ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#ረዓብ (ራኬብ)

#በብሉይ ኪዳን ረዓብ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ "ራኬብ "በመባል ትታወቃለች ነሮዋ አሮጊቷ ከተማ በምትባለው በሰባት ግንቦች በታጠረችሁ ኢያሪኮ በተባለችሁ ከተማ ነው ::

የነዌም ልጅ ኢያሱ ሄዳችሁ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ። ሄዱም፤ ረዓብም ወደሚሉአት ጋለሞታ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። የኢያሪኮም ንጉሥ፦ እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ ሲባል ወሬ ሰማ። የኢያሪኮም ንጉሥ፦ አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ።

#ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸገቻቸው፤ እርስዋም፦ አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጡ፥ ከወዴት እንደ ሆኑ ግን አላወቅሁም ፤ በሩም ሲዘጋ ሲጨልምም ሰዎቹ ወጡ፤ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፤ፈጥናችሁ አሳድዱአቸው፥ ታገኙአቸውማላችሁ አለች።

እርስዋ ግን ወደ ሰገነቱ አውጥታቸው ነበር፤ በዚያም በረበረበችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሽጋቸው ነበር።ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው፤ እሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተቈለፈ።እነዚህም ሳይተኙ ሴቲቱ ወደ እነርሱ ወደ ሰገነቱ ወጣች። ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን እንደ ሰጣችሁ፥ እናንተንም መፍራት በላያችን እንደ ወደቀ፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደ ቀለጡ አወቅሁ።

#ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።ይህንም ነገር ሰምተን ልባችን ቀለጠ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተንሣ ከዚያ ወዲያ ለማንም ነፍስ አልቀረለትም።

አሁንም፥ እባካችሁ፥ በእግዚአብሔር ማሉልኝ፥ በእውነትም ምልክት ስጡኝ፥ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደ ሠራሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድትሠሩ፥ አባቴንና እናቴንም ወንድሞቼንና እኅቶቼንም ያላቸውንም ሁሉ እንድታድኑ፥ ሰውነታችንንም ከሞት እንድታድኑ።

#ሰዎቹም፦ ይህን ነገራችንን ባትገልጪ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ ለሞት ይሆናል፤ እግዚአብሔርም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ከአንቺ ጋር ቸርነትንና እውነትን እናደርጋለን አሉአት። ቤትዋም በከተማ ቅጥር የተጠጋ ነበረና፥ እርስዋም በቅጥሩ ላይ ተቀምጣ ነበርና ከመስኮቱ በገመድ አወረደቻቸው። እርስዋም፦ አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፤ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፤ ኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለቻቸው።

#ሰዎቹም አሉአት፦ እኛ ከዚህ ካማልሽን መሐላ ንጹሐን እንሆናለን። እነሆ፥ እኛ ወደ አገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ፈትል እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው፤ አባትሽንም እናትሽንም ወንድሞችሽንም የአባትሽንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ወደ ቤትሽ ሰብስቢ። ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፥ እኛም ንጹሐን እንሆናለን፤ ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤቱ ውስጥ ያለውን አንድ እጅ ቢነካው ደሙ በእኛ ራስ ላይ ይሆናል።

ይህንን ነገራችንን ግን ብትገልጪ ከዚህ ካማልሽን መሐላ ንጹሐን እንሆናለን። እርስዋም፦ እንደ ቃላችሁ ይሁን አለች፤ ሰደደቻቸውም እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው። እነርሱም ሄደው ወደ ተራራው ደረሱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ ሦስት ቀን በዚያ ተቀመጡ፤ አሳዳጆቹም በመንገዱ ሁሉ ፈልገው አላገኙአቸውም።ኢያሱ2÷24

#በመጨረሻም ደልን ሲቀናጁ እንደ ቃሌቸው ረዓብንና ቤተሰቦቿን አዳኗቸው “ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የሰደዳቸውንም መልክተኞች ስለ ሸሸገች ጋለሞታይቱን ረዓብን፥ የአባትዋንም ቤተ ሰብ፥ ያላትንም ሁሉ ኢያሱ አዳናቸው፤ እርስዋም በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጣለች።” መጽ ኢያሱ 2፥1ጀምሮ

#ረዓብን (ራኬብን )ቢሆኑ ምን ያደርጉ ነበር?

* ፀጉረ ልውጦችን ማስጠጋት የለብኝም በለው ያጋልጧቸው ነበር?
* ወይስ እንደ ረዓብ በጥበብ ይሽጓቸው ነበር
*የረዓብን ደግነትንስ እንዴት ያዮታል ረዓብ የዋህ (ደግ) ነች ወይስ ሞኝ(ጅል)?

#ነፃ_ሀሳብዎን በነዚህ ይስደዱልን
👇👇👇👇👇👇👇
@Abenma
@YEAWEDIMERITE

#ዓውደ_ምሕረት_የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
" #ዕለት_ሳበችው_ምሕረትም_ጠቀሰችው"
_______________________________
#አባታችን_ሁልጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር። ‹‹የሚጣፍጥ ምግብን መውደድ ኃጢአትን
ያመጣል፣ሞትን ያስከትላል፡፡ ክንፍ ያላቸው የሰማይ ወፎች እንኳን በመብል ምክንያት
ይጠመዳሉ፣ ምግብ በመሻት ከምድር ላይ ይወድቃሉ በወጥመድም ይያዛሉ፡፡የሰው ልጅም
ምግብን በመውደድ በኃጢአት ይወድቃልና እኔስ ለሰውነቴ ምግብ መጠጥን
አልፈልግም፤ልብስም አልሻም ዕራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን እንደወጣሁ እንዲሁ ዕረቁቴን ወደ
መቃብር እመለሳለሁ እንጂ፡፡ከዚህ ከኃላፊው ዓለም በሞት በተለየሁ ጊዜ መብል
መጠጥንና ልብስን ማን ያስከትልልኛል?›› አሉ። ዳግመኛም‹‹ሰው:ሊደርስበ
ማይችልበት:በረሃ:እኖራለሁ፣ ነጣቂ ተኩላዎችና አራዊቶች ባሉበት እነርሱ እንዲበሉኝ
ሥጋዬን እጥላለሁ፤ ዳዊት በመዝሙር ‹የጻድቃን ሥጋቸው ለዱር አራዊት ነው› እንዳለ እኔ
ክፉ አውሬዎች፣ ተናዳፊ እባቦችና ዘንዶዎች ወዳሉበት እገባለሁ ምግብም እሆናቸው ዘንድ
እወዳለሁ››በማለት አባታችን ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ይሰጡ ነበር ነገር ግን አራዊቱ
ሁሉ እየሰገዱላቸው ይገዙላቸው ከእግራቸውም በታች ይተኙ ነበር፡፡ እንደሚታዘዝ ደቀ
መዝሙርም ይታዙላቸው ነበር፤ለጸሎትም በሚቆሙበት ጊዜ አብረዋቸው ይቆማሉ፡፡
በፊታቸውም ይጫወታሉ፡፡
#በመጨረሻም ዕለት ሳበችሁ ምሕረትም ጠቀሰችሁ ለሞትም የሚያበቃ ጽኑ ሕማም
ታመመ የሚጠጋበት የዛፍ ጥላ በሌለበት እንደ አንበሳ በበርሃ ወደቀ ለጸሎት ከቆመበት
ጊዜ አንስቶ እስከ ሞተበት ቀን ድረስ እጆቹን በትምህርተ መስቀል እንዳማተበ ነበር ። ብዙ
ግሁሳንም ወደ እርሱ መጡ #እግዚአብሔር አምላክም ብዙ የብዙ ብዙ መላእክትን
አስከትሎ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስቀድሞ ዳዊትንም በገና አስይዞ ተገለጠና
ነብሱን አክብሮ ተቀበላት፣ሳማት፣ ደስታውንም መላት መላእክትም ከዳዊት ጋር "ክቡር ሞቱ
ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር " የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው" እያሉ
በአንድነት ዘመሩለት #መዝ ፻ ፲ ፭ {፻ ፲ ፮ }÷፲ ፭
#እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ
እናውቃለን።”
#ሮሜ ፰ ፥፳ ፰
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
መጋቢት ፭ ቀን ፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (😷ተርቢኖስ ሰብስቤ😷)