❤ #በዓለ_ወልድ❤
"የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው።የሚኰንንስ ማንነው?የሞተው ይልቁንም በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፤ደግሞም ስለኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።" (ሮሜ 8:34)
ይህ የብርሃነ ዓለም የቅዱስ ጳውሎስ ቃል የቅድስት ቤተክርስትያናችን የሃይማኖት ጸሎት ነው።
በቅድስት ቤተክርስቲያን የምናምነውን እንጸልያለን፤ የምንጸልየውን እናምናለን።በሌላ አነጋገር ሃይማኖታችንን እንጸልየዋለን ፤ ጸሎታችንም ሃይማኖታችን ነው።ሃይማኖት በእግዚአብሔር ማመን፤በእርሱ መታመን ፤ እርሱንም ብቻ ተስፋ ማድረግ ነው።ሃይማኖታችን ራሱ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።ሃይማኖትን የሰጠንም እግዚአብሔር ነው።"ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት" እንዲል (ይሁዳ 1:3)።በመሆኑም ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ሃይማኖት ( በእርሱ ማመንን ) ለሰጠን ለእርሱ በጸሎት መልክ እናቀርበዋለን።ይህንንም የምናደርገው እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበትን ነገር ፍለጋ ነው።"ያለ ሃይማኖት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም"ና (ዕብ 11:6)።
በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ የተመሠረተች የማዕዘኗ ራስ ድንጋይም ኢየሱስ ክርስቶስ የሆነላት (ኤፌ 2:20) ቅድስት ቤተክርስቲያን የሐዋርያው ሃይማኖት ሃይማኖቷ ነውና ትጸልየዋለች።የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይህንን እንዴት እንደምትጸልየው ከመመልከታችን በፊት የቃሉን መልእክት በአጭሩ እንመልከት።
"የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው" ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት "ምስለ ጻድቅ ትጸድቅ" (ከጻድቅ ጋር ጻድቅ ትሆናለህ) ማለትም ለጻድቅ የጽድቁን ዋጋ ትሰጠዋለህ(መዝ 17:25) በማለት እንደተናገረው ለጻድቃን ጽድቃቸውን መስክሮ ዋጋቸው መንግሥተሰማያትን ሰጥቶ የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው።
"የሚኰንንስ ማንነው?" አልመለስ የሚሉትን በሥጋ የሚቀስፋቸው በነፍስ የሚፈርድባቸው ማን ነው? አንድም በርቱዕ ፍርዱ ሥጋንም ነፍስንም በአንድነት በገሃነም የሚቀጣ ማንነው?(ማቴ 10:28)
"የሞተው" በዕፀ መስቀል ላይ ቅዱስ ሥጋውን ከክብርት ነፍሱ በመልካም ፈቃዱ የለየው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።በሞቱ ጊዜም ፈርዷል።በቀኙ የተሰቀለውን ሲያጸድቀው (የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነውና) በግራው የተሰቀለውን ኰንኖታል።ሞቱም መፋረጃ ነው፤በሞቱ ያመኑ ሲድኑ ያላመኑት ግን ይኰነናሉ።
"ይልቁንም ከሙታን ተለይቶ የተነሣው" በኩረ ትንሣኤአችን ሆኖ በባሕርይ ሥልጣኑ ከሞት የተነሣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።በትንሣኤውም ጊዜ ፈርዷል።"እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ።የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ጠላቶቹን በኋላቸው መታቸው የዘለዓለምን ኀሣር ሰጣቸው።"(መዝ 77:65-66) ተብሎ እንደተነገረ የትንሣኤው ተቃዋሚ የሆኑትን አይሁድን፣መናፍቃንንና አጋንንትን ሲፈርድባቸው በአንጻሩ ትንሣኤውን በፍጹም ልባቸው ያመኑትን ሐዋርያትን እስከ ምድር ዳር ድረስ የትንሣኤው ምስክሮች አድርጓቸዋል(ሐዋ 1:8 ና 21-22)የጌታ ትንሣኤውም መፋረጃ ነው።በትንሣኤው ያመኑት ሲድኑ ያላመኑት ግን ይፈረድባቸዋልና።
"በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው" በእግዚአብሔርነቱ ሥልጣን የሚኖር አንድም በአምላክነቱ ከአባቱ እኩል የሆነው ንጉሣችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።እንግዲህ እግዚአብሔር ከሆነ ሥራው ምንድንነው መሥራት መቅጻት፣ማምሸት ማንጋት፣መግደል ማዳን፣ማጽደቅ መኰነን፤ሥነፍጥረትን ሁሉ ማስተዳደር ነው።ይህ ሁሉ የፍርድ ሥራ ይባላል።ሞቱም ትንሣኤውም መፋራጃ የሆነው ከእርሱ ፈራጅነት (እግዚአብሔርነት ) የተነሣ ነው።
"ስለኛ የሚማልደው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" አንድ ጊዜ ፈጽሞ ባቀረባት የዘለዓለማዊ ክህነት አገልግሎት (ለዘለዓለም የሚሆን መሥዋዕት አቅራቢነት) ያዳነን ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"የሚማልደው" የሚለው ቃል በትንቢት አንቀጽ (future tense) ቢጻፍም የሚገልጸው ግን የተፈጸመን ድርጊት ነው።እንዲህ ያሉ አገላለጾች በቅዱሳት መፃሕፍት ይገኛሉ።ለምሳሌ"ሕፃን ተወልዶልናልና" ተብሎ የተነገረው ወደፊት ስለሚወለደው አምላካችን ነው።"እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ"(መዝ 109:4) ተብሎ የተነገረለት አምላካችን የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅ ይፈርድ እንደነበር ለዘለዓለሙ የሚፈርድ ነው።ይህች የክህነት አገልግሎቱም መፋረጃ ናት።በዚህ የዘለዓለም ክህነት አገልግሎቱ የሠዋውን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የተቀበለ ሲድን ያልተቀበለ ግን ይፈረድበታልና። ይህ ሁሉ በጥቅሉ የሚያጸድቅም የሚኰንንም እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ማለት ነው።ሞቱም፣ትንሣኤውም፣ዳግም ምጽአቱም በቅድስት ቤተክርስቲያን በዓላተ ወልድ (የወልድ በዓላት) ናቸው።
የካቲት 29/2016 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ