Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
YouTube
የኪዳን ጸሎት መቅደም ትርጓሜ በአቡነ ሰላማ | Abune Selama | kidan tirguwame | ortodox tewhdo sibket 2023 | EOTC
አቡነ ሰላማ
የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ
ዜና ህይወቱ ለብፁዕ አቡነ ሰላማ (የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ)
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኀንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ስሙ በዓታ ለማርያም በተባለው ፲፱፴፬ ዓ/ም ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ ሀገራቸው ንባብና የቃል ትምህርት በሚገባ…
የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ
ዜና ህይወቱ ለብፁዕ አቡነ ሰላማ (የብፁዕ አቡነ ሰላማ አጭር የሕይወት ታሪክ)
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከአባታቸው ከአቶ ገብረ ሥላሴ ገ/መድኀንና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ ልዩ ስሙ በዓታ ለማርያም በተባለው ፲፱፴፬ ዓ/ም ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በትውልድ ሀገራቸው ንባብና የቃል ትምህርት በሚገባ…
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
+++ ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች! +++
“ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” (ኢሳ7፥14)
አማኑኤል "እግዚአብሔር ምስሌነ - እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ" የሚል ትርጉም እንዳለው መልአኩ ለቅዱስ ዮሴፍ ነግሮታል፡፡
+ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ ማለት ምን ማለት ነው ? +
እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ተለይቶ አያውቅም ሁልጊዜም በረድኤት በቸርነት በጠብቆት በመግቦት ከፍጥረቱ ጋር ነበረ አሁንም አለ፡፡ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ "እግዚአብሔር ከኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል እግዚአብሔር ከኛ ጋር ባይሆን ጠላቶቻችን በተነሡብን ጊዜ አለን አለን ስንል እንደ ጥህሎ በዋጡን እንደ እንቅትም በጠጡን ነበር።'' ብሎ መዘመሩ እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ፍጹም እንደማይለይ ያስረዳናል፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ የሚለው አማኑኤል የሚለው ስም ትርጉም ምን ያሳየናል? ቢሉ አካላዊ ቃል ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስን ነሥቶ ከኛ ጋር በተዋሕዶ አንድ መሆኑን በኩነተ ሥጋ (ሰው በመሆን) መገለጡን ያስረዳናል፡፡ (መዝ 123:1-3፣ ኤፌ 2:14-16) ቅዱስ ዮሐንስ "ቃል ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትን ተመልቶ በኛ አደረ አንድ ልጅም በአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር ክብሩን አየን፡፡" ማለቱሞ ለዚህ ነው፡፡ (ዮሐ 1:14-15)
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም መለኮት ከኛ ጋር የሆነባት ታላቅ ምሥጢር የተገለጠባት የአካላዊ ቃል መዲና መገለጫ ናት፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ተወልዶ ከኛ ጋር ሆነ በዓይናችን አየነው እጆቻችንም ዳሰሱት ከኛም ጋር ተመላለሰ። በዚህም "አምላክ የለም" የሚሉ ሰነፎች ስንፍናቸው ምክንያትን አጣ፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ የእርሱን ክብር አይቷልና። (1ዮሐ 1:1-3፣ ኢሳ 40:1-5)
ከኛ ጋር ሆኖ የቁስአካላውያንን (Materialists) ክሕደት ስላጠፋም "ማንም ሰው ያላደረገውን ተአምራት ባላደርግ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበረ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል፡፡" በማለት ተናገረ:: (ዮሐ15:24) ቅዱስ አማኑኤል ፈጣሪያችን ሀገራችንን ከጥፋት ይጠብቅልን!!!
መምህር ቢትወደድ ወርቁ
መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ ም

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🛑አዲስ ዝማሬ🛑 " ታቦተ ሥላሴ "
በዘማሪ ክብሮም ግደይ /ዘደብረ አሚን/
😲😲😲 በቅርብ ቀን ይጠብቁን❕❕❕😲😲😲
በዘማሪ ክብሮም ግደይ /ዘደብረ አሚን/
😲😲😲 በቅርብ ቀን ይጠብቁን❕❕❕😲😲😲
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
“ስለ እናንተ ሲያማልዱ፥ በእናንተ ላይ ከሚሆነው ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ይናፍቁአችኋል።” (ቅዱስ ጳውሎስ 2ኛ ቆሮ 9፥14)
--------------------------------
☞ ጻድቃን "አያማልዱም" የሚለውን ክርክር ተወውና የዘፍጥረትን መጽሐፍ ገልጠህ ፈጣሪህን ጠይቅ። ደጋጎች አይደለም ማልደው ለጥፋት በተዘጋጀች ከተማ ቢኖሩ እንኳን በከተማይቱ ስለመኖራቸው ብሎ ምሕረትን ያወርዳል።
☞ እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን በኃጢአታቸው ምክንያት በእሳትና በዲን አቃጥሎ ከመቅጣቱ አስቀድሞ ለወዳጁ ለአብርሃም "እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን? አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፥ የምድር አሕዛብም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና። ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።" ካለ በኋላ "የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥ እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸትዋ አድርገው እንደ ሆነ ወርጄ አያለሁ፤ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ።" በማለት ነገረው። ይህ ነገር በእግዚአብሔር የተነገረው አብርሃም ደጋግሞ ምን ብሎ እንደጸለየ ታስተውላለህን? "አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?"….... ዳግመኛም "ከአምሳው ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማይቱን ሁሉ በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን? "… ሦስተኛም "ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ፤ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?… አራተኛም፦ "እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፤ ምናልባት ከዚያ አሥር ቢገኙሳ?" አለ።" ቅዱሱ ሰው አብርሃም በመጨረሻ የጸለየውን ጸሎት ልብ በል "በእነዚህ በሁለት ታላላቅ ከተሞች አሥር ጻድቃንን ብታገኝ አትምርምን?" የሚል ነው። እግዚአብሔር ምን ብሎ የመለሰ ይመስልሃል? "አምሳ ሳይሆን አሥርም ጻድቃን ባገኝ እምራለሁ!!!" (ዘፍ 18:17-25)
☞ እስቲ ልጠይቅህ ዛሬ ግብረ ሰዶማዊነት የት ደርሶዋል? በደጅህ አልደረሰምን? ለቀደሙት ስለገባው ቃልኪዳን ታግሦዋል እንጂ ሰዶማውያኑ በጠፉበት ግብረ ሰዶም ዓለሙ ይጠፋ እንደነበር የታወቀ ነው። ጠቢቡ ሰሎሞን “ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል።” (ምሳ 29፥2) ብሎ ለምን ተናገረ? በጻድቃን ብዛት ሀገር እንደምትድን በተረዳ ነገር ስላወቀ አይደለምን?
☞ የጻድቃን ልመና ብቻ ሳይሆን መኖር እንኳን ከጥፋት ይታደግሃል። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።” ብሎ በምሥጢረ ምጽዓት ትምህርቱ እንዳስተማረ። (ማቴ 24፥22) እግዚአብሔር ለወዳጆቹ በሚገባው ቃልኪዳን ቁጣውን በምሕረት በትእግሥት እንደሚለውጥ መከራውን እንደሚያሳጥር ይህ የጌታ ቃል ምስክር ነው። ዓለም አልገባውም እንጂ ሐሳዊ መሲሕ የሚሠለጥንባቸው እነዚያ አስጨናቂ ወራት እንኳን የሚያጥሩት በጽኑ እምነታቸው በቀና ምግባራቸው እርሱን ላስደሰቱት ወዳጆቹ በገባው ቃልኪዳን ነው።
መድኅን ዓለም ክርስቶስ ሕያዋን ቅዱሳኑን "ሙታን" ለሚሉ ሰዱቃውያን “እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።” ብሎ የተናገረውን ቃል ልብ በልና ሙታን እንደሌሉን አውቀህ ወደ ሕይወት የተሻገሩበትን የዕረፍታቸውን ቀን እንደ ዳዊት “የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።” (መዝ116፥15) እያልክ እየዘመርክ አክብር። (ማቴ 22፥31-32)
እባክዎን ቃለ እግዚአብሔርን በማጋራት ለወዳጆችዎ ያድርሱ።
መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ጥቅምት 05 ቀን 2016 ዓ ም

++ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ! ++ (መዝ 91:13)
☞ ሞተ ሥጋ ሳያገኛቸው እግዚአብሔር የሠወራቸው ብዙ ቅዱሳን አሉ። ከነዚህም መካከል ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ አንዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ ሰው ሄኖክ ሞት ሳያገኘው የተሰወረበትን ምክንያት ሲገልጽ “ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና።” ይላል አካሄድን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ እስከምን እንደሚያደርስ ተመልከት። (ዘፍ 5፥24) አካሄዳቸውን ከእርሱ ጋር ባደረጉ ወዳጆቹ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ቸርነትና ከኃሊነት ተገልጦአልና ነቢዩ “እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ።” በማለት ተናገረ። (መዝ 4፥3) በቅዱስ ሰው ሃይማኖት፣ በጎ ምግባርና መልካምነት ኢየሱስ ክርስቶስ ይገለጣል እንጂ አይሸፈንም።
☞ ከቅዱሱ ሰው ከሄኖክ ሌላ ቀናተኛው ነቢዩ ኤልያስም ሞት ሳያገኘው በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ተነጥቆዋል። ይህንም መጽሐፍ ሲነግረን “ሲሄዱም፦ እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።” ከነቢዩ ጋር የነበረ ይህን የተመለከተና ለእግዚአብሔር የተገዛ ኤልሳዕም የነቢዩ ኤልያስ በረከት አድሮበት ተመሷል። (2ኛ ነገ 2፥11) መጽሐፍ በቅድስናቸው ለዚህ የበቁ እንዳሉ ሲነግርህ ዕፁብ ድንቅ ብለህ ማመን ማሰብም አንተንም ለክብር ያበቃሃል። ክርስቶስን በእነርሱ ሕይወት ትመለከተዋለህ እንጂ አይሠወርብህም። እንዲያም ባይሆን “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።” ባላለህም ነበር። (ዕብ 13፥7)
👇ይቀጥላል 👇
https://tttttt.me/zdk24_5_21_official

---የቀጠለ---
☞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከደቀመዛሙርቱ መካከል ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የሥጋ ሞት እንደማያገኘው ደጋግሞ ፍንጭ ሰጥቶ ነበር። በዚህም ቃሉ መሠረት ወንጌላዊው እንደተሠወረ የቤተክርስቲያን ታሪክ ይመሰክራል። (ማቴ 16:28፣ ዮሐ 21:23)
☞በዚህ መልኩ የተሠወሩ ቅዱሳን እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም። እግዚአብሔር የዘመናት ባለቤት ነውና በየዘመኑ እንዲህ አይነቱን የቸርነቱን ሥራ የሚሠራላቸው የሠራላቸውም ብዙ ወዳጆቹ አሉ። ከእነዚህም ወዳጆቹ በመለካውያን ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ ምድር መጥተው የነበሩት ጻድቁ አቡነ አረጋዊ አንዱ ናቸው። እንደ ሄኖክ አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር አድርገዋልና እግዚአብሔር ከሞተ ሥጋ ሰውሮ ወስዷቸዋል። ጻድቁ አቡነ አረጋዊ አምላካችን እግዚአብሔር "በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።" በማለት አስቀድሞ የተናገረው ቃል እንዲሁም በኋለኛው ዘመን ጌታችን “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤....... እባቦችን ይይዛሉ፥” ብሎ የተናገረው ቃል በተግባር የተፈጸመባቸውና የተፈጸመላቸው ጻድቅ ናቸው። (ማር16፥17፣ መዝ 90:13) ልዑል አምላክ ክርስቶስ ከወዳጆቹ የምንደመርበትን መልካም ሥራ ለመሥራት ያብቃን!!
ቢትወደድ ወርቁ
ጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ ም

Forwarded from ተመስገን አምላኬ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ጥቅምት 20
የታላቁ ነብይ የኤልያስ ደቀመዝሙር የነብዮ ኤልሳዕ
በዚችም ቀን የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ የሆነ የታላቁ ነቢይ የኤልሳዕ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው
በዓሉም በእንጦጦ ቅዱስ ራጉኤል ወቅዱስ ኤልያስ ይከበራል!
በመጽሐፈ ካልዕ ነገስት 2:1 ጀምሮ ታሪኩ እንደተገለጸው
ኤልሳዕ በ12 ጥማድ በሬ ከሚያርስበት ማሳ ላይ የተጠራ 12ቱንም በሬዎቹን አርዶ በአካባቢው የነበሩትን አብልቶ የሚጎትተው ሀብት የሚሳሳለት ንብረት እንዳይኖረው አርጎ የእግዚአብሔር ጥሪ በነብዩ ኤልያስ በኩል ተቀብሎ
ኤልያስን የተከተለ ነብይ ነው
ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ሲነጠቅ በእሱ የነበረ መንፈስ ሁለት እጥፍ ሆኖ ያረፈበት ታላቅ አባት ነው (ነብዩ ኤልሳዕ
የኢያሪኮም ሰዎች ኤልሳዕን ጌታችን እንደምታያት የዚች አገር ኑሮዋ ያማረ የተወደደ ነው የአገሩ ውኃ ግን ክፉ ነው ሴቶች ሲጠጡት ይመክናሉ አሉት ኤልሳዕም ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ አላቸው እነርሱም አመጡለት።
ኤልሳዕም ወደ ውኃው ምንጭ ሒዶ ያንን ጨው በውስጡ ጨመረውና እግዚአብሔር እንዲህ አለ እርሱን ከመጠጣት የተነሣ የሚሞት እንዳይኖር የሚመክንም እንዳይኖር ይህን ውኃ ለውጥኩት አለ አላቸው።
ከዚያችም ቀን በኋላ ኤልሳዕ እንደተናገረ እስከ አሁን ድረስ ያ ውኃ ተለወጠ የዚህ የነቢይ ኤልሳዕ ተአምራቱ ብዙ ነው የሶርያውን ሰው ንዕማንን ከለምጹ ያነጻው እርሱ ነው ሁለት ሙታንን አንዱን በሕይወት ሳለ ሌላውንም ከሞተ በኋላ አስነሥቷል የትንቢቱንም ወራት ፈጽሞ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ኤልሳዕ ጸሎት ይማረን በረከቱና ረድኤቱ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ "አሜን"
ከዕለቱ ስንክሳር

+ ጨለማን አስወግዶ በዓለም ላይ ያበራ ፀሐይ +
“በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።” አለ :- የጽድቅ ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ (ማቴ 13፥43)
የመልክዐ ተክለሃይማኖት ደራሲ በመልክዑ አርኬ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን "ቅዱስ አባት ሆይ አምልኰተ ጣዖት ጨለማን አስወግደህ በዓለም የምታበራ ፀሐይ አንተ መዓዛህ የተወደደ ደብረ ከርቤን ነህ? ወይስ መሠወር የማይቻላት ደብረ ጽጌን ነህ? " በማለት ያመሰግናል፡፡ ቅዱሳን ነቢያት ሐዋርያት እንዲሁም በየዘመኑ የተነሡ መምህራን ዋና ተልዕኮ ጣዖት አምልኰን በቃለ ወንጌል ማስወገድ ነው፡፡ በሰዎች ዘንድ የሚታይ የሚዳሰስ ጣዖት አለ፡፡ እንዲሁም የማይታይ የማይዳሰስ ልብም የማይባል ረቂቅ ጣዖትም አለ፡፡
በኑሯችንና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ልብ ሳንላቸው ከእግዚአብሔር አስቀድመን ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች ሁሉ ሳናውቃቸው ጣዓታት እንደሆኑብን ልናስተውል ይገባናል፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን በየዘመናቸው ከሰዎች ልቡና የሚታዩትንም ሆነ የማይታዩትን ጣዖታት በቃለ እግዚአብሔር ሲያጠፉ ኑረዋል፡፡ በዚህም በነቢዩ ዳንኤል የትንቢት መጽሐፍ "ጥበበኞቹ እንደሰማይ ፀዳል ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ፡፡" (ዳን 12፡4) ተብሎ ትንቢት ተነግሮላቸዋል፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በገድላቸው እንደተጻፈልን በዘመናቸው ጣዖታትን አጥፍተዋል፡፡ በጣዖታቱ ላይ አድረው ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጃቸውን ሰዎች ሲያታልሉ የኖሩትንም እኵያን አጋንንት በወንጌል ትምህርት ሲያሳፍሩና ሲበቀሏቸው ኑረዋል፡፡ በዚህም ለብዙዎች ብርሃን ሆነዋል፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ምን ያህል ጣዖታትን እንዳጠፉ ስንቶችን ከጣዖት አምልኰ እንዳላቀቁና አጋንንትን በወንጌል ትምህርት እንዴት እንዳወጡ ለመረዳት ገድላቸውን በእምነት ሆኖ ማንበቡ ተገቢ ይሆናል፡፡ ይኽን በሕሊናችን እንያዝና በዚህ ክፍል ጻድቁ የተገለጡበትን የምስጋና ቃል እንመልከት፡፡
+++ ተክለሃይማኖት ፀሐይ +++
በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጻፈልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ብርሃን ፀሐይ ተብሏል፡፡ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት "እግዚአብሔር ብሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማነው?" (መዝ 26፡1) በማለት ዘምሯል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም፡፡" (ዮሐ 8፡12) በማለት አስተምሯል፡፡ ጌታችን ጨለማ ያለው እርሱን አለማወቅ እንደፈቃዱ አለመመላለስ በኃጢአትና በክሕደት መኖርን ነው፡፡ (ሮሜ 13፡11-13) ብርሃን የተባለ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በእምነት ጸንተው በምግባር ቀንተው በትሩፋት አጊጠው እንደፈቃዱ የተመላለሱትንና ያገለገሉትን ወዳጆቹችንም ብርሃናት መሆናቸውን "እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ" በማለት መስክሮላቸዋል፡፡ ጌታችን ወዳጆቹ የዓለም ብርሃን የሚባሉት ብርሃን ሲሆኑ መሆኑን ሲናገርም "መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡" (ማቴ 5፡14-16) ብሎዋል፡፡ በመነሻችን እንደተመለከትነው ጻድቁ ጨለማ ጣዖትን በማስወገድ ለዓለም ብርሃን ሆነዋል፡፡ ሰዎች ልቡናቸውን ከጣዖታት መልሰው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩትም ምክንያት ሆነዋል፡፡ በመሆኑም ደራሲው የጌታችንን ቃል ይዞ ጻድቁን "ብርሃን ፀሐይ" በማለት አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን "መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ፡፡"(ያዕ 1፡17-18) በማለት የብርሃናት አባት ብሎ ጠርቶታል፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ብርሃናት ብሎ የጠራቸው የብርሃን ክርስቶስ ልጆች ወዳጆቹ ቅዱሳን መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ አምልኮ ጣዖትን እንዲያስወግዱ ኑፋቄንና ክሕደትንና እንዲያጠፋ የሰዎች ልጆችን ሕይወት በቅዱስ ቃሉ አማካኝነት እንዲያርሙና እንዲያስተካክሉ ወደ ዓለም የተላኩ ቅዱሳን ነቢያት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት በኋላ ዘመን የተነሡ ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ "እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ እግዚአብሔር አዞናል፡፡" በማለት በአንድ ቃል ተናግረዋል፡፡ (የሐዋ 13፡47) ቅዱሳን ጨለማ (ኃጢአት) በሞላው በሰው ልቡና ብርሃን ክርስቶስን የሚያበሩ ብርሃናት መሆናቸውን ትመለከታላችሁን? ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የንስሐ ስብከትን እየሰበከ የንስሐ ጥምቀትን እያጠመቀ በመንገድ የተመሰለ የሰውን ልቡና እያስተካከለ የተቀበለውን መጥምቁ ዮሐንስን "የሚነድና የሚያበራ ብርሃን" ብሎ ጠርቶታል፡፡ (ዮሐ 5፡35) መጥምቁ ዮሐንስ በጌታችን አንደበት የሚነድና የሚያበራ መብራት ተብሎ ስለምን ተመሰገነ? ወንጌልን በመስበኵ ጣዖታትን በማጥፋቱ ሰዎችን ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን በመመለሱ አይደለምን? ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፍቅር ነድደው ሰይጣንን ድል ነሥተዋል፡፡ በሕይወታቸው ክርስቶስን አብርተው በሰው ልቡና ነግሦ የነበረውን ጨለማ ኃጢአት ደርምሰዋል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጽድቅ (የእውነት ፀሐይ) እንደሆነ መንገዱን የተከተሉ ወዳጆቹም ፀሐይ ሆነው ፀሐይ ተብለዋል፡፡ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዘሪውን ምሳሌ ባስተማረበት ክፍል "በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ፡፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ፡፡" (ማቴ 13፡44) በማለትም ጭምር አስተምሮዋል፡፡ እርሱ መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሐይ ሲሆን ወዳጆቹ ደግሞ ጨረቃ ናቸው፡፡ ጨረቃ ብርሃንን የምታገኘው ከፀሐይ እንደሆነ ቅዱሳንም ጸጋን ክብርን ሥልጣንንም ያገኙት ከክርስቶስ ነውና ጌታችን "እንደ ፀሐይ ይበራሉ፡፡" ብሎ አስተማረ፡፡ እንግዲህ በቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔርን ተከትለው ጨለማ ጣዖትን ያጠፉ ደጋግ አባቶችና እናቶች ብርሃናት ፀሐይ ከዋክብት መባላቸውን ስንመለከት ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን ብርሃን ፀሐይ ብለን እንጠራቸዋለን እንጂ በጥርጥር መንፈስ ሆነን እንዴት? ለምን? ብለን አንጠይቅም፡፡
©️ መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ ም

#መልከአ_ተክለሃይማኖት
#ሰላም_ለአክናፊከ
በቀኝ ጉንህ ሦስት በግራ ጉንህ ሦስት ሆነው ለሠረፁት ፮ቱ አክናፎችህ ሰላም እላለሁ
#ቅዱሱ_አባት_ሆይ
እኔ ልጅህ የአንተን በረከት እፈልጋለሁና የቀን ጉዳይ ጥሎኝ ለእርዳታ በምፈልግህ ጊዜ በነዚያ በክንፎችህ ፈጥነህ ድረስልኝ ።

Forwarded from Zemari Samuel Tekle Official || ዘማሪ ሳሙኤል ተክሌ
YouTube
@ አዲስ መዝሙር ''ትናንትናን ተሻገርኩኝ'' ዘማሪ ሳሙኤል ተክሌ ethiopian mezmur ortodox @-mahtot @21media27
ይህ የዩቲዩብ ቻናል የእኔ የዘማሪ ሳሙኤል ተክሌ መንፈሳዊ ቻናል ሲሆን በዚህ ቻናል ላይ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ስርዐት፣ ዶግማ እና ቀኖና በጠበቀ መልኩ የምሰራቸውን ያሬዳዊ ዝማሬዎች ወደ እናንተ አደርሳለሁ።
ሰብስክራይብ፣ ላይክና ሼር በማድረግ ቤተሰብ እንድትሆኑ እጋብዛለሁ!!!
" ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን!!!"
This YouTube channel is the spiritual channel…
ሰብስክራይብ፣ ላይክና ሼር በማድረግ ቤተሰብ እንድትሆኑ እጋብዛለሁ!!!
" ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን!!!"
This YouTube channel is the spiritual channel…
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
YouTube
🛑 አዲስ ዝማሬ "መድኃኒቴ" | ዘማሪ ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) ◈ New Mezmur "Medhanite" D Zelalem Takele Zegola
#newmezmur #orthodox_mezmur #zelalem #zemari_zelalem #zegola #medhanite #ዘማሪ_ዘለዓለም #ዲያቆን_ዘለዓለም #መድኃኒቴ #መድኃኔዓለም #like #share #subscribe
MD | የእርዳታ ጥሪ ቀሲስ ፍስሐ አስማረ
1000587474208 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
171101103480311 አባይ ባንክ
163933217 በአቢሲንያ ባንክ
የሂሳብ ቁጥር ስም :- ፍስሐ አስማረ ዘለቀ / ፋንቱ ምህረቴ
በአሁኑ ወቅት ባደረባቸው የአንጀት ካንሰር በሽታ እየተሰቃዩ ሲሆን ይህንንም በሽታ በከፍተኛ ሕክምና ለመከታተል እስከ ብር 3,000,000 /ሦስት ሚሊየን ብር/ ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል
የደብራችን መደበኛ አገልጋይ የሆኑት ቀሲስ ፍስሐ አስማረ በደብሩ በጊዜያዊነት ከነሐሴ 3 ቀን 1992 ዓ.ም ጀምሮ ከተቀጠሩ በኋላ ያላቸው የሥራ ትጋት ታይቶ ከግንቦት 11 ቀን 1993 ዓ.ም ጀምሮ በቋሚነት በዲቁና እና በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው በማገልገል ላይ እያሉ ባላቸው ብቁ የቤተ ክርስቲያን ሙያ ከህዳር ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ በሊቀ ዲቁና ኃላፊነት የሥራ መደብ ሲያገለግሉ ቆይተው ከህዳር ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በቅስና የሥራ መደብ ተመድበው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡
ቀሲስ ፍስሐ አስማረ በቅስና ሥራ ብቻ ሳይወሰኑ በማህሌት አገልግሎትም ብቁ ችሎታ ያላቸው በመሆኑ ሰፊ አገልግሎት የሚሰጡ ወንድም ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት ባደረባቸው የአንጀት ካንሰር በሽታ እየተሰቃዩ ሲሆን ይህንንም በሽታ በከፍተኛ ሕክምና ለመከታተል እስከ ብር 3,000,000 /ሦስት ሚሊየን ብር/ ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል

🛑 አዲስ ዝማሬ "አብሣሬ ድንግል" ዘማሪ ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) ◈New Mezmur "Absare Dingel " D Zelalem Takele Zegola
#newmezmur #orthodox_mezmur #zemari_zelalem #zegola #አብሣሬ_ድንግል #Absare_Dingel #like #share #subscribe #ገብርኤል #ቅዱስ_ገብርኤል