌተ ጽጌም እመቤታችንቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬእየመሰለ የሚያስረዳ ድርሰት ነው፡፡ እርሷን በአበባሲ መስል ልጇን በፍሬ እርሷን በፍሬ ሲመስል ልጇን ደግሞ በአበባ እየመሰለ ይናገራል፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ “ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፣ ወየዓርግ ጽጌ እምጕንዱ - ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፤ ከሥሩምቁጥቋጦ ያፈራል “(ኢሳ . 11÷1) ብሎ ከእሴይ ዘር የምትገኘውን እመቤታችንን በበትር ፣ ከርሷ የሚገኘውን ክርስቶስን ደግሞ በጽጌ መስሎ ትንቢቱን ተናግሯል፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም ድርሰቱን በዚሁ አንጻር በመቀመር እያንዳንዱን መልክዕ እመቤታችንንና ልጇን አስተባብሮ በጽጌና በፍሬበመመሰል፣ ከዚያው በማያያዝ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ በምሥጢር፣ በታሪክ፣ በጸሎትና በመሳሰለው መልክ ድንቅ በሆነና በተዋበ ሁኔታአዋሕዶ ደርሶታል፡፡
🌿❤️ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እመቤታችንን በአበባ እየመሰለ ከተናገረው ድርሰቱ መሐከል አንዱ
“ ማዕረረ ትንቢት ማርያም ዘዘመነ ጽጌ እንግዳ
ወዘመነ ፍሬ ጽጋብ ዘዓመተ ረኃብ ፍዳ
ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ
ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእምአውግሪሁ ለይሁዳ
ፀቃውዐ መዓር ቅድው ( ጥዑም ) ወሀሊብ ፀዓዳ”
🌿❤️ በመከር ጊዜ አበባ፣ በአበባ ጊዜ ደግሞ መከር አዝመራ ማጨድና መሰብሰብ የለም፡፡ ምክንያቱም ጊዜያቸው የተለያየ ስለሆነ፡፡ ለምሳሌ በመስከረም ወር የአበባ ጊዜ በመሆኑ አዝመራ መሰብሰብ የለም፡፡ የትንቢት መከር መካተቻ የሆንሽ እንደ ዘመነ ጽጌ የረሃብን ዘመን ያስወገድሽ ማርያም ሆይ፣የኤልዳ ነቢይ ኢዩኤል ከይሁዳ ተራሮች ጣፋጭማርና ፀዐዳ ወተት ይፈሳል ብሎ የተናገረው ትንቢትበአንቺ ታወቀ፣ ተፈጸመ ፡፡ እመቤታችን ነቢያት የተናገሩት የትንቢት ዘር ተፈጸመባት፡፡ ማለትምነቢያት የአምላክን ሰው የመሆን ነገር በተለያየ ሁኔታተናግረዋል፡፡ ጌታችን ነቢያት የተናገሩት ትንቢት መፈጸሙንና ይህንን ፍጻሜ ለማየት የታደሉትሐዋርያት መሆናቸውን ‘’አንዱ ይዘራል አንዱምያጭዳል ‘’ የሚለው ቃል እውነት ሆኗል፡፡ እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኳችሁ፡፡ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ በማለት ተናግሮአል (ዮሐ.4÷37-38)፡፡ይህም ነቢያት የዘሩት ትንቢት በሐዋርያት ዘመን ለአጨዳ ለፍሬ መድረሱን መናገሩ ነው፡፡ ስለሆነም ‘’ማዕረረ ትንቢት ‘’ የትንቢት መካተቻ ማርያም አላት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፍሬ ክርስቶስን ያስገኘችና ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች እየተባለ የተነገረላት በመሆንዋ ድንግል ማርያም በአበባ ትመሰላለች፡፡
🌿❤️ ስለዚህ እመቤታችን በመከር ወራት የምትገኝ አበባናት፡፡ በመከር ጊዜ የአበባ መገኘት ያልተለመደ ስለሆነ ‘’ወዘመነጽጌ እንግዳ ‘’ እንግዳ የሆነ አበባአላት፡፡ ከዚህ በኋላ ‘’ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ፣ ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእምአውጋሪሁ ለይሁዳ፣ ፀቃውዓ መዓር ጥዑም ወሀሊበ ፀዓዳ ‘’ በማለት ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረውንትንቢት አፈጻጸም ይናገራል፡፡ ነቢዩ ኢዩኤል በዘመኑ ጽኑ ረኅብ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን በምሕረት እንደሚጐበኛቸውና ረሃቡ እንደሚጠፋ ይነግራቸው ነበር፡፡ ‘’ብዙ መብል ትበላላችሁ ትጠግቡማላችሁ፣ ከዚህ በኋላ እንዲህ ይሆናል፣ ተራሮች በተሃ ጠጅ ያንጠበጥባሉ÷ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ÷ በይሁዳም ያሉት ፏፏቴዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ ‘’ (ኢዩ 3÷18፣ 2÷26) ።
🌿❤️ በዚህ በወርኃ ጽጌ ( በዘመነ ጽጌ ) የሚጾሙክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾመ ጽጌ መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም ነው፡፡ ወይም የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ከታዘዙትከ7ቱ አጽዋማት ውጪ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራል፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡