✞ ደጓ እናቴ ማርያም ✞
1.2K subscribers
178 photos
11 videos
29 files
137 links
ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!
@embtee
@embtee

@Binyama1

@yitayal_bot

Contact @Maryamawit_bot
Download Telegram
AUD-20190119-WA0055.mp3
15.5 MB
*የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት*
*ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡ አለው*
*(ማቴ ፫ ፥ ፲፮)*
በመጋቤ አእላፍ ቀሲስ ገብረ ዮሐንስ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
*ማኅበረ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ*

@embtee
@embtee
@embtee
👉👂👆
ጾታዊ_ፍቅር_በኦርቶዶክሳዊ_እይታ_በአቤል_ተፈራMP3_128K.mp3
52.4 MB
የፆታዊ ፍቅር በኦርቶዶክስ ~~~~ ትምህርት

ክፍል 2 በ ዲ/ን አቤል ተፈራ
👂👂👂👂👂👂

@embtee
@embtee
@embtee👈
✞ ቅዱስ ቂርቆስ ሰማዕት ✞

✞ የሰማዕትነት ታላቅ ክብር ያገኘው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በነበረበት ጊዜ የነበረው መኰንን ክርስቶስን በመካድ በክርስቲያኖች ላይ መከራ ያጸናባቸው ነበር፤ ሕፃኑ ቂርቆስንም ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ይኽ ቅዱስ ሕፃን “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት መለሰለት፡፡

✞ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡

✞ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡

✞ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡

✞ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡

✞ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡

✞ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት "ምን ላድርግልኽ?" አለው፤ ሕፃን ቂርቆስም ለጌታ "ሥጋዬ በምድር ላይ አይቀበር፤ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ ፍላጎታቸውን ስጣቸው፤ ስሜ በሚጠራበት በዚያች ቦታ የከብት ዕልቂት አይምጣ፤ በሰውም ላይ ተላላፊ በሽታ በእኽልም ላይ ድርቅ የውሃም ማነስ አይኹን" አለው።

✞ መድኀኔ ዓለምም ሕፃኑ ቂርቆስን "የለመንከኝን ኹሉ እሰጥኻለሁ ሥጋኽንም ኤልያስ ባረገበት ሠረገላ ውስጥ አኖርልኻለኊ" አለው፤ ይኽነን ቅዱስ ቂርቆስ በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገታቸው ተቈረጠ፤ መድኃኒታችን ክርስቶስም በማይጠፋ አክሊል ጋረዳቸው፤ ነፍሶቻቸውም በታላቅ ክብር ዐረጉ የሰማዕትነትንም ክብር ተቀዳጁ።

☞ ጥር ፲፮ ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ዐሥራ አንድ ሺሕ አራት ሰዎች በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡

☞ ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“እግዚአብሔር ሤመ ረድኤቶ ለንእስናከ ዐቃቤ
ወስምዖ መጥበቤ
ፍትወ ምግባር ቂርቆስ ወምዑዘ ኂሩት እምከርቤ
ለዘተጽዕረ በምንዳቤ ወለዘቈስለ በጥብጣቤ
ለአባልከ ሰላም እቤ”
(እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤ በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለኊ) እያለ ሕፃኑን ሰማዕት ያወድሳል፡፡

✞ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ፦
“ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ
በልደት ንዑስ፤
ንጹሕ ከመ ዕጣን
ወፍሡሕ ከመ ወይን”፡፡
(በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል)

✞“ሰላም ለሰማዕታት እለ ምስሌሁ ፭፼ ወ፬፻፤ ፬፼ ወ፪፻፲ወ፬”፡፡
(ከርሱ ጋር ያሉ ፭፼ ከ፬፻፤ ፬፼ከ፪፻፲፬ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባቸዋል) በማለት አመስግኗል፨
[የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት የሰማዕታት በረከት ይደርብን፨

✞ ✞ ✞
ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ሰማዕት ፀሎት ይማረን በረከቱን ያሳድርብን አማላጅነቱ አይለየን ሰማዕት በረከት ያሳትፈን።

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት

❤️ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ❤️

ለመቀላቀል 👇
      ┏━━° •❈• ° ━━┓
     💚@embtee💚
💛 @embtee 💛
@embtee
      ┗━━° •❈• ° ━━┛

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

ይቆየን
4_5929344313682035659.m4a
40.9 MB
🎬 ፆታዊ ፍቅር በወንድም አቤል ተፈራ ክፍል፫
ውድ እህቶቸ አድምጡት ለሌሎችምላ እድደርስ like ሼር

@embtee
@embtee
@embtee👈ይቀላቀሉን
@embtee
AUD-20190125-WA0007.m4a
5.6 MB
*ታላቅ ስራን በኔ አድርጎአልና*

🎙ዲያቆን ዮርዳኖስ


(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 1)
----------
47፤ *📖ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤*

48፤ *የባሪያቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤*

49፤ *ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ከታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።*

50፤ *ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።*

*ማኅበረ አትናትዮስ መልስ ለአህዛብ*👆🏼👆🏼👂🏽👂🏽

ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!

@embtee
@embtee ~~~ ይቀላቀሉን
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓል ዕረፍት በሰላም አድረሳችሁ
[የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት]
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖ ጥር 21 የእመቤታችንን በዓለ ዕረፍት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች። የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር ከቆየች በኋላ፤ ዓለምን ለማዳን በዕለተ ዓርብ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜም የሚወድዳት እናቱን ለሚወድደው ደቀ መዝሙር ለዮሐንስ “እነኋት እናትኽ” በማለት አደራ በመስጠት በዮሐንስ በኩል ለሚወድደን ለእኛ የአደራ ልጆቿ እንድንኾንና የአደራ እናታችን እንድትኾን ታላቅ ስጦታን በቀራንዮ በእግረ መስቀል ሥር ሰጠን (ዮሐ ፲፱፥፳፮‐፳፯)፡፡
በዚኽም መሠረት ሐዋርያትም ከአምላካቸው የተሰጠቻቸው የአምላካቸውን እናት ይዘው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ፸፪ት ቋንቋ ገልጾላቸው ታላቅ መንፈሳዊ ኀይልን ሰጣቸው (የሐዋ 1፥፲፬)፤ ዮሐንስም በእናትነት የተቀበላት ቅድስት ድንግል ማርያምን በቤቱ 15 ዓመት አኑሯታል፡፡
ከዚያም ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት፤ ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፡፡
ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፤ ቁጥሩ ከ72 ቱ አርድዕት የኾነው ቅዱስ ኢቮዲደስ እንደጻፈው የእመቤታችን ዕረፍቷ ሲደርስ ጌታ ተገልጾ እናቱን እንዲኽ አላት:-
❖ "ዛሬ ለዘጠኝ ወራት በምድር ላይ መኖሪያዬ ኾና የቆየችውን ድንግል እናቴን የምቀበልበት እና ከእኔ ጋር ወደ ሰማያት ሰማያዊ ቦታዎች ይዤያት በመውሰድ ለመልካሙ አባቴ በስጦታ የማስረክባት ቀን ነው፣ ዳዊትም እንኳን “በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ” (መዝ ፵፬፥፲፬) እንዳለ።
ጌታም በመለኮታዊዉ እና ግሩም ድምፁ የኔ ውድ እናት ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መሓ ፪፥፲)፤ የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ወደ እኔ ነዪ (መሓ፪፥፲፫) አላት፤ አንቺ ከቄዳር ልጆችም በላይ ውብ ቆንዦ ነሽ (መሓ ፩፥፭)፤ አንቺ የተመረጥሽ ጎጆ ሆይ የመልካማ ርግብ መኖርያ ነሽ፤ አንቺ የተመረጥሽ የአትክልት ስፍራ ያለምንም ዘር እና የወንድ ሩካቤ መልካሙን ፍሬ ያፈራሽ (መሓ ፬፥፲፪)።
አንቺ የወርቅ መሶብ ሆይ መናው እውነተኛው መና እኔ እንኳን የተሰወርኹብሽ (ዘፀ ፲፮፥፴፫-፴፬)፤ አንቺ ስዉር ቅርስ እውነተኛው ብርሃን የተሰወረብሽ እና ከአንቺም ውስጥ ወጥቶ በመገለጽ በሰው ልጆች ላይ የተትረፈረፈ ሀብት ያስገኘላቸው፡፡
ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ የእኔ ውብ ርግብ ሆይ (መሓ ፮፥፱) የእኔ ቅድስት መርዐት (መሓ ፬፥፰)፣ የእኔ ንጽሕት መስክ፣ ከእኔ ጋር ወደ አትክልት ስፍራው እወስድሻለኊ (መዝ ፸፩፥፮) ከርቤ እና ጣፋጭ ቅመማ ቅመሜን እደረድርልሻለኊ (መሓ ፬፥፲፬) ከበታችሽም እንድታርፊበት ያማረውን ምንጣፍ አነጥፍልሻለኊ፤ ማርያም እናቴ ሆይ አንቺ የተባረክሽ ነሽ ወደ ምድር ወልደሽ አምጥተሽኛልና፡፡
እኔ ኹሉን መጋቢ የኾንኹትን ያጠቡ ጡቶሽን የተባረኩ ናቸው፡፡ እንዲኹም በከፍታ ቦታዎች ወደሚገኙ ሰማያዊ ስፍራዎች ወስጄሽ በአባቴ በመልካም ነገሮች እመግብሻለኊ፡፡ እስከዚያው በጉልበትሽ ላይ ያስቀመጥሺኝ ድንግል እናቴ ማርያም ሆይ በኪሩቤል ሠረገላ ላይ በማኖር ከእኔና ከቸሩ አባቴ ጋር ወደ ሰማያት እወስድሻለኊ፡፡
በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በሰይፈ ነበልባላቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡
የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ አላት፡፡
ከዚያም ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች፤ ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ የከበረ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው።
ከዚያም ልጇ “የእኔ እናት ማርያም ሆይ እግዚአብሔርን (እኔን) የሳምሽባቸው ከናፍሮችሽ የተባረኩ ናቸው፤ ወደ ምድር ሲመለከት መሠረቶቿ እንዲናጉና እንዲሸበሩ ለማድረግ የሚችለውን ከኀሊውን ልጅሽንና አምላክሽን (እኔን) ያየሽባቸው ዐይኖችሽ የተባረኩ ናቸው፤ ከሰማያት ነዋሪዎች ጋር በመላእክት ቋንቋዎች ስነጋገር የሰማሽባቸው ዦሮዎችሽ የተባረኩ ናቸው።
አንቺ ሆይ በቃሉ ኀይል ምድርን የተሸከማትን የተሸከሙት የኖርኹባቸው ታናናሾች ክንዶችሽ የተባረኩ ናቸው፡፡ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ ፍጥረትን ኹሉ የምመግበውን የመገቡት እና ያጠቡት ጡቶችሽ የተባረኩ ናቸው፡፡ በኀያሉ ዙፋን ላይ በክብር የምቀመጠውን እኔን በፍቅር ያስቀመጡኝ ጉልበቶችሽ የተባረኩ ናቸው፡፡ ለዘጠኝ ወራት የተሸከሙኝ ማሕፀኖችሽም የተባረኩ ናቸው፡፡ በመለኮታዊነቴ ብርሃን ብሩሃት የኾኑት ሥጋሽና ነፍስሽ የተባረኩ ናቸው” አላት::
ሐዋርያት በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው ለምቀኝነት አያርፉምና ቀድሞ ልጇ ሞተ፣ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ እያስተማሩ ኖሩ ከመቃብሩም ተአምራት ይደረጋል፤ አሁን ደግሞ ርሷ ሞተች፣ ተነሣች፣ ዐረገች ብለው ሊያስተምሩ አይደል፤ “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡
ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ይቤ ዮሐንስ ወኢይገድፍ ምዕቅብናየ ወዘንተ ብሂሎ ወድቀ በላዕሌሃ” ይላል (ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡ ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡
ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” ይላል የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ “ወዕጥን ሥጋሃ ለማርያም መዓልተ ወሌሊተ” ይላል የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በ
መቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ “ወፍና ሠርክ ያመጽዕ ሎቱ ራጉኤል መልአክ ኅብስተ ሰማይ” ይላል ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡
[የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከማያልቀው በረከትሽ አብዝተሽ አሳድሪብን]
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
AUD-20190201-WA0009.m4a
5.8 MB
*ዝክረ አበው*

🎙ዲያቆን ዮርዳኖስ🎙

*ቅዱስ ኤልያስ እና ቅዱስ ባስልዮስ*


(የያዕቆብ መልእክት ምዕ. 5)
----------
17፤ *ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥*

18፤ *ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች።*

*ማኅበረ አትናትዮስ መልስ ለአህዛብ*👆🏼👆🏼👂🏽👂🏽
*32:49*


@embtee
@embtee
@embtee
AUD-20190202-WA0006.m4a
15.2 MB
@embtee
@embtee
@embtee ~~ዲ/ን ዮርዳኖስ

ሶልያና ምታበራ{ያበራች } ጨረቃ
AUD-20190209-WA0004.m4a
4.6 MB
*ዓለማዊ እና መንፈሳዊ ሰው መሆን ይቻላል?*

💞 ሊቃውንት አባቶች

*👉🏾ነፃ ፍቃድ በዓለዊዉና በመንፈሳዊ እይታ ምን ይመስልላ?*

*👉🏾አንድ ሰው ዘመናዊው መንፈሳዊም ሊሆን ይችላል?*

*👉🏾ዓለማዊነት ምድንን ነው መገለጫውስ?*

*👉🏾መንፈሳዊነት ምንድን ነው መገለጫውስ?*

*👉🏾ሉላዊነት መንፈሳዊነት ላይ ምን ተፅእኖ አለው? Globalition*

@embtee
@embtee
@embtee ~~

*👉🏾ፊልም ሙዚቃ እና ስፓርታዊ ውድድሮች ዓለማዊነትን አስፋፍተዋል*

*👉🏾ራሳችሁን ስትገመግሙት መንፈሳዊ ናችሁ ወይስ አለማዊ?*

*ማኅበረ ቅዱሳን የአውደ ወራዙት መርሃ ግብር*👆🏼👆🏼👂🏽👂🏽5⃣
*26:01*

@embtee
@embtee
@embtee
✟ ̲̲̅̅የ̫̫እ̫̫መ̫̫ብ̫̫ር̫̫ሀ̫̫ን̫̫ ል̫̫ጆ̫̫ች̫̫ ̫[ማ̲̲̅̅ህ̲̲̅̅በ̲̲̅̅ር̲̲̅̅] ✟̫̫
┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶
፠ ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፍቅር ናት ኑ ተማሩ

⛔️ የእናታችን የቅድስተ ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች ኑ እንሰባሰብ

፨ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ብቻ ይቀላቀል ለመቆጠር ብቻ አይሁን

ማንም ሊያመልጠው አይገባም ለበረከት ይሳተፉ
┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽
/adminlist
Creator @yitaya
https://tttttt.me/embrhan_lijoch
AUD-20190211-WA0004.m4a
6.4 MB
*ነገረ ክርስቶስ*

🎙ሊቀ ሊቃውንት ስማዕኮነ እና ሊቃውንት🎙

*👉🏾ቅብዓት እና ጸጋ ምንድን ነው*

*ተዋህዶ ማለት ምን ማለት ነው?*

@embtee @embtee

(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 1)
----------
1፤ *📖በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።*
. . .@embtee @embtee
14፤ *ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።*
@embtee @embtee


*ማኅበረ ቅዱሳን የስብከት ወንጌል ክፍል 1⃣*👆🏼👆🏼👂🏽👂🏽
AUD-20190213-WA0005.m4a
6.3 MB
*ያለ ጭንቀት መኖር*

🎙መምህር ምእረትአብ አሰፋ


(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 6)
----------
25፤ *📖ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና ፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?*

. . .
27፤ *📖ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?*

28፤ *ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤*

29፤ *አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም።*

. . .
31፤ *እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤*

*ማኅበረ አትናትዮስ መልስ ለአህዛብ ክፍል 2⃣*👆🏼👆🏼👂🏽👂🏽
*35:26*

@embtee
@embtee 🌸🌺🌸🌺
@embtee
#የካቲት_11_ፆመ_ነነዌ_ይጀምራል
"#ምነው_ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን እንደ ሆነ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ" አለው። ትንቢተ ዮናስ 1:6 ።
#የዚህ ፆም ጊዜ ሶስት ( 3 ) ቀን ብቻ ነው ። ቀኖቹም በየዓመቱ ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ናቸው ። የነነዌ ፆም በመባጃ ሐሙስ( አቆጣጠር ) ከፍ እና ዝቅ ስለሚል አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል ።
የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህን ፆም የወሰኑት ልትጠፋ የነበረች ነነዌን በፆም ምክንያት እግዚአብሔር ይቅር ስላላት ይህን አምላካዊ ይቅርታውን ለዘለዓለም ለማሰብና ዛሬም በዚህ ዓለም ከነነዌ የከፋ ርኩሰትንና ኃጢያትን ስላለ የነነዌ ሕዝብ ይቅር ያልክ አምላክ ዛሬን ይቅር በለን ለማለት ነው

++ የነነዌ ሰዎችም እግዚአብሔርን አመኑ ለፆም አዋጅ ነገሩ
ከትልቁም ጀምሮ እስከ ትንሾቹም ማቅ ለበሱ ወሬውም ለነነዌ ንጉስ ደረሰ። እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናፀፊያውን አውልቆ ማቅንም ለበሰ። አመድ ላይም ተቀመጠ አዋጅንም አስነገረ።

++ በነነዌም ውስጥ የንጉሱንና የመኳንቱን ትእዛዝ አሳወጀ እንድህም አለ ሰዎችም እንስሶችም አንዳችም እንዳይቀምሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ። ሰወችና እንስሳትም በማቅ ይከደኑ። ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩሁ። ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይፀፀት እንደሄነ ከፅኑ ቁጣውስ ይመለስ እንደሆነ ምን ያውቃል በማለትም አሳሳበ።

++ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸውም እንደተመለሱ በስራቸውም አየ። እግዚአብሔር አምላክም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተፀፀቶ አላደረገውም
ት ዮናስ ( ፫ ፤ ፭-፲ )
የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ ቸር አባት ለሀገራችንም ለህዝባችንም ምህረትና ቸርነቱን ያብዛልን ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን አሜን ፫
ለመንፈሳዊነት ቅድሚያ እንስጥና የእግዚአብሔርን ብድራት እንጠብቅ፡ እግዚአብሔር ጾማችንን ጾመ ድህነት ጾመ ስርየት ሰይጣንን ድል መንሻ ፣የኃጥያት መደምሰሻ ፣ መንግስተ
ሰማያትን መውረሻ ያድርግልን
ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን
✟ ̲̲̅̅የ̫̫እ̫̫መ̫̫ብ̫̫ር̫̫ሀ̫̫ን̫̫ ል̫̫ጆ̫̫ች̫̫ ̫[ማ̲̲̅̅ህ̲̲̅̅በ̲̲̅̅ር̲̲̅̅] ✟̫̫
┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶
፠ ከፍቅሯ ርቃቹ የምትኖሩ ማርያም ፍቅር ናት ኑ ተማሩ

⛔️ የእናታችን የቅድስተ ድንግል ማርያም የአስራት ልጆች ኑ እንሰባሰብ

፨ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ብቻ ይቀላቀል ለመቆጠር ብቻ አይሁን

ማንም ሊያመልጠው አይገባም ለበረከት ይሳተፉ
┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽
/adminlist
Creator @yitaya
https://tttttt.me/embrhan_lijoch
Audio
*ወደ እኔ ተመለሱ*

🎙መምህር ፍቃዱ ሳህሌ

@embtee
@embtee
👉 @embtee
*📖" ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምር ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን። የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል። "*
(ትንቢተ ሚልክያስ 3:7)

*👇🏽የነነዌን ፃም እንዴት እንጹም?*
@embtee
@embtee
👉 @embtee
*📖" ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ ክፉታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ።* "
(ትንቢተ ዮናስ 1:2)

*ማኅበረ ቅዱሳን የስብከት ወንጌል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ይቅርታ በመዘግየታችን*👆🏼👆🏼👂🏽👂🏽

@embtee
@embtee
👉 @embtee