✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.21K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
Forwarded from Deleted Account
ከ ኢትዮ ሶማሌ ክልል ለተጎዱ ቤተ ክርስቲያናትና ለተሰው ሰማዕታት ቤተሰቦችማቋቋሚያ ይሆን ዘንድ በቤተክርስቲያናችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ተከፍቷል ሁላችሁም እጃችሁን ዘርጉ እንላለን።
አካውንት ቁጥር 1000254922898

የሞቱትን ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን።

ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ሼር በማድረግ ግዴታችንን እንወጣ

╔═★══════════📄══╗
@Zemaryan
@Zemaryan
@Zemaryan
╚══📃══════════★═╝
የቆራጥነት መልክት
@embtee
.ሁሉም ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሀይማኖቱን እሚያስከብርበት ግዜ ነው።
ብፅእ አባታችን አቡነ ዲዮስቆሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ስራ
አስኪያጅ እንዲህ የሚል የቆራጥነት መልክት አስተላልፈዋል። የኦርቶዶክስ ሀይማኖት መብት ይጠበቅ። የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አማኞች መብት ይጠበቅ።
የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ወጣቶች መብት ይጠበቅ። ይህ ካልሆነ ግን ከአሁን ቡሃላ ቤተ ክርስቲያን በዝምታ አታልፍም። ካህናቶቻችን ሲታረዱ አቢያተ ክርስቲይኖቻችን ሲቃጠሉ ማየት ለየ አንዳንዳችን ሞት ነው ብለዋል። እንዲህ ነው ቆራጥነት። ዛሬ ቤተ ክርስቲያ ከመቼውም በላይ መብቷን እምታስከብርበት ግዜ ነው። የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ከሁሉም በላይ ለእምነቱ ቦታ ሰጥቶ ሀይማኖቱን
የሚያስከብርበት ግዜ ነው።ዛሬ ችላ ባይነት የለም።
ዛሬ ትግስት የለም።
ዛሬ ግድየለሽነት የለም።
ዛሬ ፍራቻ የለም። @embtee
ዛሬ መጠቃት የለም።
ዛሬ መሞት የለም።
ዛሬ መናቅ የለም።
ዛሬ መዘረፍ የለም። @embtee
ዛሬ መደፈር የለም።
ዛሬ መሰደብ የለም።
ዛሬ መዘለፍ የለም።
ዛሬ ግራ ሲመታ ቀኝህን ስጥ የለም።
ሁሉም ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሀይማኖቱን እሚያስከብርበት ግዜ ነው። በመግደል ፋንታ መሞትን የመረጥነው መግደልን ስላልተማርን ነው።
@embtee
ዛሬ ግን ባንገል እንኳን እንከላከላለን። ሀይል እና ጉልበትም እንዳለንም ይታወቃል። ስለዚህ ጠላት እጅህን አንሳ ሳይገጥምህ አበሳ። በዝምታ ውስጥ ፍራቻ ሳይሆን ጀግንነትም አለ። ዝም ያለ ሁሉ ፈሪ አይደለም። ትግስት እንጂ። የቤተ ክርስቲያን መብት መጠበቅ አለበት የምትሉ አስተያየታችሁን አስቀምጡ።
ብፅእ አባታችን አቡነ ዲዮስቆሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ እንዲህ የሚል የቆራጥነት መልክት አስተላልፈዋል። ሀላፊነትዎን ይወጡ።
Share Share
@embtee
@embtee
936813289803913
#ማርያም♥️ #ዕጣን #ናት

#እርሷ #ዕጣን #ናት#ልጅዋ♥️ #የዕጣኑ #መዓዛ #ነው#የሰው #ልጅ #ክፉ #ሽታ የራቀባት እጣን፡ ምክንያተ ድኂን #ድንግል #ማርያም #ናት

#ጌታችንን #ዕጣን ይለዋል። " አንተ ውእቱ ዕጣን ኦ መድኅኒነ እስመ መጻእከ ወአድኅንከነ ተሳሀለነ" መድኅኒታችን ሆይ ዕጣን አነተ ነህ
🌿የ️ አቡነ ኪሮስ ታሪክ ባጭሩ 🌿❤️

🌹 በስምአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አሞላክ አሜን እንኻን አደረሳቹ ለአቡነ ኪሮስ ሰኔ 8 ️

🌿❤️ አባ ኪሮስ አባቱ ንጉስ ዮናስ እናቱ አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ነው፡፡ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ወለዱ፡፡ አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡
🌿❤️ በ17 ዓመቱ ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡ ከዚህ በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላእክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይተውት ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል።
@like
🌿❤️ ቃል ኪዳናቸውም ፡- መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡ በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ በተወለዱ 270 ዓመታቸው ሐምሌ 8 አርፈዋል።
ረድኤት በረከታቸው አማላጅነታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
@embtee

💓💖💛💚❤️💖💞🌹💚
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
AUD-20180925-WA0029
<unknown>
*አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል (ማቴ ፮፥ ፴፫)*
በመጋቤ ሐዲስ ያሬድ እንግዳወርቅ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

@embee
† ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን †
→በወርኃ መስከረም ብቻ በዓለ መስቀልን አራት ጊዜ ታከብራለች፡፡
የመጀመሪያው ምክንያተ ክብረ በዓል፣ በኢትዮጵያ ነግሦ የነበረው ዓፄ ዳዊት ከግብፅ ንጉሥና ሊቃነጳጳሳት የተላከለትን በቅዱስ ሉቃስ እጅ የተሳለችውን ስዕለ ማርያምን፣ በወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የተሳለውን ኩርዓተ ርእሱን ፣ ሌሎች ንዋያተ ቅድሳትን እና የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ግማደ መስቀል የግብፅ እና ኢትዮጵያ ድንበር ከነበረችው አስዋን ከተባለችው ቦታ ተረክቧል።ንጉሡ የያዘውን በረከት ወደ ኢትዮጵያ ሳያደርስ ስናር በተባለው ቦታ ዐረፈ፡፡ ከጊዜ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ የተባለው ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ተቀብሎ በደብረ ብርሃን፣ በየረር፣ በመናገሻ እና በልዩ ልዩ ተራራማ ቦታዎች ሲዘዋወር ቆይቶ “ መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አኑር ” የሚል ራእይ ተገልጦለት ቅዱስ መስቀሉን በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ በግሸን ደብረ ከርቤ አስቀምጦታል ፡፡ መጋቢት ዐሥር ቀን ደብረ ብርሃን ሲገባ ብርሃን ስለወረደና ዐፄ ዳዊት ከግብፃውያን ጳጳሳት እና ንጉሥ እጅ መስቀሉን የተረከቡበትን ቀን በማዘከር የአድባራት እና የገዳማት ሊቃውንት ልብሰ ተክህኖአቸውን ለብሰው የብር መቋሚያ እና ጸናጽል ይዘው ወደ ነገሥታቱ ሔደው ተቀጸል ጽጌ እያሉ እያሸበሸቡ ጸሎተ ወንጌል ያደርሱ ስለነበር መስከረም ዐሥር ቀን የዓፄ መስቀል በዓል ተብሎ ይከበራል፡፡
ሁለተኛው መስቀሉን በቁፋሮ ያገኘችው ንግሥት እሌኒ ደመራ ያስደመረችበት እና የእጣኑ ጢስ መስቀሉ ወደተቀበረበት ድልብ አከል ተራራ ያመለከተበት ዕለት መስከረም ዐሥራ ስድስት ቀን በመሆኑ የመስቀል ደመራ በዓል በዚሁ ዕለት ይከበራል፡፡
መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን ደግሞ ቁፋሮ ያስጀመረችበት ዕለት ሲሆን መጋቢት ዐሥር ቀን መስቀሉን አግኝታለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን አሠርታ፣ መስቀሉን አስገብታ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረችበት ዕለት ግን መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን ነው፡፡ የመስቀሉ መገኘት ጥንተ በዓሉ መጋቢት ዐሥር ቀን ቢሆንም አባቶቻችን በታወቀና በተረዳ ነገር ዋናው የመስቀል በዓል የሚከበርበት ዕለት መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን እንዲሆን አድርገዋል፡፡ በመጨረሻም መስከረም ሃያ አንድ ቀን በዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በግሸን ደብረ ከርቤ መስቀሉ ያረፈበት ዕለት ስለሆነ
“ በልደቱ ፍስሐ ፤
በጥምቀቱ ንስሐ ፤
በመስቀሉ አብርሃ፤ ” እያልን በማኅሌት፣ በዝማሬና በቅዳሴ ለዘለዓለም ስናከብረው እንኖራለን ፡፡
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው ተብሎ እንደተጻፈ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያለመስቀል የሚከናወን ሥርዓት የለም፡፡ ከካህናት አክሊል ከመነኮሳት አስኬማ ከእናቶች ቀሚስ እስከ አባቶች እጀጠባብ ድረስ የመስቀል ምልክት እያደረግን በሰውነታችን እየተነቀስን በአንገታችን እያሰርን ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር እንገልጣለን፡፡
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን እውነተኛ ፍቅር በተለያየ መንገድ አሳይቷል፡፡ ሰማይና ምድር የእርሱ የሆነ አምላክ በከብቶች ግርግም ተወለደ፡፡ የተነገረው ትንቢት የተቆጠረው ሱባዔ ሲያልቅ በመስቀሉ ተፈጸመ ብሎ ሕይወትን በመስጠት ሞታችንን በመውሰድ ፍቅሩን ገለጠ መስቀል ፍቅረ እግዚአብሔርን የሚያሳስበን የስብከታችን ርእስ የኑሮአችን መርሕ ስለሆነ በዓመት አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ዘወትር እናስበዋለን፡፡
ከዐሥራ አራተኛው መቶ ክፍለዘመን ጀምሮ በደጋግ ነገሥታቶቻችን አማካይነት ቅዱሱ መስቀል ወደ ሀገራችን እንዲገባ የዘወትር ጥረት አድርገዋል፡፡ የለመኑትን የማይረሳ የፈለጉትን የማይነሣ አምላክ መስቀሉ በሀገራችን እንዲቀመጥ ፈቃዱ ሆኖአል፡፡

💚 💚💛💛💖💖ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን

@embtee
ጥልን_በመስቀሉ_ገደለ_New_sebket_by_Memher
<unknown>
#ጥልን #በመስቀሉ #ገደለ

🌼 #መምህር #ዘላለም #ወንድሙ


#ጥልንም #በመስቀሉ #ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል #ከእግዚአብሔር ጋር #ያስታርቅ ዘንድ ነው።

መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ #ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስ

@Embtee
@EMbtee
@Embtee
➕️➕️➕️መስቀል➕️➕️በመምህር_ሳሙኤል_አስረስ
<unknown>
መስቀል

🌼 መምህር ሳሙኤል አስረስ

" ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።"
(ወደ ገላትያ ሰዎች 6:14)

┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@ EMbtee
@EMbtee
AUD-20180927-WA0038
<unknown>
*ጌታሆይ አድነን ጠፋን*
*ማቴዎስ ፰፥፳፭*
በመጋቤ ሐዲስ ቀሲስ አበበ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
AUD-20180928-WA0039
<unknown>
ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ
(ዮሐ ፫፥ ፲፬-፲፭)
በወንድም አቤል ተፈራ
ለወንድማችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

👆🏻👂🏻👂🏻👈🏻
┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
680437252108186
<unknown>
++ኢየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ++

++ኢየሱስ ክርስቶስ እና ሙሴ ++

💖 በ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ 💖


┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛
ለአስተያየቶ ይላኩልን 👉 @yitaya
ለመንፈሳዊ ልምምድ ጠቃሚ ምክሮች
++++++++++++++++++++++

በመጀመሪያ ምን ያህል አዋቂዎች ብንሆን ማወቃችን ብቻ ሊያስደስትን እና ሊያረካን አይገባም፡፡ ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ያወቅነውን በስራ ለምንተረጉምበትና ትእዛዛትን መፈፀም ለምንችልበት ሕይዎት ነው፡፡
ጌታችን የተራራው ስብከቱን ሲያጠቃልል የተናገረው ቃል ይህን ነው፡፡ ‹‹ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በአለት ላይ የሰራ ልባምን ሰው ይመስላል፣ ይህንንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሰራ ሰነፍን ሰው ይመስላል፡፡›› (ማቴ 7፣24-6) ስለዚህ እንደሰማን ለመስራት ለምግባራችን ትልቅ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል፡፡ ይህንንም ሲያረጋግጥልን ‹‹በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡›› ብሏል ካህኑም በፀሎተ ቅዳሴ (ቅድመ ወንጌል) ወንጌልን ለመስማት፣ እንደሰማንም ለመስራት በቅዱሳን ፀሎት የበቃን አድርገን›› እያለ የሚጸልየው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ ትእዛዙ ለመኖር እና ቃለ ወንጌሉን ለመፈፀም ራሳችንን እናለማምድ፡፡
መንፈሳዊ ልምምድ አንድ ሰው ለነፍሱ ድህነት ያለውን ተስፋ ያመለክታል፡፡ ስሕተቶቹን፣ ድክመቶቹን ሁሉ ለይቶ አውቆ ለማስወገድ እየጣረ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ አንተም ወንድሜ ስህተቶችህን ሌሎች
አይተው እስከሚነግርህ ድረስ መጠበቅ ሳይኖርብህ በራስህ ለይተህ እወቃቸው፡፡ምክንያቱም ያለብህን ችግር ሳታውቀው ለመንፈሳዊ ልምምድ መነሳት ስለማትችል ነው፡፡ ‹‹በሽታውን የደበቀ መድሃኒት አይገኝለትም›› ይባል የለ፡፡ ‹‹ህምምተኞች እንጂ ባለጤናዎች ባለመድሃኒት አያስፈልጋቸውም›› (ማቴ 9፤12)

ባንተ ያለውን ችግር ሌሎች ማወቃቸውም ቢሆን አያበሳጭህ፡፡ ይልቁንም በየትኛው መንፈሳዊ
መስክ ልምምድ ማድረግ እንደሚገባህ አደረርገህ ተቀበለው፡፡
በእግዚአብሔር ህግ ብርሃንነት ራስህን እየመረመርክ ድክመቶችህን ፈልግ፡፡ ትንንሽ ድክመቶች እንኳ ቢሆኑ አትናቃቸው፤ምክንያቱም
ያድጋሉና፡፡ ‹‹ወይናችን አብቧል ኑ የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮዎች፣ ጥቃቅን ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙ፡፡››(መኃ 2፣15)

#ራስህን ከማፅደቅ ተቆጠብ ለስህተቶችህም ማስተባበያ አትፈልግ ራሱን የሚያፀድቅ ሰው ዘወትር ባለበት መሔድ እንጂ የሚያሻሽለው አንድም ነገር የለምና፡፡ ምክንያቱም ባይኑ ፊት ከእርሱ በላይ ሰው የለም ለራሱ እንከን የለሽ ነው፡፡ለችግሮች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ይህን ያደረኩት በዚህ ምክንያት ነው እያለ ሲያስተባብል ወድቆ ይቀራል፡፡ለራሱ ትክክለኛ ግምት ያለው የማይመፃደቅ ሰው ግን ድክመቱን መናዘዝ ብሎም ማስወገጃውን መንገድ መለማመድ ይችላል፡፡ ችግሮችህ ስር ሰደው ሰውች ሊገልጡብህ የሚችሉበት ደረጃ ሲደርሱ የሚሰማህ መሸማቀቅ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ቀደምብለህ እራስህ ገልጠሐቸው ለመፍትሔው ልምምድ ብታደርግ ይህ ሁሉ ነገር ባንተ ላይ አይከሰትም፡፡

#ሁሌም ራስህን ሁነህ ተገኝ፡፡በሕይወትህ ቅንነት የሚነበብብህ ሰው ሁን፡፡ መጽሃፍትን ስታነብም ሆነ ስብከት ስታዳምጥ ጉድለቶችህን እየፈለክ ይሁን፡፡ ሰምተህ ለማድረግም ተነሳሳ፡፡

#የኃጢያት ስሩ አንድ ነው፡፡ ብዙ መንገዶች ቢኖሩትም እርስ በራሳቸው የተያያዙ መሆናቸውንም እርግጠኛ ሁን፡፡ አንድ የተወሰነ የሀጢያት አይነትን ለመቅረፍ ስትነሳ ሳታውቀው
ሌሎችንም እየበጣጠስክ መሆኑን እወቅ፡፡እንዲሁም አንድ በጎ ሥነ ምግባርን ለማዳበር ስትለማመድም ቢሆን ሌሎች ብዙ ሥነ ምግባራትን እያተረፍክ መሆኑን ልብ በል፡፡ ሥነ ምግባራቱም በአንድ ሠንሰለት የተያያዙ ናቸው
┏━━° •❈• ° ━━┓
@Embtee
@Embtee
@Embtee
┗━━° •❈• ° ━━┛