ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
+++ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተመቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ፤ ከመዝ ነበርኪ አስርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምዐበ መላእክት+++ቅዳሴ ማርያም+
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደች በሥስት ዓመቷ እናቷ ቅድስት ሀና ለኢያቄም " ይህች ብላቴና ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን ከቤተክርስቲያን አንሰጥምን? ኋላ አንዳች ብትሆንብን ከልጃችንም ከእግዚአብሔርም ሳንሆን እንዳንቀር"..አለችው። እርሱም መልሶ "ፍቅርሽ አያስችልሽም ብዬ ነው አንጂ እኔማ ፈቃዴ አይደለምን" አላት። ከፍቅሯ የተነሳ ከትከሻዋ አውርዳት አታውቅም አንድ ቀን ከቤት ጥላት ውጪ ወጥታ ብትመለስ መለአክ ሰውሮባት ጥራ አግኝታታለች ከዚያ በኋላ ተለይታት አታውቅም። ይህን ተባብለው ከቤተመቅደስ ወስደው ሰጧት የብጽአት ልጅ ናትና። ሊቀ ካህናቱ ዘካር ያስ በደስታ ተቀበላት ነገር ግን የምትመገበውን ከየት ላመጣ ነው ብሎ ሃ ሳብ ወስጥ ገባ ዛሬ እኛ ምን እንበላለን ምን እንጠጣለን ምንሰ እንለብሳለን ብለን እንደምንጨነቀው ነገር ግን ይህ ሁሉ ነገር እኛ ከምናስበው በላይ እንደሚያስፈልገን አምላካችን ያውቃል በወንጌሉም ስለነዚህ ጉዳዮች ከቶ አንዳንጨነቅ አስቀድመን ጽድቁን እንድንፈልግ ምግባር ከሃይማኖት ጋር አስተባብረን እንድንይዝ ጌታችን አስተምሮናል። ካህኑ ዘካርያስ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ህብስት ሰማያዊ ፣ ጽውዐ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ ፤ ዘካርያስ ይህን ሲመለከት ለኔ የመጣ ሀብት ነው ብሎ ለመቀበል ቢነሳ ወደ ላይ ራቀበት አገልጋዩ ስምኦንም ቢሞክር ራቀበት። ከዚህ በኋላ ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርምና ምናልባት ለዚህች ብላቴና የመጣ ሀብት እንደሆነ ብለው እመቤታችንን ለብቻዋ አድርገዋት ፈቀቅ ቢሉ ድንኩል ድንኩል ብላ እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፋን አንጥፎ ፤ አንድ ክንፋን ጋርዶ በቆመ ብእሲ በሰው ቁመት ያህል ቦታ አስለቅቆ መግቧት ዐረገ። ከዚያም ቤተመቅደስ አስገብተዋት በዚያ አስራ ሁለት ዓመት ኖራለች በቤተመቅደስ ቆይታዋ ብዙ ችግሮችን አሳልፋለች አይሁድ በክፉት በቅናት ጦራቸውን አንስተውባታል ነገር ግን የፍጥረት ሁሉ ጌታ ይጠብቃት ነበርና ገና ወደ ቤተመቅደስ ሳይደረሱ ቅጥሩ እሳት እየሆነ መልሷቸዋል እኛም ዛሬ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ዋጅቶ በመሠረታት በቀደሳት ምግበ ነፍስ የሆነውን የዘላለም ሕይወት የሚገኝበትን አማናዊውን የክርስቶስ ሥጋውና ደሙን አዘጋጅታ ያለዋጋ የምትሰጠንን በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳንገኝ ለነፍሳችን ዕረፍት እንዳናገኝ እንዳንፈወስ በቤቱም ሆነን ያማረ የተወደደ እንደ አቤል ያለውን መስዋዕት ፣ ምስጋና፣ ጸሎት አንዳናቀርብ ብዙዎች በኛ ላይ ይነሱ ይሆናል መሠናክል ይሆኑብን ይሆናል እኛ ግን በዚህ ነገር ሳንሸበር እመአምላክ ወላዲተ አምላክን የጠበቀ እግዚአብሔርን አምነን ተስፋ አድርገን በሃይማኖት ልንጸና በምግባር ልንታነጽ ፤ በምክረ ካህን ራሳችንን ልናስመረምር ፤ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ልንበላ ልንጠጣ ይገባል። ለዚህ ክብር እንድንበቃ እመቤታችን በምልጃዋ በቃል ኪዳኗ ታስምረን! የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን እግዚአብሔር አምላክ ያሳድርብን!!አሜን!!!
*+++ መልካም በዓል+++*

ታህሳስ 3/4/2013
@AwediMeherit
@AwediMeherit
@AwediMeherit
"የባሕርይ ገዥ ክርስቶስ ከዕለት ከሰዓት አስቀድሞ የነበረ ሲሆን የሰዎችን ልደት ዛሬ ተወለደ።" ሃይማኖተ አበው

የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የሐዋርያት ደቀ መዝሙር የነበረ አጢፎስ በሃይማኖተ አበው ላይ የልደትን ነገር በተናገረበት ድርሳኑ ይህን መሰከረ።

ክርስቶስን የባሕርይ ገዥ ጌታ አለው። ሌሎች ገዥ ቢባሉ በጸጋ በስጦታ፤ ሌሎች ጌታ ቢባሉ የምድር፤ ሌሎች ገዥ ቢባሉ በጊዜ የሚገደብ፤ በዘመን የሚወሰን ነው። ለእርሱ ግን ጌትነትን የሚሰጠው ሰጪ አልያም የሚወስድበት ወሳጅ የሌለበት የባሕርይ ገንዘቡ ነውና የባሕርይ ገዢ አለው። ዮሐ 13:13

ከዕለትና ከሰዓት አስቀድሞ ነበርም አለው። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመናት የማያረጅ እንዲሁም በጊዜ የማይወሰን ከ ብሎ መጀመርያ እስከ ብሎ መጨረሻ የሌለው ቀዳማዊ ድኃራዊ ነውና ከዕለት ከሰዓት አስቀድሞ የነበረ ብሎ መሰከረ። ዮሐ 1:1 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክቱ ቀዳማዊነቱን ሲናገር "በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት አስቀድሞ #በኩር ነው። ሁሉ በእርሱ ለእርሱ ተፈጥረዋል።" ብሎ የዘመናት ፈጣሪ ከዘመን አስቀድሞ የነበረ አምላክ መሆኑን መሰከረ። ቆላ 1:15 ጌታ በወንጌል ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር የነበረ መሆኑን ሲናገር እንዲህ አለ። "አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።" ዮሐ 17:5

ይህ የባሕርይ ገዥ ከዕለት ከዓመት ከዘመናት አስቀድሞ የነበረ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የሰዎችን ልደት ዛሬ ተወለደ ተባለ። እንዴት የሚደንቅ እንዴትስ የሚረቅ ምሥጢር ነው???

ሥጋ ያልነበረ በመለኮቱ ጥንት ያልነበረው እርሱ ጥንት ያለውን ሥጋ ስለምን ተዋሐደ? አይታይ የነበረው አምላክ የሚታይ ሥጋን ተዋሕዶ ስለምን ታየ? ስለምንስ ተዳሰሰ? በባሕርይው የማይወሰንና ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆነ አምላክ ስለምን በድንግል ማኅጸን አደረ? የማይሰጡት ቸር የማያበድሩት ባለጠጋ ሲሆን ስለምን በከብቶች በረት ተጣለ? ሰማይን በደመና የሚሸፍን በከዋክብት የሚያስጌጥ እርሱ ስለምን በጨርቅ ተጠቀለለ? ለዚህ ሁሉ መልሱ ሰው ወዳጅ የሆነ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ፍጹም ቢያፈቅረው አይደለምን? ሰው ሰውን ቢወድ ነቅ ፈልጎ ምክንያት አበጅቶ ነው። እግዚአብሔር ግን ሰውን የወደደው እንዴት ነው ቢሉ እንዲሁ ያለምክንያት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ነው። እንደውም መወደድ የሚገባን ሆነን ሳለን እንኳን አይደለም። ስንጠላው ወደደን ስናምጽና ስንርቀው ቀረበን ስንበትን ሰበሰን ጠላቶቹ ሳለን ነፍሱን ስለኛ ቤዛ ሰጥቶ ታረቀን። ዮሐ 3:16 ሮሜ 5:10 የነገሥታት ንጉስ በትሕትና ከሰማይ ከመንበሩ ወርዶ ፍቅሩን ከገለጸልን እኛማ ምን ያህል ልንዋረድ ምን ያህልስ ልንዋደድ ይገባል?

ይቆየን።

መልካም የልደት በዓል ይሁንልን።

ወልደ ተክለሃይማኖት ታኅሳስ 29 2013 ዓ.ም

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit