ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የነገረ_ቅዱሳን ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሾች

#እውነት ወይም ሐሰት በሉ

#ኛ_ ቅዱስ የሚለው ቃል ቀደሰ ካለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም የተለየ ፣ የተከበረ ፣ ማለት ነው::

ሀ) እውነት ለ ) ሐሰት

#ኛ_የቅዱሳን ቅድስናቸው የባህሪ ቅድስና ነው ::

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት

ምክንያቱም:- #የባህሪ ቅድስና ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው

#ኛ_ "ሁሰት" ከ አሥሩ የቅዱሳን ማዕረጋት መካከል አይካተትም::

ሀ)እውነት ለ) ሐሰት


#ኛ_ቅዱሳን የሚለው ገላጭ ለ ቅዱሳን #ሰዎች ብቻ የሚቀፀል ቅጽል ነው::

ሀ) እውነት ለ)ሐሰት

ምክንያቱም :-ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር
#ለቅዱሳን መላእክት
#ለቅዱሳን መጻሕፍት
#ለቅዱሳን መካናት ይቀጸላልና

#ኛ_ቅዱሳን ሰዎች ፈተና የሚገጥማቸው ከፍቃደ ሥጋቸው ብቻ ነው

ሀ) እውነት ለ) ሐሰት
ከፍቃደ ሥጋ ብቻ ሳይሆን #ለበረከት_ከእግዚአብሔር ለማሰናከል #ከሰይጣን #ከአላዊያን ነገስታት #ከጠንቆዮች ጭምር ይገጥማቸዋልና


#ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ብቻ ምረጡ

#ኛ_ከሚከተሉት ማዕረጋተ ቅዱሳን መካከል #በወጣኒነት ክፍል ውስጥ የማይመደበው ማዕረግ የቱ

ሀ )ጽዋሜ (ዝምታ ፣ አርምሞ)
ለ )ልባዌ (ልብ ማድረግ )
ሐ ) ከዊነ እሳት
መ )አንብዕ

ሐ)በፍጽምነት የሚገኝ ማዕረግ ነው

#ኛ_መፍቀሬ ጥበብ የተባለው ቅዱስ ሰለሞን "ከሞተ አንበሳ ያልሞተ ውሻ ይሻላል" ብሎ ተናግሯል:: ለመሆኑ በአንበሳና በውሻ የመሰላቸው እነማንን ነው


ሀ ) ጻድቃንን
ለ ) ኃጥዐንን
ሐ ) ጻድቃንን እና ኃጥዐንን

#ኛ_የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት የሆነው የቱ ነው

ሀ) ማማለድ (መለመን)
ለ) ማበርታት ፣ማጽናናት
ሐ) መቅጣት
መ) ሁሉም

#ኛ_ነገረ ቅዱሳን ሲባል ከቅዱሳን ሰዎች ባሻገር ሊያጠቃልል የሚገባው እነ ማንን ነው

ሀ) ቅዱሳት መላእክት
ለ) ቅዱሳት መካናትን
ሐ) ቅዱሳት መጻሕፍትን
መ) ሁሉንም


#ኛ_ ለቅዱሳን ሁሉ ሊቀርብ የሚገባው የስግደት ዓይነት የቱ ነው

ሀ) የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደት
ለ) የአምልኮት ወይም የባህሪ ስግደት
ሐ) የአስተብርኮ ስግደት
መ) ከእግዚአብሔር በስተቀር ለማንም አይሰገድም


#በአጭሩ_መልሱ

፲ ፩ #_ቅዱሳን ፈተና የሚገጥማቸው ከነማነው

#መልስ
#ከእግዚአብሔር ለበረከት
#ከሥጋ ፍቃዳቸው
#ከአላዊያን ነገስታት
#ከጠንቆዮች
#ከሰይጣን


፲ ፪ #_አስሩ የቅዱሳን መዐረጋት በሦስት ክፍል ይከፈላሉ ::ምን ምን ተብለው በአጭሩ ይብራራ(ሪ)

#መልስ
#ጸጣኒነት (ጀማሪ)
#ማዕከላዊነት
#ፍጽምነት
ወይም
#ንጽሐ ሥጋ
#ንጽሐ ነፍስ
#ንጽሐ ልቡናም ተብለው ይጠራሉ
፲ ፫ #ኛ ቅዱሳን ከአፀደ ሥጋ ባሻገር በአፀደ ነፍስ ጭምር እንደሚያማልዱ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመጥቀስ አስረዳ(ጂ)

#መልስ
#ሊቀ_ነቢያት_ቅዱስ_ሙሴ በዘመኑ ባልነበሩ ቅዱሳን ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መለመኑ እና መልስ ማግኘቱ
"፤ ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ #የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም #አስብ።"
#እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው #ክፋት_ራራ።"
(ኦሪት ዘጸአት 32÷14-14)


፲ ፬ #ኛ ሦስቱን የመላክት ከተማ ስም ማን ማን ይባላሉ

#መልስ
#ኢዮር
#ራማ
#ኤረር


፲ ፭ #_ቅዱሳንን ማክበር #እግዚአብሔርን ማክበር ማለት እንደሆነ በራስህ (ሺ) አረዳድና አገላጽ በአጭሩ አስረዳ(ጂ)

#መልስ
"፤ #እግዚአብሔር#በቅዱሳኑ ላይ #ድንቅ_ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤ እግዚአብሔርም ይመስገን።"
(መዝሙረ ዳዊት 67÷35)


"፤#እግዚአብሔር_በጻድቁ_እንደ_ተገለጠ_እወቁ፤ ።"
(መዝሙረ ዳዊት 3(4)÷3)


#መልሶቹ ዙሪያ ማንኛውንም ጥያቄ ሀሳብና አስተያየት
👇👇👇👇👇
@Amtcombot
@Amtcombot
ላይ ይላኩልን ::

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ።”
መዝ 4፥3

ብዙዎች እግዚአብሔር በጻድቃን እንደሚገለጥ ባለማወቅ የቅዱሳኑ ነገር የእግዚአብሔርን ነገር በልጦ የሸፈነው ይመስላቸዋል :: ግን ነገሩ እንዲህ አይደለም ውኃን ከጥሩ (ከጠራው) ነገርን ከሥሩ እንዲሉ የጻድቅን ትርጉም በመጀመሪያ በአጭሩ እንመልከት::
ጻድቅ የሚለው ግሥ እውነተኛ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ለብዙ ቁጥር ስንጠቀመው ጻድቃን ብለን ማናበብ እንችላለን እውነተኞች ማለታችን ነው!::
በእውነቱ "ጻድቅ" የሚለውን መቀጽል በመጀመሪያ በተገባ የሚገባው ለልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው :: እግዚአብሔር አምላክ እቀደስ አይል ቅዱስ እጸድቅም አይል ነገር ጻድቅ ነው ጽድቁም እንደ ቅዱሳን የጸጋ (የስጦታ) እንደ ሰይጣንም የሐሰት ሳይሆን ማንም ያልሰጠው ማንም የማይቀማው በባህሪው ጻድቅ እውነተኛ ቅዱስም አምላክ ነው ::“እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ #አምላካችንም_ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።” እንዲል መጽሐፍ 1ኛ ሳሙ 2፥2

ጻድቅ ወይም እውነተኛ ለመሆን በእውነት ማመን ፣ ስለ እውነት መናገር፣ ስለ እውነት ማስተማር፣ ስለ እውነት መኖር ይጠይቃል :: ታዲያ ይህ እውነት ማነው ካልን እግዚአብሔር ነው:: “እኔ መንገድና #እውነት ሕይወትም ነኝ፤ ” ዮሐ14፥6

ከእነዚህ እውነተኞቹ ጻድቃን መካከል የጽላሎሹ ኮከብ የእግዚ አርያ ዐይን ማረፊያ የፀጋ ዘአብ አብራክ የምመናን እረኛ የወንጌል አርበኛ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ግምባር ቀደም ናቸው:: ድካምን በማብዛት እንደ ነቢያት ወንጌልን በማስተማር እንደ ሐዋርያት በመገረፍ እንደ ሰማዕታት መሰለ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር በጻም በድካም ሌት ተቀን ተጉ 22ዓመት በሁለት እግራቸው ከቆሙ በኃላ ከመቆም ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራ ወደቀች በዚህም ለአፍታ ሳይዘናጉ ለ7ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው በትዕግሥት 29 ዓመት በጸሎት ተጋደሉ :: መጻሕፍ “እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን” ያዕ5፥11 ብሏልና " #ብፁህ " አልናቸው :: የሥራዬን ጽናት የሃይማኖቴን ደግነት ግለጥ እያሉ በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ ክርስቶስን ሲሰብኩ ቆይተዋል እንዲያውም በከተታ አውራጃ በዚህ በታመኑለት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲያስተምሩ ሀገሪው ሰምቶ ለዛፍ መስገድን ሊያስቆሙን ነው ከፈጣሪያችን ሊያጣሉን ነው ብለው እንደ አንበሳ ሊውጧቸው ተነሱ አባታችን ግን በልበ ሰፊነት በነገር አሳላፊነት እያለዛዘበ አስተማሯቸው ወደ ቀናች ሃይማኖትም መለሷቸው:: ይህ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ምን ያክል ድንቅ እንደሆነ የሚያመላክት ነው እንጂ የቅዱሳኑ ሕይወት የእግዚአብሔር ነገር ነገረ እግዚአብሔርን የሸፈነ አይደለም ጻድቃን ቅዱሳን “እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፥” የሚሉ ናቸውና 1ኛ ቆሮ1፥23

እንደ ልቤ የተባለውም ቅዱስ ዳዊትም “እግዚአብሔር #በቅዱሳኑ_ላይ_ድንቅ ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤ እግዚአብሔርም ይመስገን።”መዝ 67(68)፥35 ሲል የጻድቃን ሕይወት ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር የተገለጠበት ድንቅም የሚያደርግበት ለሕዝብም ኃይልን የሚያድልበት መሆኑን መስክሮልናል በዚህም ነገር እግዚአብሔር ይመሰገንበታል :: “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” ብሎ ያዘዛቸውም በእነርሱ መልካም ሕይወት የሰማይ አባታቸው እግዚአብሔር ስለሚገለጥበት ነው። ማቴ 5፥16

አንዳንድ አካላት ግን ይህን ባለ መገንዘብ ቤተክርስቲያን ከክርስቶስ ይልቅ ቅዱስ ጳውሎስን ከነገረ እግዚአብሔር ይልቅም ነገረ ቅዱሳንን አስበልጣ ትሰብካለች ይላሉ:: ነገሩ ከፈረሱ ጋሪውን እንደማስቀደም ያለ ነገር ነውና የትም አያደርስም :: ይህ ዓይነቱ አካሄድ የዋልዮሽ አካሄድ በመሆኑ መጨረሻው ገደል ነው:: የዚህ ትምህርት ምንጭም ክርስቶስ ብቻ በቂዬ ነው የምትለው የመናፍቁ ዓለም ጨዋታ ነች :: ለክርስቶስ የተቆረቆሩ በማስመሰል ምርጦቹ ቅዱሳኑን ለማራቅ አያስፈልጉም ለማለት የሚደረግ ዳርዳርታ ነች :: ቅዱሳን ማሰብ በስማቸው ዝክር ማዘከር ስማቸውን መጥራት ገድላቸውን መስማት ማሰማት የተገባ ደገኛ ሥርዓት ነው ሙሽራው ክርስቶስ ብቻ ሳይሆን ሚዜዎቹ ቅዱሳንንም መቀበል ይገባል::
እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማቴ 10፥40-41 መቀበል ከነ ሚዜዎቹ ነው ማነው? እስቲ ከውጪ የመጣ ወዳጁን አንተ ና ወደ ቤቴ ግባ የያዝከው የሻንጣ ገንዘብ ግን ከቤቴ አይገባም ብሎ ወዳጁን ስለ ገንዘቡ አልቀበልም የሚለው? ቅዱሳን የክርስቶስ ገንዘቡ ናቸው :: ያለ እነርሱ ልንቀበለው አንችልም::

“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን #ዋኖቻችሁን_አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”ዕብ 13፥7 እንግዚህ እግዚአብሔር ያከበረውን ማን ያቀለዋል ?
“በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ” ብሎ በቤቱና በቅጥሩ የማይጠፋ የዘላለም የመታሰቢያ ስም የሰጣቸው እራሱ ባለቤቱ ነው ኢሳይ56፥5
እግዚአብሔር ለጻድቃን የሰጣቸው ወይም የሚሰጣቸው ክብር በሕይወተ ሥጋ ብቻ ሳሉ አይደለም ለሞታቸውና ለአጸደ ነፍሳቸውም ጭምር የሚሆን ከብረው የሚያከብሩበት ዘላለማዊ ሥጦታ ጭምር ነው እንጂ:: “የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።” መዝ116፥15

ጻድቁም ወደ ሰማዕታት አደባባይ ሄጄ በስምህ ሰማዕትነትን እቀበል ዘንድ አውዳለውና ያን እንዳደርግ እዘዝ አሉት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መቀዳደምክን ጨረስክ ከሞት በቀር የቀረህ የለም ሁሉን ፈጽመሃል ሞትህንም እንደ ሰማዕታት ሙት አድርጌ እቀበለዋለው አላቸው :: ብዙ ቃል ኪዳንም ከሰጣቸው በኃላ አባታችን ነሐሴ 24 ቀን በ99 ዓመት ከ10ወር 10ቀናቸው ቅዱስት ነፍሳቸው ከቅዱስ ሥጋቸው ተለየች::
#የአባታችን የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት እረድኤት በረከታቸው ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትሁን !::አሜን!

#የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።” ዘኍልቁ 23፥10

.............#ይቆየን..........
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
ነሐሴ 24 ቀን 2012ዓም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፤ ...”

#መዝሙር 4፥3
#እግዚአብሔር_በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፤ ...።”
#መዝ 4፥3