ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
የሐምሌ ፀሐዮች

"በሐምሌ ልኑር እንዳመሌ" ይባላል ምነው ቢሉ ላዮ ውኃ ታቹ ጭቃ የሚሆንበት ከባድ የዝናብ ጊዜ ነውና ጣራው የሚፈስበት ቤተኛ ይልቁኑ ላጤ መኝታው ላይ ሲያፈስበት መኝታው ጋር በጆክ ይደቅናል ማብሰያው ጋር ሲያፈስበት በባሊው ይደቅናል መመገቢያው ጋር ሲያፈስበት በሳፋ ይደቅናል ስለዚህ ሁሉም ቤተኛ በሐምሌ እንደ አመሉ ይደቃቅናል። ይህ ነው ልኑር እንዳመሌ ያሰኘው። ሐምሌ እንዲ ያለች አስቸጋሪ የዝናብ ወቅት ሆና ሳለ ብሩሃን ከዋክብት የሚባሉ ጻድቃንም በዚህች በአሰቃቂ ወቅት እንኳ ሆነው ብርድና ቁሩን ሳይሰቅቁ አንገታቸውን ለሰይፍ ሰውነታቸውን ለእሳት አሳልፈው የሚሰጡ የሐምሌ ፀሐዮች ናቸው ። እንደነማን ቢሉ እንደ ቅዱስ ጳውሎስና እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ያሉ ቅዱሳን።
ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ አስፈሪ የሆነ የሐምሌ ጨለማ የነበረ ገዳይ የኦሪት ምርኮኛና የወንጌል ጠላት የክርስቲያኖች አሳዳጅ ነበር። በደማስቆ ከተማ በድንቅ አጠራር ከተጠራ በኃላ ግን የሐምሌ ጨለማው ሳዑል የሐምሌ ፀሐይ ለመሆን በቃ። በአሕዛብ ዘንድ ስሙን የሚሸከም እንደራሴ ሆነ።
ቅዱስ ጴጥሮስም ከውኃ ውጪ የተወለደ ዓሣ ለማለት በሚቻል ሆኔታ በጥብርዲያኖስ ባሕር አጠገብ የተወለደ ዋናና አሳ ማጥመድ ብቻ የሚያውቅ በባላአብቶች ስም መረብ እየጣለ የሚተዳደር ምስኪን የኔ ቢጤ ነበር ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ተከተለኝ ብሎ በጠራው ጊዜ የሐምሌ ፀሐይ ብርሃነ ዓለም ለመባል ታጨ:: አንባቢ ሆይ የሐምሌ ፀሐይ ውድና ብርቅ ናት ምክንያቱም ሐምሌ ብርቱ የዝናብ እና የቅዝቃዜ ጊዜ ናትና አንተም ውድና ብርቅ ትሆን ዘንድ ሰው በበዛበት ለመታየት ብለ አትባዝን ይልቁኑ ሰው ሲጠፋ ሰው ሆነህ ተገኝ።
የጽድቅ ፀሐይ ላሎጣባት ሐምሌ ለሆነችና ከእውነት ጋር ለተፋቻች ለላጤ ቀዳዳ ሕይወታችን በተቀደደው በኩል እየቆሙ እኸሁ የሐምሌ ፀሐዮች ቅዱሳን ናቸው።
#በረከታቸው ትደርብን!
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
አ.አ ኢትዮጵያ
ሐምሌ 05/2014 ዓ.ም