ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
“ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን #ቅዱሱን_የእግዚአብሔርን_መንፈስ አታሳዝኑ።”
| ኤፌሶን 4፥30

መቼም በዚህ በ ቲክ ታክ ዘመን እረጅምና ዝርዝር ጉዳዮችን መጻፍ እንደሞኝነት ሳይቆጠር አይቀርም ። አንድና ወጥነት ያለው ዘለግ ያለ ነገር ላይ ከመቆየት ይልቅ አጠር አጠር ያሉ ነገሮችን ለረጅም ጊዜ መከታተል የሚመረጥበት ወቅት ላይ ነን ስለዚህ ብዕሬን በአጭሩ ለማስታጠቅ እወዳለሁ።
#እግዚአብሔር_መንፈስ_ቅዱስ በየዋህቱ እርግብ ይመሰላል። እርግብ ቤት ሰርታ ከምትኖርበት ቦታዋ የፈለገ በደል ቢደርስባት ለቃ አትሄድም በድንጋይ ወርውረው ቢመቷት፣ እንቁላሎቿን ቢያፈርጡባት፣ ጫጭቶቿን ቢገሉባት ከመኖሪያዋ ጎጆ ወዴትም አትሄድም ። ሳይሰማት ሳያማት ሳይቆረቁራት ቀርቶ አይደለም የዋህ ስለሆነች ነው ። ነገር ግን ቤቷን መኖሪያዋን ያፈረሱባት እንደሆነ ላትመለስ እስከወዲያኛው ትሄዳለች።
መንፈሰ እግዚአብሔርም እንዲሁ ነው። #በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም አምነን አንድ ጊዜ በአርባና በሰማንያ ቀናችን ተጠምቀን ማደሪያ ቤቱ ካደረገን በኋላ መቼም መች ከኛ አይለይም። በአልዮ፣ በነቢብ ፣በገቢር ኃጢያት ብናሳዝ ነው ፤በምግባራችን ብናስከፋው ከቶ ከኛ አይርቅም። ነገር ግን አናውቅህም ብለን ከካድነው መቅደሱን ሰውነታችንን በክህደት ካፈረስንበት እንደ እርግቢቱ ጨርሶ ይለየናል።

ብዙዎች በራልን ተገለጠልን እያሉ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነውን በጥምቀት የከበረውን ቤተ ልቦናቸውን እያፈረሱ ከመንፈስ ቅዱስ ተለይተው ከፀጋ ተገፈው እንዲሁ ሲባዝኑ ማየት እየተለመደ መቷል። ድሮ ተናግረው አይደለም ገና ሳይናገሩ ሀሳባቸው የሚገባን ሳይቀልዱ የሚያስቁን በዐይናችን ፊት በሞገስ የሚገዝፉብን የጥበብ ሰዎች ዛሬ ግን ሁሉ ቀርቶ ብዙ አውርተው ጥቂቱ ንግግራቸው እንኳን የማይገባን ቀልደውልን ከማሳቅ ይልቅ የሚያናድዱን ግርማ ሞገሳቸው እርቆ ጥላ ቢስ የሆኑብን ብዙዎች እየመጡ ነው። ከነዚህ ሰዎች አንዱ አርቲስት #ሸዋፈራው_ደስአለኝ አንዱ ነው።
ሸዋን የወንዶች ጉዳይ ፣ ያረፈደ አራዳ ....ወዘተ በሚሉ ቆየት ባሉ ሥራዎቹ አስታውሰዋለው በጣም ከምወዳቸውና ከማከብራቸው ተዋንያን ግንባር ቀደሙ ነው ። ፌሽዋል ኤክስፕሬሽን የቃላት አጠቃቀም የድምጽ አወጣት ገጸ ባሕሪን መስሎ ሳይሆን ሆኖ የመጫወት ብቃት ያለው ባለ ግርማ ሞገስ ሙያተኛ ነበር ። ከጥቂት ግዝያት በኋላ ግን ያ ሁሉ ጠፍቶ ቀልዱ የማያምር ትወናው የሚያቅር ንግግሩም የሚያሳፍር እየሆነ መጣብኝ ምን እንደተፈጠረ በትክክል ባይገባኝም ዝም ብሎ ብቻ ከድሮው ቦታው እየወረደ እንደሆነ ይሰማኝ ነበር። ጌታን የተቀበለ ጴንጤ እንደሆነ ስሰማ ለዛ ይሆን ለዛውን የጣብኝ እያልኩ አስብ ነበር ፤ ከሰሞኑ ግን ከተራ ምዕመንነት አልፎ በፖስተር ደረጃ ሲሰብክ ሳይና ስሰማ ግን በእርግጥም የለዛ ቢስነቱ ምንጭ ከአርባ ቀኑ ማዕተብ ከቅዱሱ መንፈስ መለየቱ መሆኑ በእርግጥም ገባኝ።

አስቀድሜም እንዳልሁ አሁንም ደግሞ እላለሁ “ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን #ቅዱሱን_የእግዚአብሔርን_መንፈስ አታሳዝኑ።”
|ኤፌሶን 4፥30

አ.አ ኢትዮጲያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
የካቲት 27/2017 ዓ.ም